ቅዱሳት መጻህፍት
ኤተር ፲


ምዕራፍ ፲

አንዱ ንጉስ ሌላኛውን ተካ—አንዳንዶቹ ንጉሶች ፃድቅ ናቸው፤ ሌሎች ደግሞ ኃጢአተኞች ናቸው—ፅድቅ የበላይ ሲሆን ህዝቡ በጌታ ይባረካሉ እናም ይበለፅጋሉ።

እናም እንዲህ ሆነ ሼዝ የሔት ዘር የነበረው—ሔት በረሃቡ ሞቷል፣ እናም ከሼዝ በስተቀር ቤተሰቡ በሙሉ ሞቷል—ስለዚህ፣ ሼዝም የተጎዱትን ሰዎች ማጠናከር ጀመረ።

እናም እንዲህ ሆነ ሼዝም የአባቶቹን አሟሟት አስታወሰ፣ እናም እርሱም ጻድቃዊ የሆነ መንግስት መሰረተ፤ ምክንያቱም እርሱ ጌታ ያሬድን እና ወንድሙን ባህሩን አሻግሮ ሲያመጣቸው ያደረገውን ያስታውሳልና፤ እናም እርሱም የጌታን መንገድ ተከተለ፤ እናም እርሱም ወንዶችን እና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

እናም ታላቁ ልጁ፣ ሼዝ ተብሎ የሚጠራው በእርሱ ላይ ተነሳበት፤ ይሁን እንጂ ሼዝም እጅግ ሀብታም በመሆኑ በሌቦች ተገደለ፣ ይህም ለአባቱ ሠላምን በድጋሚ አስገኘ።

እናም እንዲህ ሆነ አባቱም በምድሪቱ ላይ ብዙ ከተሞችን አቋቋመ፣ እናም ህዝቡ በድጋሚ በምድሪቱ ላይ ተሰራጩ። እናም ሼዝም እጅግ እስከሚያረጅ ድረስ ኖረ፤ እናም ሪፕላኪሽን ወለደ። እናም እርሱ ሞተ፤ እናም ሪፕላኪሽ በእርሱ ቦታ ነገሰ።

እናም እንዲህ ሆነ ሪፕላኪሽም በጌታ ዐይን የሚሰራው ትክክል አልነበረም፤ ምክንያቱም ብዙ ሚስቶች እና እቁባቶች ነበሩትና፣ እናም በሰዎች ትከሻም ለመሸከም የማይቻል አሳረፈ፣ አዎን፣ ሰዎችንም ከባድ ቀረጥ ይቀርጣቸው ነበር፤ እናም በቀረጡም የሚያምሩ የተስፋፉ ህንጻዎች ይገነባ ነበር።

እናም ለራሱም እጅግ የሚያምር ዙፋን ሠራ፤ እናም ብዙ ወህኒ ቤቶችንም ሠራ እናም ቀረጥ የማይከፍሉትንም ሰዎች ወህኒ ቤት አስገባቸው፤ እናም ቀረጥ ለመክፈል የማይችልም እስር ቤት እንዲገባ ይደረጋል፤ እናም እርሱም እራሳቸውን እንዲደግፉ ያለማቋረጥ እንዲሰሩ አደረጋቸው፤ እናም ለመስራት ፈቃደኛ ያልሆነውንም እንዲሞት አደረገ።

ስለሆነም መልካም የሆኑ ስራውን በሙሉ አገኘ፤ አዎን፣ መልካም የሆነውን ወርቅም በእስር ቤት እንዲጣራ አደረገ፤ እናም የሚያምረውን የእጅ ሥራም በእስር ቤት እንዲሠራ አደረገ። እናም እንዲህ ሆነ በዝሙቱ እናም በእርኩሰቱ ህዝቡን አሳዝኖ ነበር።

እናም ለአርባ ሁለት ዓመታት በነገሰ ጊዜ ህዝቡ በአመፅ በእርሱ ላይ ተነስተውበት ነበር፤ እናም በድጋሚም በምድሪቱ ላይ ጦርነት ተጀመረ፤ በዚህም ሪፕላኪሽ ተገደለ፣ እናም ዘሮቹ ከምድሪቱ ተባረሩ።

እናም እንዲህ ሆነ ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ ሞሪያንተን (የሪፕላኪሽ ዘር የነበረው) ህዝቡ የተቃወማቸውን ወታደሮች በአንድነት ሰበሰበ፣ እናም ወደፊት ሔደ እናም ከህዝቡም ጋር ተዋጋ፤ እናም እርሱም በብዙ ከተሞች ላይ ሥልጣን አገኘ፤ እናም ጦርነቱም እጅግ የሚያሳዝን ነበር፤ እናም ለብዙ ዓመታትም ቆየ፤ እናም እርሱም በምድሪቱ ሁሉ ላይ ሥልጣንን አገኘ፣ እናም በምድሪቱ ላይም እራሱን ንጉስ አደረገ።

