2010–2019 (እ.አ.አ)
አታታለኝ
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


አታታለኝ

የእግዚአብሄርን ትእዛዝ ስንጠብቅ፣ ሁል ጊዜ ወደ ትክክለኛው መንገድ እንመራለን እናም አንታለልም።

ዛሬ፤ የምክር ቃሌን ለሁላችሁም አቀርባለሁ፤በተለይ ለእናንተ አዳጊ ለሆናችሁ ትውልዶች — ለህጻናት ክፍል ልጆች፣ ለወጣት ወንዶች፣ እና ለወጣት ሴቶች። በእኛ ጊዜ ባሉት በጌታ ነብይ፣ ፕሬዝዳንት ራስል ኤም ኔልሰን — በጥልቅ ትፈቀራላችሁ፣ ስለዚህም ነው ባለፈው አመት ሴኔ 2018(እ ኤ አ) “ የእስራኤል ተስፋ” በሚል ርዕስ በተላለፈ ልዩ የወጣቶች አለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ከብዙዎቻችሁ ጋር ያወሩት።1 ብዙ ጊዜ ፕሬዝዳንት ኔልሰን በትክክል “የእስራኤል ተስፋ”፣ አዳጊ የሆነው ትውልድ እና በምድር ላይ የትክክለኛው እና ህያው የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የወደፊት ተስፋ ሲሉአችሁ እንሰማቸዋለን።

ወጣት ጓደኞቼ ፤ ሁለት የቤተሰብ ታሪኮችን በማካፈል መጀመር እፈልጋለሁ።

102ኛው ዳልሜሽን

ከአመታት በፊት፣ ከስራ ወደ ቤት ስደርስ —በመሬት ላይ፣ በጋራጅ በር ላይ እና በቀዩ ሸክላ ቤታችን ላይ ነጭ ቀለም በየቦታው ተረጭቶ በማየቴ ተገረምኩ። ቦታው ላይ ያለውን ሁኔታ በደንብ ከመረመርኩ በኋላ ቀለሙ አሁንም እርጥብ እንደ ሆነ አረጋገጥኩ። የቀለም ኮቴዎች ወደ ጓሮው አመሩ ስለዚህ ተከተልኳችው። እዛ፤ የአምስት አመት ወንድ ልጄ ውሻችንን በእጁ የቀለም ብሩሽ ይዞ ሲያባርረው አገኘሁት። ቆንጆው ጥቁሩ ላብራዶር ውሻችን ግማሽ ነጭ ተቀብቷል!

““ምን እየሰራህ ነው?” በሃይለኛ ድምጽ ጠየኩ።

ወንድ ልጄ ቆመ፣ ወደ እኔ አየ፣ ወደ ውሻው ተመለከተ፣ ነጭ ቀለም ወደሚያንጠባጥበው የቀለም ብሩሽ አየና ፤ እንዲህ አለ “’ ሚሎ ልክ ፊልሙ ላይ እንዳሉት ጥቁር ነጠብጣብ ውሾች እንዲመስል ፈልጌ ነው — አወቅከው 101 ዳልሜሽን የሚለው ላይ እንዳሉት።”

ምስል
ጥቁር ላብራዶር
ምስል
ዳልሜትያን

ውሻችንን እወደዋለሁ። እሱ ፍጹም እንደሆነ አስብ ነበር፤ ያን ቀን ግን ወንድ ልጄ የተለየ ሃሳብ ነበረው።

ባለሰንበሯ የድመት ግልገል

ሁለተኛው ታሪኬ ያማከለው ከከተማ እርቆ ገጠር በሚገኝ ቤት ስለሚኖር፣ ታላቅ አጎት ግሮቨር (የሚስቱ አባት አጎት) ነው። አጎት ግሮቨር እያረጀ ነበር። ከመሞቱ በፊት ወንድ ልጆቻችን እንዲተዋወቁት አሰብን። ስለዚህ፣ አንድ ቀትር፣ ወደ ትሁት ቤቱ ረጅም የመኪና ጉዞ አደረግን። ለመጎብኘት እና ወንድ ልጆቻችንን ለማስተዋወቅ አንድ ላይ ቁጭ አልን። በንግግራችን ብዙ ሳንገፋ፣ ምናልባት አምስት እና ስድስት አመታቸው የሆኑት ሁለቱ ትንንሽ ወንድ ልጆቻችን ወደ ውጭ ወጥተው መጫወት ፈለጉ።

