ምዕራፍ ፫
የያሬድ ወንድም የጌታን ጣት አስራ ስድስቱን ድንጋዮች ሲነካ ተመለከተ—ክርስቶስ የመንፈስ አካሉን ለያሬድ ወንድም አሳየው—ፍፁም እውቀት ያላቸው በመጋረጃው ሊታገዱ አይችሉም—ተርጓሚዎች የያሬዳውያንን መዝገብ ወደ ብርሃኑ ለማምጣት ተዘጋጅተዋል።
፩ እናም እንዲህ ሆነ የያሬድ ወንድም ተራራውም እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ ሼለም ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ሔደ (እንግዲህ የተዘጋጀው ጀልባ ብዛት ስምንት ነበር) እናም ከአለት አስራ ስድስት ትናንሽ ድንጋዮች አቅልጦ አወጣ፤ እናም እነርሱም የነጡ፣ እናም እንደመስታወት ብሩህ ነበሩ፤ እናም እርሱም ተሸክሞ ወደ ተራራው ጫፍ ወሰዳቸው፣ እናም ወደ ጌታ በድጋሚ እንዲህ ሲል ጮኸ፥
፪ አቤቱ ጌታዬ በጥፋት ውሀ መከበብ አለባችሁ ብለሃል። እንግዲህ እነሆ ጌታ ሆይ፣ አገልጋይህ በፊትህ ደካማ በመሆኑ አትቆጣው፤ ምክንያቱም አንተ ቅዱስ እንደሆንክ እናም በሰማይ እንደምትኖር፤ እናም እኛ ባንተ ፊት ከንቱዎች እንደሆንን እናውቃለን፤ ሀበውድቀትም የተነሳ ለተፈጥሮአችን ያለማቋረጥ ክፉ ሆኗል፤ ይሁን እንጂ፣ ጌታ ሆይ፣ እንደፈለግነውም ከአንተ እንቀበል ዘንድ አንተን እንድንጠራ ትዕዛዝ ሰጥተኸናል።
፫ እነሆ፣ ጌታ ሆይ፣ በክፋታችን ቀጥተኸናል፣ እናም አባረኸናል፣ እናም ለእነዚህ ብዙ ዓመታትም በምድረበዳው ነበርን፤ ይሁን እንጂ፣ አንተ ለእኛ ሀመሃሪ ነህ። አቤቱ ጌታ፣ በአዘኔታም ተመልከተኝ፣ እናም ከህዝብህም ቁጣህን መልስ፣ እናም በዚህ ማዕበላዊ ባህር በጨለማ እንዲጓዙ አትፍቀድ፤ ነገር ግን ከድንጋይ ያቀለጥኳቸው እነዚህ ነገሮች ተመልከት።
፬ እናም ጌታ ሆይ፣ ሀስልጣን ሁሉ እንዳለህ፣ እናም ለሰዎች ጥቅምም ማንኛውንም ማድረግ እንደምትችል አውቃለሁ፤ ስለዚህ አቤቱ ጌታ፣ እነዚህን ድንጋዮች በጣትህ ንካቸው፣ እናም በጨለማም እንዲያበሩ አዘጋጃቸው፤ እናም ባዘጋጀነው ጀልባ ላይም ባህሩን በምናቋርጥበት ጊዜ ብርሃን ይሰጡን ዘንድ ያበሩልናል።
፭ እነሆ፣ ጌታ ሆይ፣ ይህንን ማድረግ ትችላለህ። ሰዎች በአስተሳሰባቸው አነስተኛ አድርገው የሚያዩትን ታላቅ ኃይል ሀለማሳየት እንደምትችል እናውቃለን።
፮ እናም እንዲህ ሆነ የያሬድ ወንድም እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ፣ እነሆ፣ ሀጌታ እጁን ዘርግቶ ድንጋዮቹን አንድ በአንድ በጣቱ ነካቸው። እናም ለመጋረጃው ከያሬድ ወንድም ዐይን ላይ ተወገደ፣ እናም የጌታን ጣት ተመለከተ፤ እናም ይህ ሥጋና ደም እንደለበሰ እንደ ሰው ጣት ነበር፤ እናም የያሬድ ወንድም በፍርሃት በመዋጡ በጌታ ፊት ወደቀ።
፯ እናም ጌታ የያሬድ ወንድም በመሬት ላይ መውደቁን ተመለከተ፤ እናም ጌታ እንዲህ ሲል ተናገረ፥ ተነሳ ለምን ትወድቃለህ?
