2010–2019 (እ.አ.አ)
አዘጋጁ ክህነት
ኦክተውበር 2014


አዘጋጁ ክህነት

አንድ አንድ በጣም አስፈላጊ የሁኔ ነገሮችን ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች አሉ።

በአለም ዙሪያ በተንሰራፋው የእግዚአብሔር ክህነት ተሸካሚዎች ጋር ስለተሰበሰብኩኝ በጣም ደሰተኛ ነኝ። እምነታችሁን፣ አገልግሎታችሁን እና ፀሎታችሁን አደንቃለው።

የምሽቱ መልዕክቴ ስለ አሮናዊ ክህነት ነው። ይህ መልዕክት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዝቅተኛው ክህነት”1 ተብሎ የተገለፀውን ተሸክመንየጌታን ቃል-ኪዳን ለማሳካት አስተዋፅኦ ለምናደርገው ነው። እንዲሁም “አዘጋጁ” ክህነት ተብሎም ይጥራል። ዛሬ ማታ ስለ ክብራው ዝግጁነቱ ነው የምናገረው።

የጌታ እቅድ ለስራው በዝግጁነት የተሞላ ነው። የሟችነትን ፈተናዎች እና እድሎች እንለማመድ ዘንድ ምድርን አዘጋጀልን። እዚህ ባለንበት ሰአት፣ ቅዱስ መጽሐፍት እንደሚጠሩት “የመዘጋጃ ሰአት” ውስጥ ነን።2

ነብዩ አልማ እንደ ቤተሰብ ከአባት እግዚአብሔር እና ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለዘለአለም የምንኖርበትን የዛን ለዘላለማዊ ሕይወት ዝግጁነት ወሳኝ አስፈላጊነትን ገለፀ።

እንደዚህ የምንዘጋጅበትን አስፈላጊነት አብራራ፥ “እናም ሞት በሰው ዘር ላይ መምጣቱን እንመለከታለን። አዎን ሞት ጊዜአዊ ሞት በአሙሌቅ የተነገረው፤ ይሁን እንጂ የሰው ልጅ ንስሀ ይገባ ዘንድ የተሰጠው ጊዜ ነበር። ስለሆነም ይህ ህይወት የሙከራ ጊዜ ይሆናል እግዚአብሔርን ለመገናኘት የመዘጋጃ ጊዜ፣ ከትንሳኤ በኋላ ለእኛ የተነገረው መጨረሰሻ ለሌለው ሁኔታ ለመዘጋጀት የሚሆን ጊዜ ነው።” 3

በዚህ ሟች በሆነ ሕይወት ውስጥ እንድንኖር የተሰጠን ሰአት እግዚአብሔርን ለመገናኘት እንድንዘጋጅ እንደሆነ ሁሉ፣ በአሮናዊ ክህነት ውስጥ ለማገልገል የተሰጠን ሰአት ወሳኝ እርዳታን ለሌሎች እንዴት መስጠት እንዳለብን እንድንማር የሚያዘጋጀን እድል ነው። ልክ ጌታ የሟች ሕይወትን ፈተናዎች ለማለፍ እርዳታ እንደሚሰጠን ሁሉ፣ በክህነት ዝግጅታችንም እርዳታ ይልክልናል።

መልዕክቴ ጌታ ለማዘጋጀት እንዲረዱ ለሚልካቸውን ሰዎች እና አሮናዊ ክህነትን ለተሸከሙት ሰዎች ጭምር ነው። ለአባቶች እናገራለው። ለኤጲስ ዎጶሶች እናገራለው። በክህነት ዝግጁነት ውስጥ ለወጣት ወንዶች ጓደኞች እና አስተማሪዎች እንዲሆኑ እምነት ለተሰጣቸው ለመልከፀዲክ ክህነት ተሸካሚዎች እናገራለው።

