አጠቃላይ ጉባኤ
ዘለአለማዊ እውነት
የጥቅምት 2023 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ዘለአለማዊ እውነት

እውነትን የማወቅ ግዴታችን ከዚህ በላይ አስፈላጊ ሆኖ አያውቅም።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ለእግዚአብሔር አብ እና ለልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ስላደረጋችሁት ታማኝነት አመሰግናለው፣ እናም እርስ በርሳችሁ ለምታደርጉት ፍቅር እና አገልግሎት አመሰግናችኋለሁ። እናንተ በእውነትም አስደናቂ ናችሁ!

መግቢያ

ባለቤቴ አን እና እኔ በሙሉ ጊዜ ሚስዮን መሪነት እንድናገለግል ጥሪ ከተቀበልን በኋላ፣ ቤተሰባችን ወደ አገልግሎት ከመግባታችን በፊት የእያንዳንዱን ሚስዮናውያን ስም ለማወቅ ወሰንን። ፎቶዎችን አገኘን፣ የምናጠናባቸው ወረቀቶችን አዘጋጀን፣ እና ፊቶችን ማጥናት እና ስሞችን መገምገም ጀመርን።

በዚያ ከደረስን በኋላ፣ ከሚስዮናውያን ጋር የማስተዋወቂያ ስብሰባ አደረግን። እየተገናኘን እያለን፣ የዘጠኝ አመት ልጃችንን ይህን ሲል ሰማሁ፦

“ሳም፣ ስለተዋወቅን ደስ ብሎኛል!”

“ራሄል፣ ከየት ነሽ የመጣሽው?”

“ይገርማል ዳዊት፣ ረጅም ነህ!”

ደነገጥኩኝ፣ ወደ ልጃችን ሄጄ በሹክሹክታ፣ “ሚስዮናውያንን እንደ ሽማግሌ ወይም እህት መጥራታቸውን አናስታውስ” አልኩት።

ግራ የተጋባ እይታ ሰጠኝና፣ “አባዬ፣ ስማቸውን መገምገም ያለብን መስሎኝ ነበር” አለኝ። ልጃችን በመረዳቱ ላይ በመመሥረት ትክክል ነው ብሎ ያሰበውን አድርጓል።

ስለዚህ፣ በዛሬው ዓለም ውስጥ ስለ እውነት ያለን ግንዛቤ ምንድን ነው? ያለማቋረጥ በጠንካራ አስተያየቶች፣ በተዛባ ዘገባ እና ባልተሟሉ መረጃዎች እንጠቃለን። በተመሳሳይ፣ የዚህ መረጃ ምንጮች እና መጠን እያደጉ ናቸው። እውነትን የማወቅ ግዴታችን ከዚህ በላይ አስፈላጊ ሆኖ አያውቅም።

ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነታችንን ለመመስረት እና ለማጠናከር፣ ሰላምን እና ደስታን ለማግኘት እንዲሁም መለኮታዊ አቅማችን ላይ ለመድረስ እውነት ወሳኝ ነው። ዛሬ፣ የሚቀጥሉትን ጥያቄዎች እናስብባቸው፦

  • እውነት ምንድን ነው እናም አስፈላጊ የሆነው ለምድነው?

  • እውነትን እንዴት እናገኛለን?

  • እውነትን ስናገኝ እንዴት ልናካፍል እንችላለን?

እውነት ዘለአለማዊ ነው

ጌታ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ “ነገሮች እንዳሉ፣ እንደነበሩ፣ እናም ወደፊት እንደሚሆኑ የሚታወቅበት እውነት ነው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥24) በማለት አስተምሮናል። “የተፈጠረ ወይም የተሰራ አይደለም” ((ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥29) እናም “መጨረሻም የለውም” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥66)።1 እውነት ፍጹም፣ ቋሚ እና የማይለወጥ ነው። በሌላ አነጋገር እውነት ዘለአለማዊ ነው።2

እውነት መታለልን እንድንርቅ፣3 መልካሙን ከክፉ እንድንለይ፣4 ጥበቃን እንድንቀበል፣5 መጽናናትን እና ፈውስን እንድናገኝ ይረዳናል።6 እውነት ትግባራችንን ለመምራት፣7 ነጻ ሊያደርገን፣8 ሊቀድሰን፣9 እና ወደ ዘለአለም ህይወት ሊመራን10 ይችላል።

እግዚአብሔር ዘለአለማዊ እውነትን ይገልጣል

እግዚአብሔር ከራሱ፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ፣ ከመንፈስ ቅዱስ፣ ከነቢያት፣ እና ከእኛ ጋር በተያያዙ የመገለጥ የግንኙነቶች መረብ አማካኝነት ዘለአለማዊ እውነትን ይገልጥልናል። በዚህ ሂደት ውስጥ እያንዳንዱ ተሳታፊ ስላለው ለየት ያለ ግን እርስ በርስ የተቆራኘ ሚናዎችን እንወያይ።

በመጀመሪያ፣ እግዚአብሔር የዘለአለም እውነት ምንጩ ነው።11 እሱ እና ልጁ ኢየሱስ ክርቶስ12 ስለ እውነት ፍጹም ግንዛቤ አለው እናም ሁልጊዜ ከእውነት መርሆዎች እና ህጎች ጋር በሚስማማ መንገድ ይሰራል።13 ይህ ኃይል ዓለምን እንዲፈጥሩ እና እንዲያስተዳድሩ14 እንዲሁም እያንዳንዳችንን እንዲወዱን፣ እንዲመሩን እና እንዲያሳድጉ ያስችላቸዋል።15 እነርሱ የሚደሰቱባቸውን በረከቶች እንደሰትበት ዘንድ፣ እኛም እውነትን እንድንረዳ እናም እንድንጠቀም ይፈልጉናል።16 በአካል ወይም እንደ መንፈስ ቅዱስ፣ መላእክት፣ ወይም ህያዋን ነቢያት ባሉ መልእክተኞች በኩል እውነትን ሊነግር ይችላል።

