ምዕራፍ ፲፭
ክርስቶስ አባትም ልጅም እንዴት እንደሆነ—እርሱ ያማልዳል እናም የህዝቡን አመፅ ይሸከማል—እነርሱ እና ሁሉም ቅዱሳን ነቢያት ዘሮቹ ናቸው—ትንሳኤን ያመጣል—ህፃናት ዘለዓለማዊ ህይወት ይኖራቸዋል። በ፻፵፰ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን፣ አቢናዲ እንዲህ አላቸው፥ ሀእግዚአብሔር ራሱ በሰው ልጆች መካከል እንደሚወርድና፣ ህዝቡንም ለእንደሚያድን እንድትረዱ እፈልጋለሁ።
፪ እናም በስጋ ሀበመኖሩም የተነሳ የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ይጠራል፣ እናም ሥጋውን ለለአብ ፈቃድ በማስገዛቱ አብም፣ ወልድም ነው—
፫ በእግዚአብሔር ኃይል ሀየተፀነሰ ለስለሆነም አብ ነው፤ ስጋን ለብሷልና ወልድ ነው፣ ስለዚህ አብም ወልድም ነው—
፬ እናም ሀአንድ አምላክ፣ አዎን፣ እውነተኛ የሰማይና የምድር ለዘለዓለማዊ ሐአባት ናቸው።
፭ እናም ስጋው ለመንፈስ ወይንም ወልድም ለአብ በመገዛቱ፣ አንድ አምላክ በመሆን፣ መከራን ሀበመሰቃየቱና፣ ለፈተናም ራሱን ባለመስጠቱ፤ ነገር ግን እንዲሳለቁበትና፣ ለእንዲገረፍ፣ እንዲሁም በህዝቡ እንዲጣልና ሐእንዲወገዝ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
፮ እናም ከዚህ ሁሉ በኋላ፣ በሰው ልጆች መካከል ብዙ ኃያል ድንቅ ሥራዎችን ከሰራ በኋላ ይመራል፣ አዎን፣ ኢሳይያስ ሀእንዳለው ሁሉ፣ በጉም በሸላቾቹ ፊት ዝም እንዳለው፣ እንዲሁም ለአፉን አልከፈተም።
፯ አዎን፣ እንደዚያ ቢሆንም እርሱ ይነዳል፣ ሀይሰቀላል እናም ይገደላል፣ ለየወልድም ፈቃድ በአብ ፈቃድ ተሸፍኖ፣ ስጋውም ቢሆን ሞትን እንዲቀምስ ይደረጋል።
፰ እና በሞት ላይ ሀድልን በማግኘት፣ ለሰው ልጆች ለእንዲማልድ ለወልድ ኃይልን በመስጠት፣ እንደዚህም እግዚአብሔር ሐየሞትን እስር ይበጥሳል፤
፱ ወደሰማይ በማረጉ፣ ለሰው ልጆች አንጀቱ በምህረት በመሞላቱ፣ በእነርሱና በፍርድ መካከል በመቆም ለሰዎች ልጆች በርህራሄ ይሞላል፣ የሞትን እስር በመበጣጠስ፣ ሀበራሱም ላይ ክፋታቸውንና መተላለፋቸውን በማድረግ፣ እነርሱን በማዳን፣ እናም የፍትህን ፍላጎት ለአሟልቷል።
፲ እናም አሁን እላችኋለሁ፣ ትውልዱን የሚያውጅ ማን ነው? እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ ነፍሱ ለኃጢያት መስዋዕት ሲሆን ሀዘሩን ያያል። እናም አሁን ምን ትላላችሁ? እናም ዘሩስ ማን ይሆናል?
፲፩ እነሆ እላችኋለሁ፣ ማንም ሀየነቢያቱን ቃላት የሰማ፣ አዎን የክርስቶስን መምጣት በተመለከተ የተነበዩትን ቅዱሳን ነቢያት ሁሉ—እላችኋለሁ፣ ቃላቸውን የሰሙ ሁሉ፣ እናም ጌታ ህዝቡን ማዳኑን ያመኑና፣ ለኃጢአታቸው ስርየት ያንን ቀን የሚጠብቁ፣ እላችኋለሁ፣ እነዚህ የእርሱ ዘር ናቸው፣ ወይም ለየእግዚአብሔርን መንግስት ወራሾች ናቸው።
፲፪ ኃጢአታቸውን ሀየተሸከመላቸው እነዚህ ናቸው፤ ከመተላለፋቸው እንዲያድናቸው እርሱ የሞተላቸው እነርሱ ናቸው። እናም አሁን የእርሱ ዘሮች አይደሉምን?
፲፫ አዎን፣ እናም ለትንቢት አፉን የከፈተ እያንዳንዱ፣ በመተላለፍ ያልወደቀ፣ ማለትም ዓለም ከመፈጠሩ ጀምሮ የነበሩ ቅዱሳን ነቢያት ሁሉ አይደሉምን? እነርሱ ዘሮቹ ናቸው እላችኋለሁ።
፲፬ እናም ሰላምን ሀየተናገሩት፣ መልካሙን የምስራች ዜና ያመጡት፣ ደህንነትን የተናገሩት፣ እናም ለፅዮንም አምላክሽ ነግሷል! ያሉት እነኚህ ናቸው።
፲፭ እናም አቤቱ እግራቸው በተራራው ላይ ምን ያህል ያማረ ነው!
