ምዕራፍ ፪
ያዕቆብ የሀብትን ፍቅር፣ ኩራትና፣ ምንዝርናን አወገዘ—ሰዎች ወገናቸውን ለመርዳት ሀብትን ሊሹ ይችላሉ—ጌታ ከኔፋውያን መካከል ማንኛውም ሰው ከአንድ በላይ ሚስት እንዳይኖረው አዘዘ—ጌታ በሴቶች ንፁህነት ይደሰታል። ከ፭፻፵፬–፬፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።
፩ የኔፊ ወንድም ያዕቆብ፣ ኔፊ ከሞተ በኋላ ለኔፊ ህዝብ የተናገራቸው ቃላት—
፪ አሁን፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እኔ ያዕቆብ እግዚአብሔር በሰጠኝ ሀላፊነት መሰረት፣ ሀላፊነቴን በጥሞና ለመወጣት፣ እናም ኃጢአታችሁንም ከመጎናፀፊያዬ አራግፍ ዘንድ፣ የእግዚአብሔርንም ቃል ለእናንተ አውጅ ዘንድ በዚህ ቀን ወደ ቤተ መቅደስ መጣሁ።
፫ እናም እስከዚህ ጊዜ ድረስ በተጠራሁበት ኃላፊነት ትጉህ እንደነበርኩ እናንተም ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን ባሁኑ ጊዜ ከዚህ ቀደም ከነበረኝ ይልቅ ለነፍሳችሁ ደህንነት ከፍተኛ ስሜትና ስጋት ተከፍቼአለሁ።
፬ እነሆም፣ እስከዚህ ጊዜ ድረስ እኔ በሰጠኋችሁ፣ በጌታ ቃል ታዛዦች ነበራችሁ።
፭ ነገር ግን እነሆ፣ እኔን አድምጡኝ፣ እናም ከሁሉም በላይ ሀይለኛ በሆነው የሰማይና የምድር ፈጣሪ ድጋፍ ሀሀሳባችንን በተመለከተ ልናገራችሁ እንደምችል፣ እንዴትስ ኃጢያትን መስራት እንደጀመራችሁ፣ ለእኔም በጣም የረከሰ እንደሆነ፣ አዎን፣ ለእግዚአብሔርም የረከሰ እንደሆነ እወቁ።
፮ አዎን፣ ነፍሴን ያሳዝናል እናም የልባችሁን ክፋት በተመለከተ መመስከር ስላለብኝ፣ በፈጣሪዬ ፊት በእፍረት እንድሸማቀቅ ያደርገኛል።
፯ እናም ደግሞ እናንተን በተመለከተ፣ የብዙዎቹም ስሜት በእግዚአብሔር ፊት፣ ለእግዚአብሔርም አስደሳች በሆኑት፣ እጅግ ለስላሳና ሀንፁህ፣ በቀላሉ ሊጎዱ በሚችል፣ በሚስቶቻችሁ እናም በልጆቻችሁ ፊት ለበኃይል መናገር ስላለብኝ አዝናለሁ፤
፰ እናም እነርሱ አስደሳቹን ሀየእግዚአብሔርን ቃል፣ አዎን፣ የቆሰለውን ነፍስ የሚፈውሰው ቃል ለመስማት ወደዚህ እንዲመጡ እገምታለሁ።
፱ ስለሆነም፣ እንደወንጀላችሁ እናንተን ለመገሰፅ፣ የቆሰሉትን ቁስላቸው ለመዳንና ለመፈወስ ሳይሆን እንዲሰፋ ለማድረግ፤ እናም ያልቆሰሉት ደግሞ አስደሳቹን የእግዚአብሔር ቃል ከመጋበዝ ይልቅ ነፍሳቸውን ለመውጋት እናም በቀላሉ ሊጎዳ የሚችል አዕምሮአቸውን ለማቁሰል ከእግዚአብሔር በተቀበልሁት ጥብቅ ትዕዛዝ ምክንያትም በመገደዴ ነፍሴን ተጨቁኗል።
