ምዕራፍ ፳፩
መሲሁ ለአህዛብ ብርሃን ይሆናል እንዲሁም እስረኞችን ያስለቅቃል—እስራኤልም በኋለኛው ቀናት በኃይል ትሰበሰባለች—ንጉሶችም የእነርሱ አሳዳጊ አባቶች ይሆናሉ። ኢሳይያስ ፵፱ን አነፃፀር። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም እንደገና፤ እናንተ የተገነጠላችሁና በህዝቦቼ እረኞች ኃጢያት የተነሳ ለቃችሁ እንድትወጡ የተደረጋችሁ የእስራኤል ቤት ሆይ ስሙ፤ አዎን እናንተ የተገነጠላችሁ ሁሉ፣ በስፋት የተበተናችሁ በሙሉ፣ ከእኔ ህዝቦች የሆንሽ የእስራኤል ቤት ሆይ። ሀደሴቶች ሆይ ስሙኝ፣ እናንተም ለበሩቅ ያላችሁ ህዝቦች አድምጡኝ፤ ጌታ ከማህፀን ጠርቶኛል፣ ከእናቴም ማህጸን ጀምሮ ስሜን አንስቶአል።
፪ እናም እርሱ አፌን እንደተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፤ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፣ እንደተወለወለ ፍላፃም አድርጎኛል፤ በሰገባውም ውስጥ ሸሽጎኛል፤
፫ እናም እርሱ እስራኤል ሆይ፣ አንተ ሀአሽከሬ ነህ፣ በአንተም እከብራለሁ አለኝ።
፬ ከዚያም እኔ በከንቱ ደከምኩ፣ ምንም ጥቅም ለሌለውና በከንቱ ጉልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ በእርግጥ ከጌታ ዘንድ ስራዬም በአምላኬ ዘንድ ነው አልሁ።
፭ እናም አሁን ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ አሽከር እሆነው ዘንድ ከማህፀን ጀምሮ ሀየሰራኝ ጌታ እንዲህ ይላል፣ እስራኤልን ባትሰበሰብም፣ ግን በጌታ ዐይን ተከባሪ እሆናለሁ፣ አምላኬም ጉልበቴ ይሆንልኛል።
፮ እናም እንዲህ አለ፥ አንተ የያዕቆብን ሀነገዶች እንድታስነሳና ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመልስ አገልጋይ መሆንህ እጅግ ቀላል ነገር ነው። እስከምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለለአህዛብ ሐብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።
፯ ጌታ፣ የእስራኤል መድኃኒት፣ ቅዱሱ፣ ሰዎች ለሚንቁት፣ ህዝብ ለሚጠላው፣ ለገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፥ ጌታ ታማኝ ስለሆነ ነገሥታት አይተው ይነሳሉ፣ መሳፍንትም ደግሞ ይሰግዳሉ።
፰ ጌታ እንዲህ ይላል፥ በተወደደም ጊዜ ሰምቼሀለሁ፣ የባህር ደሴቶች ሆይ፣ እናም በደህንነት ቀንም ረድቼሃለሁ፤ እናም እጠብቅህማለሁ፣ ምድርን ታቀና ዘንድ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ ሀአገልጋዬን እንደ ቃል ኪዳን አድርጌ ለህዝቡ እሰጥሀለሁ፤
፱ ሀለእስረኞቹ፣ ውጡ፣ ለበጨለማም ለተቀመጡትም፣ ተገለጡ በላቸው። በመንገድም ላይ ይበላሉ፣ ሐማሰማርያቸውም በወና ኮረብታ ሁሉ ላይ ይሆናል።
፲ አይራቡም፣ አይጠሙም፣ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጎዳቸውም፤ የሚራራላቸው ይመራቸዋል፣ እንዲሁም በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋል።
፲፩ እናም ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፣ ሀጎዳኖቼም ከፍ ይላሉ።
፲፪ ከእዚያም የእስራኤል ቤት ሆይ ተመልከቱ፣ ሀእነዚህ ከሩቅ፣ እናም አቤቱ፣ ከሰሜን፣ ከምዕራብ እነዚህም ከሲኒም አገር ይመጣሉ።
