አጠቃላይ ጉባኤ
ለመቀበል እና ለመከተል ትሁት መሆን
የጥቅምት 2023 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ለመቀበል እና ለመከተል ትሁት መሆን

ትህትና ወደ እግዚአብሔር ፊት ለመመለስ ለመዘጋጀት አስገዳጅ መስፈርት ነው።

በአልማ አምስተኛ ምእራፍ ውስጥ እንደዚህ አይነት እራስን የሚገመግም ጥያቄ ተጠይቋል፣ “በዚህ ጊዜ ለመሞት ብትጠሩ በራሳችሁ፣ እኔ በሚገባ ትሁት ነኝን?”1 ያ ጥያቄ ወደ እግዚአብሔር ፊት ለመመለስ ለመዘጋጀት ትህትና አስገዳጅ መስፈርት እንደሆነ ያሳያል።

ሁላችንም ብቁ በሆነ መልኩ ትሁት እንደሆንን ማሰብ እንወዳለን፣ ነገር ግን በህይወት ውስጥ የተወሰኑ ልምዶች ኩሩው ተፈጥሯዊው ወንድ ወይም ሴት ብዙ ጊዜ በውስጣችን እንዳለ እንድንገነዘብ ያደርገናል።

ከአመታት በፊት፣ ሁለት ሴት ልጆቻችን እቤት በሚኖሩበት ጊዜ፣ ሃላፊ ሆኜ እሰራበት የነበረውን የኩባንያውን የቢዝነስ ክፍል እነሱን እና ባላቤቴን ላሳያቸው ወሰንኩኝ።

እውነተኛው አላማዬ ግን የነበረው ከቤታችን በተለየ መልኩ ሁሉም ያዘዝኳቸውን ነገር ሳያንገራግሩ የሚፈፅሙበት ቦታ እንደሆነ ላሳያቸው ነበር። ከፊት ባለው በር ላይ ስንደርስ በሩ ባለመክፈቱ ተገርሜ ነበር፣ ብዙ ጊዜ መኪናዬ በሩ ጋር ሲደርስ በራሱ ይከፈት ነበር። በምትኩ፣ በህይወቴ አይቼው የማላውቀው የደህንነት ጥበቃ ሰራተኛ ወደ መኪናው መጣና የኩባንያዬን መታወቂያ ጠየቀኝ።

ወደ ቅጥር ግቢው ውስጥ በመኪናዬ ለመግባት መታወቂያ አስፈልጎኝ እንደማያውቅ ነገርኩት እና “ከማን ጋር እያወራህ እንዳለህ ታቃለህን? ስል ታዋቂውን የኩራት ሰው ጥያቄ ጠየቅኩት።

ለእርሱም እንዲህ ሲል መለሰ፣ “የኩባንያ መታወቂ ስለሌለህ ማንነትህን ማወቅ አልችልም እና እኔ በዚህ በር ላይ ሳለው ካለ ትክክለኛ መታወቂያ ወደ ቅጥር ግቢው ውስጥ ለመግባት አይፈቀድልህም።”

በኋላ መስታወቱ በመመልከት ሴት ልጆቼ ምን አስተያየት እንዳላት ለማየት ፈለኩኝ፣ ነገር ግን እነርሱ በዚያ ቅጽበት እያንዳንዷን ደቂቃ እየተዝናኑበት እንደነበረ አውቄ ነበር! ከጎኔ የነበረችው ባለቤቴ ባህሪዬን በመቃወም ጭንቅላቷን እያነቃነቀች ነበር። ከዚያም የመጨረሻው አማራጬ የጥበቃ ሰራተኛውን በመጥፎ ሁኔታ ስላናገርኩት በጣም ይቅርታን መጠየቅ ነበር። “ይቅርታ ተደርጎልሃል፣ ነገር ግን ካለ ድርጅቱ መታወቂያ ዛሬ መግባት አትችልም” አለ።

ትሁት ላለመሆን ስንመርጥ እንዋረዳለን፦ ምናልባት ይህንን ጠቃሚ ትምህርት በመማር መታወቂያዬን ለማምጣት በዝግታ ወደ ቤት ነዳሁ።

በምሳሌ መፅሃፍ ውስጥ ይህን እናገኛለን፣ “ሰውን ትእቢቱ ያዋርደዋል፣ መንፈሱን የሚያዋርድ ግን ክብርን ይቀበላል።”2 ትህትናን ለማዳበር በወንጌል አውድ ውስጥ በትክክል ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ይኖርብናል።