፲፮ እናም እንደገና፣ ሰላምን በተራራው ላይ የሚያውጁ እግራቸው እንዴት ያማረ ነው?
፲፯ እናም እንደገና፣ አዎን፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከዘለዓለም በተራራው ላይ ሰላምን የሚያውጁት እግራቸው እንዴት ያማረ ነው!
፲፰ እናም እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ይህ ብቻም አይደለም። ሀየሰላም መስራቹ የምስራች ወሬን ያመጣው፣ ህዝቡን ያዳነው አዎን፣ ያውም ጌታ ቢሆን እንኳን፤ አዎን፣ ለህዝቡ ደህንነትን የሰጠው፣ ለእግሮቹ በተራራው ላይ ምን ያህል ያማሩ ናቸው።
፲፱ ከዓለም ሀመፈጠር ጀምሮ የተዘጋጀው ለህዝቡ ያደረገው ቤዛነት ባይሆን ኖሮ፣ ይህ ባይሆን ኖሮ የሰው ዘር በሙሉ ለመጥፋት ነበረባቸው እላችኋለሁ።
፳ ነገር ግን እነሆ፣ የሞት እስር ይበጠሳል፣ እናም ወልድም ይነግሳል፣ በሞት ላይ ስልጣን ይኖረዋልም፣ ስለዚህ፣ የሞትን ትንሣኤ ያመጣል።
፳፩ እናም ትንሳኤ፣ እንዲያውም ሀየመጀመሪያው ትንሣኤ፣ አዎን፣ ትንሣኤውም እንኳን ለነበሩትና፣ አሁን ላሉት፣ እናም ወደፊት ለሚኖሩት እስከ ክርስቶስ ትንሳኤም ድረስ እንኳን ይመጣል፤ እንዲህም ተብሎ ነው ይጠራልና።
፳፪ እናም አሁን፣ ሁሉም ነቢያትና፣ በቃላቸው ያመኑት ሁሉ፣ ወይም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁ ሁሉ፣ በመጀመሪያው ትንሳኤ ይነሳሉ፣ ስለዚህ፣ የመጀመሪያው ትንሣኤ ናቸው።
፳፫ ካዳናቸው ከእግዚአብሔር ጋር ሀለመኖር ይነሳሉ፤ እንደዚህም የሞትን እስር ለበበጠሰው፣ በክርስቶስ በኩል ዘለዓለማዊ ህይወት ያገኛሉ።
፳፬ እናም እነዚህ በመጀመሪያው ትንሣኤ ቦታ ያላቸው ናቸው፤ እነዚህም ባለማወቃቸው፣ ሀደህንነት ሳይታወጅላቸው፣ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የሞቱት ናቸው። እናም ጌታ የእነዚህ መታደስን ያመጣል፤ በመጀመሪያው ትንሣኤ ቦታ፣ ወይም በጌታ በመዳን ዘለዓለማዊ ህይወት ይኖራቸዋልም።
፳፭ እናም ትናንሽ ሀልጆች ዘለዓለማዊ ህይወት ይኖራቸዋል።
፳፮ ነገር ግን እነሆ፣ እናም በእግዚአብሔር ፊት ሀፍሩና ተንቀጥቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ይገባችኋልና፣ ጌታም በእርሱ ላይ ለያመፀውንና በኃጢያት ሐየሞተውን አያድንምና፤ አዎን፣ እንዲሁም ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ በኃጢአታቸው የሞቱትም፣ ወደው በእግዚአብሔር ላይ ያመፁትም፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚያውቁ እናም የማይጠብቁትም ሁሉ፣ በመጀመሪያው ትንሳኤ ቦታ መያልኖራቸው ሠእነዚህ ናቸው።
፳፯ ስለዚህ እናንተስ መንቀጥቀጥ አይገባችሁምን? ደህንነት እንደነዚህ ላሉት ለማናቸውም አይመጣም፣ ጌታ እንደዚህ ያሉትን ማናቸውንም አያድንምና፤ አዎን፣ ጌታ እንዲህ አይነቱን ሊያድን አይቻለውምና፣ እራሱን ሊክድ አይችልምና፣ ሀፍትህ በሰው ላይ ቅጣት ለመስጠት መብት ሲኖራት መካድ አይችልምና።
፳፰ እናም አሁን እንዲህ እላችኋለሁ፣ የጌታ ደህንነት ለሁሉም ሀገር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ህዝብ ሀየሚታወጅበት ጊዜ ይመጣል።
፳፱ አዎን፣ ጌታ፣ ሀጠባቂዎችህ ድምፃቸውን ከፍ ያደርጋሉ፣ በአንድነትም ይዘምራሉ፤ ጌታ ፅዮንን በድጋሚ ሲያመጣ ዐይን ለዐይን ይተያያሉና።
፴ በደስታ በድንገት ውጡ፤ የፈራረሳችሁ የኢየሩሳሌም ቦታዎች በአንድነት ዘምሩ፤ ጌታ ህዝቡን አፅናንቷል፣ ኢየሩሳሌምን አድኗልና።
፴፩ ጌታ ቅዱስ ክንዱን በሁሉ ሀገሮች ዐይን ላይ ገልጧል፤ እናም የአለም ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።