ከመፅሐፈ ሙሴ
የተመረጡ ምንባቦች
ከመፅሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውስጥ ልዩ እትም፣ ከሰኔ ፲፰፻፴–የካቲት ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ ለነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደተገለጡለት።
ምእራፍ ፩
[ሰኔ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.)]
እግዚአብሔር እራሱን ለሙሴ ገለጠ—ሙሴ ተለወጠ—እርሱም ከሰይጣን ጋር ፊት ለፊት ተጋፈጠ—ሙሴ ብዙ ሰው የሚኖርባቸው አለማትን አየ—ቁጥራቸው ታላቅ የሆኑ አለማት በወልድ ተፈጥረው ነበር—የእግዚአብሔር ስራና ክብር የሰውን ህያውነትና ዘለአለማዊ ህይወትን ማምጣት ነው።
፩ ሙሴ እጅግ በጣም ከፍ ያለ ተራራ ላይ በተነጠቀበት ጊዜ እርሱ ሀለሙሴ ለየተናገራቸው የእግዚአብሔር ቃላት፣
፪ እናም እርሱም እግዚአብሔርን ሀፊት ለፊት ለአየው፣ እናም ከእርሱም ጋር ተነጋገረ፣ እናም የእግዚአብሔር ሐክብርም በሙሴ ላይ ነበር፤ በዚህ ምክንያትም ሙሴ በእርሱ ፊት መለመፅናት ችሏል።
፫ እና እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዲህ አለው፥ እነሆ፣ እኔ ሀሁሉን የሚገዛ ጌታ እግዚአብሔር ነኝ፣ እናም መጨረሻ የሌለውም ስሜ ነው፤ ለቀናቶቼ መጀመሪያ እና ለአመታቴም ፍጻሜ የለኝምና፤ እና ይህስ ለመጨረሻ የለውም አይደለምን?
፬ እናም እነሆ፣ አንተ ልጄ ነህ፤ ስለዚህ ሀተመልከት፣ እናም ለየእጄን ስራ አሳይሀለሁኝ፤ ነገር ግን ሁሉንም አይደለም፣ ሐስራዎቼ መመጨረሻ የላቸውም፣ እና ሠቃላቶቼም፣ በምንም አያልቁምና።
፭ ስለዚህ የእኔን ክብር ካላየ በስተቀር ማንም ሰው ሁሉንም ስራዎቼን ማየት አይችልም፤ እናም ማንም ሰው የእኔን ክብር ሙላት አይቶ፣ እና በምድር ላይ በስጋው ለመቅረት አይችልም።
፮ ልጄ ሙሴ፣ የምትሰራልኝ ስራ አለኝ፤ እና አንተም በአንድያ ልጄ ሀአምሳል ነህ፤ እናም ለአንድያ ልጄም ሐአዳኝ ነው ይሆናልም፣ መበጸጋና ሠበእውነት ተሞልቷልና፤ ነገር ግን ከእኔ ሌላ ረምንም አምላክ የለም፣ እና ሁሉም ነገሮች እኔ ዘንድ አሉ፣ ሁሉንም ነገሮች ሰአውቃቸዋለሁና።
፯ አሁንም እነሆ፣ ልጄ ሙሴ ይህን አንድ ነገር አሳይሀለሁ፣ በአለም ውስጥ ነህና፣ እናም ለአንተም ይህን አሳይሀለሁኝ።
፰ እናም እንዲህ ሆነ፣ ሙሴም ተመለከተ፣ እና የተፈጠረበትን ሀአለም ተመለከተ፤ እናም ሙሴም አለምንና የአለምን፣ እና የአሁን እና ተፈጥረው የነበሩትን የሰዎች ልጆችን መጨረሻ ለተመለከተ፣ በእነዚህም በጣም ተደነቀ እናም ሐተገረመ።