በአለም ዙሪያ ላላችሁት እና ይህንን ከጊዜ በኋላ ልምታዳምጡት ወይም ለምትሰሙት ለብዙዎቻችሁ በውዳሴ እና በምስጋና እናገራለው።

በወጣትነቴ ጊዜ ስለነበሩት የቅርንጫፍ ፕሬዘደንት እና ኤጲስ ቆጶስ ባልናገር እሳሳታለው። በ12 አመቴ በትንሽዬ ቅርንጫፍ በአሜሪካ ምስራቃዊ አካል ውስጥ ዲያቆን ሆንኩኝ። ቅርንጫፉ በጣም ትንሽዬ ከመሆኑ የተነሳ የቅርንጫፉ ፕሬዘደንት የነበረው አባቴ መሀከላዊ እድሜ ያለውን ሰው ቤተክርስቲያኑን እንዲቀላቀል እስከሚጋብዝ ድረስ ታላቅ ወንድሜ እና እኔ ብቻ ነበር አሮናዊ ክህነት ተሸካሚ የነበርነው።

አዲስ የተለወጠው አሮናዊ ክህነት ተቀበለ እና ጎን ለጎንም በአሮናዊ ክህነት ላይ እንዲያስተባብር ጥሪ ተቀበለ። ባሏ ለሞተባት ሴት የሆነ ነገር ለማድረግ ስንሄድ ወንድሜን እና እኔን ተቀላቅሎን እብሮን ሲሄድ እነዛን የሚያምሩ የበልግ ቅጠሎችን ትላንት እንደተከሰተ ያህል አሁንም ድረስ አስታውሳለው። የስራው እቅድ ምን እንደነበር አላስታውስም፣ ነገር ግን በኋላ የተረዳሁትን ጌታ ሀጢያታችን ይሰረይ ዘንድ እና እርሱን ለማየት እንዘጋጅ ዘንድ መስራት አለብን ብሎ ያለውን ስንሰራ ያገዘንን የክህነት ኃይል እንደተሰማኝ አስታውሳለው።

አሁን ወደ ኋላ ስመለከት፣ ጌታ ሁለት ወንዶችን እንዲዘጋጁ ለመርዳት ብሎም አንድ ቀን ኤጲስ ቆጶሶች ሆነው ለድሆች እና ለተቸገሩት እንዲታዘዙ እንዲሁም የመዘጋጃ ክህነት የበላይ ሆነው መምራት እንዲችሉ ለመርዳት ለአዲሱ ተለዋጭ የቅርንጫፍ ፕሬዘደንቱ ጥሪ ስለሰጠው ምስጋና አቀርባለው።

የእኛ ቤተሰብ በዩታ ውስጥ ወደ ትልቅ ዋርድ ሲሄድ ዲያቆን ነበርኩኝ። በአሮናዊ ክህነት ውስጥ የምልአተ ጉባኤ ኃይል ሲሰማኝ የመጀመሪያዬ ነበር። ከዛ በኋላ የኤጲስ ቆጶሱን ኃይል እና በረከት በካህናት ምልአተ ጉባኤ ላይ ሲመሩ ሲሰማኝ የመጀመሪያዬ ነበር።

ኤጲስ ቆጶሱ በካህናት ምልአተ ጉባኤ ውስጥ የመጀመሪያ እረዳት አድርጎ ጠራኝ። ስራ ቢበዛበት እና ሌሎች ተሰጦ ያላቸውን ሰዎች መጥራት ቢችልም እንኳን ምልአተ ጉባኤውን እራሱ እንዳስተማረ አስታውሳለው። ክፍሉ ውስጥ የነበሩትን ወንበሮች በክብ አስተካክሎ አስቀመጠ። በቀኙ በኩል ወንበር ላይ አስቀመጠኝ።