ሁለተኛ፣ መንፈስ ቅዱስ ስለ እውነት ሁሉ ይመሰክራል።17 እውነትን ለእኛ በቀጥታ ይገልጻል እናም ሌሎች ስለሚያስተምሩት እውነቶችም ይመሰክራል። ከመንፈስ የሚመጡ ግንዛቤዎች እንደ ሀሳቦች ወደ አእምሯችን እና ወደ ልባችን እንደ ስሜቶች ይመጣሉ።18

አራተኛ፣ ነቢያት ከእግዚአብሔር እውነትን ተቀብለው ያንን እውነት ለእኛ ያካፍላሉ።19 በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከነበሩት ከድሮ ነቢያት20 እና በአጠቃላይ ጉባኤ ወቅት ከህያዋን ነቢያት እንዲሁም ከሌሎች በይፋ የመገናኛ መንገዶች እውነትን እንማራለን።

በመጨረሻም፣ እናንተ እና እኔ በዚህ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና እንጫወታለን። እግዚአብሔር እውነትን እንድንፈልግ፣ እንድናውቅ፣ እና እንድንሰራበት ይፈልገናል። እውነትን የመቀበል እና የመተግበር አቅማችን ከአብ እና ከወልድ ጋር ባለን ግንኙነት ጥንካሬ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ተጽእኖ ባለን ምላሽ እና ከኋለኛው ቀን ነቢያት ጋር ባለን አሰላለፍ ላይ የተመሰረተ ነው።

ሰይጣን የሚሠራው ከእውነት እንድንርቅ መሆኑን ማስታወስ አለብን። ያለ እውነት የዘለአለም ህይወት ማግኘት እንደማንችል ያውቃል። እኛን ግራ ለማጋባት እና ከእግዚአብሔር ከተነገረው ነገር ለማዘናጋት የእውነትን ሰንሰለት ከዓለማዊ ፍልስፍናዎች ጋር ይሸምናል።21

ዘለአለማዊ እውነትን መፈለግ፣ ማወቅ እና መተግበር

ዘለአለማዊ እውነትን በምንፈልግበት ጊዜ፣22 የሚከተሉት ሁለት ጥያቄዎች ሃሳቡ ከእግዚአብሔር ወይም ከሌላ ምንጭ የመጣ እንደሆን ለማወቅ ይረዱናል።

  • ሐሳቡ ቅዱሳት መጻሕፍት ወይም ህያዋን ነቢያት ያለማቋረጥ የሚያስተምሩት ነውን?

  • ሃሳቡ በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት የተረጋገጠ ነውን?

እግዚአብሔር እውነትን በነቢያት በኩል ይገልጣል፣ እናም መንፈስ ቅዱስ እነዚያን እውነቶች ለእኛ ያረጋግጣል እናም እንድንጠቀምባቸው ይረዳናል።23 እነዚህን መንፈሳዊ መነሳሻዎች ለመፈለግ እና ሲመጡም ለመቀበል መዘጋጀት አለብን።24 ትሁት ስንሆን፣25 ከልባችን ስንጸልይና የእግዚአብሔርን ቃል ስናጠና፣26 እናም ትእዛዛቱን ስንጠብቅ27 የመንፈስን ምስክርነት እንቀበላለን።

መንፈስ ቅዱስ ልዩ እውነትን ካረጋገጠልን በኋላ፣ ያን መርህ በተግባር ስናውል በጥልቅ ለመረዳት እንችላለን። በጊዜ ሂደት፣ መርህን በተከታታይ ስንኖር፣ የዚያን እውነት እርግጠኛ እውቀት እናገኛለን።28

ለምሳሌ እኔ ስህተት ሰርቻለሁ እናም ለደካማ ምርጫዎች ተፀፅቻለሁ። ነገር ግን በጸሎት፣ በማጥናት እና በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን፣ የንስሐን መርህ ምስክር ተቀብያለሁ።29 ንስሀ መግባት ስቀጥል፣ ስለ ንስሀ ያለኝ ግንዛቤ እየጠነከረ መጣ። ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ልጁ ይበልጥ እንደቀረብኩ ተሰማኝ። በየእለቱ የንስሐን በረከቶች ስለማገኝ፣ ኃጢአት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንደሚሰረይ አሁን አውቃለሁ30

እውነት ገና ሳይገለጥ በእግዚአብሔር መታመን

ስለዚህ ገና ያልተገለጠን እውነት ከልባችን ስንፈልግ ምን ማድረግ አለብን? የማይመጡ የሚመስሉ መልሶችን ለማግኘት ለምንናፍቀው ታላቅ አዘኔታ አለኝ።

ጆሴፍ ስሚዝ ጌታ “ነገሩን በተመለከተ … እስካሳውቅ ድረስ ዝም በል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥37) በማለት መክሮት ነበር።

እናም ለኤማ ስሚዝም “ስላላየሻቸው ነገሮች አታጉረምርሚ፣ ከአንቺ እና ከአለም ታግደዋል፣ ይህም ወደፊት በሚመጣው በእኔ ዘንድ ጥበብ ነው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥4) በማለት አብራርቷል።

እኔም በልብ ለሚሰሙ ያቄዎች መልሶች ፈልጌአለሁ። ብዙ መልሶች መጥተዋል፣ አንዳንዶች አልመጡም።31 የእግዚአብሔርን ጥበብ እና ፍቅር በማመን፣ ትእዛዛቱን በመጠበቅ እና በምናውቀው ላይ በመታመን ስንጠብቅ፣ የሁሉንም ነገር እውነት እስኪገልጥ ድረስ ሰላም እንድናገኝ ይረዳናል።32

ትምህርትን እና ፖሊሲዎችን መረዳት

እውነትን በምንፈልግበት ጊዜ፣ በወንጌላዊ ትምህርት እና በፖሊሲ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ይረዳል። ወንጌላዊ ትምህርት የሚያጠቁመው እንደ የአምላክ ተፈጥሮ፣ የመዳን እቅድ፣ እና የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት አይነት ዘለአለማዊ እውነቶችን ነው። ፖሊሲ በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የወንጌላዊ ትምህርት አተገባበር ነው። ፖሊሲዎች እኛ ቤተክርስቲያንን በሥርዓት እንድናስተዳድር ያግዙናል።