፱ እና እግዚአብሔርም ከሙሴ ፊት ሄደ፣ ክብሩም በሙሴ ላይ አልነበረም፤ እና ሙሴንም ለብቻው ተትቶ ነበር። እና ለብቻው ሲተውም፣ ወደ ምድር ወደቀ።
፲ እንዲህም ሆነ፣ ከብዙ ሰአታት በኋላ ነበር የሙሴ ተሰጥኦ ሀጥንካሬው እንደሰው ተመልሶ የመጣለት፤ እናም ለእራሱም እንዲህ አለ፥ አሁን፣ በዚህ ምክንያት ከዚህ በፊት እንዳላሰብኩት ሰው ለምንም እንዳልሆነ አወቅሁኝ።
፲፩ ነገር ግን አሁን አይኖቼ ሀእግዚአብሔርን አይተዋል፤ ነገር ግን ለበተሰጥኦ አይኖቼ ሳይሆን በመንፈሳዊ አይኖቼ ነው፣ የተሰጥኦ አይኖቼ ሊያዩት አይችሉምና፤ በእርሱ ፊት ስቆምም ሐጠውልጌ እና መእሞት ነበርና፤ ነገር ግን ክብሩ በእኔ ላይ ነበር፤ እና ሠፊቱን አየሁ፣ በእርሱ ፊት ረተለውጬ ነበርና።
፲፪ እንዲህም ሆነ ሙሴም እነዚህን ቃላት ሲናገር፣ እነሆ፣ ሀሰይጣን ለሊፈትነው እንዲህ በማለት መጣ፥ የሰው ልጅ ሙሴ ሆይ፣ አምልከኝ።
፲፫ እናም እንዲህ ሆነ፣ ሙሴም ሰይጣንን ተመለከተው እና አለ፤ ማን ነህ? እነሆ፣ እኔ በአንድያ ልጅ አምሳል የሆንኩት የእግዚአብሔር ሀልጅ ነኝ፤ እናም አመልክህስ ዘንድ ክብርህ የት አለ?
፲፬ እነሆ፣ ክብሩ በእኔ ላይ ካልሆነና በፊቱ ሀካልተለወጥኩኝ በስተቀር እግዚአብሔርን ማየት አልችልም። ነገር ግን በተፈጥሮአዊው ሰውነቴ አንተን ማየት እችላለሁኝ። በርግጥ፣ ይህ እውነት አይደለም?
፲፭ የአምላኬ ስም የተባረከ ይሁን፣ የእርሱ መንፈስ ከእኔ ሙሉ አልተገለለምና፣ ወይም ክብርህ የት ነው፣ ይህም ለእኔ ጭለማ ነውና? እናም በአንተና በእግዚአብሔር መካከል መፍረድ እችላለሁ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝና፥ እግዚአብሔርን ሀአምልክ፣ እርሱንም ብቻ ለአገልግል።
፲፮ ከዚህ ሂድ፣ አንተ ሰይጣን፤ አታታልለኝ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎኛልና፥ አንተ በአንድያ ልጄ ሀአምሳል ነህ።
፲፯ ከሚነደው ሀጥሻ ውስጥም በጠራኝ ጊዜ ትእዛዛትንም ደግሞ እንዲህ በማለት ሰጥቶኛል፥ አምላክህን በአንድያ ልጄ ስም ለጥራ፣ እናም አምልከኝ።
፲፰ ደግሞም ሙሴ አለ፥ ሌላ የምጠይቀው ነገሮች ስላሉኝ፣ እግዚአብሔርን መጥራት አላቆምም፥ ክብሩ በእኔ ላይ ነበርና፣ ስለዚህ በአንተና በእርሱ መካከል መፍረድ እችላለሁ። ከዚህ ሂድ፣ ሰይጣን።
፲፱ አሁንም፣ እነዚህን ቃላት ሙሴ ሲናገር፣ ሰይጣን በታላቅ ድምፅ ጮኸ፣ እናም በምድርም ላይ እየጮኸ ተናገረ፣ እናም እንዲህ በማለት አዘዘ፥ እኔ ሀአንድያ ልጅ ነኝ፣ አምልከኝ።