የተወሰኑ ሰዎች ትሁት መሆንን ከሌሎች ነገሮች ለምሳሌ ድሃ ከመሆን ጋር ያመሳስሉታል። ነገር ግን ድሃ ሆነው ኩሩ የሆኑ እና ሃብታም ሆነው ትሁት የሆኑ ብዙዎች አሉ። በጣም አይናፋር የሆኑ ወይም ዝቅ ያለ የራስ መተማመን ያላቸው ሌሎች ሰዎች ትሁት የሆነ የውጪ ገጽታ ሊኖራቸው ይችላል ነገር ግን አንዳንዴ ከስር በኩራት የተሞሉ ናቸው።

ታዲያ ትህትና ምንድን ነው? ወንጌሌን ስበኩ እንደሚለው. “ለጌታ ፍቃድ እራስን ለመስጠት ፍቃደኛ መሆን ማለት ነው።… ሊማር የሚችል አይነት ሰው ማለት ነው። … [ይህም] መንፈሳዊ እድገት ለማድረግ ሃይል የሚሰጥ ወሳኝ ነገር ነው።”3

በዚህ ክርስቶስ መሰል ባህሪ ለማዳበር በእርግጥ ለሁላችንም ብዙ እድሎች አሉ። የነብያችንን ምክር በመከተል እንዴ ትሁት እንደሆንን ወይም መሆን እንዳለብን በመጀመሪያ ማንሳት እፈልጋለሁ። ለእኛ በግለሰብ ደረጃ የሚጠየቅ ድንገተኛ ጥያቄ ይህ ሊሆን ይችላል፦

  • በሁሉም መስተጋብራችን ውስጥ የቤተክርስቲያኗን ሙሉ ስም እንጠቅሳለንን? ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፣ “የጌታን ስም ከጌታ ቤተክርስቲያን ማውጣት ለሰይጣን ታላቅ ድል ነው።”4

  • የነቢያችንን ልዩ ግብዣ በመቀበል እግዚአብሄር በህይወታችን እንዲያሸንፍ እየፈቀድን ነውን? “በዛሬው ጊዜ በየትኛውም ቦታ ያሉ አባሎቻችን የጭፍን ጥላቻ አመለካከቶችን እና ድርጊቶችን በፍጥነት ትተው እንዲወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ።”5

  • ነብያችን እንዳስተማሩት፦የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ከሰዎች ፍልስፍና በላይ በማመን አለምን እያሸነፍን ነውን?6

  • ለሰዎች እና ስለ ሰዎች አወንታዊ ነገሮችን በመናገር ሰላም ፈጣሪዎች ሆነናልን? ፕሬዘደንት ኔልሰን ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ የሚከተለውን አስተምረውናል፦ “ፊት ለፊቱም ሆነ ከኋላ ስለሌላ ሰው ልንለው የምንችለው ምግባረ መልካም፣ የሚያስደስት ወይም መልካም ሃተታ ወይም ምስጋና የሚያሰጥ ማንኛውም ነገር ካለ—ይህ የእኛ የግንኙነት መስፈርት መሆን አለበት።”7

እነዚህ ቀላል ግን ሃይለኛ መመሪያዎች ናቸው። አስታውሱ፣ የሙሴ ሰዎች ለመፈወስ ማድረግ የነበረባቸው ከፍ ያደረገውን የነሃስ እባብ በትር መመልከት ነበር። 8 ነገር ግን “በድርጊቱ ቀላልነት የተነሳ የጠፉ ብዙዎች ነበሩ።”9

በዚህ ጉባኤ ውቅት የነቢያቶቻችንን እና የሐርያቶቻችንን የማይታክት ምክር ሰምተናል እንዲሁም ገና እንሰማለን። ትህትናን ለማዳበር እና ጠንካራ ሃሳቦቻችንን ጌታ በእነዚህ በተመረጡ መሪዎች አማካኝነት በሚናገረው የበለጠ ጠንካራ በሆነ እምነት የምንተካበትጥሩ አጋጣሚ ነው።

ከሁሉም በላይ፣ ትህትናን በማዳበር ውስጥ፣ በራሳችን ጥረት ብቻ ችግሮቻችንን ማሸነፍ ወይም ሙሉ አቅማችንን ማሳካት እንደማንችል መረዳት እና መቀብል ይኖርብናል። በአለም ዙሪያ ያሉ አነቃቂ ተናጋሪዎች፣ ፀሃፊዎች፣ አሰልጣኞች እና ተጽእኖ ፈጣሪዎች በተለይም በዲጂታል መድረክ ላይ ያሉት፣ ሁሉም ነገር በእኛ እና በተግባሮቻችን ላይ የተመሰረቱ ናቸው ይላሉ። አለም በስጋ ክንድ ይተማመናል።