አጎት ግሮቨር፣ ጥያቄአችውን ሰምቶ ፊታቸው ላይ በፊቱ ጎንበስ አለ። ፊቱ በጣም የጠወለገ እና ያልተለመደ በመሆኑ ወንድ ልጆቻችን ትንሽ ፈርተው ነበር። ጠጠር ባለ ድምጽ፣ “ተጠንቀቁ— ውጭ ብዙ ሽንታቸው በጣም የሚሸት አውሬዎች አሉ” አላቸው ። ይህን ስንሰማ፤ ሊሳ እና እኔ ከመደንገጥ በላይ ፤ በአውሬው እንዳይረጩ ተጨንቀን ነበር። ወንድ ልጆቻችን ወዲያው ለመጫወት ወደ ውጭ ወጡ። እኛ ጉብኝታችንን ቀጠልን።

ምስል
አጥቢ እንስሳ

በኋላ ወደ ቤት ለመሄድ መኪና ውስጥ ስንገባ፣ ወንድ ልጆቼን “አውሬዎቹን አያችሁ?” ብዬ ጠየኳቸው። አንደኛው “አይ፣ ምንም አላየንም፣ ነገር ግን ነጭ ሸንተረር ያለው ጥቁር የድመት ግልገል አይተናል” አለ።

ታላቁ አታላይ

የእነዚህ የዋህ ህጻናት ስለህይወት እና እውነታ አዲስ ነገርን የማግኘት ታሪክ እያንዳንዳችንን ፈገግ ሊያስብለን ይችላል። ነገር ግን በተጨማሪ ጥልቅ የሆነ ሃሳብን ያሳያል።

በመጀመሪያው ታሪክ ላይ፤ ትንሹ ወንድ ልጃችን ቆንጆ ውሻ እንደ ቤት እንስሳ አለው፤ ቢሆንም፤ አንድ ጣሳ ቀለም እና የቀለም ቡርሽ በእጁ ይዞ፣ የራሱን ምናባዊ እውነታ ለመፍጠር ቆርጦ ነበር።

በሁለተኛው ታሪክ፤ ወንዶቹ አውሬውን ከማግኘት ሊመጣ የሚችለውን አደጋ አላወቁም ነበር። ምን እንዳገኙ በትክክል ባለመለየታቸው፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ራሳቸውን ለትልቅ አደጋ አጋልጠው ነበረ። እነዚህ ታሪኮች ስለተሳሳተ ማንነት ናቸው—ትክክለኛው ነገርን ሌላነገር አድርጎ በማሰብ የሆነ። በእያንዳንዱ ታሪክ ውጤቱ ትንሽ ነበረ።

ነገር ግን፣ ብዙዎች ዛሬ በጣም ትልቅ በሆነ ልኬት ከእነዚህ ተመሳሳይ ችግሮች ጋር ይታገላሉ ። ወይም የነገሮች እውነታን በትክክለኛ ማንነታቸው አያዩአቸውም፤ ወይም በእውነታው አይረኩም፤ እንደ ራሳቸው ስሜት ወይም ጣዕም ድጋሚ ለመፍጠር ይሞክራሉ። በተጨማሪም፤ ዛሬ ሆነ ብለው እኛን ከማይለወጥ እውነት የሚያሸሹ ብዙ ሀይሎች አሉ። እነዚህ ማታለያዎች እና ውሸቶች ከትንሽ የማንነት ስህተቶችባሻገር ትንሽ ያልሆነ አደገኛ ውጤት ሊያመጡ ይችላሉ።

