ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
መጋቢት 11–17 ፦ “ድንቅ ነገርን እና ተአምራትን።” 2 ኔፊ 26–30


“መጋቢት 11–17 ፦ ‘ድንቅ ነገርን እና ተአምራትን።’ 2 ኔፊ 26–30፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 11–17 (እ.አ.አ)። 2 ኔፊ 26–30፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ምስል
ኢየሱስ ለአንዲት ሴት እጁን እየዘረጋ

እጅህን ይዞ ይመራሃል [He Will Lead Thee by the Hand]፣ በሳንድራ ራስት

መጋቢት 11–17 ፦ “ድንቅ ነገርን እና ተአምራትን”

2 ኔፊ 26–30

ኔፊ “የመጨረሻ ቀናትን በተመለከተ እተነብይላችኋለሁ፣” ብሎ ፃፈ (2 ኒፊ 26፥14)። በሌላ አባባል፣ ስለ ቀናችን እየፃፈ ነበር። ሰዎች የእግዚአብሔርን ኃይል እና ተአምራት ስለካዱ፤ ሰፊ ቅናት እና ግጭትም ስለነበር እሱ ስለተናገረው ነገር ለመጨነቅ ምክንያት ነበረው። ነገር ግን ከእነዚህ በጠላት ከሚመሩት የኋለኛው ቀን “የጨለማ [አሰራሮች]” (2 ኔፊ 26፥10፣ 22) በተጨማሪ በእግዚአብሔር በራሱ ስለሚመራ “ድንቅ ነገር እና ተአምራት” ኔፊ ተናግሯል (2 ኔፊ 27፥26)። ለዚያ ስራ ዋናው ነገር አንድ መጽሐፍ ነው—የሴይጣንን ውሸቶች የሚያጋልጥ እና ጻድቃንን የሚሰበስብ መጽሐፍ። መጽሐፉ መፅሐፈ ሞርሞን ነው፣ ድንቁ ስራ በኋለኛው ቀናት የጌታ ቤተክርስቲያን ስራ ነው፣ እንዲሁም ተአምራቱ—ቢያንስ በከፊል—ድክመቶች ቢኖሩንም እንኳን እግዚአብሔር ሁላችንም እንድንሳተፍ መጋበዙ ነው።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

2 ኔፊ 26–2729–30

እግዚአብሔር መፅሐፈ ሞርሞንን ለቀናችን አዘጋጀ

2 ኔፊ 26–27 ውስጥ፣ ኔፊ ከኢሳያስ የቀድሞ ትንቢት ውስጥ ጠቀሰ (ኢሳይያስን 29 ይመልከቱ) እናም ለህዝቡ እና ለመዝገባቸው ለመፅሐፈ ሞርሞን ተግባራዊ አደረገው። መፅሐፈ ሞርሞን ሙሉ በሙሉ ከመፃፉ በፊት እንኳን አንድ ቀን “ለሰው ልጆች ታላቅ ዋጋ [እንደሚኖረው]” በራዕይ አማካኝነት አወቀ (2 ኔፊ 28፥2)። መፅሐፈ ሞርሞን ለእናንተ ለምንድን ነው ታላቅ ዋጋ ያለው? 2 ኔፊ 29–30 ስታነቡ ይህን ጥያቄ አስቡ። በመጽሐፈ ሞርሞን አማካኝነት እግዚአብሔር ምን “ድንቅ ነገርን” (2 ኔፊ 27:26) በዓለም እና በህይወታችሁ ውስጥ እያከናወነ ነው?

በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ 1፥62–65ን ይመልከቱ።

ምስል
የሴሚነሪ መለያ

2 ኔፊ 26፥23–33

ኢየሱስ ክርስቶስ ሁላችንም ወደ እርሱ እንድንቀርብ ይጋብዘናል።

2 ኔፊ 26፥23–24 ውስጥ ልትመለከቱት የምትችሉት ብዙ ውብ እውነቶች አሉ። ለምሳሌ፣ “ለዓለም ጥቅም” እና ለእናንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገውን ማሰብ ትችላላችሁ። “ሁሉንም ሰዎች” እንዲሁም እናንተን እንዴት ነው “ወደ እርሱ የሚመራው”? ለእርሱ የፍቅር መግለጫዎች ምላሽ ምን ለማድረግ ተነሳሳችሁ?

