ምዕራፍ ፲፪
ነቢዩ ኤተር ህዝቡ በእግዚአብሔር እንዲያምኑ አበረታታ—ሞሮኒ አስገራሚ የሆኑትን እናም በእምነት የተሰሩትን ድንቅ ነገሮች አስታወሰ—የያሬድ ወንድም እምነቱ ክርስቶስን ለማየት አስቻለው—ጌታ ሰዎች ትሁት ይሆኑ ዘንድ ድካምን ይሰጣቸዋል—የያሬድ ወንድም የዜሪንን ተራራ በእምነት አንቀሳቀሰ—እምነት፣ ተስፋ፣ እና ልግስና ለደህንነት አስፈላጊ ናቸው—ሞሮኒ ኢየሱስን ፊት ለፊት አየው።
፩ እናም እንዲህ ሆነ የኤተር ዘመን ሀበቆሪያንተመር ዘመን ነበር፤ እናም ቆሪያንተመር በምድሪቱ በሙሉ ላይ ንጉስ ነበር።
፪ እናም ሀኤተርም የጌታ ነቢይ ነበር፤ ስለዚህ ኤተር በቆሪያንተመር ዘመን ተነሳ፤ እናም ለህዝቡ መተንበይ ጀመረ፣ በውስጡ በነበረው የጌታ መንፈስ መንስኤ ለሊታገት አይቻልምና።
፫ እርሱም ከማለዳ ጀምሮ ፀሐይ እስከምትጠልቅ ህዝቡም ንሰሃ በመግባት በእግዚአብሔር እንዲያምኑ አለበለዚያ ሀእንደሚጠፉ በመምከር፣ ለእነርሱም ለበእምነት ሁሉም ነገሮች ለመሟላት እንደሚችሉ በመንገር ሐጮኸ—
፬ ስለሆነም፣ በእግዚአብሔር የሚያምን በእርግጥ ለተሻለ ዓለም፣ አዎን፣ በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ በኩል ያለውን ስፍራ እንኳ ለማግኘት ሀተስፋ ይኖረዋል፤ ይኸውም ተስፋ በእምነት የሚመጣ ነው፤ ተስፋም ለሰዎች ነፍስ ለእንደመሃልቅ ነው፤ እነርሱንም ፅኑ እና የማይነቃነቁ እንዲሆኑ እናም ሁልጊዜም በርካታ ሐመልካም ነገሮችን እንዲሰሩ፤ እግዚአብሔርንም መእንዲያከብሩ ያደርጋቸዋል።
፭ እናም እንዲህ ሆነ ኤተር ታላቅ እና አስገራሚ ነገሮችን ለህዝቡ ተነበየላቸው፤ እነርሱ ግን ስላላዩት አላመኑበትም።
፮ እናም አሁን፣ እኔ ሞሮኒ፣ ስለነዚህ ነገሮች በመጠኑ እናገራለሁ፤ ሀእምነት ለተስፋ የምናደርጋቸው ነገሮች ነገር ግን ሐየማናያቸው መሆኑን ለዓለምም አሳያለሁ፤ ስለዚህ፣ ስላላያችሁ አትከራከሩ፣ ምክንያቱም እምነታችሁ መእስከሚፈተን ድረስ ምስክርነትን አትቀበሉምና።
፯ ምክንያቱም ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በኋላ እራሱን ለአባቶቻችን ያሳየው በእምነት ነበር፤ እነርሱም በእርሱ እምነት እስከሚኖራቸው ድረስ እራሱን አልገለፀላቸውም፤ ስለሆነም፣ አንዳንዶቹ በእርሱ ላይ እምነት ሳይኖራቸው አልቀረም፣ ምክንያቱም እራሱን ለዓለም አላሳየምና።
፰ ነገር ግን ሰዎች በማመናቸው እራሱን ለዓለም አሳይቷል፣ እናም የአብንም ስም አክብሯል፣ እና ሌሎች ከሰማያዊው ስጦታ ይካፈሉ ዘንድ፣ ባልተመለከቷቸውም ነገሮች ተስፋ ያደርጉ ዘንድ መንገዱን አዘጋጅቷል።