ሰይጣን፤ የውሸት አባት እና ታላቁ አታላይ፤ ነገሮችን እንዳሉ እንድንጠይቅ ያደርገናል ከዚያም ዘላለማዊ እውነትን እንድንተው ወይም የበለጠ ወደ ሚያስደስት ነገር ይለውጣቸዋል። “ከእግዚአብሄር ቅዱሳን ጋር ጦርነት ይፈጥራል”2 ሺህ ዓመታትን የእግዚአብሃርን ልጆች እንዴትጥሩን መጥፎ ነውእናምመጥፎን ጥሩ ነው እንዲሉ የማሳመን ቸሎትታን ሲቀምር እና ሲለማመድ ቆይቷል።

ሽንቱን የሚረጭ አውሬ የድመት ግልገል እንደሆነ፤ ወይም ቀለም በመቀባት፣ ላብራዶርን ወደ ዳልሜሽን መለወጥ እንደሚቻል በህይወት ያሉ ሰዎችን በማሳመን እራሱን ስመጥር አድርጓል።

ምስል
ሙሴ እግዚአብሄርን ፊት ለፊት አየው

አሁን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ወደ ሚገኘው የዚህ መሠረታዊ መርህ ምሳሌ እንመልከት ፣ የጌታ ነብይ የሆነው ሙሴ ከተመሳሳይ ችግር ጋር ፊት ለፊት ሲጋፈጥ። “ሙሴም ከፍ ወዳለ ተራራ ተነጠቀ፤ … ጌታን ፊት ለፊት አየው፣ እናም ከእርሱ ጋር አወራ”3 እግዚአብሄር ሙሴን ስለዘላለማዊው ማንነቱ አስተማረው። ምንም እንኳን ሙሴ ሟች እና ፍጹም ያልሆነ ቢሆንም፣ “በአንዲያ ልጄ አምሳል፤ እናም አንድያ ልጄ … አዳኝ ይሆናል።”ብሎ እግዚአብሄር ሙሴን አስተማረው።4

ሙሴ፤ በዚህ አስደናቂ ራዕይ፤ እግዚአብሄርን ተመለከተ እና ስለራሱ ጠቃሚ ነገር ተማረ፤ ምንም እንኳን ሟች ቢሆንም፣ እርሱ የእዚአብሄር ልጅ መሆኑን።

ይሄ ድንቅ ራዕይ ሲገባደድ ምን እንደተፈጠረ በማስተዋል አዳምጡ። እንዲህም ሆነ … ሰይጣን ሊፈትነው እንዲህ በማለት መጣ፥ የሰው ልጅ ሙሴ ሆይ፣ አምልከኝ። 5 ሙሴም በድፍረት “’ አንተማን ነህ? እነሆ፣ እኔ በአንድያ ልጅ አምሳል የሆንኩት የእግዚአብሔር ልጅነኝ፤ እናም አመልክህስ ዘንድ ያንተ ክብር የት አለ?”6 ብሎ መለሰ።

በሌላ ቃል፤ ሙሴ ያለው “ ማንነቴን ስለማውቅ ልታታልለኝ አትችልም። በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥሬአለሁ። የእርሱ ክብር እና ብርሃን የለህም። ታዲያ ለምን አመልክሀለሁ ወይም በወጥመድህ እና በማሳትህ ለምን እወድቃለሁ?” ነው።