ማንበባችሁን ቀጥሉና በቁጥር 25–33 ውስጥ ስለ አዳኙ እውነቶችን ፈልጉ። በተለይም የእርሱን ግብዣዎች ልብ በሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ለእናንተ ያለውን መልእክት በአንድ ዓረፍተ ነገር እንዴት ታጠቃልላላችሁ? እንደ “ወደ ኢየሱስ ኑ [Come unto Jesus]” (መዝሙር፣ ቁጥር 117) ያለ መዝሙር አእምሯችሁን ለተጨማሪ ግንዛቤዎች ሊከፍት ይችላል።

እነዚህ ጥቅሶች ከሌሎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት እና ሌሎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ በምትጋብዙበት መንገድ ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ አስቡ። በሽማግሌ ዲ. ታድ ክርስቶፈርሰን “የመቀላቀል ትምህርት [The Doctrine of Belonging]” [ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ) 53–56) መልዕክት ላይ የተወሰኑ ሃሳቦችን ልታገኙ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም 3 ኔፊ 18፥30–32፤ ዳልን ኤች ኦክስ፣ “አዳኛችን ለእኛ ምን አደረገልን? [What Has Our Savior Done for Us?]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2021 (እ.አ.አ)፣ 75–77፤ የወንጌል ርዕሶች “የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን መቀላቀል፣” በወንጌል ቤተ መጽሐፍት ይመልከቱ።

ዝምታን አትፍሩ። ጥሩ ጥያቄዎች ለመመለስ ጊዜ ይወስዳሉ። መመርመርን፣ ማሰብን እና መነሳሳትን ይጠይቃሉ። ለጥያቄ መልስ በመጠባበቅ የምታሳልፉት ጊዜ የማሰላሰል ቅዱስ ጊዜ መሆን ይችላል። ወደ ሌላ ነገር በመሄድ ይህን ጊዜ ቶሎ የማጠናቀቅን ፈተና አስወግዱ።

2 ኔፊ 28

ሰይጣን ለማታለል ይፈልጋል።

ብዙዎቹ የሰይጣን ውሸቶች እና ዘዴዎች በ2 ኔፊ 28 ውስጥ ተገልፀዋል። በቁጥር 6፣ 8፣ 21–23፣ 29 ውስጥ ፈልጓቸው። ስለ ሰይጣን ውሸቶች ማወቅ ለምን ያስፈልጋችኋል? ጠላት ሊያታልላችሁ ሲሞክር ምን ታደርጋላችሁ?

ከታች የተዘረዘሩት የሰይጣንን ውሸቶች የሚቃወሙ የተወሰኑ ምዕራፎች ናቸው። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉትን እውነተኛ ትምህርቶች በ2 ኔፊ 28 ውስጥ ኔፊ ካስጠነቀቀን የተሳሳተ ትምህርት ጋር ለማዛመድ ሞክሩ፦

በተጨማሪም ጌሪ ኢ. ስቲቭንሰን፣ “አታታለኝ [Deceive Me Not]፣”ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 93–96 ይመልከቱ።

2 ኔፊ 28፥27–31፤ 29

እግዚአብሔር ልጆቹን ለመምራት ራዕይ መስጠቱን ቀጥሏል።

እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ በበቂ የእግዚአብሔር ቃል ተባርከናል። ነገር ግን፣ ኔፊ እንዳስጠነቀቀው፣ “በቂ እንዳለን” በፍፁም ሊሰማን አይገባም። በ2 ኔፊ 28:27–31 እና 2 ኔፊ 29 ውስጥ ማስጠንቀቂያዎችን ስታነቡ፣ እንደነዚህ ያሉትን ጥያቄዎች አስቡ።

  • እግዚአብሔር ለእርሱ ቃል ምን እንዲሰማኝ እና እንድመልስ ይፈልጋል?

  • የበለጠ እውነትን ከእግዚአብሔር ስለመቀበል አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የሚቃወሙት ለምንድን ነው? (2 ኔፊ 28፥28)። እንደዚህ ተሰምቶኝ ያውቃል? እንደዚያ ከሆነ፣ እንዴት መቀየር እችላለሁ?

  • የእግዚአብሔር ቃል መቀበል ማለት ምን ማለት ነው? የእርሱን ቃል የበለጠ መቀበል እንደምፈልግ እንዴት ላሳየው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትምፕችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

2 ኔፊ 26፥23–28፣ 33

ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉም ወደ እርሱ እንዲመጡ ይፈልጋል።

  • በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉትን የአዳኙን ግብዣዎች ለልጆቻችሁ ለማስተማር፣ ሰዎችን እንደ የልደት ድግስ ያለ የተለየ ዝግጅት ላይ ስለጋበዙበት ጊዜ ከእነሱ ጋር ማውራት ትችላላችሁ። ከዚያም 2 ኔፊ 26፥23–28ን በጋራ ማንበብ እና ኢየሱስ ምን እንድናደርግ እየጋበዘን እንደሆነ ለማወቅ ሞክሩ። ልጆቻችሁ አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጣ ለመጋበዝ ካርድን ማዘጋጀት ይወዱ ይሆናል። ከእነዚህን ጥቅሶች ውስጥ ሃረግን በግብዣቸው ውስጥ እንዲጠቀሙ አበረታቷቸው።

