2010–2019 (እ.አ.አ)
የአዳኙ እጅ ሲነካ
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


የአዳኙ እጅ ሲነካ

ወደ እሱ ስንመጣ ፣እኛን ለመፈወስ ሆነ ወይም ማንኛውንም ሁኔታ ለመጋፈጥ ጥንካሬን ለመስጠት እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ይመጣል፡፡

በግምት ከሁለት ሺህ አመታት በፊት አዳኙ ስለ ብጹእነት እና ሌሎች የወንጌል መርሆች ካስተማረ በኋላ ከተራራው ላይ ወረደ፡፡ እየተራመደ እያለ ፤ ለምጽ የያዘው አንድ ሰው ወደ እሱ ቀረበ፡፡ በክርስቶስ ፊት ተንበርክኮ ከህመሞ ፈውስን ሲለምን ውዳሴን እና አክብሮትን አሳይቷል፡፡ ጥያቄው ቀላል ነበር፤ “ጌታ ሆይ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ”

አዳኙም ከዛ እጁን ዘርግቶ እናም እየነካው “እወዳለው፤ ንጻ አለው፡፡”1

ስለዚህም አዳኛችን ሊባርከን እንደሚፈልግ እንማራለን፡፡ አንዳንድ በረከቶች ቶሎ ሊመጡ ይችላሉ፣ ሎሎች ጊዜ ለወስዱ ይችላሉ፣ እና አንዳንዶች ከዚህ ህይወት በኋላ እንኳን ሊመጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን በረከቶች በሰአታቸው ይመጣሉ፡፡

እንደ ለምጻሙ የሱን ፈቃድ በመቀበል እና እሱ ሊባርከን እንደሚፈልግ በማወቅ ችግሮቻችንን ለመጋፈጥ፣ ማንኛውንም አይነት ፈተናዎችን ለማሸነፍ በዚህ ህይወት ውስጥ ሀይልን እና መጽናናትን ማግኘት እንችላለን፡፡ ማንኛውንም ችግር ለመጋፈጥ፣ ማንኛውንም አይነት ፈተና ለማሸነፍ፣ እና ነገሮች እንዳሉ እንድንረዳቸው እና እንድንቋቋማቸው ሀይልን ማግኘት እንችላለን፡፡ በእርግጥ በጣም ከባድ በሆነው የህይወቱ ጊዜ ውስጥ ለአባቱ “ፈቃድህ ይሁን” ባለበት ጊዜ የአዳኙ መቋቋም ሀይል ጨምሯል፡፡2

ለምጻሙ በጉራ ወይም በማስገደድ አልነበረም ጥያቄውን ያቀረበው፡፡ ቃሎቹ፤ ትህትና የተሞላባቸው ሆነው በትልቅ ግምት የተሞሉ ነገር ግን የአዳኙ ፈቃድ እንዲፈጸም በልባዊ ፍላጎት የተሞላ እንደሆነ ያሳያሉ፡፡ ይህ ወደ ክርስቶስ ልንመጣበት የሚገባን የጸባይ ምሳሌ ነው፡፡ የአዳኙ ፍላጎት አሁንም እና ለሁልጊዜም ለሟች እና ዘላለማዊ ህይወታችን ምርጡ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነን ነው ወደ እሱ መምጣት ያለብን፡፡ እኛ የሌለንን ዘላለማዊ እይታ እሱ አለው፡፡ የሱ ፈቃድ እንደነበረው የኛም ፈቃዳችን በአባት ፈቃድ እንዲዋጥ በልባዊ ፍላጎት ወደ ክርስቶስ መምጣት አለብን፡፡3 ይህ ለዘላለማዊ ህይወት ያዘጋጀነናል፡፡3

