መፅሐፈ ሞዛያ
ምዕራፍ ፩
ንጉስ ቢንያም ለልጆቹ የአባቶቻቸውን ቋንቋ እና ትንቢት አስተማረ—ኃይማኖታቸውና ስልጣኔያቸው የተጠበቁት በተለያዩ ሠሌዳዎች ላይ በተጠበቁት መዝገቦች ምክንያት ነው—ሞዛያ ለንጉስነት ተመርጧል እናም መዛግብቱና ሌሎችም ነገሮች አደራ ተሰጥተውታል። ከ፻፴–፻፳፬ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን የንጉሥ ቢንያም ከሆኑት ህዝቦች ሁሉ መካከል ሀበዛራሔምላ ምድር ሁሉ ከዚያ በኋላ ፀብ አልነበረም፣ ስለዚህ ንጉሥ ቢንያም በቀሪው ዘመኑ ሁሉ ዘላቂ ሠላም ነበረው።
፪ እናም እንዲህ ሆነ ሦስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እናም ስማቸውን ሞዛያና፣ ሔሎሩምና፣ ሔለማን ብሎ ጠራቸው። እናም አስተዋይ ሰዎች ይሆኑ ዘንድና፣ በጌታ እጅ የተሰጣቸውን በአባቶቻቸው አንደበት ስለተነገሩት ትንቢቶች ያውቁ ዘንድ በአባቶቻቸው ሀቋንቋ ሁሉ ለእንዲማሩ አደረገ።
፫ እናም ደግሞ በነሀስ ሠሌዳዎች ላይ የተቀረፀውን ታሪክ በተመለከተ እንዲህ ሲል አስተማራቸው፥ እነዚህን ታሪኮችና ትዕዛዛት የያዙት እነዚህ ሀሠሌዳዎች ባይኖሩ ኖሮ በአሁኑም ጊዜ እንኳን ቢሆን የእግዚአብሔርን ሚስጥር ባለማወቅ ለበድንቁርና እንደምንሰቃይ ልጆቼ እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ።
፬ በእነዚህ ሠሌዳዎች እርዳታ ካልሆነ በቀር አባታችን ሌሂ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ለልጆቹ በማስታወስ ለማስተማር አይቻለውም ነበር፤ ምክንያቱም የግብፃውያንን ሀቋንቋ የተማረ ስለሆነ እነዚህን ፅሁፎች ለማንበብ ይቻለዋል፣ እናም ልጆቹ ልጆቻቸውን ማስተማር ይችሉ ዘንድ ይህንኑ ልጆቹን አስተማራቸው፣ እናም ስለዚህ እስከዚህ ጊዜም ድረስ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ይፈፅማሉ።
፭ ልጆቼ እንዲህ እላችኋለሁ፥ እኛ የእርሱን ሀሚስጥር ለአንብበን እንገነዘብ ዘንድ በእግዚአብሔር እጅ ሐየተቀመጡትና የተጠበቁት እነዚህ ነገሮች፣ እንዲሁም ሁልጊዜም ከዐይናችን ስር ያሉት ትዕዛዛቱ ባይኖሩ ኖሮ አባቶቻችንም እንኳን ቢሆኑ እምነት አጥተው ይመነምኑ ነበር፣ እናም ስለእነዚህ ነገሮች ምንም እንደማያውቁት፣ ወይም በሚያስተምሩአቸው ጊዜም ስህተት በሆነው በአባቶቻቸው መወግ ምክንያት እንደማያምኑት ወንድሞቻችን እንደላማናውያን እንሆን ነበር።
፮ ልጆቼ ሆይ፣ እነዚህ አባባሎች እውነት መሆናቸውን፣ እናም ደግሞ እነዚህ መዛግብት ሀእውነት እንደሆኑ እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ። እናም ኢየሩሳሌምን ለቀው ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን የአባቶቻችንን አባባሎች መዛግብትን የያዙ የኔፊ ሰሌዳዎችን ደግሞ ተመልከቱ፣ እነርሱም እውነተኛ ናቸው፤ እናም እኛ የእነርሱን እርግጠኝነት እናውቃለን ምክንያቱም እነርሱ በዐይኖቻችን ፊት ቀርበዋል።
፯ እናም አሁን፣ ልጆቼ፣ እናንተ ትጠቀሙ ዘንድ እነርሱን በትጋት ሀመፈተሽን አንድታስታውሱ እፈልጋለሁ፤ እናም ጌታ ለአባቶቻችን በገባው ለቃል ኪዳን መሰረት በምድሪቱ ሐትበለፅጉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መእንድትጠብቁ እፈልጋለሁ።