ወንጌላዊ ትምህርት መቼም የማይለወጥ ሲሆን ፖሊሲ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ይስተካከላል። ጌታ በነቢያቱ በኩል ወንጌላዊ ትምህርቱን ለመጠበቅ እና የቤተክርስቲያንን ፖሊሲዎች እንደ ልጆቹ ፍላጎት ለማሻሻል ይሰራል።

በሚያሳዝን ሁኔታ፣ አንዳንድ ጊዜ ፖሊሲን ከወንጌላዊ ትምህርት ጋር እንደባልቃለን። ልዩነቱን ካልተረዳን፣ ፖሊሲዎች ሲቀየሩ በተሳሳተ ሃሳብ የምንጓዝ ወደመሆን አድጋ ላይ ያደርሰናል፣ እናም አንዳንድ ሰዎች የእግዚአብሔርን ጥበብ ወይም የነቢያትን የመገለጥ ሚና ለመጠራጠር እንዲጀምሩ ሊያደርግ ይችላል።33

ዘለአለማዊ እውነትን ማስተማር

እውነትን ከእግዚአብሔር ስናገኝ ያንን እውቀት ለሌሎች እንድናካፍል ያበረታታናል።34 ይህንን የምናደርገው በክፍል ውስጥ ስናስተምር፣ ልጅን ስንመራ ወይም ከጓደኛ ጋር ስለወንጌል እውነት ስንወያይ ነው።

አላማችን የመንፈስ ቅዱስን የመለወጥ ሀይል በሚጋብዝ መልኩ እውነትን ማስተማር ነው35 ከጌታ እና ከነቢያቱ የተሰጡ ሊረዱ የሚችሉ አንዳንድ ቀላል ግብዣዎችን ላካፍላችሁ።36

  1. የሰማይ አባት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና መሠረታዊ ትምህርታቸውን ማእከላዊ አድርጉ።37

  2. በቅዱሳት መጻህፍት እና በኋለኛው ቀን ነቢያት ትምህርቶች መሰረት ላይ ጽኑ።38

  3. በብዙ ሥልጣናዊ ምስክሮች አማካይነት በተቋቋመው ትምህርት ላይ ተደገፉ።39

  4. ግምቶችን፣ የግል አስተያየቶችን ወይም ዓለማዊ ሃሳቦችን አስወግዱ።40

  5. ሚዛናዊ ግንዛቤን ለማጎልበት የትምህርት ነጥብን በተዛማጅ የወንጌል እውነቶች አውድ አስተምሩ።41

  6. የመንፈስን ተጽዕኖ የሚጋብዙ የማስተማሪያ ዘዴዎችን ተጠቀሙ።42

  7. አለመግባባትን ለማስወገድ ግልጽ በሆነ መንገድ ተነጋገሩ።43

እውነትን በፍቅር መናገር

እውነትን የምናስተምርበት መንገድ በጣም አስፈላጊ ነው። ጳውሎስ “እውነትን በፍቅር” እንድንናገር አበረታቶናል (ኤፌሶን 4፥14–15 ተመልከቱ)። ይህ ማለት እውነት ክርስቶስን በሚመስል ፍቅር ሲተላለፍ ሌላውን ለመባረክ ከሁሉ የተሻለ እድል አለው ማለት ነው።44

ያለ ፍቅር የተነገረ እውነት የመፍረድ፣ የተስፋ መቁረጥ እና የብቸኝነት ስሜትን ያስከትላል። ብዙውን ጊዜ ወደ ብስጭት እና መለያየት አልፎ ተርፎም ግጭት ያስከትላል። በሌላ በኩል እውነት የሌለው ፍቅር ባዶ ነው እንዲሁም የማደግ ተስፋ የለውም።

እውነትም ፍቅርም ለመንፈሳዊ እድገታችን ወሳኝ ናቸው።45 እውነት የዘለአለምን ህይወት ለማግኘት፣ አስፈላጊ የሆኑትን ትምህርቶች፣ መርሆች እና ህጎች የሚያዘጋጅ ሲሆን፣ እውነትን በፍቅር መናገር እውነት የሆነውን ለመቀበል እና በተግባር ለማዋል የሚያስፈልገውን መነሳሳት ይፈጥራል።

በትዕግስት ዘለአለማዊ እውነትን በፍቅር ላስተማሩኝ ሰዎች ለዘለአለም አመስጋኝ ነኝ።

መደምደሚያ

ለማጠቃለል ያህል፣ ለነፍሴ መልህቅ የሆኑትን ዘለአለማዊ እውነቶችን ላካፍል። ዛሬ የተብራሩትን መሰረተ መርሆች በመከተል የእነዚህን እውነቶች እውቀት አግኝቻለሁ።

እግዚአብሔር አፍቃሪ የሰማይ አባታችን እንደሆነ አውቃለሁ።46 እርሱም ሁሉን የሚያውቅ፣47 ሁሉን ቻይ፣48 እና በፍጹም የሚያፈቅር ነው።49 እርሱ የዘለአለም ህይወትን ለማግኘት እና እርሱን እንድንመስል እቅድ ፈጥሯል።50

እንደዚያ እቅድ አካል ከኃጢአት እና ከሞት ያድነን ዘንድ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኳል።51 የአብን ፈቃድ እንድንፈጽም52 እና ሌሎችን እንድንወድ አስተምሮናል።53 ለኃጢአታችን ዋጋን በመክፈል54 በፈቃዱም ነፍሱን በመስቀል ላይ አሳልፎ ሰጥቷል።55 ከሞም በሶስተኛው ቀን ተነሳ።56 በክርስቶስ እና በጸጋው፣ እኛም ከሞት እንነሳለን፣57 ይቅርታ ለማግኘት እንችላለን፣58 እናም በስቃያችን ጥንካሬ ማግኘት እንችላለን።59

ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ቤተክርስቲያኑን አቋቋመ።60 በጊዜ ሂደት፣ ቤተክርስቲያኑ ተለወጠች፣ እውነቶችም ጠፉ።61 ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን እና የወንጌል እውነቶችን በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል በዳግም መለሰ።62 እናም ዛሬ፣ ክርስቶስ በህያዋን ነቢያት እና ሐዋርያት አማካኝነት ቤተክርስቲያኑን መምራት ቀጥሏል።63