  • በዚህ ጽሁፍ መጨረሻ ላይ ያለው ምስል ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ሰዎችን ያሳያል። 2 ኔፊ 26፥33ን ስታነቡ ምናልባት ልጆቻችሁ እነዚህን ምስሎች ማየት ይችላሉ። ልጆቻችሁ በምስሉ ውስጥ እያንዳንዱን ሰው እና እራሳቸውን ሲጠቁሙ፣ “ኢየሱስ ሁሉም ወደ እርሱ እንዲመጡ ይጋብዛል፤” የሚለውን ሃረግ መደጋገም ይችላሉ። ወደ ኢየሱስ እንዴት እንመጣለን?

  • እንደ “አብሬህ እጓዛለው [I’ll Walk with You]” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 140–41)፣ ያለ ሁሉንም ሰዎች ስለመውደድ የሚናገር መዝሙር የ2 ኔፊ 26፥33ን መልዕክት እንድታስተምሩ ሊረዳችሁ ይችላል።

2 ኔፊ 28፥229፥7–1130፥3–6

መጽሐፈ ሞርሞን በረከት ነው።

  • ልጆቻችሁ መፅሐፈ ሞርሞን “ታላቅ ዋጋ” እንዳለው እንዲሰማቸው ለመርዳት (2 ኔፊ 28፥2)፣ አንድን ቅጂ እንደ ስጦታ በመጠቅለል በውስጡ ምን እንዳለ እንዲገምቱ አድርጓቸው። በ2 ኔፊ 30፥3–6 ውስጥ ፍንጭ መፈለግ ይችላሉ። መፅሐፈ ሞርሞን ለእናንተ ለምን ትልቅ ዋጋ እንዳለው ለልጆቻችሁ ንገሩ እንዲሁም ስሜታቸውን እንዲያካፍሉ አድርጓቸው።

  • “መፅሐፈ ሞርሞንን ማንበብ አያስፈልገኝም። መጽሐፍ ቅዱስን አስቀድሜ አንብቢያለሁ” የሚልን ጓደኛ እንዲያስቡ ልጆቻችሁን ለመጠየቅ አስቡ። ለጓደኛችን ምን ማለት እንችላለን? ለምን እግዚአብሔር ሁለቱም መጽሐፍት እንዲኖረን እንደፈለገ ለመማር 2 ኔፊ 29፥7–11ን በጋራ አንብቡ።

2 ኔፊ 28፥30–31

የሰማይ አባት ትንሽ በትንሽ ያስተምረኛል።

  • ምናልባት “ደረጃ በደረጃ” ምን ማለት እንደሆነ ልጆቻችሁ እንዲገነዘቡ የሚረዳ የተግባር ትምህርትን ልታስቡ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ እንቆቅልሾችን መገጣጠም ወይም በብሎኮች አንድ ቁራጭ በአንድ ቁራጭ የሆነ ነገርን መገንባት ይችላሉ። ወይም ክህሎትን፣ ለምሳሌ ገመድ ማሰርን ወይም ስዕል መሳልን ደረጃ በደረጃ ልታስተምሯቸው ትችላላችሁ። ከዚያም 2 ኔፊ 28፥30ን ማንበብ እና እግዚአብሔር አንድን እውነት አንድ በአንድ እንዴት እንደሚያስተምረን መወያየት ትችላላችሁ።

  • ሌላው ሃሳብ ደግሞ ከ2 ኔፊ 28፥30 አንድን ሃረግ በመምረጥ አንድ ቃል ተራ በተራ ለመጻፍ ሞክሩ። ይሄ እግዚአብሔር እውነትን የሚሰጠን መንገድ የሆነው እንዴት ነው? እግዚአብሔር እውነትን “በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ በስርአት ላይ ስርአት፣ ጥቂት በዚህ፣ ጥቂት በዚያ” እያደረገ የሚሰጠን ለምንድን ነው? ከእርሱ ብዙ እውነትን ለመቀበል እንደምንፈልግ እግዚአብሔርን የምናሳየው እንዴት ነው?

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘትየዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ተመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ በህዝብ መካከል

ክርስቶስ በመካከል [Christ in the Midst]፣ በጁዲዝኤ. መር