በሚያስተምርበት ሰአት በትከሻው ላይ እመለከት ነበር። አልፎ አልፎ እግሩ ላይ ያለውን በሌዘር ጥራዝ ውስጥ የተቀመጠውን በጥንቃቄ የተፃፈውን ማስታወሻ እና በሌላ ጉልበቱ ላይ የከፈታቸውን ያረጁትን እና በቀለም የተቀቡትን ቅዱስ መጽሐፎች ወደ ታች ተመለከተ። በመጽሐፈ ዳንኤል ውስጥ የተናገረውን የጀግንነት ታሪክ እና በአዳኙ ላይ ያለውን ምስክርነት የተናገረውን ማስታወስ እችላለው።

ጌታ ለእርሱ ክህነት ተሸካሚዎች መዘጋጃ ጓደኞችን እንዴት በጥንቃቄ እንደሚመርጥ ሁል ጊዜ አስታውሳለው።

ኤጲስ ቆጶሴ የሚደነቁ አማካሪዎች ነበሩት፣ እና በዛ ሰአት ባለተረዳሁት ምክንያት ከአንዴ በላይ እቤት ጠርቶኝ እንዲህ ብሎኛል፣ “አንድ አንድ ጉብኝቶችን ለማድረግ አብረኸኝ እንድትሄድ እፈልጋለው።” አንድ ጊዜ የጠራኝ ብቻዋን ወደምትኖር ባሏ ወደሞተባት እና ምግብ ወደሌላት ቤት ሊወስደኝ ነበር። ወደ ቤት ስንመለስ፣ መኪናውን አቆመ፣ ያረጀውን ቅዱስ መጽሐፎቹን ከፈተ እና ያቺን ባሏ የሞተባትን ሴት እራሷን ብቻ ለመንከባከብ ሳይሆን ወደፊት በሆነ ሰአት ላይ ሌሎችን ለመርዳት ኃይል እንዳላት ለምን እንደተመለከታት ነገረኝ።

ሌላኛው ጉብኝት ከቤተክርስቲያን ለረጅም ጊዜ ወደቀረው ሰው ነበር። ኤጲስ ቆጶሴ ከቅዱሳኖች ጋር ተመልሶ እንዲሆን ጋበዘው። ለእኔ የማይወደድ እና የሚያምፅ ጠላት ሆኖ ለተሰማኝ ሰው እሱ ግን የነበረውን ፍቅር ተሰማኝ።

በሌላም አጋጣሚ ሁለት ትንሽ ሴት ልጆች በጠጪ ወላጆቻቸው እኛን በር ላይ እንዲያገኙን የተላኩትን ጎበኘን። ትንሾቹ ሴት ልጆች ወላጆቻቸው መተኛታቸውን በበሩ እስክሪን ስር ተናገሩ። ኤጲስ ቆጶሱ ለእነሱ መናገሩን፣ ፈገግ ማለቱን እና ጥሩነታቸውን ማወደሱን ለእኔ ለ10 ደቂቃዎች ወይም ከዚያ በላይ ለሚሆን ሰአት ቀጠለ። ከዛ ስንመለስ በዝግታ እንዲህ አለ፣ “ያ መልካም ጉብኝት ነበር። እነዛ ትንሽ ሴት ልጆች እኛ መምጣታችንን በፍፁም አይረሱም።”

ታላቅ የክህነት ጓደኛ መስጠት የሚችላቸው ሁለት በረከቶቸ እምነት መጣል እና የመንከባከብ ምሳሌ ናቸው። ወንድ ልጄ ከእሱ የበለጠ ብዙ የክህነት ልምዶች የለውን የቤት ለቤት አስተማሪ ጓደኛ ሲቀበል ያንን አይቻለው። የእሱ ጓደኛ ሁለት ጊዜ የሚስዮን ፕሬዘደንት ሆኗል እና በሌላ የአመራር ቦታዎች ላይ አገልግሏል።