ወደ ክርስቶስ ስንመጣ በመጨረሻ “በእርሱ ፍፁማን [ልንሆን]”(ሞሮኒ 10፥32)፣ “የደስታን ሙላት” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥33)ልናገኝ እንዲሁም “አብ ያለውን ሁሉ” ልንቀበል እንደምንችል አውቃለሁ። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥38)። ስለዚህ ዘለዓለማዊ እውነታ በኢየሱስ ክርስቶስ የተቀደሰ ስም እመሰክራለሁ፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. በተጨማሪም መዝሙር 117፥2ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥39ን ተመልከቱ።

  2. “ከአንዳንዶች ጥርጣሬ በተቃራኒ ትክክል እና ስህተት የሚባል ነገር አለ ። በእውነት ፍጹም እውነት—የዘለአለማዊ እውነት አለ። በዘመናችን ካሉት መቅሰፍቶች መካከል አንዱ በጣም ጥቂት ሰዎች ለእውነት ወደየት እንደሚዞሩ የሚያውቁ መሆናቸው ነው” (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ንፁህ እውነት፣ ንፁህ ትምህርት እና ንፁህ ራዕይ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 6)።

  3. ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፥37ን ተመልከቱ።

  4. ሞሮኒ 7፥19ን ተመልከቱ።

  5. 2 ኔፊ 1፥9ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 17፥8 ይመልከቱ።

  6. ያዕቆብ 2፥8ን ተመልከቱ።

  7. መዝሙር 119፥1052 ኔፊ 32፥3

  8. ዮሃንስ 8፥32ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 98፥8 ይመልከቱ።

  9. ዮሀንስ 17፥17ን ይመልከቱ።

  10. 2 ኔፊ 31፥20ን ይመልከቱ።

  11. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥11–1393፥36 ይመልከቱ።

  12. ዮሀንስ 5፥19–207፥168፥2618፥37ሙሴ 1፥6 ይመልከቱ።

  13. አልማ 42፥12–26ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥41 ይመልከቱ

  14. ሙሴ 1፥30–39 ይመልከቱ።

  15. 2 ኔፊ 26፥24 ይመልከቱ።

  16. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥8–9፣ ተመልከቱ።

  17. ዮሀንስ 16፥13ያዕቆብ 4፥13ሞሮኒ 10፥5ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥1475፥1076፥1291፥4124፥97ን ይመልከቱ።

  18. ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 6፥22–238፥2–3ን ተመልከቱ።

  19. ኤርሚያስ 1፥5፣ 7አሞጽ 3፥7ማቴዎስ 28፥16–20ሞሮኒ 7፥31ትምህት እና ቃል ኪዳኖች 1፥3821፥1–643፥1–7ን ይመልከቱ። ነቢይ “በእግዚአብሔር የተጠራ እና ለእርሱ የሚናገር ሰው ማለት ነው። እንደ እግዚአብሔር መልእክተኛ፣ ነቢይ ትእዛዛትን፣ ትንቢቶችን፣ እና ራዕዮችን ከእግዚአብሔር ይቀበላል። ሀላፊነቱም የእግዚአብሔር ፈቃድ እናም እውነተኛ ጸባዩን ለሰው ዘር ማሳወቅና ከእነርሱ ጋር ያለ ግንኙንትን ትርጉም ማሳየት ነው። ነቢይ ኃጢያትን ይወግዛል እናም ስለውጤቱም አስቀድሞ ይናገራል። ጻድቅን ይሰብካል። አንዳንዴም፣ ነቢይ ለሰው ዘር ጥቅም ስለወደፊት አስቀድሞ እንዲናገር ሊነሳሳ ይችላል። የመጀመሪያ ሀላፊነቱ ግን ስለክርስቶስ ምስክርነት መስጠት ነው። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዘደንት ዛሬ የእግዚአብሔር ነቢይ ነው። የቀዳማዊ አመራር አባላት እና አስራ ሁለቱ ሐዋርያት እንደ ነቢያት፣ ባለ ራእዮች እና ገላጭዎች ይደገፋሉ” (የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “ነቢይ፣ የወንጌል ቤተመጻህፍት)። የእነዚህ መሰረታዊ ወርሆች ምሳሌዎች በእነዚህ ህይወቶች ውስጥ ይገኛሉ፦ አዳም (ሙሴ 6፥51–62 ይመልከቱ)፣ ሔኖክ (ሙሴ 6፥26–36 ይመልከቱ)፣ ኖኅ (ሙሴ 8፥19፣ 23–24 ይመልከቱ)፣ አብርሐም (ዘፍጥረት 12፥1–3አብርሐም 2፥8–9 ይመልከቱ)፣ ሙሴ (ዘጸዓት 3፥1–15ሙሴ 1፥1–6፣ 25–26 ይመልከቱ)፣ ጴጥሮስ (ማኤዎስ 16፥13–19 ይመልከቱ)፣ እና ጆሴፍ ስሚዝ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥6–1020፥221፥4–6 ይመልከቱ)።

  20. 2 ጢሞቴዎስ 3፥16ን ተመልከቱ።

  21. ዮሀንስ 8፥442 ኔፊ 2፥18ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥39 ሙሴ 4፥4ን ይመልከቱ።

  22. 1 ኔፊ 10፥19ን ተመልከቱ። ፕሬዘደንት ዳለን ኤች. ኦክስ እንዳስተማሩት፦ “[የእግዚአብሔርን] እውነት ስንፈልግ እና ለዚህ ፍለጋ ምንጮችን በምንመርጥበት ጊዜ መጠንቀቅ አለብን። ዓለማዊ ታዋቂነትን ወይም ሥልጣንን እንደ ብቁ ምንጮች አድርገን መቁጠር የለብንም። … ስለ ሃይማኖት እውነትን በምንፈልግበት ጊዜ ለዚያ ፍለጋ ተስማሚ የሆኑ መንፈሳዊ ዘዴዎችን የሆኑትን ጸሎት፣ የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት፣ እና ቅዱሳት መጻህፍት እና የዘመናችን ነቢያት ቃል ማጥናት መጠቀም አለብን፣” (“እውነት እና እቅዱ፣ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 25)።