እናም እራሱንም ንጉስ ካደረገ በኋላ የህዝቡን ሸክም አቀለለ፣ በዚህም በህዝቡ አመለካከት ተወዳጅነትን አገኘ፣ እናም እነርሱም ንጉሳቸው አድርገው ቀቡት።

፲፩ እናም ህዝቡን በፍትህ ገዛ፣ ነገር ግን በርካታ ዝሙትን ስለሚፈፅም ለራሱ ትክክል አላደረገም፤ ስለዚህ ከጌታ ፊት ተለየ።

፲፪ እናም እንዲህ ሆነ ሞሪያንተን ብዙ ከተሞችን ሠራ፣ እናም ህዝቡም በእርሱ ንግስናም በህንፃዎች፣ እናም በወርቅ፣ እናም በብር፣ እናም እህል በማብቀል፣ እናም ከብቶችን በማርባት፣ እጅግ ሀብታሞች ሆኑ፣ እናም እንደዚህ አይነት ነገሮችም እንደቀደሙት ጊዜያት ሆኑላቸው።

፲፫ እናም ሞሪያንተን እጅግ ታላቅ ለሆነ እድሜ ኖረ፣ እና ከዚያም ቂምን ወለደ፤ እናም ቂምም በአባቱ ምትክ ነገሰ፤ እናም ለስምንት ዓመታት ነገሰ፣ እናም አባቱም ሞተ። እንዲህ ሆነ ቂም በፅድቅ አልነገሰም፣ ስለሆነም በጌታ አልተወደደም።

፲፬ እናም ወንድሙም በአመፅ ተነሳበት፣ በዚህም በእስር እንዲሆን አደረገው፤ እናም በዘመኑ ሁሉ በእስር ቤት ተቀመጠ፤ እናም በእስር እያለ ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን ወለደ፣ እናም በእርጅናውም ሌዊን ወለደ፤ እናም ሞተ።

፲፭ እናም እንዲህ ሆነ ሌዊ አባቱ ከሞተ በኋላ ለአርባ ሁለት ዓመታት በእስር ቤት አገለገለ። እናም ከምድሪቱ ንጉስ ጋር ተዋጋ፣ እናም በዚህ መንግስቱን ለራሱ አገኘ።

፲፮ እናም መንግስቱንም እራሱ ካገኘው በኋላ በጌታ ዐይን መልካም የሆነውን አደረገ፤ እናም ህዝቦቹ በምድሪቱ ላይ በለፀጉ፣ እናም እስከ እርጅናውም በመልካም ሁኔታ ኖረ፤ እናም ሴቶችን እና ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እናም ደግሞ በእርሱ ምትክ ንጉስ አድርጎ የቀባውን ቆሮምን ወለደ።

፲፯ እናም እንዲህ ሆነ ቆሮምም በዘመኑ ሁሉ በጌታ ፊት መልካም የሆነውን ነገርን ሠራ፤ እናም ብዙ ሴቶች እና ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እናም ለረጅም ጊዜ በምድር ላይ ከኖረ በኋላ፣ ልክ እንደሌሎቹ ምድራዊያን ሁሉ ህይወቱ አለፈች፤ እናም ኪሽም በእርሱ ምትክ ነገሰ።

፲፰ እናም እንዲህ ሆነ ኪሽም ደግሞ ሞተ፣ እናም ሊብ በእርሱ ምትክ ነገሰ።

፲፱ እናም እንዲህ ሆነ ሊብም ደግሞ በጌታ ፊት መልካም የሆነን ነገር አደረገ። እናም በሊብ ዘመን መርዛማዎቹም እባቦች ጠፍተው ነበር። ስለሆነም ህዝቡም በምድሪቱ በስተደቡብ በኩል ምግብ ለማደን ተጓዙ፣ ምክንያቱም በጫካ አውሬዎች ተሸፍኖ ነበርና። እናም ሊብም ደግሞ ታላቅ አዳኝ ሆነ።

እናም በምድሪቱ ቀጭን በሆነው፣ ምድሪቱን የሚከፍለው ባህር ባለበት ሥፍራ አጠገብ ታላቅ ከተማን ሠሩ።

፳፩ እናም በምድሪቱም በስተደቡብ በኩል ያለውን ምድረበዳ የዱር አውሬ ለማግኘት ሲሉ ጠበቁት። እናም በስተሰሜን ያለው ምድር በሙሉ በነዋሪዎች ተሸፍኗል።