፱ ስለዚህ፣ እናንተ ደግሞ ተስፋን ማድረግ፣ እናም እምነት ካላችሁ ከስጦታው ተካፋዮች ለመሆን ትችላላችሁ።
፲ እነሆ የጥንቶቹም ቅዱስ ወደሆነው የእግዚአብሔር ስርዓት ሀየሚጠሩት በእምነታቸው ነበር።
፲፩ ስለሆነም፣ በእምነት ነበር የሙሴ ህግ የተሰጠው። ነገር ግን እግዚአብሔርም በልጁ ስጦታም ይበልጥ ሀየተመረጠውን መንገድ አዘጋጅቷል፤ እናም ይህም የተሟላው በእምነት ነው።
፲፪ በሰው ልጆች መካከል ሀእምነት ከሌለ እግዚአብሔር በመካከላቸው ለተአምር መስራት አይችልም፤ ስለሆነም እስከሚያምኑ ድረስ እራሱን አልገለፀላቸውም።
፲፫ እነሆ፣ የአልማ እና የአሙሌቅ እምነትም ነው ሀወህኒ ቤቱ ወደምድር እንዲወድቅ ያደረገው።
፲፬ እነሆ፣ የኔፊና የሌሂ እምነት ነበር ላማናውያንን ሀእንዲለወጡ ያደረገው፣ ስለሆነም እነርሱም በእሳት እና ለበመንፈስ ቅዱስ ተጠመቁ።
፲፭ እነሆ፣ ሀየአሞን እና የወንድሙ እምነት ነበር ታላቅ የሆነ ተአምር በላማናውያን መካከል ለየሠራው።
፲፮ አዎን፣ ከክርስቶስ በፊት የነበሩትም እንኳን እናም ደግሞ ከእርሱ በኋላ የነበሩት ሀተአምር የሚሰሩት ሁሉም የሰሯቸው ለበእምነት ነበር።
፲፯ እናም ሦስቱ ደቀመዛሙርት ሞትን ሀእንዳይቀምሱ ቃል ኪዳን የተገባላቸው በእምነት ነበር፤ እናም እምነት እስከሚኖራቸው ድረስ ቃልኪዳኑን አላገኙም ነበር።
፲፰ እናም በማንኛውም ጊዜም እንኳን እምነት እስከሚኖራቸው ድረስ ተአምራትን ማንም አልሰራም፤ ስለዚህ እነርሱ አስቀድመው በእግዚአብሔር ልጅ አምነዋል።
፲፱ እናም ክርስቶስ ሀከመምጣቱም በፊት እንኳን በእምነታቸው እጅግ የበረቱ ብዙዎች ነበሩ፤ እነርሱም ለበመጋረጃው ስር ሊጠበቁ አልተቻሉም፤ ነገር ግን በእውነትም በእምነት አይን ያዩአቸውን ነገሮች በዐይኖቻቸው አይተዋል እናም ተደስተዋል።
፳ እናም እነሆ፣ በዚህ መዝገብ ውስጥም ከእነዚህ አንዱ የያሬድን ወንድም መሆኑን አይተናል፤ እርሱም በእግዚአብሔር እምነቱ ታላቅ በመሆኑ እግዚአብሔርም ሀበጣቶቹ ሲያመለክት፣ ለእርሱም በተናገራቸው ቃላት ምክንያት፣ ከያሬድ ወንድም እይታ ሊደብቀው አልቻለም፤ ቃላቱንም እርሱ በእምነቱ ያገኛቸው ነበሩ።
፳፩ እናም የያሬድ ወንድም የጌታን ጣት ከተመለከተ በኋላ፣ የያሬድ ወንድም በእምነቱ ሀቃል ኪዳን ስለተቀበለ፣ ጌታ ከእርሱ ምንም ነገር ከእይታው ሊሰውርበትም አልቻለም፤ ስለዚህ እርሱም ሁሉንም ነገሮች አሳየው ምክንያቱም ለከመጋረጃው ውጪ ከእንግዲህ ሊያስቀምጠው አይቻለውምና።