  23. ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እንዳስተማሩት፦ “ሐዋርያት እና ነቢያት… የእግዚአብሔርን ቃል ያውጃሉ፣ ነገር ግን በአጠቃላይ ወንዶች እና ሴቶች እና ልጆችም እንኳ ከጸሎት እና ቅዱሳት መጻህፍትን በማጥናት ከመለኮታዊ መነሳሳት መማር እና መመራት እንደሚችሉ እናምናለን። … የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ከሰማይ አባታቸው ጋር ቀጣይነት ያለው ግንኙነትን የሚያመቻች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ተሰጥቷቸዋል። … ይህ ማለት ግን እያንዳንዱ አባል ስለ ቤተክርስቲያን ይናገራል ወይም አስተምህሮዋን መግለፅ ይችላል ማለት አይደለም ነገር ግን እያንዳንዱ የህይወቱን ተግዳሮቶች እና እድሎች ለመቋቋም መለኮታዊ መመሪያ ማግኘት ይችላል” (“የክርስቶስ ወንጌላዊ ትምህርት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2012፣ 89–90፣ ማስታወሻ 2)።

  24. 2 ኔፊ 33፥1–2 ይመልከቱ።

  25. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥28ን ይመልከቱ።

  26. ሞሮኒ 10፥3–5ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 9፥7–984፥85ን ይመልከቱ።

  27. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 5፥3563፥2393፥27–28ን ይመልከቱ። ልባዊ ጥረት ብናደርግም አንዳንዶቻችን በአእምሮ ጤና ተግዳሮቶች የተነሳ መንፈስን ለመስማት ልንታገል እንችላለን። ድብርት፣ ጭንቀት እና ሌሎች የነርቭ ሁኔታዎች መንፈስ ቅዱስን በማወቅ ላይ ውስብስብነትን ይጨምራሉ። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች፣ ጌታ ወንጌልን እንድንኖር ይጋብዘናል፣ እናም ይባርከናል (ሞዛያ 2፥41 ተመልከቱ)። እንደ ቅዱስ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ በአገልግሎት መካፈል ወይም በተፈጥሮ ጊዜ ማሳለፍን የመሳሰሉ ተጨማሪ ተግባራትን መፈለግ እንችላለን፣ ያም የመንፈስ ፍሬዎችን እንድንሰማ (ገላትያ 5፥22–23 ተመልከቱ) እና ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ያጠናክርልናል።

    ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላችን እንደገለጹት፦ “ታዲያ እናንተ ወይም የምትወዷቸው ሰዎች አእምሯዊ ወይም ስሜታዊ ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ምን ምላሽ ትሰጣላችሁ? ከሁሉም በላይ፣ እናንተ ልትረዱት ከምትችሉት በላይ በሚወዳችሁ የሰማይ አባታችሁ ላይ እምነት አይጥፉ። የጌታን መንፈስ ወደ ህይወታችሁ የሚያመጡትን በጊዜ የተፈተኑ የአምልኮ ልምምዶችን በታማኝነት ተከተሉ። ለመንፈሳዊ ደህንነታችሁ ሀላፊነት ያላቸውን ሰዎች ምክር ጠይቁ። የክህነት በረከቶችን ጠይቁ እና በፍቅር ተጠቀሟቸው። በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባንን ውሰዱ እና ፍጹም የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ ተስፋዎች ያዙ። በእግዚአብሔር እመኑ። ሁሉም ሌላ ፍንጭ ተስፋ እንደጠፋ ሲናገር ብዙዎቹ ሲመጡ አይቻለሁ። ተስፋ በምንም አይጠፋም” (“እንደተሰበረ እቃ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 40–41)።

  28. ዮሀንስ 7፥17አልማ 32፥26–34ን ተመልከቱ። በመጨረሻ፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር እስክንረዳ ድረስ እውነትን “በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በስርአት ላይ ስርአት” እንድናገኝ ይፈልጋል (ምሳሌ 28፥52 ኔፊ 28፥30ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6793፥28ን ይመልከቱ)።

  29. 1 ዮሃንስ 1፥9–102፥1–2ን ተመልከቱ።

  30. ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲሁ ገልጸዋል፦ “ዘወትር እና በየቀኑ ንስሃ ላይ ትኩረት ከማድረግ ይበልጥ ነጻ የሚያወጣ፣ ይበልጥ ከፍ ወዳለ ክብር የሚያደርስ እና በግለሰብ ደረጃ ለምናደርገው እድገት ጠቃሚ የሆነ ነገር የለም። ንስሃ አንድ ጊዜ የሚደረግ ክስተት ሳይሆን ሂደት ነው። ለደስታ እና ለአእምሮ ሰላም ዋናው ቁልፍ ነው። ከእምነት ጋር ሲጣመር፣ ንስሐ የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ ኃይል ማግኘት ያስችላል (“የተሻለ ማድረግ እና የተሻልን መሆን እንችላለንሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 67)።

  31. እግዚአብሔር ከእኛ አንዳንድ ዘለአለማዊ እውነቶችን የሚከለክልበትን ሁሉንም ምክንያቶች አላውቅም፣ ነገር ግን ሽማግሌ ኦርሰን ኤፍ. ዊትኒ አስደናቂ ግንዛቤን ሰጥተዋል- “ሳያዩ ማመን የተባረከ ነው፣ በእምነት የሰው ልጅ ምድራዊ ህልውና ልምምድ አንዱ የሆነው ታላቅ መንፈሳዊ እድገት ይመጣል። እውቀት እምነትን በመዋጥ መለማመድን ይከለክላል፣ በዚህም እድገትን ያደናቅፋል። ‘እውቀት ኃይል ነው፤’ እናም ሁሉም ነገር በጊዜው መታወቅ አለበት። ነገር ግን ያለጊዜው ያለ እውቀት—ትክክለኛ ባልሆነ ጊዜ ማወቅ—የዕድገትም ሆነ የደስታ ገዳይ ነው” (“The Divinity of Jesus Christ [የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮትነት]፣” Improvement Era [ማሻሻያ ዘመን]፣ ጥር 1926 (እ.አ.አ)፣ 222፤ በተጨማሪ ሊያሆና፣ ታህሳስ 2003 (እ.አ.አ) ተመልከቱ)።

