የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ቆሮንቶስ ፯


ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ቆሮንቶስ ፯፥፩–፪፣ ፭፣ ፳፮፣ ፳፱–፴፫፣ ፴፰። ከ፩ ቆሮንቶስ ፯፥፩–፪፣ ፭፣ ፳፮፣ ፳፱–፴፰ ጋር አነጻፅሩ

ጳውሎስ ጋብቻ የሚፈለግ እንደሆነ አስተማረ። በሚስዮን የተጠሩት፣ ግን፣ በአገልግሎታቸው ጊዜ ያላገቡ ቢሆኑ እግዚአብሔርን በተሻለ ለማገልገል ይችላሉ።

፩ አሁን እናንተ እንዲህ ብላችሁ ስለ ጻፋችሁልኝ ነገሮች በሚመለከት፣ ከሴት ጋር አለመገናኘት ለሰው መልካም ነው።

፪ ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት እላችኋለሁ።

፭ ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፣ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ።

፳፮ እንግዲህ ስለ አሁኑ ችግር ይህ መልካም ይመስለኛል፤ ሰው እንዲህ ሆኖ ቢኖር ታላቅ መልካም ያደርጋልና።

፳፱ ነገር ግን ወደአገልግሎት ለተጠራችሁት እናገራለሁ። ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፣ ዘመኑ አጭር ነው፣ ወደ አገልግሎት እንድትላኩ ዘንድ። እንዲሁም ሚስቶች ያሉአቸውም እንደሌላቸው ይሆናሉ፤ እናንተ ተጠርታችኋል እና የጌታን ስራ ለመስራት ተመርጣችኋልና።

፴ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ ይሆንብላቸዋል፤ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፣ እና የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው ይሆንላቸዋል፤

፴፩ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሆናሉ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና።

፴፪ ነገር ግን ወንድሞች ጥሪአችሁን እንድታጎሉ ፍላጎቴ ነው። ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባልና፤ ስለዚህ ያሸንፋል።

፴፫ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፤ ስለዚህ ልዩነት አለ፣ ተደናቅፎአልና።

፴፰ እንዲሁም ያገባ እርሱም መልካም አደረገ፤ ያላገባም እርሱም የተሻለ አደረገ።