ወደ ክርስቶስ የመጣው ለምጻም የተሸከመውን የአካላዊ እና ስሜታዊ ስቃይ ለማሰብ በጣም ይከብዳል፡፡ ለምጽ ነርቭን እና ቆዳን የአካል መበላሸትን እና የአካል ስንኩልነትን በመፍጠር ይጎዳል፡፡ በተጨማሪም ወደ ትልቅ ማህበራዊ ተቀባይነት ማጣት ያመራል፡፡ በለምጽ የተጠቃ አንድ ሰው ሚወዱትን ሰዎች ትተው እናም ከማህበረሰብ ራሱነን አግሎ መሄድ አለበት፡፡ ለምጻሞች በአካላዊም እና መንፈሳዊም መልኩ ንጹህ ያልሆኑ ተብለው ነበር የሚወሰዱት፡፡ በዚህ ምክንያት የሙሴ ህግ ለምጻሞች የተቀደደ ልብስ አእንዲለብሱ እና ሲራመዱ ንጹህ ያልሆነ እያሉ እንዲናገሩ ያደርግ ነበር፡፡40 የታመሙ እና የተጠሉ ለምጻሞች በተተው ቤቶች ወይም መቃብሮች ውስጥ ኖሩ፡፡5 አዳኙን የቀረበው ለምጻም ልቡ የተሰበረ እንደሆነ ለማሰብ አይከብድም፡፡

በአንድ መንገድ ወይም በሌላ በኛ ድርጊት ሆነ በሌሎች ወይም ልንቆጣጠረው በምንችለው ሁኔታ ወይም በማትችሉት ነገር እኛም ስብራት ሊሰማን ይችላል፡፡ በንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ውስጥ የኛን ፍቃድ በሱ እጅ ላይ ማሰቀመጥ እንችላለን፡፡

ከተወሰነ አመታት በፊት ፤ዙልማ፤ የኔ ክፋይ አንድ ከአንዱ ልጃችን ሰርግ ሁለት ሳምንት ቀደም ብሎ ከባድ ዜና ተቀበለች፡፡ በጆሮ ከረጢት ውስጥ እጢ በቅሏል እና በፍጥነት እያደገ ነበር፡፡ ፊቷ ማበጥ ጀመረ፣ እናም ከባድ ቀዶ ጥገና በአስቸኳይ ማደረግ ነበረባት፡፡ ብዙ ሃሳቦች በአይምሮዋ ውስጥ ተመላለሱ እናም ልቧን ተጫናት፡፡ እጢው አደገኛ ነበር ? እንዴት ሰውነቷ ያገግማል? ፊቷ ሽባ ይሆናል? ህመሙ ምን ያህል ሀይለኛ ይሆናል? ፊታ ቋሚ ጠባሳ ይኖረዋል? እጢው ከወጣ በኋላ ተመልሶ ይመጣል? የልጇ ሰርግ ላይ መገኘት ትችል ይሆን?ሽ በቀዶ ጥገናው ክፍል ውስጥ ተኝታ ፣ ስብራት ተሰማት፡፡

በዛ በጣም አስፈላጊ ጊዜ ውስጥ ፣ የጌታን ፈቃድ መቀበል እንዳለባት መንፈሱ አንሾካሾከላት፡፡ ከዚያም እምነቷን እግዚአብሄር ላይ ለማድረግ ወሰነች። ውጤቱ ምንም ይሁን ለሷ የተሻለ እንደሆነ በሃይል ተሰማት ። ከትንሽ ጊዜም በኋላ ወደ ቀዶ ጥገና እንቅልፍ ወደቀች፡፡

ከዛም በኋላ በቀን ማሰታወሻዋ ላይ እንዲህ ገጠመች በቀዶ ጠጋኙ ጠረፔዛ ላይ በፊትህ ተንበረከኩ እናም ለአንተ ፈቃድ ራሴን አሳለፍኩ፡፡ ከአንተ ምንም መጥፎ ነገር እንደማይመጣ በማወቄ ፤ወደ አንተ መዞር እንደምችል አውቄያለው፡

የሷን ፈቃድ ለአባቷ በመስጠቷ ሀይል እና መጽናናትን አገኘች፡፡ ያን ቀን እግዚአብሄር በትልቁ ባርኳታል፡፡

ያለንበት ሁኔታ መንም ቢሆን ወደ ክርስቶስ ለመምጣት እምነታችንን መለማመድ እና የምንተማመንበትን እግዚአብሄር ማግኘት እንችላለን፡፡ ከልጆቼ መሃል አንዱ እንዲህ ጻፈ