፳፪ እናም እነርሱም እጅግ ሠራተኞች ነበሩ፤ እናም እርስ በርሳቸውም ጥቅምን ያገኙ ዘንድ ይጓዙ፣ እናም ይሸጡ፣ እናም ይለዋወጡ ነበር።

፳፫ እናም በሁሉም አይነት የብረት አፈር፣ እናም ወርቅ፣ እናም ብር፣ እናም ብረት፣ እናም ነሀስ፣ እናም ሁሉም አይነት ብረታ ብረቶች ይሰሩ ነበር፤ እናም ከመሬትም ቆፍረው ያወጡት ነበር፤ ስለዚህ፣ ከወርቅ፣ እናም ከብር፣ እናም ከብረት፣ እናም ከመዳብ የብረት አፈር ለማግኘት አፈር ይቆልሉ ነበር። እናም መልካም ሥራዎችን ሁሉ ሠርተዋል።

፳፬ እናም ሀርና የተፈተለ ጥሩ በፍታ ነበሯቸው፤ እናም ዕርቃናቸውን ይሸፍኑበትም ዘንድ ሁሉንም አይነት ልብሶች ሠሩ።

፳፭ እናም መሬቱን ለማረስ፣ እናም አርሰውም ለመዝራት፤ ለመሰብሰብ፣ እናም ለመቆፈር፣ እናም ደግሞ ለመውቃት ሁሉንም አይነት መሳሪያዎች ሠሩ።

፳፮ እናም በእንሰሳቶቹም ተረድተው ስራቸውን ለመስራት ሁሉንም መሳሪያዎች ሠሩ።

፳፯ እናም ሁሉንም አይነት የጦር መሳሪያዎች ሠሩ። እናም እጅግ አስገራሚ የእጅ ሥራዎችን ሁሉ ሠሩ።

፳፰ እናም ማንኛውም ህዝብ ከዚህ የበለጠ ሊባረክ እናም በጌታም እጅ በጭራሽ ሊሳካለት አይቻለውም። እናም ከምድሪቱም ይበልጥ በተመረጠችው ምድር ላይ ነበሩም፣ ጌታ ይህን ተናግሯልና።

፳፱ እናም እንዲህ ሆነ ሊብ ለብዙ ዓመታት ኖረ፣ እናም ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ እናም ደግሞ እርሱም ሔርቶምን ወለደ።

እናም እንዲህ ሆነ ሔርቶምም በአባቱ ምትክ ነገሰ። እናም ሔርቶም ለሃያ አራት ዓመታት በነገሰ ጊዜ፣ እነሆ፣ መንግስቱ ከእርሱ ተወሰደ። እናም ለብዙ ዓመታት፣ አዎን በቀሪው ዘመኑ ሁሉ በግዞት አገለገለ።

፴፩ እናም ሔትን ወለደ፣ እናም ሔትም በዘመኑ ሁሉ በግዞት ኖረ። እናም ሔትም አሮንን ወለደ፣ እናም አሮንም በዘመኑ ሁሉ በእስር ኖረ፤ እናም እርሱም አምኒጋዳን ወለደ፣ እናም አምኒጋዳም ደግሞ በዘመኑ ሁሉ በግዞት ኖረ፤ እናም እርሱም ቆሪያንቱምን ወለደ፣ እናም ቆሪያንቱምም በዘመኑ ሁሉ በግዞት ኖረ፤ እናም እርሱም ቆምን ወለደ።

፴፪ እናም እንዲህ ሆነ ቆምም ከመንግስቱ ግማሽ የሚሆነውን ወደ እርሱ ሳበ። እናም እርሱም በግማሽ መንግስቱ ለአርባ ሁለት ዓመታት ነገሠ፤ እናም እርሱም ከንጉስ አምጊድ ጋር ለመዋጋት ሔደ፤ እናም እነርሱም ለብዙ ዓመታት ተዋጉ፣ በዚያን ጊዜም ቆም በአምጊድ ላይ ኃይልን አገኘ እናም በተቀረው መንግስት ላይም ኃይልን አገኘ።

፴፫ እናም በቆም ዘመንም በምድሪቱ ዘራፊዎች መምጣት ጀመሩ፤ እናም የጥንቱን ዕቅድ ተከተሉ፤ እናም እንደጥንቱም መሃላቸውን ፈፀሙ፣ እናም መንግስቱን ለማጥፋት በድጋሚ ተመኙ።

፴፬ እንግዲህ ቆምም ከእነርሱ ጋር ለረጅም ጊዜ ተዋጋ፤ ይሁን እንጂ፣ አላሸነፋቸውም ነበር።