፳ እንዲህም ሆነ ሙሴም በጣም መፍራት ጀመረ፤ እናም ሲፈራም፣ ሀየሲኦልን መራራነትን አየ። ይህም ቢሆን እግዚአብሔርን ለበመጥራት ጥንካሬን ተቀበለ፣ እና እንዲህም በማለት አዘዘ፥ ሰይጣን ከእኔ ዘንድ ሂድ፣ የክብር አምላክ የሆነውን ይህን አንድ እግዚአብሔርን ብቻ አመልካለሁና።
፳፩ አሁንምሀሰይጣን መንቀጥቀጥ ጀመረ፣ እናም ምድርም ተንቀጠቀጠች፤ እናም ሙሴም ጥንካሬን ተቀበለ፣ እና እንዲህም በማለት እግዚአብሔርን ጠራ፥ ሰይጣን፣ በአንድያ ልጅ ስም፣ ከዚህ ሂድ።
፳፪ እንዲህም ሆነ ሰይጣን በታላቅ ድምጽ በማልቀስና በመጮኽ፣ እናም በጥርስ ሀማፏጨት አነባ፤ እናም ከዚያ እንዲሁም ከሙሴ ዘንድም ሄደ ሙሴም አላየውም።
፳፫ አሁንም ስለነዚህ ነገሮች ሙሴ ምስክርነትን ሰጠ፤ ነገር ግን በተንኮል ምክንያት ይህ በሰው ልጆች መካከል አልተገኘም።
፳፬ እንዲህም ሆነ ሰይጣን ከሙሴ ፊት ሲሄድ፣ ሰለአብና ወልድ ምስክር በሚሰጠው ሀመንፈስ ቅዱስ በመሞላት፣ ሙሴ አይኑን ወደሰማይ አነሳ፤
፳፭ እና የእግዚአብሔርን ስም በመጥራት የእርሱን ክብር እንደገና አየ፣ ይህም በእርሱ ላይ አርፎ ነበርና፤ እና እንዲህም የሚል ድምፅንም ሰማ፥ ሙሴ የተባረክ ነህ፣ እኔ፣ ሁሉን የሚገዛው፣ መርጬሀለሁና፣ እና ከብዙ ሀውሀዎች በላይ ጠንካራ ትሆናለህ፣ እንደ ለአምላክ እንደሆንክ አይነት ሐትእዛዝህን ያከብሩታልና።
፳፮ እናም አስተውል፣ እስከመጨረሻዎቹ ቀናትህም ድረስ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ አንተ ህዝቤን፣ እንዲሁም ሀየተመረጠውን ለእስራኤልን፣ ሐከባርነት ቀንበር መታድናቸዋለህና።
፳፯ እንዲህም ሆነ ድምጹም እየተናገረ እያለ፣ ሙሴ አይኑን ዞር ዞር አደረገ እና ምድርን፣ አዎን ሁሉንም፣ ሀአየ፤ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ለይቶ በማወቅም ያላየው አንድ የመጨረሻ ትንሽ መጠንም አልነበረም።
፳፰ እናም በዚያ ነዋሪዎችንም ደግሞ አየ፣ እና ያላየው አንድም ነፍስ አልነበረም፤ እና እነርሱንም በእግዚአብሔር መንፈስ ለይቶ አወቃቸው፤ እናም ቁጥራቸውም ታላቅ፣ እንዲሁም እንደ ባህር ዳርቻ እንደሚገኙ አሸዋ ተቆጥረው አያልቁም ነበር።
፳፱ እና ብዙ መሬቶችንም አየ፤ እና እያንዳንዱም መሬት ሀምድር ተብለው ተጠርተው ነበር፣ እናም በእነዚህ ላይ ነዋሪዎች ነበሩ።
፴ እንዲህም ሆነ ሙሴም እንዲህ በማለት እግዚአብሔርን ጠራ፥ እባክህ ንገረኝ፣ እንዴት እነዚህ ነገሮች እንዲህ ሆኑ እናም በምን እነዚህን ሰራሀቸው?