አሁን እንዴት ሙሴ በተጨማሪ እንደመለሰ አስተውሉ ። “ከዚህ ዞር በል፣ ሰይጣን፤ አታታልለኝ 7አለ።

ሙሴ ከጠላት ለሚመጣበት ፈተና ከሰጠው ጠንካራ መልስ ብዙ መማር እንችላለን። በፈተና ተጽዕኖ ውስጥ ስትሆኑ ተመሳሳይ መልስ እንድትሰጡ እጋብዛችኋለሁ። የነፍሳችሁን ጠላት እንዲህ ብላችሁ እዘዙት ”ዞር በልልን! አንተ ምንም ክብርየለህም። አትፈትነኝ ወይም አትዋሸኝ! የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆንኩ አውቃለሁና። እናም ሁልጊዜም ለእርዳታው አምላኬን እጠራዋለሁ።”

ጠላት ግን እኛን ለመበጥበጥ ያለውን አሳሳች ምኞቱን እና ዝቅ ማድረጉን በቀላሉ አይተውም። ለሙሴም ቢሆን የዘላለም ማንነቱን ለማስረሳት ፈልጎ እንደዛው ነው ያደረገው። ።

ልክ እንደ ልጅ እየተነጫነጨ፣ “ ሰይጣን በታላቅ ድምፅ ጮኸ፣ እናም በምድርም ላይ እየጮኸ ተናገረ፣ እናም እንዲህ በማለት አዘዘ፥ እኔ አንድያ ልጅ ነኝ፣ አምልከኝ።” 8

እስቲ እንከልሰው። ምን እንዳለ ሰማችሁ? ““እኔ አንድያ ልጅ ነኝ። እኔንአምልከኝ!”

ከዛም ታላቁ አታላይ በሀይል “አታስቡ፣ አልጎዳችሁም—እኔ ሽንቴ በጣም የሚሸት እንስሳ አይደለሁም፣ ምንም የማላውቅ ጥቁር እና ነጭ ሸንተረር የድመት ግልገል ነኝ አለ።”

ምስል
ሙሴ ሴይጣንን ሲያስወጣ

ከዚያም ሙሴ ወደ እግዚአብሄር ተጣራ መለኮታዊ ሀይልን ከእርሱ ተቀበለ። ምንም እንኳን ጠላት ቢንቀጠቀጥም እና መሬትን ቢያንቀጠቅጥ፣ ሙሴ አልተንበረከከም። ድምጹ እርግጠኛ እና ጥርት ያለ ነበረ። “ሰይጣን፣ ከእኔ ዘንድ ሂድ“ በማለት አዘዘ፥ “የክብር አምላክ የሆነውን ይህን አንድ እግዚአብሔርን ብቻ አመልካለሁና።” 9

በስተመጨረሻም “… ከሙሴ አካባቢ … ጠፋ።”10

ጌታ ለሙሴ ታይቶ ለታዛዥነቱ ከባረከው በኋላ፤ እንዲህ አለው፤

“የተባረክ ነህ፣ ሙሴ … አንተ ከብዙ ውሀዎች በላይ ጠንካራ ትሆናለህ።”…

እናም አስተውል፣ እስከመጨረሻዎቹ ቀናትህም ድረስ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ።”11

ማናችንም በህይወት ምንም አይነት ደረጃ ላይ ብንሆን፤ የሙሴ ለጠላት አለመገዛት ጥርት ያለ እና እውቀት የሚጨምር ምሳሌ ነው። ለግላችሁ በጣም ጠንካራ መልእክት ነው— እሱ ሊያታልላችሁ ሲሞክር ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ። እናንተም፤ እንደ ሙሴ፣ በሰማያዊ የእርዳታ ስጦታ ተባርካችኋል።

