2010–2019 (እ.አ.አ)
እነዚህ ነገሮችን ለእራሴ አውቃለው
ኦክተውበር 2014


እነዚህ ነገሮችን ለእራሴ አውቃለው

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን እንደሆነ እና ጆሴፍ ስሚዝ የመልሶ መቋቋም ነብይ እንደነበር ለራሳችን ማወቅ እንችላለን።

ውድ ወንድሞች፣ በፕሬዘደንት ቶማስ  ኤስ. ሞንሰን የግል ምሳሌ እና የክህነት አገልግሎት በተደጋጋሚ ተነሳስተናል። በቅርቡ፣ ብዚ ዲያቆኖች “ስለ ፕሬዘደንት ሞንሰን የበለጠ ምን ታደንቃላችሁ?” ተብለው ተጠይቀው ነበር። አንድ ዲያቆን ፕሬዘደንት ሞንሰን ልጅ በነበረበት ጊዜ አሻንጉሊቶቹን ለተቸገረ ጓደኛው እንዴት እንደሰጠው ተናገረ። ሌላኛው ፕሬዘደንት ሞንሰን በዋርዱ ውስጥ ባላቸውን በሞት ያጡ ሴቶችን እንዴት አንደተንከበከበ ገለፅ። ሶስተኛው በወጣትነት እድሜው ሐዋርያ ሆኖ እንደተጠራ እና በአለም ዙሪያ ያሉ ህዝቦችን እንደባረከ አስታወቀ። ከዛ አንድ ወጣት ሰውዬ “ስለ ፕሬዘደንት ሞንሰን የበለጠ የማደንቀው ጠንካራ ምስክርነቱን ነው አለ።”።

በእርግጥ፣ የነብያችንን ለየት ያለ የአዳኙን የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነትን እና ሁሌ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት የመከተል ቆራጥነቱን ሁላችንም ተሰምቶናል። ባካፈለው በእያንዳንዱ ተሞክሮ፣ ፕሬዘደንት ሞንሰን ወንጌልን በበለጠ ሁኔታ እንድንኖር እና የግል ምስክርነታችንን እንድንሻ እና እንድናሳድግ ይጋብዘናል። ከትንሽ ጉባኤዎች በፊት በዚህ መነጋገሪያ ላይ ሆኖ ያለውን አስታውሱ፥ “ጠንካራ መሆን እንድንችል እና ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ በመጎተት የሚገፋንን ሁሉ መቋቋም እንችል ዘንድ …  የራሳችን ምስክርነት ሊኖረን ይገባል። 12 አመታችሁ ይሁን 112- ወይም በየትኛውም መሀከለኛ ቦታ ላይ ሁኑ- የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እውነት እንደሆነ ማወቅ ትችላላችሁ።”1

ምንም እንኳን የዛሬ ምሽት መልዕክቴ ክ 112 አመት ይልቅ ወደ 12 አመት ለሚጠጉት ነው፣ የማካፍለው መርህ እያንዳንዱን ይመለከታል። ለፕሬዘደን ሞንሰን ቃል መልስ በመስጠት፣ እያንዳንዳችን ለራሳችን ወንጌሉ እውነት እንደሆነ እናውቃለን ወይ? ብዬ እጠይቃለው። በድፍረት ምስክርነታችን በትክክል የራሳችን ነው ብለን ማለት እንችላለን? ፕሬዘደንት ሞንሰንን በድጋሜ ለመጥቀስ፥ “የአዳኛችን እና የወንጌሉ ጠንካራ ምስክርነት ከሀጢያት እና በዙሪያችሁ ካሉት መጥፎ ነገሮች እንደሚጠብቃችሁ እገልፃለው። … የእነዚህን ነገሪች ምስክርነት ከሌላችሁ፣ ለማግኘት ማድረግ ያለባችሁን አስፈላጊ ነገሮች አድርጉ። የራሳችሁን ምስክርነት ማግኘት ለእናንተ በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም የሌሎች ሰዎች ምስክርነት እስከተወሰነ ቦታ ነው ሊያደርሳችሁ የሚችለው።”2

እነዚህ ነገሮችን ለእራሴ አውቃለው

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እውነት መሆኑን መማራችን፣ በሕይወት ውስጥ ያለ ትልቅ እና ደስ የሚያሰኝ ተሞክሮ ሊሆን ይችላል። የልጅ ጠረኞቹ “እናቶቻችን እንደሚያውቁት አንጠራጠርም”3 እንዳሉት በሌሎች ሰዎች ምስክርነት ላይ በመመርኮዝ ልንጀምር እንችላለን። ይሄ ለመጀመር መልካም ቦታ ነው። ነገር ግን ከዛ ጀመረን መገንባት አለብን። ወንጌልን በመኖር ለመጠንከር ምስክርነታችንን እንደመቀበል እና ማጠንከር የበለጠ ምንም ጠቃሚ ነገር የለም። አልማ “እነዚህ ነገሮችን ለእራሴ አውቃለው” ብሎ እንዳወጀው እኛም ማወጅ መቻል አለብን።4