፲፫ ምክንያቱም ጌታ ህዝቡን አፅናንቶአልና፣ በተሰቃዩትም ላይ ምህረትን ያደርጋልና ሰማያት ሆይ ሀዘምሩ፣ እናም ምድር ሆይ ተደሰቱ፣ በምስራቅ ያሉ ህዝቦችሽ ይቋቋማሉና፤ እናም ለመዘመር ተነሱ፣ ተራሮች ሆይ ከእንግዲህ አይቀጡምና።
፲፬ እነሆ ፅዮን ግን እንዲህ ብላለች፥ ጌታ ትቶኛል እናም ጌታዬ እረስቶኛል—ነገር ግን እርሱ እንዳልረሳ ያሳያል።
፲፭ በእውኑ ሀሴት ከማህፀንዋ ለተወለደው ወንድ ልጅ እስከማትራራ ድረስ የምታጠባውን ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፣ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነርሱ ይረሱ ይሆናል እኔ ግን ለአልረሳሽም።
፲፮ እነሆ እኔ በእጄ ሀመዳፍ ቀርጬሻለሁ፣ ግንቦችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።
፲፯ ልጆችሽ ያወደሙሽ ላይ ይፈጥናሉ፣ እናም ሀያጠፉሽ ከአንቺ ዘንድ ይወጣሉ።
፲፰ ዓይንሽን አንስተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፣ እናም እነሆ እነዚህ ሁሉ እራሳቸውን ሀሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። እኔ ህያው እንደሆንኩ፣ እነዚህን ሁሉ እንደጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፣ እንደሙሽራም ትጎናፀፊያቸዋለሽ፣ ይላል ጌታ።
፲፱ ባድማሽና ውድማሽ፣ ወናም የሆነው ምድርሽ፣ እናም የጥፋትሽ ምድር ከሚኖሩብሽ የተነሳ ዛሬ ጠባብ ትሆናለች፣ የዋጡሽም ይርቃሉና።
፳ የመጀመሪያውን ካጣሽ በኋላ ያገኘሻቸው ልጆችሽ በጆሮሽ ስፍራ፥ በጣም ሀጠቦኛልና እንቀመጥ ዘንድ ቦታ አስፊልኝ ይላሉ።
፳፩ በዚያም ጊዜ ሀአንቺም በልብሽ ትያለሽ፥ የወላድ መካን ሆኜና፣ እኔም ለብቸኛ ሆኜ፣ ታስሬና ተቅበዝብዤ እያለሁ እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፣ እነዚህስ ወዴት ነበሩ?
፳፪ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ እነሆ እጄን ወደ ሀአህዛብ አነሳለሁ፣ ለአርማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም ሐበክንዳቸው ያመጡአቸዋል፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ይሸከሟቸዋል።
፳፫ ሀነገሥታትም ለአሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፣ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ፊቶቻቸውን ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፣ እና የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤ እኔንም ሐየጠበቁ አያፍሩምና።
፳፬ በውኑ ብዝበዛ ከኃያል እጅ ይወሰዳልን? ወይስ ሀህጋዊ ምርኮኞች ያመልጣሉን?
፳፭ ጌታ ግን እንዲህ ይላል፣ በሃያላን የተማረኩም ይወሰዳሉ፣ የአሸባሪም አደን ይወሰዳል፤ ምክንያቱም ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፣ ልጆችሽንም አድናለሁ።
፳፮ እናም ሀአስጨናቂዎችሽን ስጋቸውን አስበላቸዋለሁ፤ እንደጣፋጭም ወይን ጠጅም በደማቸው ይሰክራሉ፤ እናም ስጋ ለባሹም ሁሉ እኔ ጌታ አዳኝሽና መድኃኒትሽና፣ የያዕቆብም ለኃያል እንደሆንኩ ሐያውቃሉ።