፳፪ እናም እነዚህ ነገሮች በአህዛብ አማካኝነት ለወንድሞቻቸው እንዲመጡ አባቶቻችን ሀቃል ኪዳንን ያገኙት በእምነት ነው፤ ስለዚህ ጌታ፣ አዎን ኢየሱስ ክርስቶስም እንኳን፣ እኔን አዞኛል።
፳፫ እናም እንዲህ ስል ተናገርኩት፥ ጌታ ሆይ፣ ስንፅፍ ሀደካሞች በመሆናችን አህዛብ ይሳለቁብናል፤ ጌታ በእምነታችን በሚገባ እንድንናገር አድርጎናል፣ ነገር ግን በጽሁፍ ለኃያላን እንድንሆን አላደረገንምና፤ መንፈስ ቅዱስንም ስለሰጠሃቸው እነዚህን ሰዎች ሁሉ ብዙ ለመናገር እንዲችሉ አድርገኻቸዋልና።
፳፬ እናም በእጆቻችን አስቸጋሪነት ምክንያትም ትንሽ ብቻ ሀእንድንፅፍ አድርገኸናል። እነሆ፣ እንደያሬድ ወንድም በይበልጥ መፃፍ እንድንችል አላደረግኽንም፣ ምክንያቱም ሰዎች እንዲያነቡት የሚገፋፉበት ኃያል እንዲሆኑ እርሱ የፃፋቸውን ነገሮች እንዳንተው ሁሉ ኃያል አድርገሃቸዋል።
፳፭ ቃላቶቻችንን ደግሞ መፃፍ እስከማንችል ድረስ ኃያል እና ታላቅ አደረክ፤ ስለዚህ በምንፅፍበት ጊዜም ደካማነታችንን እንመለከታለን፣ እናም ቃላቶቹን በምናስቀምጥበትም እንደናቀፋለን፤ እናም አህዛብ በቃላችን ሀእንደሚሳለቁብን እፈራለሁ።
፳፮ እናም ይህን በምናገርበት ጊዜ፣ ጌታ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ ሞኞች ሀይሳለቃሉ ነገር ግን ያዝናሉ፤ እናም ፀጋዬ ለየዋሆች በቂ ነው፣ እነርሱም በድካማችሁ ብልጫ አይወስዱባችሁም።
፳፯ እናም ሰዎች ወደ እኔ የሚመጡ ከሆኑ ሀድክመታቸውን አሳያቸዋለሁ። ሰዎች ትሁት እንዲሆኑ ድካምን ለእሰጣቸዋለሁ፤ እናም ሐፀጋዬም እራሳቸውን በፊቴ መዝቅ ላደረጉ ሁሉ በቂ ነው፤ እነርሱም በፊቴ እራሳቸውን ዝቅ ካደረጉ፣ እናም በእኔም እምነት ካላቸው፣ ከዚያም ሠደካማ የሆኑትን ለእነርሱ ጠንካራ እንዲሆኑ አደርጋለሁ።
፳፰ እነሆ፣ ለአህዛብ ድካማቸውን አሳያቸዋለሁ፣ እናም ሀእምነት፤ ተስፋ እና ልግስና ወደ እኔ—የፅድቅ ምንጭ ሁሉ ወደሆነው እንደሚያመጣቸው አሳያቸዋለሁ።
፳፱ እናም እኔ ሞሮኒ፣ እነዚህን ቃላት በመስማቴ ተፅናንቼ ነበር እናም እንዲህ አልኩኝ፥ አቤቱ ጌታ የፅድቅ ፈቃድህ ይከናወናል፤ ምክንያቱም አንተ ለሰው ልጆች እንደእምነታቸው እንደምታከናውን አውቃለሁና፤
፴ የያሬድ ወንድም የዜሪንን ተራራ ተንቀሳቀስ ሲለው—እርሱም ሀተንቀሳቀሶ ነበር። እናም እምነት ባይኖረው አይንቀሳቀስም ነበር፣ ስለዚህ አንተም ለሰዎች እንደ እምነታቸው ትሰራለህ።
