2010–2019 (እ.አ.አ)
በጀልባዋ ላይ ቆዩ እና ጠብቁ!
ኦክተውበር 2014


በጀልባዋ ላይ ቆዩ እና ጠብቁ!

አትኩሮታችንን በጌታ ላይ ካደረግን፣ መነፃፀር የማይችል በረከቶች ቃል ተገብተውልናል።

በቅርቡ፣ ጓደኛዬ ወንድ ልጁን በዪታ ደቡብ ምስራቃማ ውስጥ ወደሚገኘው ኮሎራዶ ወንዝ በፏፏቴ ሸለቆ ውስጥ ለሽርሽር ወሰደው። ሸለቆው ለ14 ሚይልሱ (23 ኪሎ ሜትሩ) በፍጥነት በሚምዘገዘገው አደገኛ ሊሆን በሚቸለው ፏፏቴው ታዋቂ ነው።

ለጀብዱአቸው ዝግጅት፣ በጥንቃቄ ስለ ግላዊ ዝግጁነት እና የተለመዱ እና ድብቅ የሆኑ አደጋዎችን የያዘውን የብሔራዊ ፓርክ አገልግሎትን ድረገፅ ከለሱ።

በጉዞው መጀመሪያ ላይ፣ አንድ ልምድ ያለው የወንዙ መሪ ሶስት ቁልፍ የሆኑ በፏፏቴው ውስጥ የስብስቡን ደህንነት የተሞላበት ጉዞ የሚያረጋግጡ ህገ ደንቦች ላይ በማተኮር አስፈላጊ የደህንነት መመሪያዎችን ከለሰ። “ህገ ደንብ ቁጥር አንድ፥ ጀልባው ውስጥ ቆዩ!ህገ ደንብ ቁጥር ሁለት፥ ሁሌም የሕይወት ጃኬቱን ልበሱ!ህገ ደንብ ቁጥር ሶስት፥ ሁሌም በሁለት እጃችሁ ያዙ!” እሱ ከዛ በበለጠ አትኩሮት እንዲህ አለ፣ “ከሁሉም በላይ፣ ህገ ደንብ አንድን አስታውሱ፥ በጀልናው ውስጥ ቁዩ!!”

ይህ ጀብድነት የእኛን የሟች ጉዞ አስታወሰኝ። ብዙዎቻችን በሕይወታችን ውስጥ የሕይወትን ሰላማዊ ጊዜ ስናደንቀው እንገኛለን። በሌላ ጊዜ በ14 ማይሌች ውስጥ ከሚገኘው የፏፏቴ ሸለቆ ጋር የሚነፃፀሩ ከባድ ጊዜዎች ለምሳሌ እንደ አካላዊ እና አእምሮአዊ የጤና ጉዳዮች፣ የምንወደው ሰው ሞት፣ ያልተሳኩ ህልሞች እና ተስፋዎች እና ለሌላ ሰዎች ደግሞ የሕይወት ችግሮች፣ ጥያቄዎች እና ጥርጣሬዎች ሲያጋጥሙ የሚከሰት የእምነት ጉድለቶችያጋጥሙናል።

ጌታ በመልካምነቱ ጀልባን፣ እንደ የሕይወት ጃኬት፣ እና የሕይወትን ወንዝ የመሳሰሉትን ወደ መጨረሻ መድረሻችን እንድንደርስ የሚረዱንን ምሪት እና የደህንነት መመሪያዎችን የሚሰጡ ልምድ ያላቸው የወንዝ መሪዎችን አስፈላጊ አቅርቦቶችን ጨመሮ እርዳታ ሰጥቶናል።

ህገ ደንብ አንድን እናስብ፥“በጀልባው ስጥ ቆዩ!”

ፕሬዘደንት ብሬጌም ያንግ “አስተማማኝ ፅዮንን” እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተጠቅመውታል።

በአንድ አጋጣሚ ላይ እንደዚህ አለ፥“በውቅያኖሱ መሀል ውስጥ ነን። መአበል ይመጣል፣ እና መርከበኞች እንደሚሉት መርከቧ ለመንሳፈፍ እየተቸገረች ነው። አንዱ፣ ‘እዚህ አልቆይም ይቺ “የፅዮን መርከብ ነች ብዬ አላምንም።‘ነገር ግን በውቅያኖሱ መሀል ነው ያለነው። ‘አያገባኝም እዚህ አልቆይም። ኮቱን አወለቀ እና ከመርከቡ ላይ ዘለለ። አይሰምጥም?አዎ። ይህንን ቤተክርስቲያን ለሚተዉ ሁሉ ይሄ ነው የሚከሰተው። ‘አስተማማኟ የፅዮን መርከብ ነች፣ ሁላችንም እንቆይበት።”1