“እናም እርግጠኝነታቸውን እንደማውቅስ እንዴት ልትገምቱ ትችላላችሁ?” አልማ ቀጠለ። እነሆ እነዚህ እንዲታወቁኝ የሆኑት በእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ነው። እነሆ እነዚህን ነገሮች ለራሴ ለማወቅ ለብሱ ቀናት ፆሜአለው አንዲሁም ፀልያለው። እናም አሁን እውነት መሆናቸውን አውቄአለው።”5

አባቴ ያየውን ነገር ለማየት ተመኘው

ልክ እንደ አልማ፣ ኔፊም እውነታውን ለራሱ ለማወቅ ችሏል። አባቱ ብዙ መንፈሳዊ ተሞክሮዎቹን ሲናገር ከሰማ በኋላ፣ ኔፊ አባቱ ያወቀውን ለማወቅ ፈለገ። ይሄ ዝምብሎ በቀላሉ ከመፈለግ የዘለለ ነበር- የተራበበት እና የተጠማበት ነገር ነበር። ምንም እንኳን “እጅግ በጣም ወጣት” ቢሆንም “የእግዚአብሔርን ሚስጥራቶች ለማወቅ ትልቅ ፍላጎት”6 ነበረው። “እነዚህን ነገሮች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለማየት እናም ለመስማት እናም ለማወቅ”7 ፈለገ።

ኔፊ “ቁጭ ብሎ በልቡ ሲያሰላስል” “በመንፈስ ውስጥ… እጅግ በጣም ከፍ ባለ ተራራ ላይ” ተወስዶ “ምን ትፈልጋለህ?” ተብሎ ተጠየቀ። የእሱም መልስ ቀላል ነበር “አባቴ ያየውን ነገር ማየት እፈልጋለው ”8 በአማኝ ልቡ እና በታታሪ ሙከራው ምክንያት፣ ኔፊ በድንቅ ተሞክሮ ተባርኮ ነበር። የአዳኙን የኢየሱስ ክርስቶስ ውልደት፣ ሕይወት እና ስቅለት ምስክርነትን ተቀበለ፤ የመጽሐፈ ሞርሞንን መምጣት እና በመጨረሻው ቀናት የወንጌልን መልሶ መቋቋም ተመለከተ- ሁሉም ነገር የሆነው ለራሱ ለማወቅ በነበረው ቅን ፍላጎት ምክንያት ውጤት ነበር።9

እነዚህ ከጌታ ጋር የነበረው የግል አጋጣሚዎች ኔፊን በቅርብ ለሚያጋጥሙት ችግሮቸና ፈተናዎች አዘጋጁት። ሌሎቹ ቤተሰቦቹ ሲታገሉ በጥንካሬ እንዲቆም አስቻሉት። ይህን ማድረግ የቻለው ለራሱ ስለተማረ እና ለእራሱ ስላወቀ ነው። የራሱ ምስክርነትን በማግኘት ተባርኮ ነበር።

እግዚአብሔርን ይጠይቅ

ልክ እንደ ኔፊ፣ ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝም መንፈሳዊ ለሆኑ እውነታዎች “እይምሮው ወሳኝ ለሀሆነ ነፀብራቅ ሲጠራ” “እጅግ በጣም ወጣት” ነበር። ጆሴፍ ስለ ሐይማኖት በሚጋጭ እና ግራ በሚያጋባ ነገሮች በመከበቡ ሰአቱ “የታላቅ አለመረጋጋት” ነበር። የትኛው ቤተክርስቲያን እውነት እንደነበር ለማወቅ ፈለገ።10 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉት “ማንኛውም ጥበብ የጎደለው፣ እግዚአብሔርን ይጠይቅ”11 በሚሉት በእነዚህ ቃላቶች በመነሳሳት መልስ ለማግኘት ለራሱ ተንቀሳቀሰ። በሚያምረው የፀደይ ጠዋት በ1820፣ በጫካ ውስጥ ገባ እና በፀሎት ተንበረከከ። በእምነቱ ምክንያት እና እግዚአብሔር ለእሱ ለየት ያለ ስራ ስላለው፣ ጆሴፍ የእግዚአብሔር አባትን እና የልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን ክብራዊ እይታ ተቀበለ እናም የሚያደርገው ነገር ምን እንደነበር ለራሱ አወቀ።

