ቅዱሳት መጻህፍት
ሞሮኒ ፬


ምዕራፍ ፬

ሽማግሌዎች እና ካህናት የቅዱስ ቁርባንን ዳቦ እንዴት እንደሚባርኩት ተገልጿል። ፬፻–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ሽማግሌዎቻቸው እናም ካህናቶቻቸው የክርስቶስን ስጋና ደም ለቤተክርስቲያን በመባረክ የሚያስተላልፉት ስርዓት፤ እናም በረከቱንም የሚያደርጉት እንደ ክርስቶስ ትዕዛዝ ነው፣ ስለዚህ ስርዓቱም ትክክል እንደሆነም እናውቃለን፤ እናም ሽማግሌው ወይም ካህኑ ይባርኩታል—

እናም ከቤተክርስቲያኗ አባላትም ጋር ይንበረከካሉ፣ እናም በክርስቶስ ስምም እንዲህ ሲሉ ወደ አብ ይፀልያሉ፥

አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ዳቦ ለሚቋደሱት ነፍሳት ሁሉ የልጅህን አካል በማስታወስ እንዲበሉት እና፣ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ እነርሱ የልጅህን ስም በላያቸው ላይ ለመውሰድ ፈቃደኞች መሆናቸውን፣ እና ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱና እርሱ የሰጣቸውን ትእዛዛት እንደሚጠብቁ ለአንተም ይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ መንፈስ ሁልጊዜ እንዲኖራቸው ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሃለን። አሜን።