፴፩ እናም እነሆ፣ የጌታ ክብር በሙሴ ላይ አርፎ ነበር፣ ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፣ እና ከእርሱም ጋር ሀፊት ለፊት ተነጋገረ። እናም ጌታ አምላክ ለሙሴ እንዲህ አለው፤ በራሴ ለአላማ እነዚህን ነገሮች ሰርቼአለሁ። ይህም ጥበብ ነው እናም ይህም በእኔ ዘንድ ይቀራል።
፴፪ እና በሀይሌ ሀቃልም፣ እንዲሁም ለበጸጋና ሐበእውነት በተሞላው አንድያ ልጄ እነዚህን ፈጠርኩኝ።
፴፫ እና ለመቁጠር የማይቻል ሀአለማትንም ለፈጠርኩኝ፤ እና የፈጠርኳቸውም ለራሴ አላማ ነው፤ እና ሐአንድያ ልጄ በሆነው ወልድም እነዚህን ፈጠርኳቸው።
፴፬ ከሁሉም ሀየመጀመሪያ ሰውንም በትርጉም ለብዙ የሚባለውን ሐአዳም ብዬ ጠራሁት።
፴፭ ነገር ግን ስለዚህ ምድርና በዚህ ስለሚኖሩት ታሪክ ብቻ ነው የምሰጥህ። እነሆ፣ በሀይሌ ቃል ያለፉ ብዙ አለማት አሉ። እና አሁን የሚኖሩ ብዙዎችም አሉ፣ እና በሰው ለመቆጠር የሚያዳግቱ ናቸው፤ ነገር ግን ሁሉም ነገሮች በእኔ የሚቆጠሩ ናቸው፣ የእኔ ናቸው እና ሀአውቃቸዋለሁና።
፴፮ እንዲህም ሆነ ሙሴ ለጌታ እንዲህ ብሎ ተናገረ፥ እግዚአብሔር ሆይ፣ ለአገልጋይህ ርህራሄ ይሰማህ፣ እና ስለዚህ ምድርና ኗሪዎቿ እናም ስለሰማያት ንገረኝ፣ ከዚያም አገልጋይህ ይረካል።
፴፯ እናም ጌታ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ ሲል ተናገረ፣ ሀሰማያት፣ እነርሱም ብዙ ናቸው፣ እና በሰው ሊቆጠሩም አይችሉም፤ ነገር ግን በእኔ ይቆጠራሉ፣ የእኔ ናቸውና።
፴፰ እና አንድ ምድር ስታልፍ፣ እና የዚያም ሰማያት እንዲሁም ሌላ ይመጣል፤ እናም ለስራዬ እና ለቃላቶቼ ምንም ሀመጨረሻ የላቸውም።
፴፱ እነሆ፣ የሰውን ሀህያውነት እና ለዘለአለማዊ ህይወት ማምጣት ሐስራዬ እና መክብሬ ይህ ነው።
፵ አሁንም፣ ልጄ ሙሴ፣ ስለቆምክባት ምድር በሚመለከት እነግርሀለሁ፤ እና የምናገራቸውንም ነገሮች ሀጻፍ።
፵፩ እናም የሰው ልጆች ቃላቴን እንደማይረባ በሚመለከቱበትና ከጻፍካቸው ውስጥ ብዙ ቃላትን ሀበሚያወጡበት ጊዜ፣ እነሆ፣ እንደ አንተ ለአይነት ሌላንም አስነሳለሁ፤ እና ሐእነዚህም ከሚያምኑት ሰው ልጆች ጋር ሁሉ መካከል እንደገና ይገኛሉ።
፵፪ (እነዚህ ቃላት ለሙሴ ሀየተነገሩትም በተራራ ላይ ነው፣ የዚህም ስም በሰዎች ልጆች አይታወቅም። አሁንም እነዚህ ለእናንተም ተነግረዋል። ከሚያምኑት ሌላ በስተቀር ለማንም አታሳይ። እንዲህም ይሁን። አሜን።)