ቅዱሳት መጻህፍት
፩ ኔፊ ፫


ምዕራፍ ፫

የሌሂ ወንዶች ልጆች የነሀስ ሰሌዳዎቹን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ—ላባን ሰሌዳዎቹን አልሰጥም አለ—ኔፊ ወንድሞቹን ገሰፀ እና አበረታታ—ላባን ንብረታቸውን ቀማቸው እናም ሊገድላቸውም ሞከረ—ላማንና ልሙኤል ኔፊንና ሳምን መቷቸው፣ እናም መልአክ ገሰፃቸው። ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

እና እንዲህ ሆነ እኔ፣ ኔፊ፣ ከጌታ ጋር ከተነጋገርኩ በኋላ ወደ አባቴ ድንኳን ተመለስኩ።

እናም እንዲህ ሆነ እርሱ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ እነሆ ሕልምን አልሜአለሁ፣ በእርሱም ጌታ አንተና ወንድሞችህ ወደ ኢየሩሳሌም እንድትመለሱ አዞኛል።

እነሆም ላባን የአይሁዶችን መዝገብና ደግሞም የቅድመ አባቶቼን የትውልድ ሐረግ መጽሐፍ አለው፣ እናም እነርሱ በነሐስ ሰሌዳ ላይ የተቀረፁ ናቸው።

ስለዚህ አንተና ወንድሞችህ ወደ ላባን ቤት ሄዳችሁ መዝገቦቹን ፈልጋችሁ ወደዚህ ወደ ምድረበዳ እንድታመጡዋቸው ሲል ጌታ አዞኛል።

እናም አሁን እነሆ ወንድሞችህ ከእነርሱ የፈለግሁትን ነገር ከባድ ነው በማለት አጉረመረሙ፣ ነገር ግን እነሆ ይህን ከእነርሱ የፈለኩት እኔ አይደለሁም፣ ነገር ግን ይህ የጌታ ትዕዛዝ ነው።

ስለዚህ ሂድ ልጄ፣ አንተ ስላላጉረመረምክ በጌታ የተደገፍክ ትሆናለህ።

እናም እንዲህ ሆነ እኔ፣ ኔፊ፣ አባቴን እንዲህ አልኩት፥ እሄዳለሁ፣ ጌታ ያዘዘኝንም ነገሮች አደርጋለሁ፣ ምክንያቱም ጌታ ያዘዛቸውን ትዕዛዛት የሚሟሉበትን መንገድ ካላዘጋጀ በቀር ለሰው ልጆች ትዕዛዛትን እንደማይሰጥ አውቃለሁና።

እናም እንዲህ ሆነ አባቴ እነዚህን ቃላት በሰማ ጊዜ እጅግ ተደሰተ፣ እኔም በጌታ መባረኬን አወቋልና።

እና እኔ፣ ኔፊና ወንድሞቼ ድንኳናችንን ይዘን ወደ ኢየሩሳሌም ምድር ለመሄድ በምድረበዳ ጉዞአችንን ጀመርን።

እናም እንዲህ ሆነ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ምድር በሄድን ጊዜ እኔና ወንድሞቼ እርስ በእርስ ተመካከርን።

፲፩ እናም ማን ወደ ላባን ቤት መሄድ እንዳለበት ዕጣ ተጣጣልን። እናም እንዲህ ሆነ ዕጣው በላማን ላይ ወደቀ፤ እናም ላማን ወደ ላባን ቤት ሄደ፣ በቤቱም ተቀምጦ ሳለ አናገረው።

፲፪ እና ላባንን በነሐስ ሰሌዳዎች ላይ የተቀረፁትንና የአባቴን ትውልድ ሐረግ የያዙትን መዝገቦች ጠየቀው።

፲፫ እናም እንዲህ ሆነ ላባን ተናደደ፣ እናም ከፊቱም አባረረው፣ እና መዝገቦቹን እንዲወስድ አላደረገውም፣ ስለሆነም አለው፥ እነሆ አንተ ወንበዴ ነህ እናም እገድልሀለሁ።

፲፬ ነገር ግን ላማን ከእርሱ ፊት ሸሸ፣ ላባን ያደረገውንም ነገር ለእኛ ነገረን። እኛም እጅግ አዘንን እና ወንድሞቼ ወደ አባቴ ዘንድ ወደ ምድረበዳው ለመመለስ ተዘጋጁ።

፲፭ ነገር ግን እነሆ እኔ ለእነርሱ እንዲህ አልኳቸው፥ ጌታ ህያው እንደሆነ፣ እኛም እስካለን ድረስ ጌታ ያዘዘንን ሳናከናውን ወደአባታችን ወደ ምድረበዳ አንመለስም።

