አጠቃላይ ጉባኤ
እህቶች በፅዮን
የጥቅምት 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


እህቶች በፅዮን

እናንተም እስራኤልን በመሰብሰብ እና የጽዮን ህዝብ በመፍጠር ረገድ ወሳኝ ኃይል ትሆናላችሁ።

ውድ እህቶቼ፣ በአለም ታሪክ ውስጥ አስደናቂ በሆነ በዚህ ጊዜ ንግግር ለመስጠት በመቻሌ ምስጋና ይሰማኛል። በየቀኑ፣ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ወደ ምድር ወደሚመጣበት የከበረ ጊዜ እየተቃረብን ነው። እርሱ ከመምጣቱ በፊት ስለሚሆኑቱ የሚያስፈሩት አስከፊ ክስተቶች አንዳንድ ነገሮች እናውቃለን፣ ሆኖም እርሱ ከመምጣቱ በፊት ስለሚፈጸሙ ክቡር ተስፋዎች በማወቃችን ልባችን በደስታ እና በልበ-ሙሉነት ያብጣል።

እንደ ሰማይ አባት ውድ ሴት ልጆች፣ እና በመንግስቱ እንደምትገኙ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሴት ልጆች፣1 ወደፊት በሚሆነው ታላቅ ጊዜ አስፈላጊ ክፍል አላችሁ። አዳኝ ወደተሰበሰቡ እና የሔኖክ ከተማ ህዝቦች እንዳደረጉት ለመኖር ወደተዘጋጁ ሰዎች እንደሚመጣ እናውቃለን። ህዝቡም በኢየሱስ ክርስቶች እምነት አንድ ነበሩ እናም በፍጹም ንጹህ ሆነው ወደሰማይ አርገዋል።

በሔኖክ ህዝቦች ላይ ምን እንደሚደርስ እና በዚህ የዘመን ፍጻሜ ምን እንደሚደርስ ጌታ የገለጸው ማብራሪያ በዚህ አለ፥

“ምድር የምታርፍበትም ቀን ይመጣል፣ ነገር ግን ከዚያ ቀን በፊት ሰማያት ይጠቁራሉ፣ የጭለማም መጋረጃ ምድርን ይሸፍናል፤ እና ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፣ ዳግም በምድርም፤ በሰው ልጆችም መካከልም ታላቅ ስቃይ ይኖራል፣ ነገር ግን ህዝቤን አተርፋቸዋለሁ፤

“እና ፅድቅን ከሰማያት እሰዳለሁ፤ እና ስለ አንድያ ልጄ፣ ከሙታን ትንሳኤውን፣ አዎን፣ እና ስለሁሉም ሰዎች ከሞት ስለመነሳት እንዲመሰክርም እውነትን ከምድር እልካለሁ፤ እና እንደ ጥፋት ውሀ ፅድቅና እውነት ምድርን አንድታጸዳት፣ የእኔ ተመራጮችን ከምድር አራት ማእዘናት ወደ አዘጋጀሁት ስፍራ፣ ቅዱስ ከተማ፣ ወገባቸውን እንዲታጠቁ እና ለእኔ መመለሻ ወደፊት ይጠብቁ ዘንድ እንዲሰበሰቡ አደርጋለሁ፤ በዚያም ድንኳኔም ይገኛልና፣ እና ይህችም ፅዮን፣ አዲስቷ ኢየሩሳሌም ተብላ ትጠራለች።

“ጌታም ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ አንተና ከተማህ ሁሉ በዚያ ትገናኛቸዋለህ፣ እናም በእቅፋችንም እንቀበላቸዋለን፣ እነርሱም ያዩናል፤ እና አንገታቸውን እናቅፋለን፣ እና እነርሱም አንገታችንን ያቅፋሉ፣ እና እንሳሳማለን፤

“እኔም በዚያ መኖሪያዬ ይሆናል፣ እና ከፈጠርኳቸው ሁሉ ውስጥ የምትመጣው ፅዮን ትሆናለች፤ እና ለአንድ ሺ አመታትም ምድር ታርፋለች።”2

እናንት እህቶች፣ ሴቶች ልጆቻችሁ፣ የልጅ ልጆቻችሁ፣ እና እናንተ የተንከባከባችኋቸው ሴቶች ያንን ከአዳኝ ጋር በክብር ህብረት የሚቀላቀሉ ሰዎችን ህብረተሰብ ለመፍጠር እምብርት ይሆናሉ። እናንተም እስራኤልን በመሰብሰብ እና በአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ውስጥ በሰላም የሚኖር የጽዮን ህዝብ በመፍጠር ረገድ ወሳኝ ኃይል ትሆናላችሁ።

