የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፬


ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፬፥፩–፬።ዮሐንስ ፬፥፩–፪ ጋር አነጻፅሩ

ፈሪሳውያን ኢየሱስን ለመግደል ፈለጉ። እርሱም ጥቂት ጥምቀቶችን አከናወነ፣ ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ ተጨማሪዎችን አከናወኑ።

እንግዲህ። ኢየሱስ ከዮሐንስ ይልቅ ደቀ መዛሙርት ያደርጋል ያጠምቅማል ማለትን ፈሪሳውያን እንደ ሰሙ፣

በትጋት ሊገድሉት የሚፈልጉበት መንገድ ፈለጉ፤ ብዙዎች ዮሐንስን እንደ ነቢይ ተቀብለውት ነበርና፣ ነገር ግን በኢየሱስ አላመኑም።

ምንም እንኳን እርሱ ከደቀመዛሙርቱ እንዳጠመቁት ያህል ባያጠምቅም፣ አሁን ጌታ ይህን አውቋል፤

እርስ በርሳችው እንደሚከባበሩ ምሳሌ ለማሳየት ፈቀደላቸው።

ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፬፥፳፮።ዮሐንስ ፬፥፳፬ ጋር አነጻፅሩ

እግዚአብሔር መንፈሱን በእውነት ለሚያምኑት ቃል ገባ።

፳፮ ለእነዚህ አይነትም እግዚአብሔር መንፈሱን ቃል ገብቷል። የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።