፴፩ ምክንያቱም ለደቀመዛሙርቱም ራስህን እንደዚህ አሳይተሃል፤ ባንተም ሀካመኑ እናም በስምህ ከተናገሩ በኋላ ራስህን በታላቅ ኃይል አሳይተሃቸዋልና።
፴፪ እናም ደግሞ ለሰዎች ቤት፣ አዎን፣ በአባትህም ሀቤት እንኳን ማዘጋጀትህን መናገርህን አስታውሳለሁ፤ በዚህም ሰው የላቀ ለተስፋ ይኖረው ዘንድ ነው፤ ስለሆነም ሰው ተስፋ ማድረግ ይገባዋል፣ አለበለዚያ አንተ ያዘጋጀኸውን ሥፍራ በውርስ ሊቀበል አይችልም።
፴፫ እናም በድጋሚ፣ ለሰዎች ልጆች ስፍራቸውን ለማዘጋጀት እንደገና ታነሳው ዘንድ ህይወትህን አሳልፈህ ለአለም እስከመስጠት ድረስ ዓለምን ሀመውደድህን መናገርህን አስታውሳለሁ።
፴፬ እናም አሁን ይህ ለሰዎች ልጆች የነበረህ ሀፍቅር ልግስና እንደሆነ አውቃለሁ፤ ስለዚህ ሰዎች ልግስና ከሌላቸው በአባትህ መኖሪያ ያዘጋጀኸውን ስፍራ ሊወርሱ አይችሉም።
፴፭ ስለዚህ፣ እኛ ደካሞች በመሆናችን አህዛብ ልግስና ከሌላቸው ትፈትናቸዋለህ እናም ሀተሰጦአቸውም ይወሰድባቸዋል፤ አዎን፣ ያንን የተቀበሉትንም እንኳን፣ እናም በብዛት ላላቸውም ይጨመርላቸዋል ያልከውን በዚህ ነገር አውቀዋለሁ።
፴፮ እናም እንዲህ ሆነ አህዛብ ልግስና ይኖራቸው ዘንድ ሀጸጋ እንዲሰጣቸው ወደ ጌታ ፀለይሁ።
፴፯ እናም እንዲህ ሆነ ጌታም እንዲህ አለኝ፥ ልግስና ከሌላቸው አንተ ግድ የለህም፣ አንተ ታማኝ ነበርክ፤ ስለዚህ፣ ልብስህ ሀይነፃል። እናም ለድካምህን በማየትህ በአባቴ ቤት ባዘጋጀሁልህ ቦታ እንድትቀመጥ ጠንካራ ትደረጋለህ።
፴፰ እናም አሁን እኔ ሞሮኒ፣ አህዛቦችን አዎን እናም ደግሞ የምወዳቸው ወንድሞቼን በክርስቶስ ሀየፍርድ ወንበር ፊት እስካገኛቸው እሰናበታችኋለሁ፤ በዚያም ሰዎችም በሙሉ ለልብሶቼ በእናንተ ደም እንዳልተበከሉ ያውቃሉ።
፴፱ እና ከዚያም ኢየሱስን ሀማየቴን ታውቃላችሁ፣ እናም እርሱም ለፊት ለፊት ተናግሮኛል፣ እናም እነዚህን ነገሮች በተመለከተ አንድ ሰው ለሌላ እንደሚናገርም፣ በራሴ ቋንቋ በግልፅ በትህትና ነግሮኛል፤
፵ እናም በፅሁፍ ደካማ በመሆኔም ጥቂቱን ብቻ ፅፌአለሁ።
፵፩ እናም እንግዲህ፣ ነቢያት እና ሐዋሪያት የፃፉለትን ይህንን ኢየሱስን ሀእንድትፈልጉት እመክራችኋለሁ፤ በዚህም የእግዚአብሔር አብ ፀጋ፣ እናም ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስና፣ ስለእነርሱ ለየሚመሰክረው መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥና፣ ከእናንተ ጋር ለዘለዓለም ይኑር። አሜን።