ነቢዩ እንዳለው የእግዚአብሄ ፊት ከጸሃይ በላይ ደማቅ ነው

ጸጉሩ ደሞ ከበረዶ በላይ ነጭ ነው፡፡

ድምጹ ደግሞ እንደሚወርድ ወንዝ ያጓራል፣

እናም ከሱ አንጻር ሰው ምንም ነው…

እኔ እንኳን ምንም እንዳልሆንኩ ሳውቅ መሰበር ተሰማኝ፡፡

እናም ከዛ ጊዜ በኋላ ነው ላምነው ወደ ምችለው እግዚአብሄር በመንገዳገድ የምሄደው፡፡

እናም ከዛ ጊዜ በኋላ ነው ላምነው የምችለውን እግዚአብሄር የማገኘው፡፡6

ልናምነው የምንችለው እግዚአብሄር በያንዳንዱ ሁኔታ ተስፋችንን ይጨምራል። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ስለሚወደን እና ለኛ የተሻለውን ስለሚፈልግ ልናምነው እንችላለን፡፡

ለምጻሙ ወደፊት የቀረበው በተስፋ ሀይል አማካኝነት ነው፡፡ አለም ምንም መፍትሄ አልሰጠውም ፤ መጽናናትንም እንኳን፡፡ ስለዚህ የአዳኙ ትንሽ እሱን መንካት ለመላ ነፍሱ እንደ ዳበሳ ነው የተሰማው፡፡ በአዳኙ እጁ በመነካቱ ለምጻሙ የተሰማውን ጥልቅ የምስጋና ስሜቶች፤ በተለይ ደግሞ “እወዳለው ንጻ” የሚለውን ቃላት ሲሰማ የተሰማውን ማለም ብቻ ነው የምንችለው፡፡

ታሪኩ “ወዲያውም ለምጹ ነጻ፡፡”ብሎ ይገልጻል፡፡7

እኛም የአዳኙን አፍቃሪ፣ ፈዋሽ እጆች ሲነኩን ሊሰማን ይችላል፡፡ ንጹህ እንድንሆን ሊረዳን እንደሚፈልግ በማወቃችን ምን አይነት ሀሴት፣ ተስፋ፣ እና ምሰጋና ወደ ነፍሳችን ይመጣል፡፡ ወደ እሱ ስንመጣ ፣እኛን ለመፈወስ ሆነ ወይም ማንኛውንም ሁኔታ ለመጋፈጥ ጥንካሬን ለመስጠት እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ይመጣል፡፡

በማንኛውም መጠን —የኛን ሳይሆን— የሱን ፈቃድ መቀበል ያለንበትን ሁኔታዎች እንድንረዳ ይረዳናል፡፡ ምንም መጥፎ ነገር ከእግዚአብሄር ሊመጣ አይችልም፡፡ ለኛ የተሻለው ምን እንደሆነ ያውቃል፡፡ ምናልባት ወዲያውኑ ሸክማችንን ሊያነሳ አይችልም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለአልማ እና ለህዝቦቹ እንዳደረገው፤ እነዛ ሸክሞች ቀላል እንደሆኑ እንዲሰማን ያደርጋል፡፡8 በመጨረሻም በቃልኪዳኖች ምክንያት ወይ በዚህ ሕይወት ወይም በተቀደሰው ትንሳኤ ሸክሞቹ ይነሳሉ፡፡9

የሱ ፈቃድ እንዲሆን ልባዊ ፍላጎት፣ የመሲሃችንን መለኮታዊ ተፈጥሮ ከመረዳት ጋር ለምጻሙ ለመንጻት ያሳየውን አይነት እምነት እንድናሳድግ ይረዳናል፡፡ እየሱስ ክርስቶስ የፍቅር አምላክ ነው፣የተስፋ አምላክ ነው፣ የፈውስ አምላክ ነው፣ሊባርከን እና ንጹህ እንድንሆን ሊረዳን የሚፈልግ አምላክ ነው፡፡ እዚህ ምድር ላይ ከመምጣቱ በፊት እሱ እኛ ወደ መተላለፍ ስንገባ ሊያድነን ይህን ነበር የፈለገው፡፡ በጌተሰማኒ የሀጢያትን ክፍያ በሚከፍልበት ጊዜ በሰው አዕምሮ ሊታሰብ የማይችል ህመም ሲያጋጥመው ያን ነበር የፈለገው፡፡ አሁን በአባቱ ፊት በኛ ቦታ ሲለምንልን ያንን ነው የሚፈልገው፡፡10 ለዛ ነው አሁንም ድምጹ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለው” እያለ የሚያስተጋባው፡፡11