፰ እናም በዚህ መፅሐፍ ያልተፃፉትን በጣም ብዙ ተጨማሪ ነገሮችን ንጉስ ቢንያም ለልጆቹ አስተማረ።
፱ እናም እንዲህ ሆነ ንጉስ ቢንያም ልጆቹን ማስተማር ከጨረሰ በኋላ አረጀ፣ እናም በቅርቡ ምድር ሁሉ ወደሚሄዱበት መሄድ እንዳለበት ተመለከተ፤ ስለዚህ መንግስቱን ከልጆቹ ለአንደኛው ልጁ መስጠት ተገቢ መሆኑን አሰበ።
፲ ስለዚህ፣ ሞዛያን በፊቱ እንዲመጣ አደረገ፤ እናም እነዚህ ለእርሱ የተናገራቸው ቃላት ናቸው፥ ልጄ በዚህ ምድር ሁሉ በዚህ ህዝብ ሁሉ ወይም ሀበዛራሔምላ ህዝብ እናም በምድሪቱ በሚኖሩት በሞዛያ ህዝብ መካከል በአንድ ላይ ይሰበሰቡ ዘንድ አዋጅን እንድታውጅ እፈልጋለሁ፤ በማግስቱም ጌታ እግዚአብሔር ለእኛ በሰጠን በዚህ ህዝብ ላይ አንተ ለንጉስና ገዢ መሆንህን በራሴ አንደበት ለህዝቤ አስታውቃለሁ።
፲፩ እናም ከዚህ በተጨማሪ፣ ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም ምድር ካወጣቸው ህዝቦች መካከል ይለዩ ዘንድ ለዚህ ህዝብ ሀስም እሰጣለሁ፤ እናም ይህንን የማደርገው እነርሱ የጌታን ትዕዛዛት በመጠበቅ ትጉህ ስለነበሩ ነው።
፲፪ እናም ሀበመተላለፍ ካልሆነ በቀር ሊደመሰስ የማይችል ስም እሰጣቸዋለሁ።
፲፫ አዎን፣ እናም በተጨማሪ እልሀለሁ፥ እነዚህ እጅግ በጌታ የተወደዱ ሰዎች ወደ ሀመተላለፍ ቢወድቁ፣ እናም ኃጢአተኞችና፣ ዝሙትን አድራጊዎች ቢሆኑ፤ ጌታ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፣ በዚህም እንደ ወንድሞቻቸውም ለደካሞች ይሆናሉ፤ እናም ከዚህ ቀደም አባቶቻችንን እንዳዳናቸው ወደር በሌለውና ድንቅ ሃይሉ ከእንግዲህ ሐአያድናቸውም።
፲፬ እንዲህም እልሀለሁ፣ ለአባቶቻችን ባደረገው ጥበቃ እጁን ባይዘረጋ ኖሮ እነርሱ በላማናውያን እጅ በወደቁ እናም በጥላቻቸው ተጎጂ በሆኑ ነበር።
፲፭ እናም እንዲህ ሆነ ንጉስ ቢንያም ለልጁ ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ፣ የንግስታቱን አገዛዝ የተመለከቱ ጉዳዮችን ሁሉ በኃላፊነት ሰጠው።
፲፮ እናም በተጨማሪ፣ ደግሞ ሀበነሀስ ሰሌዳዎች ላይ የተፃፉትን ታሪኮች በተመለከተ፣ እናም ደግሞ የኔፊን ስሌዳዎች በተመለከተና፣ ደግሞ የላባንን ለሳንጃ፣ እንዲሁም እያንዳንዳቸው ለእርሱ በሚሰጡት ትኩረትና ትጋት መሰረት ይመሩበት ዘንድ በጌታ እጅ የተዘጋጀውን አባቶቻቸውን ከምድረበዳ የመራውን ሐኳሱን ወይም መሪውን ኃላፊነት ሰጠው።
፲፯ ስለዚህ፣ እምነት ባጡበት ጊዜ በጉዞአቸው አልበለፀጉም ወይም እድገትንም አላገኙም ነበር፣ ነገር ግን ሀወደኋላ ተወስደው ነበር፣ እናም የእግዚአብሔርን መከፋት በእነርሱ ላይ አመጣባቸው፤ እናም ስለዚህ ሀላፊነታቸውን እንዲያስታውሱ ለማነሳሳት በረሃብና በቁስል መቅሰፍት ተመተው ነበር።
፲፰ እናም አሁን፣ እንዲህ ሆነ ሞዛያ ሔደና፣ አባቱ እንዳዘዘው አደረገ፤ እናም በዛራሔምላ ምድር ላሉት ህዝቦች ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ በመሄድ አባቱ የሚናገረውን ቃላት እንዲያደምጡ በአንድ ላይ ይሰበሰቡ ዘንድ አወጀላቸው።