፰ እናም ለጌታ እንዲህ አለው፥ የጌታን ጣት ተመለከትኩ፣ እናም ይመታኛል ብዬ ፈራሁኝ፤ ምክንያቱም ጌታ ሥጋና ደም እንዳለውም አላውቅም ነበርና።
፱ እናም ጌታ እንዲህ አለው፥ በእምነትህ የተነሳ ሀሥጋና ደም እንደምለብስ ተመለከትህ፤ እናም ከዚህ በፊት ማንም ሰው እንደአንተ ያለ ታላቅ እምነት ያለው በጭራሽ በፊቴ አልመጣም፤ ይህ ባይሆን ኖሮ ጣቴን ለማየት አትችልም ነበር። ከዚህ የበለጠን ነገር አይተሃልን?
፲ እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ አላየሁም፤ ጌታ ሆይ፣ ራስህን አሳየኝ።
፲፩ እናም ጌታ እንዲህ አለው፥ የምናገርህን ቃላት ታምናለህን?
፲፪ እናም እርሱ እንዲህ ሲል መለሰለት፥ አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ አንተ እውነት እንደምትናገር አውቃለሁ፤ አንተ የእውነት አምላክ ነህና፣ ሀለመዋሸት አትችልም።
፲፫ እናም እርሱም እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ፣ እነሆ፣ ጌታ ራሱን ሀአሳየው፣ እናም እንዲህ አለው፥ እነዚህን ነገሮች ለበማወቅህ አንተ ከመውደቅ ድነሃል፤ ስለዚህ እኔ ባለሁበት ተመልሰሀል፣ ስለዚህም ራሴን ሐአሳይቼሀለሁ።
፲፬ እነሆ፣ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ህዝቤን ሀለማዳን የተዘጋጀሁ እኔ ነኝ። እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ። እኔ ለአብም ወልድም ነኝ። በእኔም የሰው ዘር በሙሉ፣ እንዲሁም በስሜም የሚያምኑትም፣ የዘለዓለም ሐህይወትን ያገኛሉ፤ እናም እነርሱም መወንድና ሴት ልጆቼም ይሆናሉ።
፲፭ እናም እኔ ለፈጠርኩት ሰው በጭራሽ ራሴን አላሳየሁም፤ ምክንያቱም ማንም አንተ እንዳደረግኸው በእኔ ሀያመነ አልነበረምና። አንተ በእኔ ለአምሳል መፈጠርህን ተመልክተሃልን? አዎን፣ ሰዎች ሁሉ እንኳ በመጀመሪያ የተፈጠሩት በእኔ አምሳል ነው።
፲፮ እነሆ፣ ይህ ሰውነት፣ አሁን የተመለከትከው፣ ሀመንፈሳዊው ሰውነቴ ነው፤ እናም ሰውን የፈጠርኩት በመንፈስ አካሌ አምሳል ነው፤ እናም በመንፈስ ለአንተ እንደታየሁት ለህዝቤም በሥጋ እታያለሁ።
፲፯ እናም እንግዲህ እንዳልኩት እኔ ሞሮኒ ስለተፃፉት ስለነዚህ ነገሮች ሙሉ ታሪክን መፃፍ አልችልም፤ ስለዚህ ኢየሱስ ለኔፋውያን እራሱን እንዳሳየው በዚሁ መልክ ለዚህ ሰው ሀራሱን በመንፈስ አሳይቷል ማለቱ ይበቃኛል።