በሌላ አጋጣሚ፣ ፕሬዘደንት ያንግ ሕይወት መልካም ሲሆን ሲባረኩ መንገዳቸውን ስለሚያጡት ሰዎችም እንደሚጨነቅ ተናገረ፥ “ፀጥ ባለ አየር ውስጥ ነው፣ አስተማማኟ የፅዮን መርከብ በተረጋጋ ንፋስ ውስጥ ስትንሳፈፍ እና ሁሉም ተሳፍሮ ሳለ፣ አንዳንድ ወንድሞች በትናንሽ ጀልባዎች ላይ ለመዋኘት ሲወጡ፣ እና አንዳንዶቹ ሲሰምጡ፣ ሌሎች ሲወሰዱ እና ሌሎች እንደገና ወደ መርከቧ ይመለሳሉ። በአስተማማኝ መርከቧ ላይ እንቆይ፣ እና ወደ ወደቡ በደህና ትሸከመናለች። ልትጨነቁ አይገባም።”2

በመጨረሻም፣ ፕሬዘደንት ያንግ ቅዱሳኖችን እንዲህ አስታወሰ፥ “በአስተማማኟ የፅዮን መርከብ ላይ ነን።…እግዚአብሔር መሪውን ይዟል እና እዛም ይሆናል።… ሁሉም መልካም ነው። ጌታ እዚ ስለሆነ፣ ሀሌሉያን ዘምሩ። በቃሉ ያፅፈናል፣ ይመራናል እናም ይጠቁመናል። ሰዎች በአምላካቸው ሙሉ መተማመን የሚኖራቸው ከሆነ፣ ቃል-ኪዳቸውን እንዲሁም አምላካቸውን የማይተዉ ከሆነ፣ በትክክል ይመራናል።”3

ዛሬ የምናየውን ፈተናዎች ከግምት በማስገባት፣ እንዴት ነው በአስተማማኟ የፅዮን መርከብ ላይ የምንቆየው?

እንዲህ ነው የምናደርገው!በኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን እምነት እና ለወንጌሉ ያለንን ታማኝነት በሕይወታችን ውስጥ አንዴ ሳይሆን በተደጋጋሚ በመጨመር ቀጣይነት ያለው ለውጥ መለማመድ አለብን። አልማ እንዲህ ጠየቀ፣ “እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞቼ እንዲህ እላችኋለው፤ የልብ መለወጥን የተለማመዳችሁ ከሆነ፣ እናም የአዳኛችሁን የፍቅር ዜማ ለመዘመር ከተሰማችሁ፣ አሁንም ሊሰማችሁ ይችላልን?”4

ልምድ ያለው የወንዝ መሪ ዛሬ እንደ ቤተክርስቲያኗ ሐዋርያቶች እና ነብያቶች እንዲሁም ተነሳሱ የሀገር ውስጥ የክህነት ረዳት መሪዎች ሊወሰድ ይችላል።በደህንነት ለመጨረሻ ወደምንሄድበት ቦታ እንድንደርስ ይረዱናል።

በቅርቡ፣ በአዲስ የሚስዮን ፕሬዘደንቶች ትምህርታዊ ጉባኤ ላይ ተናገርኩኝ እና እነዚህን መሪዎች መከርኩኝ፥

“የሚስዮኑን አይኖች በቤተክርስቲያን መሪዎች ላይ አቆዩ። በተሳሳተ መንገድ አንመራችሁም እናም ልንመራችሁም አንችልም።

“ሚስዮናችሁን እየናቸውን በእኛ ላይ እንዲያተኩሩ በምታስተምሩበት ጊዜ፣ የሰማይ አባት እና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የበላይ ሆኖ የመምራት ቁልፉ ባላቸው በክህነት መሪዎች አማካኝነት ከሚያደርጉት ይልቅ የቤተክርስቲያኗን ጉዳይ እንዴት እንደሚያስተዳድሩ የበለጠ የሚያውቁ የሚመስላቸውን በፍፁም እንዳይከተሉ አስተምሯቸው።