፲ ነገር ግን ስራው ታላቅ ቢሆንም፣ በእግዚአብሔር ጥብቅ ሀትዕዛዝ መሰረት ማድረግ፣ እናም በልበ ንፁህና፣ በተሰበረ ልብ ፊት፣ እናም ሁሉን በሚገዛ አምላክ ለበሚቃኘው ዐይን ፊት ስለበደላችሁና ስለእርኩሰታችሁ መናገር አለብኝ።
፲፩ ስለሆነም፣ እንደእግዚአብሔር ቃል ሀግልፅነት እውነቱን ልነግራችሁ ይገባል። እነሆም ጌታን ስጠይቅ፣ ቃሉ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፥ ያዕቆብ ነገ ወደ ቤተ መቅደሱ ሂድ፣ እናም ለዚህ ህዝብ የምሰጥህን ቃል አውጅ።
፲፪ እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞቼ፣ ለእናንተ የማውጀው ቃል ይህ ነው፣ ብዙዎቻችሁ ወርቅና፣ ብር፣ እንዲሁም ለእናንተና ለዘሮቻችሁ ሀየቃል ኪዳን ምድር በሆነችው በዚህች ምድር ውስጥ በይበልጥ የያዘችውን ሁሉንም ዓይነት የከበረ ለብረት መፈለግ ጀምራችኋል።
፲፫ እናም የአምላክ እጅ በሰፊው ባርኳችኋል፣ ብዙ ሀብትንም አግኝታችኋል፤ አንዳንዶቻችሁም ከወንድሞቻችሁ በበለጠ ስለተቀበላችሁ በልባችሁ ኩራት ሀከፍ ብላችኋል፣ እናም በለበሳችሁትም ልብስ ውድነት አንገታችሁን አደንድናችኋል፣ ራሳችሁንም ከፍ አድርጋችኋል፣ እናም ራሳችሁን ከወንድሞቻችሁ የተሻላችሁ ስለሚመስላችሁ እነርሱን አሳዳችኋቸዋል።
፲፬ እናም አሁን፣ ወንድሞቼ፣ እግዚአብሔር በዚህ ነገር ከበደል ነጻ ያደርገናል ብላችሁ ትገምታላችሁን? እነሆ፣ አይሆንም እላችኋለሁ። ነገር ግን እርሱ ይፈርድባችኋል፣ እናም እናንተ በእነዚህ ነገሮች የምትቀጥሉ ከሆነ ፍርዱ በፍጥነት ይመጣባችኋል።
፲፭ አቤቱ መውጋት እንደሚችል፣ እናም በቅፅበት ዐይኑ ቅኝት ወደ አፈር ሊመታችሁ እንደሚችል ቢያሳያችሁ!
፲፮ አቤቱ ከክፋትና ከእርኩሰት ነፃ ቢያደርጋችሁ። እናም፣ አቤቱ የትዕዛዙን ቃል ብትሰሙና፣ ይህ የልባችሁ ክፋት ነፍሳችሁን ሀእንዲያጠፋ ባትፈቅዱ!
፲፯ ወንድሞቻችሁ እንደ እራሳችሁ አስቡአቸው፣ እናም እነርሱም ልክ እንደ እናንተ ሀሀብታም ይሆኑ ዘንድ፣ ከሁሉም ጋር ተገናኚ እናም ለበንብረታችሁ ነፃ ሁኑ።
፲፰ ነገር ግን ሀሀብትን ከመፈለጋችሁ በፊት፣ የእግዚአብሔርን ለመንግስት ፈልጉ።
፲፱ እናም በክርስቶስ ተስፋን ካገኛችሁ በኋላ፣ የምትፈልጉአቸው ከሆነ ሀብትን ታገኛላችሁ፤ እነዚህንም ሀመልካም ለማድረግ ዓላማ—የተራቆቱትን ለማልበስ፣ የተራቡትንም ለመመገብ፣ ምርኮኞችንም ነፃ ለማውጣት፣ እናም ለታመሙና ለተሰቃዩ ፋታን ለመስጠት ትፈልጓቸዋላችሁ።
፳ እናም አሁን፣ ወንድሞቼ፣ ኩራትን በሚመለከት ተናግሬአችኋለሁ፤ እናም እግዚአብሔር በሰጣችሁ ነገሮች የተነሳ በልባችሁ ኩራት ጎረቤቶቻችሁን ያሰቃያችሁ፣ እንዲሁም ያሳደዳችሁ ስለዚህ ምን ትላላችሁ?