ትዕዛዛት እና በረከቶች

እንዴት ነው ልክ ሙሴ እንዳገኘው እርዳታ እንዳትታለሉ ወይም ወደ ፈተና እንዳትገቡ የሰማይ እርዳታን ማግኘት የምትችሉት? በዘመናት ሁሉ ከመለኮታዊ እርዳታ ጋር ጥርት ያለ የመገናኛ መንገድ ጌታ እራሱ በዚህ ዘመን አዘጋጅቷል፤ እንዲህም አለ “ስለዚህም እኔ ጌታ በምድር ነዋሪዎች ላይ የሚመጣውን መቅሰፍት በማወቄ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊን ጠራሁት እናም ከሰማይም ተናገርኩት እንዲሁም ትእዛዛትን ሰጠሁት” 12 በቀላል ቃላት፣ “መጨረሻን ከመጀመሪያ” 13 የሚያውቀው ጌታ ልዩ የሆኑ የእኛን ቀን ችግሮች ያውቃል ማለት እንችላለን። ስለዚህ፤ ችግሮች እና ፈተናዎችን አብዛኛዎቹ ከጠላት የማታለል ጫና እና ውጊያ ቀጥታ ውጤት የሆኑትን እንድንቋቋም ለእኛ መንገድ አዘጋጅቶልናል።

መንገዱ ቀላል ነው። በአገልጋዮቹ አማካኝነት፤እኛ ልጆቹን እግዚአብሄር ይናገረናል፣ ፤ ትዕዛዛትን ይሰጠናል። የጠቀስኩትን ጥቅስ እንደገና ልንደግመው እንችላለን።“እኔ ጌታ… አገልጋዬን [ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን] ጠራሁት እና ከሰማይ አነጋገርሁት እናም ትእዛዛት ሰጥቼዋለሁ።” ይሄ የክብር እውነት አይደለምን?

ከልብ የመነጨ ምስክርነቴን አካፍላችኋለው ጌታ ከሰማይ በሁሉም እውነታ ዮሴፍ ስሚዝን ከመጀመሪያው ታላቅ ራእይ ጀምሮ ተናግሮታል። በእኛ ጊዜ ደግሞ ለፕሬዝዳንት ኔልሰንን ይናገረዋል። እግዚአብሄር ልጆቹ በዚህ ምድር ደስታን እና በሚቀጥለው ክብርን እንዲያገኙ ባለፉት ዘመናት ከነብያቶች ጋር እንደተነጋገረ እና ትእዛዝን ይሰጣቸው እንደነበር እመሰክራለሁ።

አሁንም በህይወት ላለው ነብያችን እግዚአብሄር ትእዛዛትን መስጠት ቀጥሎአል። ለምሳሌ ያህል ፡ ይበልጥ ቤትን ያማከለ፣ በቤተክርስቲያን የተደገፈ የተመጣጠነ የወንጌል መመሪያ ፤ የቤት ለቤት እና የጉብኝት ትምህርትን በአገልግሎት ተተክቷል፤ የቤተ መቅደስ ፖሊሲዎች እና ስርዓቶች ላይ ማሻሻያ እና በ2020 እ.ኤ.አ አዲሱ የወጣቶች እና የልጆች ፕሮግራ ይጀምራል። መልካም እና ርህሩህ በሆነው በሚወደን በሰማይ አባታችን እና የአዳኛችንን ቤተክርስቲያን በድጋሚ ለመለሰው እና በእኛ ዘመን ነብይ በጠራው በልጁ፣ በኢየሱሰ ክርስቶስ ፤ እደነቃለሁ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዳግም መመለስ አስፈሪጅማሬ ከ ሙላትሰአት ጋር ያመዛዝናል።

ክፋት በፍጹም ደስታ ሆኖ አያውቅም።

ለነብያቶች የተሰጠውን ትእዛዛት መታዘዝ ፤ በጠላት መገፋትን እና መታለልን መከላከያ ብቻ ሳይሆን ቀጣይ የሆነ ሀሴትን እና ደስታን እንድንካፈል የሚያደርግ ቁልፍ ነው። ይህ መለኮታዊ ቀመር ቀለል ያለ ነው-ጽድቅ ፣ ወይም ለትእዛዛት መታዘዝ ፣ በረከቶችን ያስገኛል ፣ እና በረከቶች በሕይወታችን ውስጥ ደስታን ወይም ሐሴትን ያመጣሉ ፡፡