“በአገልግሎቴ ውስጥ የጠፉት እና ግራ የተጋቡት ሰዎች በተደጋጋሚ ቀዳሚ አመራሮች እና የአስራሁለት ምልአተ ጉባኤዎች ህብረት ባለው ድምፅ ሲናገሩ በእዛ ጊዜ የጌታ ድምፅ መሆኑን የረሱ ሰዎች እንደሆነ አረጋግጫለው። ጌታ ‘በራሴ ድምፅም ሆነ ወይም በአገልጋዮቼ ድምፅ አንድ ነው’ እያለ ያስታውሰናል።”[ት. እና ቃ. 1:38].”5

በሌላ አነጋገር፣ አስተማማኙን የፅዮን መርከብ ትተው ይወድቃሉ፤ ያምፃሉ። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ለአጭር እና ከዛ በኋላ ለእረጅም ጊዜ ለእነሱ ብቻ ሳይሆን ለቤተሰባቸውም ጨምሮ ያልታሰበ ተያያዥ ውጤት ያጋጥማቸዋል።

የእኛ የሀገር ውስጥ መሪዎች፣ ልምድ እንዳላቸው የወንዝ መሪዎች፣ በሕይወት ልምዶች ተመክረዋል፤ ስልጠና ወስደዋል እና በሐዋርያቶች እና በነብያቶች እና በሌላ የቤተክርስቲያን መኮንኖች፤ እና በተለይም ደግሞ በጌታ በራሱ ተመክረዋል። በዚ አመት በሌላ አጋጣሚ ላይ፣ ለቤተክርስቲያኗ ወጣት ጎልማሶች በግንቦት የሲ.ኢ.ኤስ. መንፈሳዊ ስርጭት ላይ ተናገርኩኝ። እንደዚህም አልኩኝ፥

በዚ አመት በሌላ አጋጣሚ ላይ፣ ለቤተክርስቲያኗ ወጣት ጎልማሶች በግንቦት የሲ.ኢ.ኤስ. መንፈሳዊ ስርጭት ላይ ተናገርኩኝ። እንደዚህም አልኩኝ፥

“አንድ አንድ ሰዎች የቤተክርስቲያን መሪዎች ለተራ ሰዎች የሚከሰተውን ነገር ችላ እንደሚሉ እንደሚያስቡ ሰምቻለው። የረሱት ነገር ቢኖር እኛ ልምዶች ያሉን ወንዶች እና ሴቶች ነን እና ሕይወታችንን በብዙ ቦታዎች ኖረናል እና ከተለያየ አይነት መነሻ ካላቸው ሰዎች ጋር አብረን ሰርተናል። የአሁኑ የቤተክርስቲያን የቤት ስራዎቻችን ፖለቲከኞችን፣ ሀይማኖተኞችን፣ የንግድ ሰራተኞችን እና የበጎ አድራጎት መሪዎችን እንድናገኝ በአለም ዙሪያ እንድንዘዋወር ያደርጉናል። ምንም እንኳን በዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ የአሜሪካ ፕሬዘደንት መኖሪያ ቤትን እና በአለም ዙሪያ ያሉትን የሀገራትን መሪዎች ብንጎበኝም፣ በምድር ላይ በጣም ድሀ የሆኑ ለእነሱምአገልግሎት የሰጠንባቸውን ቤቶችንም ጎብኝተናል።

“ህይወታችንን እና አገልግሎታችንን በእርጋታ ስታስቡት፣ ሌሎች ትንሾች ከሚያደርጉት በበለጠ እኛ አለምን እንደምናይ እና እንደምንለማመድ ትስማማላችሁ። ከብዙ ሰዎች ይልቅ እኛ በአለም ላይ እየተካሄደ ያለውን ነገሮች እናያለን።

“ስለ ግለሰቡ እና ስለ ቤተክርስቲያን መሪዎች የጋራ ጥበብ መፅናናትን ሊሰጥ የሚችል ነገር አለ። ሁሉንም ነገሮች፣ የተለያዩ የሕዝብ ህጎች እና ፖሊሲዎችን፣ ቅሬታዎችን፣ ሀዘኖችን እና በቤተሰባችን ውስጥ ሞትን አይተናል።በህይወታችሁ የሚያጋጥሟችሁ ምን እንደሆኑ እናውቃለን” 6

