ምዕራፍ ፮
ኔፊ ስለ እግዚአብሔር ነገሮች ፃፈ—የኔፊ ዓላማ ሰዎችን ወደ አብርሃም አምላክ መጥተው እንዲድኑ ማስረዳት ነው። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እና አሁን እኔ፣ ኔፊ፣ የአባቶቼን የትውልድ ሀረግ በዚህ ሀየመዝገቤ ክፍል አልፅፍም፣ በማንኛውም ጊዜ ቢሆን በዚህ በምፅፍበት ለሰሌዳ ላይ አልፅፈውም፤ ሐአባቴ ባቆየው መዝገብ ላይ ተፅፏልና፤ ስለዚህ በዚህ ሥራ ውስጥ አልፅፈውም።
፪ እኛ ሀየዮሴፍ ትውልዶች ነን ማለት ብቻ ይበቃኛል።
፫ ሁሉንም የአባቴን ነገሮች በመፃፍ ጥንቁቅ መሆኔ ልዩነት አያመጣም፣ ሀበእነዚህ ሰሌዳ ላይ መፃፍ አይችሉምና፣ እኔ የእግዚአብሔርን ነገሮች ለመፃፍ ቦታውን እፈልገዋለሁና።
፬ ሙሉ አላማዬም ሰዎችን ወደ አብርሃም አምላክ፣ ወደ ይስሀቅ አምላክና፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ሀእንዲመጡና እንዲድኑ ለለማሳመን ነውና።
፭ ስለዚህ፣ ለዓለም ሀአስደሳች የሆኑትን ነገሮች እኔ አልፅፍም፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔርና ከዓለም ላልሆኑት የሚያስደስቱ ነገሮችን እፅፋለሁ።
፮ ስለዚህ ሰሌዳዎቹን ለሰው ልጆች ዋጋ በሌላቸው ነገሮች እንዳይሞሏቸው ለዘሮቼ ትዕዛዝን እሰጣለሁ።