ከተመደበላቸው ቤተሰቦች ውስጥ አንዱን ከመጎብኘታቸው በፊት ያ ልምድ ያለው የክህነት መሪ ልጄን በቤታችን ውስጥ ለመጎብኘት ጠየቀ። እንዳዳምጥ ፈቀዱልኝ። እርዳታ በመጠየቅ በፀሎት ጀመረ። ከዛ ለልጄ እንደዚ አለ፥ “ንስሀ እንዲገቡ ጥሪ የሚመስል ትምህርት ማስተማር እንዳለብን አስባለው። መልዕክቱን ከእኔ በጥሩ ሁኔታ ከሚወስዱ ይልቅ ካንተ እንደሚወስዱ አስባለው። ስለዛ ምን ይሰማሃል?”

ልጄ የተጣለበትን እምነት ሲቀበል የነበረው የዛ ሰአት ደስታ አሁንም ይሰማኛል።

ኤጲስ ቆጶሱ ያንን ጓደኝነት በድንገት አልነበረም አንድ ላይ ያደረገው። በትልቁ ጓደኛ ጥንቃቄ በተሞላበት ዝግጅት ስለእዘ ቤተሰብ ምን ማስተማር እንዳለባቸው በተማረው ስሜት ነበር። መልዕክቱን እሱ ማካፈል እደሌለበት እና ልምድ የሌለው ወጣት የእግዚአብሔርን ልጆች ለንስሀ እና ለደህንነት እንዲጠራ እምነት እንዲጥልበት ተሰማው።

የጉብኝታቸውን ውጤት አላውቅም፣ ነገር ግን ኤጲስ ቆጶሱ፣ የመልከፀዲቅ ክህነት ተሸካሚ እና ጌታ ልጁን የክህነት ሰው እናም አንድ ቀን ኤጲስ ቆጶስ እንዲሆን እያዘጋጁት እንደነበር አውቃለው።

አሁን፣ እነዚህን መሰል የክህነት ዝግጅት ውጤት ታሪኮች ካያችሁት እና በሕይወታችሁ ውስጥ ከተለማመዳችሁት ለእናንተ የተለመዱ ናቸው። አውቃችኋል እና እንደዚህ አይነት ኤጲስ ቆጶስ፣ ጓደኞች እና ወላጆች ሆናችኋል። ከፊታችሁ እንደሚኖር የሚያውቀውን በክህነት ተግባሮች ዝግጅታችሁ ውስጥ የጌታን እጅ አይታችኋል።

በክህነት ውስጥ ሁላችንም ጌታ ሌሎችን እንዲያዘጋጅ ለመርዳት ግዴታ አለብን። አንድ አንድ በጣም አስፈላጊ የሁኔ ነገሮችን ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች አሉ። ትምህርቶችን ለማስተማር ከምንጠቀመው ኃይለኛ ቃላቶች በላቀ መልኩ ትምህርቱን የመኖር ምሳሌአችን ይሆናል።

በክህነት አገልግሎታችን ውስጥ አስፈላጊው ሰዎችን በእምነት፣ በንስሀ፣ በጥምቀት፣ እና መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ወደ ክርስቶስ መጋበዝ ነው። ለምሳሌ ፕሬዘደንት ሞንሰን በእነዛ ትምህርቶች ላይ ልብ የሚያነሳሳ ስብከት ተጥተዋል። ነገር ግን በቶሮንቶ ሚስዮን የበላይ ሆኖ ሲመራ ከሰዎች፣ ከሚስዮኖች እና ከቤተክርስቲያን ጓደኞች ጋር ያደረገው ነገር ወደ ተግባር አነሳስቶኛል።