ጌታ በነቢዮቹ በኩል ለእናንተ የተስፋ ቃል ሰጥቷል። በሴቶች መረዳጃ ማህበር የመጀመሪያ ቀናት፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለእህቶች እንዲህ አለ፣ “በመብቶቻችሁ መሰረት የምትኖሩ ከሆናችሁ፣ መላእክት አጋሮቻችሁእንዳይሆኑ ሊከለከሉ አይቻሉም።”4

ያም አስገራሚ ችሎታ በእናንተ ውስጥ ይገኛል፣ እናም እናንተ ለዚህ እየተዘጋጃችሁ ናችሁ።

ፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ እንዳሉት፥

“እናንተ እህቶች … አባታችሁ ለልጆቹ ባለው ዘለአለማዊ ደስታ እና ደህናነት እቅድ ውስጥ ሁለተኛ ደረጃ ያላሁ አይደላችሁም።” እናንተ የእቅዱ ፍጹም አስፈላጊ ክፍል ናችሁ።

“ያለእናንተ እቅዱ አይሰራም። ያለእናንተ ፕሮግራሙ በሙሉ አይሳካም። …

“እያንዳንዳችሁ በመለኮታዊ የብኩርና መብት የተባረካችሁ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ ናችሁ።”4

የአሁኑ ነቢያችን፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ እናንተ በአዳኝ መመለስ ዝግጅት ውስጥ ስላላችሁ ክፍል ይህን መግልጫ ሰጥተዋል።

“በቤተሰብ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ሚስቶች፣ እናቶች እና አያቶች፤ እንደ እህቶች እና አክስቶች፣ እንደ መምህሮች እና መሪዎች፣ እና በተለይም እንደ ተምሳሌቶች እና የእምነት ጠባቂዎች ሁሌ እነዚህ ሴቶች ያላቸውን ተፅእኖ መመዘን የማይቻል ነው።

“ከአዳም እና ሄዋን ጊዜያት ጀምሮ ባሉት በእያንዳንዱ የወንጌል ዘመናት ውስጥ ይሄ እውነት ነበር። ይህ የዘመን ፍጻሜ ከሌሎቹ ሁሉ የተለየ በመሆኑ ምክንያት፣ የዚህ ዘመን ሴቶች ከማንኛውም ሌሎች ዘመን ሴቶች ሁሉ የተለዩ ናቸው። ይሄ ልዩነት እድሎችን እና ሀላፊነቶችንም ጨምሮ ያመጣል።”5

ይህ የዘመን ፍጻሜ ልዩ የሆነው ጌታ እንደ ሔኖክ ከተማ አይነት ለመሆን እንድንዘጋጅ ስለሚረዳን ነው። በነቢያቱ እና በሐዋሪያቱ በኩል የፅዮን ህዝቦች ቅያሬ ምን አይነት እንደሚሆን ገልጿል።

ሽማግሌ ብሩስ አር. መካንኪ እንዳሉት፥

“[የሔኖክ] ቀንም የጥፋት እና የክፋት ቀን፣ የጭለማ እና የአመጽ ቀን፣ የጦርነት እና የውድመት ቀን፣ ምድር በውሀ ወደጸዳችበት የሚመራ ቀን ነበር።

“ሔኖክ፣ ግን፣ ታማኝ ነበር። እርሱም ‘ጌታን አየ፣’ እናም ከእርሱም ጋር ‘ፊት ለፊት’ አንድ ሰው ከሌላ ጋር እንደሚነጋገር ተነጋገረ። (ሙሴ 7፥4።) ጌታም ለአለም ንስሀን እንዲሰብክ፣ እናም ‘በአብ እና በጸጋና በእውነት በተሞላው በወልድ፣ እና ስለአብና ወልድ ምስክር በሚሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲያጠምቅ ትእዛዝም’ ተሰጠው።’ (ሙሴ 7፥11።) ሔኖክ ቃል ኪዳኖችን ገባ እናም እውነተኛ አማኞችን ሰበሰበ፣ ሁሉም በጣም ታመኝ ሆነው ‘ጌታ መጣ እና ከህዝቡም ጋር ኖረ፣ እና እነርሱም በፅድቅ ኖሩ፣’ እናም ከበላይ ተባርከው ነበር። ‘እነርሱ አንድ ልብ እና አንድ አእምሮ ስለነበሩ፣ እና በጽድቅም ስለኖሩ፣ ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው፤ እና በመካከላቸውም ማንም ድሀ አልነበረም።’ (ሙሴ 7፥18።) …

“ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ከጠራቸው በኋላ፣ ቅዱሳት መጻህፍት ‘የቅድስና፣ እንዲሁም፣ ፅዮን፣ ተብሎ የተጠራ ከተማም መሰረተ፣’ ያም ፅዮን ‘ወደ ሰማይ ተመለሰች፣’ በዚያም ‘እግዚአብሔር ወደ እቅፉ ተቀብሏታልና፤ እና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ፅዮን ጠፋች የሚል አባባል ነበር።’ (ሙሴ 7፥19፣ 21፣ 69።)

“ጌታ ፅዮንን እንደገና ሲያመጣ፣ እናም የዚህችም ነዋሪዎች ከምትመሰረተው ከአዲስ ኢየሩሳሌም ጋር አንድ ሲሆኑ፣ ወደሰማይ የተወሰደችው ይህችም ፅዮን፣ ትመለሳለች።”6

ያለፈው መቅድም ከሆነ፣ በአዳኝ በሚመጣበት ጊዜ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለገቡት ቃል-ኪዳኖች በጥልቀት የተወሰኑ ሴት ልጆች እርሱ በሚመጣበት ጊዜ እርሱን ለመቀበል ከተዘጋጁት ከግማሽ በላይ ይሆናሉ። ግን ቁጥሩ ምንም ቢሆን፣ ለዚያ ጽዮን በተዘጋጁት ሰዎች መካከል አንድነትን በመፍጠር ረገድ ያደረጋችሁት አስተዋጽኦ ከግማሽ እጅግ የሚልቅ ይሆናል።

ያም እንደሚፈጸም ለምን እንደማምን ልንገራችሁ። መፅሐፈ ሞርሞን ስለ ፅዮን ህዝብ ታሪክ ይናገራል። ከሞት ከተነሳው አዳኝ ከተማሩ፣ ከተወደዱ፣ እና ከተባረኩ በኋላ “በህዝቡ ልብ ውስጥ ባለው የእግዚአብሔር ፍቅር የተነሳ፣ በምድሪቱ ፀብ” እንዳልነበረ አስታውሱ።7

የሰማይ አባት ሴት ልጆች ክርክሮችን ለማስቀረት እና ባላቸው የእግዚአብሔር ፍቅር ጽድቅን ለማስፋፋት እናም የእግዚአብሔር ፍቅር በሚያገለግሏቸው ሰዎች እንዲገኝ እንደሚያደርጉ የእኔ ተሞክሮ አስተምሮኛል።

ትንንሽ ቅርንጫፋችን በልጅነት ቤቴ ውስጥ ሲገናኝ በወጣትነቴ አይቻለሁ። እኔና ወንድሜ ብቸኛ የአሮናዊ የክህነት ተሸካሚዎች፣ አባቴም ብቸኛው የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች ነበርን። የቅርንጫፍ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘዳንት ባሏ በቤተክርስቲያኗ አገልግሎት ደስተኛ ያልሆነ ሀይማኖቷን የቀየረች ነበረች። አባላቱ ሁሉም በቤታቸው ውስጥ የክህነት ስልጣን የሌላቸው ሽማግሌ እህቶች ነበሩ። እናቴ እና እነዚያ እህቶች ያለማቋረጥ እርስ በእርሳቸው ሲዋደዱ፣ ከፍ ከፍ ሲደራረጉ፣ እና ሲተሳሰቡ ተመልክቻለሁ። የፅዮን ቅፅበታዊ እይታ እንደተሰጠኝ አሁን ገባኝ።

በታማኝ ሴቶች ተጽዕኖ ምክንያት ያለኝ ትምህርት በኒው ሜክሲኮ አልበከርኪ ውስጥ በሚገኘው ትንሽ የቤተክርስቲያን ቅርንጫፍ ውስጥ ቀጠለ። የቅርንጫፉ ፕሬዘዳንት ሚስት፣ የአውራጃው ፕሬዘዳንት ሚስት እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዝዳንት የእያንዳንዱን አዲስ መጪ እና ተቀያሪን ልብ ሲያሞቁ ተመለከትኩ። ከአልበከርኪ ወጥቼ በሄድኩበት እሁድ፣ ለሁለት አመት በዚያ ያሉት እህቶችን ተፅዕኖ ከተመለከትኩኝ በኋላ፣ የመጀመሪያው ካስማ ተደራጀ። አሁን ጌታ በእዚያ ቤተመቅደስ አኑሯል።