  32. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥5–10ን ተመልከቱ። እንዲሁም ጌታ ሃይረም ስሚዝን “ቃሌን ለማወጅ አትፈልግ፣ ነገር ግን አስቀድመህ ቃሌን ለማግኘት ፈልግ። … ዝም በል [እና] ቃሌን አጥና” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥21–22)። ነቢዩ አልማ ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ምሳሌን ሰጥቷል፦ “አሁን እነዚህ ሚስጥሮች ሙሉ በሙሉ ለእኔ አልታወቁኝም፤ ስለዚህ ይበልጥ ከመናገር ልቆጠብ” (አልማ 37፥11)። ለልጁ ቆሪያንተንም “እግዚአብሔር እራሱ ካልሆነ በቀር ማንም የማያውቃቸው ብዙ በአምላክ የተደበቁ ምስጢሮች አሉ” (አልማ 40፥3) በማለት አብራርቷል። እኔ ደግሞ ኔፊ ሊመልስ ያልቻለውን ጥያቄ ሲያቀርብ በሰጠው ምላሽ ብርታት አግኝቻለሁ “[እግዚአብሔር] ልጆቹን እንደሚወድ አውቃለሁ፤ ይሁን እንጂ የሁሉን ነገሮች ትርጉም አላውቅም” (1 Nephi 11፥17)።

  33. በተመሳሳይ፣ ባህላዊ ወጎች ወንጌላዊ ትምህርቶች ወይም ፖሊሲ አይደሉም። ወንጌላዊ ትምህርትን እና ፖሊሲን እንድንከተል የሚረዱን ከሆነ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን በእውነተኛ መርሆዎች ላይ ካልተመሰረቱ መንፈሳዊ እድገታችንን ሊያደናቅፉ ይችላሉ። በኢየሱስ ክርስቶስ ያለ እምነታችንን የማይገነቡ ወይም ወደ ዘለአለማዊ ህይወት እንድናድግ የማይረዱን ወጎችን ማስወገድ አለብን።

  34. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 15፥588፥77–78ን ይመልከቱ።

  35. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥21–23ን ተመልከቱ።

  36. በየካቲት 2023 (እ.አ.አ) በቀዳሚ አመራር እና በአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ ከጸደቀው “የትምህርትን ንጽህና ማሪጋገጫ መርሆዎች” ከተባለው ሰነድ የተወሰደ።

  37. 1 ኔፊ 15፥14ን ተመልከቱ። ጌታ አገልጋዮቹ የወንጌሉ ዋና ክፍል ባልሆኑት መመሪያዎች ወይም ሀሳቦች ላይ ከማተኮር እንዲቆጠቡ አዝዟቸዋል፤ “እናም የተወሳሰበ የቤተክርስቲያን ትምህርቶችን አትናገር፣ ነገር ግን ንስሀን እናም በአዳኛችን እምነትን፣ በጥምቀት እናም በእሳት አዎን እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃጢአት እንደሚሰረይ አውጅ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥31)።

    ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን በአዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ እና በቤዛነት መስዋዕቱ ስጦታ ላይ እናተኩር” በማለት ገልጿል፡። ይህ ከራሳችን ህይወት ልምድ መናገር ወይም የሌሎችን ሃሳቦች ማካፈል አንችልም ማለት አይደለም። ርዕሰ ጉዳያችን ስለ ቤተሰብ ወይም አገልግሎት ወይም ቤተመቅደሶች ወይም የቅርብ ጊዜ ምስዮን ሊሆን ቢችልም፣ ሁሉም ነገር… ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መጠቆም አለበት” (“ስለ ክርስቶስ እንናገራለንሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 89–90)።

  38. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥2–3፣ 8ን ተመልከቱ። ነቢዩ አልማ ወንጌልን እንዲሰብኩ የተሾሙትን “እርሱ ካስተማራቸው እና በቅዱሳን ነቢያት አፍ ከተናገራቸው ነገሮች በቀር ምንም እንዳያስተምሩ” (ሞዛያ 18፥19) መክሯቸዋል።

    ፕሬዘደንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ፡ “የቤተክርስቲያኗን መሰረታዊ ትምህርቶች በመደበኛ ስራዎች ልክ እንዳሉት እና ትምህርቶችን የማወጅ ሀላፊነት ባለባቸው በነቢያት እንደሚያስተምሩት ማስተማር አለብን” ብለዋል፣ (“ጌታ መከሩን ያበዛል” [ምሽት ከአጠቃላይ ባለስልጣን ጋር፣ የካቲት 6 ቀን 1998 (እ.አ.አ)፣ በTaching Seminary: Preservice Readings [2004 (እ.አ.አ)]፣ 96)።

    ሽማግሌ ዲ ቶድ ክሪስቶፈርሰን “ዛሬ በቤተክርስቲያኗ፣ እንደ ጥንት፣ የክርስቶስን ትምህርት መመስረት ወይም ከትምህርት ዞር የሚለውን ማስተካከል የመለኮታዊ ራዕይ ስራ ነው” በማለት መስክረዋል። (“The Doctrine of Christ [የክርስቶስ ወንጌላዊ ትምህርት]፣” 86)