በጆሴፍ ተሞክሮ ውስጥ ተግባራዊ ልታደርጉት የምትችሉትን የራሳችሁን ምስክርነት የማግኘት እና የማጠንከር መንገድ ተመለከታችሁን? የሴፍ መጽሐፍ ቅዱሶች ልቡን ዘልቀው እንዲገቡ ፈቀደ። በጥልቅ አሰላሰለባቸው እናም ወደ ራሱ ሁኔታ ተጋባራዊ አደረገባቸው። ከዛ ባወቀው ነገር ላይ ተግባራዊ አደረገ። ውጤቱ ክብራማው የመጀመሪያው ራዕይ- እና ክእሱ በኋላ የመጡት ሁሉም ነገሮች ነበሩ። ይህች ቤተክርስቲያን በግልፅ የተመሰረተችው ማንም ሰው- የ14 አመት ገበሬ ልጅ ጨምሮ- “እግዚአብሔርን መጠየቅ” እና ለፀሎቱ መልስ መቀበል በሚችልበት መርህ ላይ ነበር።

ስለዚህ ምስክርነት ምንድን ነው?

የቤተክርስቲያን አባሎች ብዙውን ጊዜ የወንጌል ምስክርነታቸው በጣም ዋጋ ያለው ንብረታቸው እንደሆነ ሲናገሩ እንሰማለን። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ እኛ የሚመጣ የእግዚአብሔር ቅዱስ ስጦታ ነው። ስናጠና፣ ስንፀልይ እና ወንጌልን ስንኖር የምንቀበለው ፀጥ ያለ፣ የማይናወጥ እውነታ ነው። የምንማረው እና የምናደርገው ነገር ትክክል እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ሲመሰክርልን የሚሰማን ስሜት ነው።

አንዳንድ ሰዎች ምስክርነት እንደ መብራት ማብሪያ እና ማጥፊያ እንደሆነ ይናገራሉ- በርቷል ወይም ጠፍቷል፤ ምስክርነት አላቹ ወይም የላቹም። በእውን፣ ምስክርነት በበለጠ ሁኔታ በተለያየ የእድገት ደረጃ እና ልማት እንደለ ዛፍ ነው። አንዳንድ በምድር ላይ ያሉ እረጅም ዛፎች በምዕራብ አሜሪካ ውስጥ በሚገኘው በሬድዉድ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ይገኛሉ። በእነዚህ እጅግ ታላቅ ዛፎች ስር ስትቆሙ፣ እያንዳንዱ ዛፍ ከትንሽዬ ፍሬ እንዳደገ ማሰቡ በጣም ይደንቃል። ምስክርነታችንም ልክ እንደዚህ ነው። ምንም እንኳን በነጠላ መንፈሳዊ ተሞክሮ ቢጀምሩም፣ ተደጋጋሚነት ባለው ምገባ እና ቀጣይነት ባለው መንፈሳዊ ተሞክሮዎች በጊዜ ውስጥ ያድጋሉ እንዲሁም ይለመልማሉ።

ነብዩ አልማ ምስክርነትን እንዴት እንደምናዳብር ማባራራቱ አያስደንቅም፣ ወደ ዛፍ ሰለሚያድገው ፍሬ ተናገር። “ስፍራን ከሰጣችሁት፣ ዘሩ በልባችሁ ከበቀለ፣ እነሆ እውነተኛ ዘር ከሆነ ወይም መልካም ዘር ከሆነ፣ ባለማመናችሁ የጌታን መንፈስ በመቃወም የማትጥሉት ከሆነ፣… እርሱም በልባቹ ውስጥ ማደግ ይጀምራል፤ እናም ይህ እድገት በልባቹ ውስጥ ሲሰማ በውስጣቹ እንዲህ ማለት ትጀምራላቹ- ይህ መልካም ዘር ነው ወይንም ቃሉ መልካም መሆን አለበት፣ ምክንያቱም መንፈሴን ከፍ እድርጓልና፣ አዎን ግንዛቤዬን ያበራልኝ ጀምሯል፣ አዎን ለኔም አስደሳች መሆን ጀምሯል።”12