በክህነት ዝግጅት ውስጥ ከ“ንገረኝ” ይልቅ “አሳየኝ” ይቆጠራል።

ለዛም ነው ቅዱስ መጽሐፍቶች በክህነት ውስጥ እኛን ለማዘጋጀት በጣም አስፈላጊ የሆኑት። በምሳሌ የተሞሉ ናቸው። 4አልማ የመልአኩን ትዕዛዝ ተከትሎ እና በፍጥነት ክፉ ሰዎችን በአሞኒሀ ተመልሶ ለማስተማር ሲሄድ የማየው ያህል ይሰማኛል። ነብዩ ዮሴፍ እስር ቤት ውስጥ ሳለ ድፍረት እንዲሚያገኝ እና እየተጠበቀ እንደሆነ በእግዚአብሔር ሲነገረው ያለውን ቅዝቃዜ ይሰማኛል።5 ያንን ጥቅስ በአይምሮአችን ውስጥ በመያዝ በአገልግሎታችን ውስጥ ከባድ በሚመስልበት ሰአት ለመፅናት መዘጋጀት እንችላለን።

ወጣት የክህነት ተሸካሚን ላይ እምነት የሚጥል አባት ወይም ኤጲስ ቆጶስ ወይም ታላቅ የቤት ለቤት አስተማሪ ሕይወቱን መቀየር ይችላል። አባቴ አንድ ጊዜ በአስራሁለት ሐዋርያት ምልአተ ጉባኤ አባል በሳይንስ እና ሐይማኖት ላይ አጭር ወረቀት እንዲፅፍ ተጠይቆ ነበር። አባቴ ሳይንቲስት እና ታማኝ የክህነት ተሸካሚ ነበር። የፃፈውን ወረቀት ሰጥቶኝ ያለኝን ነገር አሁንም ድረስ አስታውሳለው፥ “እንካ፣ ከመላኬ በፊት፣ እንድታነበው እፈልጋለው። ትክክል መሆኑን አንተ ታውቃለህ።” 32 አመቱ ነበር፣ እና በማይለካ መልኩ ጠቢብ እና ጎበዝ ነበር።

አሁንም ድረስ በእዛ ታላቅ አባት እና የክህነት ተሸካሚ እምነት ተጠናክሪያለው። እምነቱ በእኔ ላይ እንዳልነበረ አውቃለው፣ ነገር ግን ትክክል የነበረውን ሊነግረኝ በሚችለው እና በሚነግረኝ በእዛ እግዚአብሔር ላይ ነበር። ወቅታዊ የሆነው ርህራሄአችሁ ወጣት የክህነት ተሸካሚን በዝግጅቱ ውስጥ ያንን የመሰለ እምነት በምታሳዩት ሰአት ልትባርኩት ትችላለህ። የሆነ ቀን ዶክተሮች ይሞታል ያሉትን ህፃን ለመፈወስ በረከቱን ለመደምደም እጆቹን ሲያስቀምጥ የመነሳሳትን የተረጋጋ ስሜት እንዲያምን ይረዳዋል። ያ እምነት ከአንዴ በላይ እረድቶኛል።

ሌሎችን በክህነት ውስጥ የማዘጋጀት ውጤታችን ምን ያህል ከምንወዳቸው ጋር ተመጣጥኖ ይመጣል። ያ በተለየ ሁኔታ ማስተካከል ሲኖርብን ትክክል ይሆናል። አንድ የክህነት ተሸካሚ ስነ-ስርዓትን ሲያከናውን ሲሳሳት ያለውን ጊዜ አስቡ። ያ በጣም ወሳኝ ነገር ነው። አንድ አንድ ጊዜ ስህተቱ የገሀድ ማስተካከያን ይጠይቃል፣ ይሄም የንዴት፣ የእፍረት ስሜት እና የመወገድ ስሜት ሊያመጣ ይችላል።

የጌታን ምክር ታስታውሳላችሁ፥ “በመንፈስ ቅዱስ ስንመራ በትክክለኛው ሰአት በግልፅነት ማረም አለብን፣ እናም ከዛ በኋላ እንደጠላት እንዳንታይ ላረመነው ሰው የጨመረ ፍቅር እናሳይ” 6