ሆኖም ፤ ጠላት ሙሴን ለማተለል እንደሞከረው ፤በተመሳሳይ መንገድ እናንተንም ለማታለል ይሞክራል። ሁልግዜም እሱ ያልሆንውን ነገር ለመሆን ያስመስላል፡፡ ሁልግዜ እሱ ትክክልኛ ማንነቱን ለመደበቅ ይጥራል፡፡ መታዘዝ ህይወታችሁን በመከራ እንደሚሞላ እና ደስችሁን ይስርቃል ብሎ ይናገራል፡፡

አንዳንድ የማታለያ ዘዴዎቹን ማስብ ትችላላችሁ ? ለአብነት ፤ በመጠጥ እና በአደንዛዥ እፆች ውስጥ ያለውን ጉዳት ያሳንስና በምትኩ እርካታን እንደሚያስገኝ ይመክራል፡፡ ደካማ ንፅፅሮችን እና የታሰበ እውነታን ጨምሮ በማኅበራዊ ሚዲያ ውስጥ ሊኖሩ በሚችሉ የተለያዩ አሉታዊ ነገሮች ውስጥ ያስገባናል። በተጨማሪም ፣ እንደ አጸያፊ ምስሎች ፣ በሳይበር ጉልበተኞች በሌሎች ላይ ከባድ ጥቃቶች ፣ እና በኢንተርኔት እና በልባችን እና በአዕምሯችን ላይ ጥርጣሬ እና ፍርሃትን ለመሳሰሉ እንደ ጉዳት ወይም ሥቃይ ያሉ በቀጥታ መስመር ላይ ለሚገኙ ሌሎች ጎጂ ይዞታዎች ያጋልጠናል ፡፡ በዝግታ በማታለል “ዝም ብላችሁ ተከተሉኝ፤ በእርግጠኝነት ደስተኛ ትሆናላችሁ” ብሎ ያንሾካሽካል።

ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት በመጸሃፈ ሞርሞን ነብይ የተጻፈው ቃል ለእኛ ቀን ይሰራል ፤“ክፋትበፍጹምደስታ ሆኖ አያውቅም።”14 የሰይጣንን ማታለሎች እንዳሉ እናስተውላቸው። ነፍሳችንን ሊያጠፋ እና የዚህ ህይወት ደስታችንን እና የመጭውን ክብራችንን መስረቅ የሚፈልገውን ውሸቱን እና ግፊቱን ለመቋቋም እና ለማየት እንቻል።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ታማኝ እና ንቁ በመሆን መቀጠል አለብን፤ እውነትን የምንለይበት እና በአገልጋዮቹ አማካኝነት የጌታን ድምጽ የምንሰማበት ብቸኛው መንገድ ያ ስለሆነ። “መንፈስ እውነቱን ይናገራል እንጂ አይዋሽምና። እነዚህ ነገሮች ለነፍሳችን ደህንነት በግልፅ ተገልጠውልናል። እግዚአብሔር ደግሞ ለጥንቶቹ ነቢያት ተናግሯቸዋልና።15 የሀያሉ እግዚአብሔር ቅዱሳን ነን፣ የእሳኤል ተስፋ! እኛ እንደናቀፋለን? “ውጊያውን መሸሽ ወይም መተው አለብን?” አይ! … ለእግዚአብሄር ትእዛዛ፣ ነፍስ፣ ልብ፣ እና እጅ፣ በታማኝነት እና እውነት ሁሌ እንቆማለን።”16

ስለ እስራኤል ቅዱስ— ስለ እርሱ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነቴን እሰጣለሁ። ስለ ቀጣይ ፍቅሩ፣እውነቱ እና በማያልቀው እና ዘላለማዊ በሆነው መስዋዕትነቱ እውን ስለሆነው ደስታ ምስክርነቴን እሰጣለሁ። ትዛዛቱን ስንጠብቅ፣ ሁል ጊዜ ወደ ትክክለኛው መንገድ እንመራለን እናም አንታለልም። በቅዱሱ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።