እንዲህ ነው ምስክርነት በተደጋጋሚ የሚጀምረው፥ በቅዱስማ፣ በብሩሀማ፣ የእግዚአብሔር ቃል እውነት እንደሆነ በሚያረጋግጥልን ስሜት ላይ የሚገለፅ ነው። ይሁን እንጂ፣ እነዚህ ስሜቶች ድንቀ እንደመሆናቸው መጠን፣ የመጀመሪያው ብቻ ናቸው። የቀይ እንጨት ዛፍን የመጀመሪያው ትንሽዬ ጉንቁል ካበበ በኋላ ከመሳደግ በዘለለ ሁኔታ፣ ምስክርነታችሁን የማሳደግ ስራችሁ አላለቀም። እነዚህን ቀድመው የሚታዩትን መንፈሳዊ ማነሳሻዎችን ችላ የምንል ከሆነ፣ ቅዱስ መጽሐፍትን በማንበብ እና በመፀለይ እና የበለጠ መንፈሳዊ ልምዶችን በመሻት መመገባችንን ካልቀጠልን፣ ስሜታችን ይጠፋል እናም ምስክርነታችን ይኮመሽሻል።

አልማ እንዳስቀመጠው፥ “ዛፉን ከተዋችሁት፣ እናም ለእንክብካቤው ማሰብ ካቆማችሁ እነሆ ስር አያገኝም እናም የፀኃይ ሙቀት መጥቶ ባቃጠለው ጊዜ ስር ስለሌለው ይደርቃል እናም ትቆርጡትና ትጥሉታላችሁ።”13

ብዙውን ጊዜ ምስክርነቶቻችን በማይገመት ሁኔታ በተደጋጋሚ እንክብካቢያችን እና ታታሪ ስራችን አማካኝነት ልክ እንደ ዛፍ ነው የሚያድጉት። “ነገር ግን ቃሉን የምትንከባከቡ ከሆነ አዎን በታላቅ ትጋት፣ ትዕስት እና እምነታችሁ ዛፉ ማደግ ሲጀምር ፍሬውን በመጠበቅ የምትንከባከቡት ከሆነ ዛፉ ስር ያወጣል እናም እነሆ ዛፉም ወደ ዘላለማዊው ሕይወት ያድጋል።”14

አሁን ሰአቱ ነው፡ ዛሬ ቀኑ ነው

የግሌ ምስክርነት መጽሐፈ ሞርሞንን ትምህርት ሳጠና እና ሳሰላስል ጀመረ። በትህትና ፀሎት እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ስንበረከከ፣ መንፈስ ቅዱስ ለነፍሴ ያነበብኩት ነገር እውነት እንደነበር መሰከረ። ይህ የቀደመ ምስክር ፕሬዘደንት ሞንሰን “መጽሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ስናውቅ ከዛ ጆሴፍ ስሚዝ በእርግጥ ነብይ እንደነበር እና የዘላለማዊ አባት እግዚአብሔርን እና ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ማየቱ፣ እንዲሁም ወንጌሉ በመጨረሻው ቀናት በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት መልሶ መቋቋሙን- እንዲሁም የአሮናዊ እና የመልከፀዲቃዊ ክህነቶችን መልሶ መቋቋም ይከተለዋል” 15 ብሎ እንዳስተማረው ለብዙዎች የወንጌል ምስክርነቴ አቀጣጣይ ሆነ። ከዛ ቀን ጀመሮ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እውነት መሆኑን መንፈስ ቅዱስ ያረጋግጥልኝ ብዙ ቅዱስ ተሞክሮዎች ነበሩኝ። ከአልማ ጋር በእርግጠኝነት እነዚህ ነገሮችን ለእራሴ አውቃለው ማለት እችላለው።

የእኔ ወጣት ጓደኞች፣ ወንጌሉ እውነት እንደሆነ ለራሳችን ለመማር ወይም ለማረጋገጥ ዛሬ ሰአቱ ነው እንዲሁም ዛሬ ቀኑ ነው። ያንን ስራ ለማከናወን የራሳችንን ምስክርነት ለማግኘት እና ለማዳበር የአልማ፣ የኔፊ፣ እና የወጣቱ ጆሴፍ ስሚዝ እምነት ሊኖረን ይገባል፣

ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት ወጣት ዲያቆን፣ ፕሬዘደንት ሞንሰንን ስለ ምስክርነቱ አደንቀዋለው። ልክ ቀይ እንጨት ትልቅ ሆኖ እንደሚያድገው፣ የፕሬዘደንት ሞንሰን ምስክርነትም ከጊዜ በኋለ ማደግ እና መዳበር ነበረበት። ልክ ፕሬዘደንት ሞንሰን ኢየሱስ ክርስቶስ የአለማችን አዳኝ እና መድሀኒት እንደሆነ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የመልሶ መቋቋም፣ የእግዚአብሔር ክህነት መቋቋም ጨምሮ ነብይ እንደነበር ለራሳችን ለማወቅ እችንላለን። ያንን ቅዱስ ክህነት ተሸክመናል። እነዚህን ነገሮች እንማር እናም ለራሳችን እምድናውቅ ትሁት ፀሎቴ ነው። ቅዱስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።