2010–2019 (እ.አ.አ)
እንደገና እስከምንገናኝ ድረስ
ኦክተውበር 2014


እንደገና እስከምንገናኝ ድረስ

ሁላችንም የሰማነውን እውነታዎች እናሰላስል እና ይህ ጉባኤ ሲጀምር ከነበርነው በበለጠ ቆራጥ ደቀ መዝሙሮች እንድንሆን ይርዱን።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ሁለት የአነሳሽ መልዕክቶችን ክብራዊ ቀኖች ተካፍለናል። በዚህ የጉባኤ ስብሰባዎች ውስጥ የነበረውን መንፈስ ስንካፈል ልቦቻችን ተነክተዋል እናም እምነታችን ጠንክሯል። ስናጠቃልል፣ የሰማይ አባታችንን ለእኛ ላለው ለብዙ በረከቶቹ እናመሰግነዋለን።

በስብሰባዎቹ ውስጥ በተሰጡት ውብ መዝሙሮች ከፍ ብለናል እንዲሁም ተነሳስተናል። የተሰጡት ፀሎቶች ወደ ሰማይ አቅርበውናል።

የመላ ቤተክርስቲያኗን ልባዊ ምስጋና በዚህ ጉባኤ ከጥሪ ለተሰናበቱት ሰዎች ልግለፅ። እንናፍቃቸዋለን። ለጌታ ስራ ላበረከቱት አስተዋፅዎ እጅግ ብዙ ነበር እናም በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ይሰማል።

ወደ ቤቶቻችን ከዚህ በፊት ከነበርነው በተሻለ ትንሽ የተሻልን ለመሆን ወስነን እንመለስ። ትንሽ ደጎች እና በለጠ ሀሳቢዎች እንሁን። ለአባል ጓደኞቻችን ብቻ ሳይሆን የእኛ እምነት ተከታይ ላልሆኑትም ጭምር እጃችንን ለእርዳታ እንዘርጋ። ከእነሱ ጋር ስንቀራረብ፣ ለእነሱ ያለንን ክብር እናሳያቸው።

ሁል ቀን በፈተናዎች የሚቸገሩ ሰዎች አሉ። መቆርቆራችንን እና የእርዳታ እጃችንን ለእነሱ እናሳይ። እርስ በራሳችን ስንተሳሰብ፣ እንባረካለን።

አዛውንቶችን እና የቤት እስረኛ ለሆኑትን እናስታውስ። እንርሱን ለመጎብኘት ጊዜ ሰንወስድ፣ እንደተወደዱ እና ቦታ እንደተሰጣቸው ያውቃሉ። “ደካሞች ለመርዳት፣ የወረዱ እጆችን ወደ ላይ ለመደገፍ እና የደከሙ ጉልነቶች ለማጠንከር”1 ያለብንን ሀላፊነት እንከተል።

ትክክለኛውን ነገር በሁሉም ጊዜ እና በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ለማድረግ በመሞከር የማንዋሽ እና ሀቀኛ ሰዎች እንሁን። ስለሆነም “በአለም ውስጥ ብርሀኖች እሆንን” የክርስቶስ አማኝ ተከታዮች፣ የፅድቅ ምሳሌዎች እንሁን። 2

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ለእኔ ብላችሁ ለፀለያችሁት ፀሎት አመሰግናችኋለው። በሙሉ ልቤ እና ጥንካዬ የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለማድረግ እና እርሱን እና እናንተን ለማገልገል በምጥርበት ጊዜ አጠንክረውኛል፣ ከፍ አድርገውኛል።

ይህንን ጉባኤ ለቀን ስንወጣ፣ የሰማይን በረከቶች በእያንዳንዳችሁ ላይ አስተላልፋለው። ከቤቶቻችሁ እርቃችሁ ላላችሁ ሰዎች ወደ እነሱ በሰላም ተመለሱ እና ሁሉንም ነገሮች በሰላም አግኙ። ሁላችንም የሰማነውን እውነታዎች እናሰላስል እና ይህ ጉባኤ ሲጀምር ከነበርነው በበለጠ ቆራጥ ደቀ መዝሙሮች እንድንሆን ይርዱን።

በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ መልሰን እሰከምንገናኝ፣ የጌታ በረከቶች በላያችሁ ላይ እንዲሁም በእርግጥ በሁላችንም ላይ እንዲሆን እጠይቃለው። ይህንንም የማደርገው ቅዱስ በሆነው ስሙ- በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በጌታችን እና በአዳኛችን ስም ነው፣ አሜን።