ነገር ግን ዳግም በተመለሰው ወንጌል አማካኝነት በሰማይ አባት በጎነት እና በአዳኛችን የሃጢያት ክፍያ ላይ በደንብ ጥገኛ እንደሆንን ተምረናል “ምክንያቱም በጸጋ የምንድነው የምንችለውን ካደረግን በኋላ እንደሆነ እናውቃለንና።”10 ለዚያ ነው ከእግዚአብሔር ጋር ቃልኪዳኖችን መግባት እና መጠበቅ በጣም ጠቃሚ የሆነው፣ ይህን ማድረግ በሃጢያት ክፍያው አማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስን የሚፈውስ፣ የሚያስችል እና የሚፈጽም ሃይል ሙሉ አቅርቦት ይሰጠናል።

በየሳምንቱ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባን መካፈል እና በተደጋጋሚ በቤተመቅደስ ውስጥ ማምለክ እና በሥርአቶች ውስጥ መሳተፍ እንዲሁም ቃልኪዳኖችን መቀበል እና ማደስ በሰማይ አባት እና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ጥገኛ መሆናቸንን እንደምንገነዘብ ምልክት ነው። ያ በመላ ችግሮቻችን ውስጥ ይረዳን ዘንድ የእነርሱን ሃይል በህይወታችን ውስጥ ይጋብዛል እናም በመጨረሻ የተፈጠርንበትን አላማ ያሳካል።

ብዙም ሳይርቅ የትህትናዬ ደረጃ እና በጌታ ላይ ያለኝን ጥገኝነት መረዳቴ በድጋሚ ተፈተነ። መፍትሄ ለመስጠት በጣም ከባድ ሁኔታ ወደሆነበት ቦታ አጭር በረራ ለማድረግ ወደ አየር ማረፊያ በታክሲ እየሄድኩኝ ነበር። የቤተክርስቲያን አባል ያልሆነው የታክሲ ሹፌር በመስታወቱ ውስጥ አየኝና፣ “ዛሬ ደህና እንዳልሆንክ ማየት እችላለሁ!” አለኝ

“ማየት ትችላለህ?” ብዬ ጠየኩኝ።

“በሚገባ” አለ። ከዚያም እንዲህ የሚል መልስ ሰጠ፣ “አንተ በዙሪያህ በጣም አሉታዊ ስሜት ልይገኛል!”

በጣም ከባድ ሁኔታ እንዳጋጠመኝ ገለጽኩለት እናም እንዲህ ብሎ ጠየቀኝ፣ “መፍትሄ ለመስጠት ባለህ አቅም ሁሉን ነገር አድርጋሃል?”

የተቻለኝን ነገር በሙሉ እንዳደረኩኝ መለስኩኝ።

እሱ ከዚያም ልረሳው የማልችለውን አንድ ነገር እንዲህ አለ፣ “ስለዚህ ይህን ለእግዚአብሔር ተወው እና ሁሉም ነገር ይሳካል።”

“ከማን ጋር እያወራህ መሆኑን ታውቃለህን?” የሚለውን ጥያቄ ለመጠየቅ ተፈትኜ እደነበር እናዘዛለው። ነገር ግን አላደረኩትም! ያደረኩት ነገር ቢኖር በዚያ የአንድ ሰአት በረራ ውስጥ መለኮታዊ እርዳታ በመጠየቅ እራሴን በጌታ ፊት ትሁት ማድረግ ነበር። ከአውሮፕላኑ ስወርድ፣ መፍትሄ የሚፈልገው ከባዱ ሁኔታ መስመሩን እንደያዘ እና የኔ መገኘት ከአሁን በኋላ አስፈላጊ እንዳልሆነ ተማርኩኝ።

ወንድሞች እና እህቶች የጌታ ትእዛዝ፣ ግብዣ እና ቃልኪዳን ግልጽ እና አጽናኝ ነው፦ “ትሁት ሁን፤ እና ጌታ አምላክህ እጅህን ይዞ ይመራሀል፣ እና ለጸሎቶችህም መልስ ይሰጥሀል።”11

የነቢያቶቻችንን ምክር በመከተል ትሁት እንሁን በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተቀበልናቸው ሥርአቶች እና ቃልኪዳኖች አማካኝነት እግዚአብሔር እና ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እኛን መቀየር እንደሚችሉ፣ በዚህ ህይወት ውስጥ ወደ ተሻለ ማንነት እንደሚቀይሩን እና አንድ ቀን በክርስቶስ ፍጹም እንደሚያደርጉን እንቀበል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።