ምዕራፍ ፲፬
አትፍረዱ፤ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ ከሃሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ በማለት ኢየሱስ አዘዘ—የአባታቸውን ፈቃድ ለሚያደርጉ የደህንነትን ቃል ገብቶላቸዋል—ማቴዎስ ፯ን አነጻፅሩ። ፴፬ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እናም አሁን እንዲህ ሆነ ኢየሱስ እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ በድጋሚ ወደ ህዝቡ ተመለሰ፣ እናም በድጋሚ አፉን ከፍቶ እንዲህ አላቸው፥ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ እንዳይፈረድባችሁ ሀአትፍረዱ።
፪ ሀበምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፤ እናም በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ደግሞም ይሰፈርላችኋል።
፫ እናም በወንድማችሁ ዐይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያላችሁ፤ ነገር ግን በዐይናችሁ ያለውን ምሰሶ ስለምን አትመለከቱም?
፬ ወይም ወንድማችሁን ከዐይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትሉታላችሁ? እናም እነሆ በዐይናችሁ ምሰሶ አለ።
፭ እናንተ ግብዞች አስቀድማችሁ በዐይናችሁ ያለውን ሀምሰሶ አውጡ፤ እናም ከዚያም በኋላ ከወንድማችሁ ዐይን ጉድፉን ታወጡ ዘንድ አጥርታችሁ ታያላችሁ።
፮ በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ ሀየተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።
፯ ሀለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።
፰ የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፣ እናም የሚፈልግም ያገኛል፤ እናም ለሚያንኳኩ ይከፈትላቸዋል።
፱ ወይም ከእናንተ ልጁ ዳቦ ቢለምነው ድንጋይ የሚሰጠው ማነው?
፲ ወይም ዓሳስ ቢለምነው እባብ ይሰጠዋልን?
፲፩ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፣ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው?
፲፪ ስለሆነም፣ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም ደግሞ እንዲሁ ሀአድርጉላቸው፣ ህግም ነቢያትም ይህ ነውና።
፲፫ ሀበጠበበው ደጅ ግቡ፣ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ለትልቅ ነውና፤ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙ ናቸው፤
፲፬ ምክንያቱም ወደ ህይወት የሚወስደው ሀደጁ ለየጠበበ፣ መንገዱም የቀጠነ ስለሆነ፣ የሚያገኙትም ሐጥቂቶች ናቸው።
፲፭ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፣ ነገር ግን ውስጣቸው ነጣቂ ተኩላ ከሆኑ ሀከሀሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።
፲፮ ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን፣ ወይም ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?
፲፯ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፤ ክፉ ዛፍም መጥፎ ፍሬ ያፈራል።
፲፰ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፣ ወይንም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬን ማፍራት አይቻለውም።
፲፱ መልካም ፍሬ ሀየማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፣ ወደ እሳትም ይጣላል።
፳ ስለዚህ፣ ሀከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ።
፳፩ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፣ ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።
፳፪ በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣ በስምህ ትንቢትን አልተናገርንምን፣ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፣ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ሀይሉኛል።
፳፫ እናም ከቶ ሀአላውቃችሁም፣ እናንተ አመፀኞች፣ ከእኔ ለራቁ ብዬ አሳውቃቸዋለሁ።
፳፬ ስለዚህ፣ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ፣ ቤቱን ሀበአለት ላይ እንደሰራ እንደ ጠቢብ ሰው አመሳስለዋለሁ—
፳፭ እናም ሀዝናብ ወረደና፣ የጥፋት ውሀም መጣ፤ እናም ነፋስ ነፈሰና፣ ቤቱን ገፋው፤ እናም በአለትም ላይ ስለተመሰረተ ለአልወደቀም።
፳፮ እናም ይህንን ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሁሉ ቤቱን ሀበአሸዋ ላይ እንደሰራ ሰነፍ ሰው ይመሳሰላል—
፳፯ እናም ዝናቡ ወረደና፣ የጥፋት ውሀም መጣ፣ እናም ነፋሱ ነፈሰና፣ ቤቱን ገፋው፤ ወደቀና፣ አወዳደቁም ታላቅ ነበር።