፲፮ ስለዚህ የጌታን ትዕዛዝ በመጠበቅ ታማኝ እንሁን፣ ስለዚህ ወደ አባታችን ርስት ምድር እንውረድ፣ እነሆ ወርቅን፣ ብርንና ሁሉን ሀብቶችን ትቷልና። እናም ይህን ሁሉ ያደረገው በጌታ ትዕዛዛት ምክንያት ነው።

፲፯ ኢየሩሳሌም በህዝቡ ክፋት ምክንያት መጥፋት እንዳለባት ያውቅ ነበርና።

፲፰ እነሆም እነርሱ የነቢያትን ቃላት አልተቀበሉም፣ ስለዚህ አባቴ ከምድሪቱ እንዲወጣ ከታዘዘ በኋላ በዚያ ሀገር ቢቆይ ኖሮ እነሆ እርሱም ደግሞ ይጠፋ ነበር። ስለዚህ፣ ከምድሪቷ መውጣት ነበረበት።

፲፱ እናም የአባቶቻችንን ቋንቋ ለልጆቻችን እናቆይ ዘንድ እነዚህን መዝገቦች ማግኘታችን የእግዚአብሔር ጥበብ ነው

እናም ደግሞ ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ እስከ አሁን ጊዜ ድረስ በመንፈስና በእግዚአብሔር ኃይል ተሰጥቷቸው በቅዱሳን ነቢያት የተነገሩትን ቃላት ሁሉ እንድንጠብቅላቸው ዘንድ ነው።

፳፩ እናም እንዲህ ሆነ በዚህ አይነት አነጋገር ነበር የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመጠበቅ ታማኝ እንዲሆኑ አሳመንኳቸው።

፳፪ እናም እንዲህ ሆነ ወደ ርስታችን ምድር ወረድንና ወርቃችንንና፣ ብራችንን፣ እንዲሁም የከበሩ ነገሮቻችንን በአንድነት ሰበሰብን።

፳፫ እና እነዚህን ነገሮች ከሰበሰብን በኋላ ወደ ላባን ቤት ተመልሰን ሄድን።

፳፬ እናም እንዲህ ሆነ ላባን ቤት ገባንና በነሀስ ሰሌዳዎች ላይ የተቀረፁትን መዛግብት እንዲሰጠን ለዚህም ወርቃችንን፣ ብራችንንና፣ ሁሉንም የከበሩ ነገሮቻችንን እንደምንሰጠው ነገርነው።

፳፭ እናም እንዲህ ሆነ ላባን ንብረታችን እጅግ ታላቅ እንደሆነ ባየ ጊዜ ተመኘው፣ በዚህም ምክንያት ወደ ውጪ አባረረንና ንብረታችንን ይወስድ ዘንድ አገልጋዮቹን እንዲገድሉን ላከብን።

፳፮ እናም እንዲህ ሆነ እኛ ከላባን አገልጋዮች ፊት ሸሸን ንብረታችንን ከኋላችን ትተን እንድንሄድ ተገደድን፣ እና ይህም በላባን እጆች ውስጥ ወደቀ።

፳፯ እናም እንዲህ ሆነ ወደ ምድረበዳ ሸሸን፣ የላባን አገልጋዮች ሊይዙን አልቻሉም፣ እናም እራሳችንን በአለት ዋሻ ውስጥ ደበቅን።

፳፰ እናም እንዲህ ሆነ ላማን በእኔም ሆነ በአባቴ ተናደደ፤ ልሙኤልም እንደዛው የላማንን ቃላት አድምጦአልና። ስለዚህ ላማንና ልሙኤልም እኛን ታናናሽ ወንድሞቻቸውን ብዙ አስፈሪ ቃላት ተናገሩን፣ በበትርም መቱን።

፳፱ እናም እንዲህ ሆነ እነርሱ በበትር በመቱን ጊዜ፣ እነሆም የጌታ መልአክ መጥቶ በፊታቸው ቆመ፣ እንዲህም ብሎ ተናገራቸው፥ ለምን ታናሽ ወንድማችሁን በበትር ትመታላችሁ? ጌታ እርሱን በእናንተ ላይ ገዢ ይሆን ዘንድ እንደመረጠውና ይህም በአመፃችሁ ምክንያት እንደሆነ አታውቁምን? እነሆ እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ትመለሳላችሁ፣ እናም ጌታ ላባንን አሳልፎ በእጃችሁ ላይ ይጥለዋል።

እናም መልአኩ ለእኛ ከተናገረ በኋላ ሄደ።

፴፩ እናም መልአኩም ከሄደ በኋላ ላማንና ልሙኤል እንዲህ ሲሉ ማጉረምረም ጀመሩ፣ ጌታ ላባንን አሳልፎ በእጃችን ይጥለው ዘንድ እንዴት ይቻላል? እነሆ እርሱ ሀይለኛ ነው፣ እናም አምሳዎችን ሰዎችን ሊያዝ ይችላል፣ አዎን፣ አምሳዎችንም መግደል ይችላል፣ እኛንስ መግደል እንዴት አይቻለውም?