ከህገ ደንብ ቁጥር አንድ ጋር እንደተጠቀምኩት፣ ህገ ደንብ ሁለትን እና ሶስትን አስታውሱ፥ ሁሌ የሕይወት ጃኬቱን ልበሱ እና በሁለት እጆቻችሁ ያዙ። የጌታ ቃሎች በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ እና በሐዋርያቶች እና ነብያቶች ትምህርት ውስጥ እንደሚገኙት፣ ምክርን እና አቅጣጫን ስንከተል እንደ መንፈሳዊ የሕይወት ጃኬት ያገለግሉናል እንዲሁም በሁት እጆቻችን እንዴት እንደምንይዝ እንድናውቅ ይረዱናል።

ልክ እንደ ሞዛያ ወንድ ልጆች “እውነትን በማወቅ የጠነከሩ” መሆን አለብን።“በቀላሉ የሚረዱ” ወንዶች እና ሴቶች መሆን እንችላለን። ይህ ደግሞ ሊከናወን የሚችለው“የእግዚአብሔርን ቃል ያውቁ ዘንድ ቅዱሳን መጽሐፍትን በትጋት የሚያጠኑ” ስንሆን ብቻ ነው።7

ቅዱሳን መጽሐፍትን እና ያለፉ እና አሁን ያሉ ሐዋርያቶችን እና ነብያቶችን ቃሎች በመመርመር፣ የክርስቶስን ትምህርት በማጥናት፣ በመኖር እና በመውደድ ላይ ማተኮር እንችላለን።

የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብን ከማዳበር በተጨማሪም፣ እንደ ሞዛያ ልጆች መሆን እና እራሳችንን“ለበለጠ ፀሎት እና ፆም”8 መስጠት ይኖርብናል።8

እነዚህ በቀላሉ የማይለኩ ነገሮች ታላቅ ጠቀሜታ ያላቸው ይመስላል። በእነዚህ ቀላል ነገሮች ላይ በአትኩሮት ቆዩ እናም መረበሽን አስወግዱ።

በፈተናዎች እና በችግሮች ጊዜ ወይም ፀጥ ባለ ጊዜም በጀልባዋ ላይ ያልቆዩ ሰዎችን እና በሁለት እጃቸው ያልያዙ ሰዎችን ሳውቅ፣ ብዙዎቹ በወንጌል መአከላዊ እውነታዎች ላይ በመጀመሪያ ደረጃ ቤተክርስቲያኗን የተቀላቀሉበትን ምክንያት፣ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ሆነው የቆዩበትን ምክንያት እና የወንጌልን ደንቦች ንቁ ሆነው የኖሩበትን ምክንያት እና ሌሎችን እራሳቸውን በማዋል፣ በአገልግሎት በመባረክ እና ቤተክርስቲያኗ በሕይወታቸው ውስጥ “መንፈሳዊ መመገቢያእና የእድገት ቦታ” የሆነበትን መንገዶች አትኩሮት ማጣታቸውን አይቻለው። 9

ዮሴፍ ስሚዝ ይህንን መአላዊ እውነታ እንደዚህ በማለት አስተማረ፥ “የሐይማኖታችን መሰረታዊ መርሆች የሐዋርያቶች እና የነብያቶች ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሞተ፣ እንደተቀበረ እና በሶስተኛው ቀን እንደገና እንደተነሳ እና ወደ ሰማይ እንዳረገ ያላቸው ምስክርነትነው፤ እናም ስለ ሐይማኖታችን ያሉት ሌሎቹ ነገሮች ለእነዚህ ነገሮች ቅጥያዎች ናቸው።”10

ትኩረታችንን በጌታ ላይ ካደረግን፣ ሊወዳደር የማይችል በረከት ቃል ተገብቶልናል፥ “ስለሆነም በክርስቶስ ባላችሁ ጠንካራ እምነት መቀል አለባችሁ፣ ተስፋ ብርሀን፣ እናም የእግዚአብሔርና ሰዎች ሁሉ ፍቅር ይኖራችኋል። ስለሆነም አብም የምትቀጥሉ ከሆነ፣ የክርስቶስን ቃል ብትመገቡ፣ እናም እስከመጨረሻው ብትፀኑ፣ እነሆ የዘለአለም ሕይወት ይኖራችኋል የላል።”11

አንድ አንድ ጊዜ አማኝ ኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች እና ቅን መርማሪዎች በመሰረታዊው መርሆች ይልቅ በቅጥያው ላይ ትኩረት መስጠት ይጀምራሉ። ሴጣን ከቀላሉ እና ከግልፁ መልሶ የተቋቋመው ወንጌል የተምታታን እንድንሆን ሲፈትነን ነው። የሚምታቱት ሰዎች ብዙውን ጊዜ ትንሽ ጠቀሜታ ያላቸው ድርጊቶች ላይ ወይም ትምህርቶች ላይ ትኩረት በመስጠታቸው ምክንያት ቅዱስ ቁርባን መውሰድን ይተዋሉ።