፲፰ እናም እርሱም ለኔፋውያን እንዳስተማራቸው አስተምሮታል፤ እናም ይህን ሁሉ ያደረገው ጌታ ብዙ ታላላቅ ስራዎችን ባሳየው ምክንያት ይህ ሰው አምላክ መሆኑን ያውቅ ዘንድ ነው።
፲፱ እናም ይህ ሰው ከነበረው እውቀትም የተነሳ ሀበመጋረጃው ውስጥ ከመመልከት ሊጠበቅ አልቻለም፤ እናም የኢየሱስን ጣት ተመለከተ፤ በተመለከተም ጊዜ በፍርሃት ወደቀ፤ ምክንያቱም የጌታ ጣት መሆኑን አውቋልና፤ እናም እንግዲህ እምነት የለውም፣ ምክንያቱም ምንም ባለመጠራጠር ያውቃለና።
፳ ስለዚህ፣ ይህን የእግዚአብሔር ፍፁም የሆነ እውቀት ስላለው፣ በመጋረጃው ውስጥ ሊጠበቅ ሀአልተቻለውም፤ ስለዚህ ኢየሱስን ተመለከተው፤ እናም እርሱም አስተማረው።
፳፩ እናም እንዲህ ሆነ ጌታ የያሬድን ወንድም እንዲህ አለው፥ እነሆ፣ ስሜን በሥጋ ሆኜ ለማስከበር ሀእስከምመጣበት ጊዜ ድረስ እነዚህ ያየሃቸውን እናም የሰማሃቸውን ነገሮች ወደዓለም እንዲሄዱ አትፍቀድ፤ ስለዚህ፣ ያየሃቸውን እናም የሰማሃቸውን ነገሮች አስቀምጥ፣ እናም ለማንም አታሳይ።
፳፪ እናም እነሆ፣ ወደ እኔ በምትመጣበት ጊዜም ፃፈው፣ እናም ማንም ሊተረጉማቸው እንዳይችልም አሽገው፤ ምክንያቱም ለማንበብ በማይቻል ቋንቋ ትጽፋቸዋለህና።
፳፫ እናም እነሆ፣ እነዚህን ሀሁለት ድንጋዮች እሰጥሃለሁ፣ እናም ደግሞ ከምትጽፋቸው ነገሮች ጋር ትቀብራቸዋለህ።
፳፬ እነሆም የምትጽፈው ቋንቋ አምታትቼዋለሁ፤ ስለዚህ አንተ የምትፅፋቸውን ነገሮች በራሴ ጊዜም እነዚህ ድንጋዮች ለሰዎች አይኖች እንዲያደምቋቸው አደርጋለሁ።
፳፭ እናም ጌታም እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ፣ ለያሬድ ወንድም የምድር ሀፍጡር የሆኑትን ሁሉ፣ እናም ደግሞ ሊሆኑ የሚችሉትን በሙሉ አሳየው፤ እናም እስከምድር ዳርቻም ከያሬድ ወንድም ፊት አልደበቀውም።
፳፮ ከዚህ በፊትም በእርሱ ሀየሚያምን ለከሆነ ሁሉንም ነገሮች ሊያሳየው እንደሚችል ተናግሮታልና—ለእርሱም ያሳየዋል፤ ስለዚህ ጌታ ከእርሱ ሊደብቅ የሚቻለው ምንም ነገር የለም፤ ምክንያቱም ጌታ ሐሁሉንም ነገሮች ሊያሳየው እንደሚችል ያውቃልና።
፳፯ እናም ጌታ እንዲህ አለው፥ እነዚህን ነገሮች ፃፍ፣ እናም ሀአትማቸው፣ እናም የራሴ ጊዜ ሲደርስ ለሰው ልጆች አሳያቸዋለሁ።
፳፰ እናም እንዲህ ሆነ ጌታም የተቀበላቸውን ሁለት ሀድንጋዮች እንዲያሽጋቸው እናም ጌታም ለሰው ልጆች እስከሚያሳያቸው እርሱ ለማንም እንዳያሳያቸው አዘዘው።