ለማድረግ አቅሙ ስላለው ሊፈውሰን እና ከፍ ሊያደርገን ይችላላል፡፡ በሁሉም ነገር ሊረዳን እንዲችል እናም ሊፈውሰን እና ከፍ ሊያረገን እንዲችል አንጀቱ በምህረት እንዲሞላ የሰውነትን እና የመንፈስን ህመም ሁሉ በላዩ ላይ ወሰደ፡፡12 የኢሳያስ ቃላት በአቢናዲ እንደተነገሩት ፣በቆንጆ እና በሚነካ መልኩ አስቀምጦታል፤

በእውነት ስቃያችንን ተቀበለ፤ እናም ሀዘናችንን ተሸከመ፤

ነገር ግን ስለመተላለፋችን እርሱ ቆሰለ፤ ስለበደላችንም ደቀቀ፤ የሰላማችን ተግሳፅ በእርሱ ላይ ነበር፤ እናም በቁስሉ ተፈወስን።13

ይህን ተመሳሳዩን ሀሳብ በዚህ ግጥም ውስጥ እንማራለን፤

“የናዝሬት አናጺ ሆይ፣

በፊት የተሰበረውን ልብ ጠግን፣

እስከ ሞት ድረስ የተሰባበረውን ህይወት፤ ይህ ምሽትን ወደ ሞት የሰባበረ ህይወት፤

ኦ አናጺው ልትጠግናቸው ትችላለህ? ”

እናም በደግ እና በዝግጁ እጁ

የሱ ጣፋጭ ህይወት ተሰፍቷል

በተሰበረ ህይወታችን ውስጥ ፤እሰከቆምን ድረስ

አዲስ ፍጥረት— “ አዲስ ነገረር ሁሉ ፡፡”

“የተሰበረው የልብ ክፍል፣

ፍላጎት፣ ምኞት፣ ተስፋ እና እምነት

አንተ ወደ ፍጹም ክፍል ቀርጸህ አውጣ

ኦ፣ የናዝሬት አናጺ!”14

በማንኛውም መልኩ ንጹህ ካልሆናችሁ፣ ስብራት ከተሰማችሁ፣ ንጹህ መሆን እንደምትችሉ እወቁ፣ እሱ ስለሚወዳችሁ መጠገን ትችላላችሁ፡፡ ከሱ ምንም መጥፎ ነገር ሊመጣ እንደማይችል ተማመኑ፡፡

እሱ “ከሁሉም ነገሮች በታች(ስለ)ወረደ” በህይወታችን ውስጥ የተሰበሩ ነገሮች ሁሉ አንዲጠገኑ ያስችላል እናም ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ እንችላለን፡፡ 15 በምድር እና በሰማይ ላይ ያሉ ነገሮች ሁሉ በሱ ይታረቃሉ 16

ሁሉንም አስፈላጊ ደረጃዎች ወስደን ወደ ክርስቶስ እንምጣ፡፡ ይህን ስናደርግ “ጌታ ሆይ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ሃሳባችን አንድ ይሁን፡፡ እንዲህ ስናደርግ “እወዳለው ንጻ” ከሚለው ከጣፋጩ የሚያሰተጋባው ድምጹ ጎን የመምህሩን ፈዋሽ ንኪት መቀበል እንችላለን፡፡

አዳኙ ልናምነው የምንችለው እግዚአብሔር ነው፡፡ የተቀባው እሱ ክርስቶስ ነው በቅዱስ ስሙ የምመሰክርለት መሲህ እየሱስ ክርስቶስ አሜን፡፡