ሌሎች በሚያጋጥማቸው ጥያቄዎች እና ጥርጣሬዎች ላይ ሊያተኩሩ ይችላሉ። በእርግጥ፣ ጥያቄዎችን መኖር እና ጥርጣሬዎችን ማጋጠም እራሱን ከሰጠ ደቀ መዝሙር ጋር አይዛመድም። በቅርቡ፣ የቀዳሚ አመራር እና የአስራሁለቱ ሐዋርያት ምልአተ ጉባኤ ምክር ቤት ይህንን ደነገገ፥ “ከጊዜ ወደ ጊዜ የቤተክርስቲያን አባሎች ስለ ቤተክርስቲያን ትምህርቶች፣ ታሪኮች ወይም ተግባሮች ጥያቄዎች እንደሚኖራቸው ይገባናል። አባሎች ሁሌ እነዚህን ጥያቄዎች ለመጠየቅ እና በቅንነት ታላቅ መረዳትን ለመሻት ነፃ ናቸው።”12

አስታውሱ፣ ዮሴፍ ስሚዝ እራሱ መልሶ መቋቋሙን የጀመረ ጥያቄዎች ነበሩት። መልስ የሚሻ ነበር እና ልክ እንደ አብርሐም ለሕይወት በጣም አስፈላጊ የሆነውን መልስ አገኘ።

አስፈላጊ ጥያቄዎች የበለጠ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች ላይ ማለትም የሰማይ አባታችን እቅድ እና የአዳኝ የሀጥያት ክፍያው ላይ ያተኩራሉ። ፍለጋችን ደጎች፣ ረጋ ያልን፣ ወዳጆች፣ ይቅር ባዮች፣ ታጋሾች እና እራሳችንን የሰጠን ደቀ መዝሙሮች እንድንሆን ሊመራን ይገባል። ጳውሎስ “እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም የሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ህግ ይፈፅም” ብሎ እንዳስተማረው ፍቃደኞች መሆን አለብን።13

የሌላን ሸክም መሸከም መርዳትን፣ መደገፍን፣ እና እያንዳንዱን የታመሙትን፣ ደካሞችን፣ በመንፈስ እና በአካል ድሀ የሆኑትን፣ ለማኞችን እና የተረበሹትን ጨምሮ እንዲሁም ሌሎች አባል ደቀ መዝሙሮችን በጌታ ለተወሰነ ጊዜ እንዲያገለግሉ የተጠሩትን የቤተክርስቲያን መሪዎችን ጭምር መርዳት ያከላትታል።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ጀልባው ላይ ቁዩ፣ የሕይወት ጃኬታችሁን ተጠቀሙ፣ በሁለት እጆቻችሁ ያዙ። መምታታትን አስወግዱ! ማንኛችሁም ከጀልባው ብትወድቁ፣ እንፈልጋችኋለን፣ እናገኛችኋለን እናም እናገለግላችኋለን እና አባታችን እገግዚአብሔር እና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳሉበት የመርከብ መሪ እና በትክክል ወደሚመሩን ወደ አስተማማኟ የፅዮን መርከብ መልሰን በድህና እንጎትታችኋለን። ለእነዚህም ነገሮች በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Teachings of Presidents of the Church: Brigham Young (1997), 82–83.

  2. ብሪገም ያንግ፣ “Discourse,” Deseret News, Jan. 27, 1858, 373.

  3. ብሪገም ያንግ፣ “Remarks,” Deseret News, Nov. 18, 1857, 201.

  4. አልማ 5፥26

  5. ኤም. ራስል ባለርድ፣ “Mission Leadership” (seminar for new mission presidents, June 25, 2014).

  6. ኤም. ራስል ባለርድ፣ “Be Still, and Know That I Am God” (Church Educational System devotional, May 4, 2014); LDS.org/broadcasts.

  7. አልማ 17፥2

  8. አልማ 17፥3

  9. የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለትሐዋሪያት ደብዳቤ፣ June 28, 2014.

  10. ጆሴፍ ስሚዝ፣ Elders’ Journal, July 1838, 44.

  11. 2 ኔፊ 31፥20

  12. የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለትሐዋሪያት ደብዳቤ፣ ሰኔ 28, 2014።

  13. ገላቲያ 6፥2