  39. 2 ቆሮንቶስ 13፥12 ኔፊ 11፥3ኤተር 5፥4ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥28ን ተመልከቱ። ሽማግሌ ኒል ኤል. አንደርሰን እንዲህ ብለዋል፦ “ጥቂቶች ከአስርተ አመታት በፊት በአንድ የቤተክርስትያን መሪ የተናገረ፣ ከእኛ ትምህርት ጋር የማይጣጣም የሚመስል ቃል ሲያገኙ እምነታቸውን ይጠራጠራሉ። የቤተክርስቲያንን ትምህርት የሚመራ አንድ ጠቃሚ መሰረታዊ መርህ አለ። ወንጌላዊ ትምህርትን 15ቱም የቀዳሚ አመራር አባላት እና የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት አባላት ያስተምራሉ። በአንድ ንግግር ግልጽ ባልሆነ አንቀጽ ውስጥ አልተደበቀም። እውነተኛ መሰረታዊ መርሆዎችን ብዙዎች በተደጋጋሚ ያስተምራሉ። የእኛን ወንጌላዊ ትምህርት ለማግኘት አስቸጋሪ አይደለም” (“Trial of Your Faith [የእምነታችሁ መፈተን]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2012 (እ.አ.አ)፣ 41)።

    ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰንም በተመሳሳይ ሁኔታ እንዳስተማሩት፣ “የቤተክርስትያን መሪ የሚናገረው እያንዳንዱ ቃል፣ ያለፈውም ሆነ አሁን፣ የግድ ትምህርትን ያካተተ እንዳልሆነ መታወስ አለበት። አንድ መሪ በአንድ ጊዜ የሚሰጠው መግለጫ ምንም እንኳን በደንብ የታሰበበት ቢሆንም፣ ለመላው ቤተክርስቲያን ይፋዊ ወይም አስገዳጅነት የሌለው የግል አስተያየትን የሚወክል እንደሆነ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የምንረዳው ነው” (“የክርስቶስ ወንጌላዊ ትምህርት፣” 88)።

  40. 3 ኔፊ 11፥32፣ 40ን ተመልከቱ። ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ እንዲህ አሉ፦ “የቤተክርስትያኗን ትምህርት በንጽህና ስለመጠበቅ አስፈላጊነት አስቀድሜ ተናግሬ ነበር። … ለዚህ ጉዳይ እጨነቃለሁ። ትምህርትን በማስተማር ወቅት ትናንሽ ስህተቶች ወደ ትልቅ እና መጥፎ ውሸት ሊመሩ ይችላሉ” (Teachings of Gordon B. Hinckley [1997 (እ፣አ፣አ)]፣ 620)።

    ፕሬዘደንት ዳልን ኤች. ኦክስ እንዳስጠናቀቁት፣ አንዳንድ “ከነቢይ ትምህርቶች ጥቂት ዓረፍተ ነገሮችን መርጠው የፖለቲካ አጀንዳቸውን ወይም ሌላ የግል ዓላማቸውን ለመደገፍ የሚጠቀሙባቸው አሉ። … የነቢይን ቃል የግል አጀንዳን ፖለቲካዊም ሆነ የገንዘብ ወይም ሌላ ነገር ለመደገፍ ማጣመም ነቢዩን ለመጠምዘዝ መሞከር እንጂ እርሱን መከተል አይደለም” (“Our Strengths Can Become Our Downfall” [Brigham Young University devotional፣ June 7፣ 1992]፣ 7፣ speeches.byu.edu).

    ፕሬዘደንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ እንዳስጠናቀቁን፦ “መንፈስ ቅዱስ እውነት መሆኑን ሲያረጋግጥ ትምህርት ኃይሉን ያገኛል። … መንፈስ ቅዱስ ስለሚያስፈልገን፣ እውነተኛውን ትምህርት ከማስተማር ባለፈ እንዳንሄድ መጠንቀቅ አለብን። መንፈስ ቅዱስ የእውነት መንፈስ ነው። የእርሱ ማረጋገጫ የሚጋበዘው ግምቶችን ወይም የግል ትርጓሜዎችን በማስወገድ ነው። ይህን ማድረግ ከባድ ሊሆን ይችላል። … አዲስ ወይም ቀስቃሽ ነገር መሞከር ፈታኝ ነው። ነገር ግን እውነተኛውን ትምህርት ብቻ ለማስተማር ስንጠነቀቅ መንፈስ ቅዱስ አጋራችን እንዲሆን እንጋብዛለን። የሐሰት አስተምህሮቶች ጋር መጠጋትን ከምንከላከላቸው በጣም አስተማማኝ መንገዶች መካከል አንዱ በቀላል መንገድ ለማስተማር መምረጥ ነው። ደህንነት የሚገኘው በቀላልነት ነው፣ የሚጠፋውም ትንሽ ነው” [“ትምህርት የማስተማር ሃይልሊያሆና፣ ሰኔ 1999 (እ.አ.አ)፣ 86]።

    ሽማግሌ ዴል ጂ. ሬንለንድ እንዳስተማሩት፦ “ታላቅ እውቀትን መሻት የመንፈሳዊ እድገት ጠቃሚ አካል ነው፣ ነገር ግን እባካችሁን ተጠንቀቁ። ምክንያት ራዕይን አይተካም። ግምታዊ ምክንያት ወደ ታላቅ እውቀት አይመራም፣ ነገር ግን ወደ መታለል ወይም ትኩረታችንን ከተገለጠው ሊያስቀይር ይችላል” (“መለኮታዊ ተፈጥሯችሁ እና ዘለአለማዊ እጣ ፈንታሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 70).

  41. ማቴዎስ 23፥23ን ይመልከቱ። ፕሬዘደንት ጆሴፍ ፍ. ስሚዝ እንዳስጠነቀቁት፦ “የእውነትን ሽርፍራፊ ወስዶ እንደ ሙሉ ነገር መቁጠር ሞኝነት ነው። … ሁሉም የተገለጡ የክርስቶስ ወንጌል መርሆች በደህንነት እቅድ ውስጥ አስፈላጊ እና ወሳኝ ናቸው።” በመቀጠልም እንዲህ ሲል አብራርተዋል፦ “ከእነዚህ አንዱን በመውሰድ ከጠቅላላው የወንጌል እውነት እቅድ መነጠል፣ ልዩ የጊዜ ማሳለፊያ ማድረግ እናም ለደህንነታችን እና ለእድገታችን መመካት ጥሩ ፖሊሲም ሆነ ትክክለኛ ትምህርት አይደለም። … ሁሉም አስፈላጊ ናቸው” (የወንጌል ትምህርት፣ 5ኛ እትም [1939 (እ.አ.አ)]፣ 122)።