በሁለት ግዛቶች ተሰራጭተው የነበሩትን ትናንሽ ቅርንጫፎችን በበላይነት በሚመራው የአውራጃ አመራር ውስጥ ወዳገለገልኩበት ቦስተን ተዛወርኩ። ልብን ለማለስለስ በሚረዱ አፍቃሪ እና ይቅር ባይ ሴቶች ከአንድ ጊዜ በላይ የተፈቱ ውዝግቦች ነበሩ። ቦስተንን ለቅቄ በሄድኩበት እሁድም፣ የቀዳሚ አመራር አባል በማሳቹሴትስ ውስጥ የመጀመሪያውን ካስማ አደራጁ። የአውራጃው ፕሬዝዳንት በአንድ ወቅት ይኖሩበት ከነበረው ቦታ ቅርበት አሁን እዚያ ቤተመቅደስ አለ። በታማኝ እና አፍቃሪ ሚስት ተጽዕኖ ምክንያት፣ እርሱ ወደ ቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴ እንዲገባ ሆኑ፣ እና በኋላም እንደ ካስማ ፕሬዝዳንት እና ከዚያም እንደ ሚሲዮን ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ ተጠርተው ነበር።

እህቶች፣ ከልዩ ስጦታዎች ጋር የእግዚአብሔር ሴት ልጆች የመሆን በረከት ተሰጥቷችኋል። ሌሎችን ለመንከባከብ እና በጽዮን ማህበረሰብ ውስጥ አብረው ለመኖር ብቁ ለመሆን ወደሚያስችሏቸው ወደ ፍቅር እና ንጹህነት ከፍ የሚያደርግ መንፈሳዊ ችሎታ ወደ ሟች ህይወት አምጥታችኋል። ለሰማይ አባት ሴት ልጆች በልዩ የተደራጀው የቤተክርስቲያኑ የመጀመሪያ ድርጅት፣ እንዲሁም የሴቶች መረዳጃ ማህበር “ልግስና በምንም አትወድቅም” የሚል መፈክር ያለው በአጋጣሚ አይደለም።

ልግስና የኢየሱስ ክርስቶስ ንፁህ ፍቅር ነው። እናም ለረጅም ጊዜ በተጠበቀና የተስፋ ቃል በተገባላት በጽዮን ውስጥ በማህበራዊ ኑሮ ለመኖር የላቀ ስጦታ እናንተን እና የምታፈቅሯቸውን እና የምታገለግሏቸውን ብቁ የሚያደርገው በእርሱ እና በማያልቅ የኃጢያት ክፍያው እምነት ነው። በዚያም በጽዮን ውስጥ እህቶች ትሆናላችሁ፣ በዚያም በጌታ በአካል የተወደዳችሁ እና የተባረካችሁ ትሆናላችሁ።

እናንተ በምድር ላይ የጌታ መንግስት ዜጋዎች እንደሆናችሁ እመሰክራለሁ። እናንተም ወደ አለም ሌሎችን ለመባረክ ቃል ከገባችሁባቸው ከልዩ ስጦታዎች ጋር የላካችሁ የአፍቃሪ የሰማይ አባት ሴት ልጆች ናችሁ። ጌታ በመንፈስ ቅዱስ በኩል እጃችሁን ይዞ እንደሚመራችሁ የተስፋ ቃል እሰጣችኋለሁ። ህዝቡን እርሱ ቃል የገባበት ፅዮን እንዲሆኑ ለማዘጋጀት ስትረዱ እርሱም በፊታችሁ ይሄዳል። ይህንን የምመሰክረው ቅዱስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 25፥1 ይመልከቱ።

  2. ሙሴ 7፥61–64፤ ትኩረት ተጨምሮበታል።

  3. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ] (2007 እ.አ.አ)፣ 454፤ ትኩረት ተጨምሮበታል።

  4. ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “የቤተክርስቲያኗ ሴቶችኤንዛይን፣ ህዳር 1996 (እ.አ.አ)፣ 67።

  5. ርስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለእህቶቼ ልመና፣” Liahona፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 95–96፤ አትኩሮት ተጨምሯል።

  6. Bruce R. McConkie, “Building Zion,” Tambuli, Sept. 1977, 13; emphasis added.

  7. 4 ኔፊ 1፥15