“የጨመረ” የሚለው ቃል የክህነት ተሸካሚዎችን በማዘጋጀት ውስጥ እርማት ሲፈልጉ ለየት ያለ ትርጉም አለው። ቃሉ በፊት ከነበረው የጨመረ ፍቅርን ሀሳብ ይሰጣል። መታየት ያለበት የጨመረ ፍቅር ነው። የክህነት ተሸካሚዎችን እያዘጋጀን ያለነው ሰዎች ሲማሩ በትክክል ስህተት ስለሚሰሩ የቀደመ እና ቀጣይነት ያለውን ፍቅር ሊሰማቸው ይገባል። ለድክመታቸው ከምናሳየው ሀዘኔታ የዘለለ መሆን አለበት።

ጌታ እራሱ እነዛን የዝቅተኛ ክህነት ሰዎች አቅማቸውን እና ለእርሱ ያላቸውን አመለካከት በሚያከብር መልኩ ጠብቆታል። መጥምቁ ዮሐንስ በዮሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ኳድሪ ላይ እጁን ጭኖ “በአገልጋይ ጓደኞቹ ላይ በመሲሁ ስም አሮናዊ ክህነትን የመላዕክት የአገልግሎት ቁልፎችን እና የንስሀ ወንጌልን እና ለሀጢያት ስርየት በመጥለቅ መጠመቅን የያዘውን ሰጣቸው። እናም እንደገና ከምድር የሌዊ ወንድ ልጆች ለጌታ በፅድቅ መስዋት እስከሚያቅርቡ ድረስ በፍፁም አይወሰድም።”7

አሮናዊ ክህነት ለትልቁ መልከፀዲቅ ክህነት ቅጣይ ነው።8 እንደ ሁሉም ክህነቶች ክህነት፣ የቤተክርስቲያኑ ፕሬዘደንት በመዘጋጃ ክህነት ላይ የበላይ ሆኖ ይመራል። ለብዙ አመታት የጠፉትን ማዳን የሚለው መልዕክቱ ፍፁም በሆነ ሁኔታ የንስሀ እና የጥምቀት ወንጌልን ወደ ሌሎች ሕይወት የመውሰድ ሀላፊነትን ይሞላል።

የዲያቆን፣ የአስተማሪዎች እና የካህናት ምልአተ ጉባኤ እያንዳንዱን አባል ወደ ጌታ ለመሳብ በተደጋጋሚ ይመክራሉ። አመራሮች አባሎችን በእምነት እና በፍቅር ለሌሎች እንዲደርሱ ይመድባሉ። ዲያቆኖች ቅዱስ ቁርባንን በክብር እና በእምነት አባሎች የሀጢያት ክፍያውን ውጤት እንዲሰማቸው በማድረግ እና እነዛን ቅዱስ ምልክቶች ሲካፈሉ ትዕዛዞቸን እንዲጠብቁ ለማድረግ ያሳልፋሉ።

አስተማሪዎች እና ካህናት ከጓደኞቻቸው ጋር ቤተክርስቲያኑን ሰው በሰው የመጠበቅ ሀላፊነታቸውን ለማሟላት ይፀልያሉ። እናም እነዛ ጓደኞች የቤተሰብ እራሶች ፍላጎቶች እና ተስፋዎች ሲማሩ በጋራ ይፀልያሉ። ይህንን ሲያደርጉ፣ በራሳቸው ቤተሰብ ውስጥ በእምነት ለመምራት ለታላቁ ቀን እየተዘጋጁ ነው።

በክህነት ውስጥ በጋራ የሚያገለግሉ ሰዎች ጌታን ወደ ቤተክርስቲያኑ እንዲመጣ ሰዎችን እያዘጋጁ እንደሆነ እምሰክራለው። እግዚሀብሔር አባት በሕይወት አለ። ኢየሱስ ክርሰቶስ እንደሆነ እና እንደሚወደን አውቃለው። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን የጌታ በሕይወት ያለ ነብይ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለው፣ አሜን።