    ሽማግሌ ኒል ኤ. ማክስዌል እንደገለጹት፦ “የወንጌል መርሆች… ጥምረትን ይጠይቃሉ። አንዳቸው ከሌላው ሲነጠሉ ወይም ሲገለሉ፣ የሰዎች ትርጓሜ እና የእነዚህ አስተምህሮቶች አተገባበር የማይጨበጥ ሊሆን ይችላል። ፍቅር በሰባተኛው ትእዛዝ ካልተረጋገጠ ሥጋዊ ሊሆን ይችላል። አምስተኛው ትእዛዝ ወላጆችን ለማክበር የሚሰጠው ትኩረት በመጀመሪያው ትእዛዝ ካልተረጋገጠ በቀር፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ለተሳሳቱ ወላጆች ያለ ቅድመ ሁኔታ ታማኝነትን ሊያመጣ ይችላል። … ትዕግስት እንኳን ‘በመንፈስ ቅዱስ በሚገፋፋበት ጊዜ በመገሰጽ’(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥43) ሚዛናዊ ይሆናል [“እነሆ ጠላትም ተባብሯል፣” ኢንዛይን፣ ግንቦት 1993 (እ.አ.አ) 78–79]።

    ፕሬዘደንት ሜሪየን ጂ. ሮምኒ እንዳብራሩት፣ “[ቅዱሳት መጻህፍትን] በኢየሱስ በተመከሩት መሰረት ለማወቅ ዓላማ መፈለግ፣ አስቀድሞ የተወሰነ መደምደሚያን ለመደገፍ ወደ አገልግሎት ሊጫኑ የሚችሉ ጥቅሶችን ለማግኘት ከማደን የራቀ ነው” (“የታላቅ ዋጋ መዛግብት”፣ ኤንዛይን፣ መስከረም 1980 (እ.አ.አ)፣ 3)።

  42. 1 ቆሮንቶስ 2፥4ሞሮኒ 6፥9 ይመልከቱ። ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ መንፈሳዊ መታነጽ በሚመራ መንገድ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማስተላለፍ አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል፦ “ጌታ ‘እውነትን ሊያስተምር በተላከው በአጽናኝ መንፈስ’ ወንጌልን ከማስተማር የበለጠ አጽንዖት የሚሰጥ ምክር ለቤተክርስቲያን አልሰጠም። ወንጌልን ‘በእውነት መንፈስ’ እናስተምራለን? እንዲህም ጠይቋል። ወይንስ የምናስተምረው ‘በሌላ መንገድ [ነው]? በሌላ መንገድ ከሆነ፣ ከእግዚአብሔር አይደለም’ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥14፣ 17–18) በማለት ያስጠነቅቃል። … የሰማይ መንፈስ ሳይነሳሳ ዘለአለማዊ ትምህርት ሊካሄድ አይችልም። … አባሎቻችን የሚፈልጉት ይህንን ነው። … እምነታቸው እንዲጠናከር እና ተስፋቸው እንዲታደስ ይፈልጋሉ። እነርሱ፣ ባጭሩ፣ የእግዚአብሔርን መልካም ቃል እንዲመገቡ፣ በሰማያት ሃይል እንዲበረቱ ይፈልጋሉ” (“ከእግዚአብሔር የመጣ አስተማሪኢንዛይን፣ ግንቦት 1998 (እ.አ.አ)፣ 26)።

  43. አልማ 13፥23ን ተመልከቱ። ስለሰማይ አባታችን ሲናገሩ፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንደመሰከሩት፣ “እርሱ የሚያነጋግረው በቀላል፣ በጸጥተኛ፣ እናበሚያስደንቅ ሁኔታ ግልፅ ሆኖ ጋራ ለመገባት በማንችልበት መንገድ ነው” [“እሱን ስሙትሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ) 89]።

  44. መዝሙር 26፥3ሮሜ 13፥101 ቆሮንቶስ 13፥1–81 ዮሀንስ 3፥18ን ይመልከቱ።

  45. መዝሙር 40፥11ን ይመልከቱ።

  46. ሮሜ 8፥16ን ይመልከቱ።

  47. 1 ሳሙኤል 2፥3ማቴዎስ 6፥82 ኔፊ 2፥24 9፥20ን ይመልከቱ።

  48. ዘፍጥረት 17፥1ኤርምያስ 32፥171 ኔፊ 7፥12አልማ 26፥35ን ይመልከቱ።

  49. ኤርምያስ 31፥31 ዮሀንስ 4፥7–10አልማ 26፥37 ተመልከቱ።

  50. 2 ኔፊ 9ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥17–31ሙሴ 6፥52–62ን ተመልከቱ።

  51. ዮሃንስ 3፥161 ዮሃንስ 4፥9–10ን ተመልከቱ።

  52. ዮሀንስ 8፥293 ኔፊ 27፥13 ይመልከቱ

  53. ዮሃንስ 15፥121 ዮሃንስ 3፥11ን ተመልከቱ።

  54. ሉቃስ 22፥39–46ን ተመልከቱ።

  55. ዮሃንስ 19፥16–30ን ተመልከቱ።

  56. ዮሐንስ 20፥1–18ን ይመልከቱ።

  57. 1 ቆሮንቶስ 15፥20–22ሞዛያ 15፥20–2416፥7–9ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥16–17

  58. የሐዋሪያት ስራ 11፥17–181 ጢማቴዎስ 1፥14–16አልማ 34፥8–10ሞሮኒ 6፥2–3፣ 8ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥13–19 ይመልከቱ።

  59. ማቴዎስ 11፥28–302 ቆሮንቶስ 12፥7–10ፊልጵስዮስ 4፥13አልማ 26፥11–13 ይመልከቱ።

  60. ማቴዎስ 16፥18–19ኤፌሶን 2፥20ን ይመልከቱ።

  61. ማቴዎስ 24፥24የሐዋርያት ስራ 20፥28–30ን ይመልከቱ።

  62. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥1–421፥1–727፥12110135፥3የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥1–20 ይመልከቱ

  63. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥14፣ 3843፥1–7107፥91–92 ይመልከቱ።