፳፩ እንዲህ አይነት ነገሮች ስጋን ሁሉ ለፈጠረው የረከሱ ናቸው ብላችሁ አታስቡምን? እናም አንዱ ፍጡር እንደሌላው በፊቱ የከበረ ነው። ሁሉም ስጋም ከአፈር ነው፤ እናም ሀትዕዛዛቱን ይጠብቁና እርሱን ለዘለዓለም ያከብሩት ዘንድ ለተመሳሳይ ዓላማ ፈጥሯቸዋል።
፳፪ እናም አሁን ይህን ኩራት በተመለከተ ለእናንተ ንግግሬን አቆማለሁ። እናም የከፋ ወንጀልን በተመለከተ ለእናንተ መናገር ባይኖርብኝ፣ ልቤ በእናንተ እጅግ ትደሰት ነበር።
፳፫ ነገር ግን በከፋው ወንጀላችሁ የተነሳ የእግዚአብሔር ቃል ከብዶኛል። እነሆም ጌታ እንዲህ ይላል—ይህ ህዝብ በክፋት ቀስ በቀስ ማደግ ይጀምራል፤ ቅዱሳት መጻሕፍትንም አይረዱም፣ ምክንያቱም የዳዊትንና ልጁ ሰለሞንን በተመለከተ በተፃፉት ነገሮች የተነሳ ዝሙትን በመፈፀማቸው ለእራሳቸው ምክንያትን ይፈልጋሉ።
፳፬ እነሆ፣ ዳዊትና ሀሰለሞን በእውነት ብዙ ለሚስቶችና ዕቁባቶች ነበሩአቸው፣ ይህም በፊቴ የረከሰ ነበር ይላል ጌታ።
፳፭ ስለዚህ፣ ጌታ እንዲህ ይላል፣ ይህን ህዝብ ለራሴ ሀፃድቅ ቅርንጫፍ ከዮሴፍ የወገብ ፍሬ አስነሳ ዘንድ በኃያል ክንዴ ከኢየሩሳሌም ምድር አውጥቼዋለሁ።
፳፮ ስለሆነም፣ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህ ህዝብ እንደ ጥንቶቹ እንዲያደርግ አይፈቅድም።
፳፯ ስለሆነም፣ ወንድሞቼ እኔን ስሙኝ፣ እናም የጌታንም ቃል አድምጡ—በመካከላችሁ ሀከአንድ ሚስት በቀር ሌላ አይኑረው፤ እና ዕቁባቶች ምንም አይኑረው።
፳፰ እኔ ጌታ እግዚአብሔር በሴቶች ሀንፅህና እደሰታለሁና። እናም ማመንዘር በእኔ ፊት የረከሰ ነው፤ ይላል የሰራዊት ጌታ።
፳፱ ስለሆነም፣ ይህ ህዝብ ትዕዛዛቴን ይጠብቃል፣ ወይም ምድሪቱ በእነርሱ የተነሳ ሀየተረገመች ትሁን ይላል የሰራዊት ጌታ።
፴ እኔ ለራሴ ሀዘርን ለማቆም ከፈለኩኝ፣ ህዝቤን አዛለሁ፤ አለበለዚያ እነርሱ እነዚህን ነገሮች ያዳምጣሉ ይላል የሰራዊት ጌታ።
፴፩ እነሆ እኔ ጌታ በኢየሩሳሌም ምድር ውስጥ፣ አዎን፣ እናም በህዝቤ ምድር ሁሉ፣ በባሎቻቸው ክፋትና እርኩሰት የተነሳ የህዝቤን ሴት ልጆች ሀዘንን ተመልክቻለሁ፣ እናም ልቅሶአቸውን ሰምቻለሁ።
፴፪ እናም የሰራዊት ጌታ፣ ከኢየሩሳሌም ምድር እንዲወጡ ያደረኩአቸው፣ የዚህ ህዝብ መልካም ሴት ልጆች ጩኸት ወደ እኔ በህዝቤ ወንዶች ላይ ይመጣ ዘንድ አልፈቅድም ይላል የሰራዊት ጌታ።
፴፫ በከባድ እርግማን፣ እንዲሁም ለጥፋታቸውም፣ ካልጎበኘኋቸው በቀር የህዝቤ ሴት ልጆች በሩህሩህነታቸው የተነሳ በምርኮ አይወሰዱም፤ ምክንያቱም እነርሱ ሀዝሙትን እንደጥንቶቹ አይፈፅሙም ይላል የሰራዊት ጌታ።
፴፬ እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞቼ፣ እነዚህ ትዕዛዛት ለአባታችን ሌሂ ተሰጥተውት እንደነበር ታውቃላችሁ፤ ስለሆነም በፊትም ታውቋቸዋላችሁ፤ እናም ማድረግ የማይገባችሁን እነዚህን ነገሮች በማድረጋችሁ ለታላቅ እርግማን መጥታችኋል።
፴፭ እነሆ፣ ከወንድሞቻችን ከላማናውያን የበለጠ ሀበደል ሰርታችኋል። በእነርሱም ፊት መጥፎ ምሳሌዎች በመሆናችሁ፣ የሩህሩህ ሚስቶቻችሁን ልብም ሰብራችኋል፣ የልጆቻችሁንም መተማመን አጥታችኋል፤ እናም በልባቸው ጥልቅ ሀዘን በእናንተ ላይ ወደ እግዚአብሔር መጥተዋል። እናም በእናንተ ላይ በሚወርደው በእግዚአብሔር ቃል ጥብቅነት የተነሳ፣ ብዙ ልቦች በሀዘን ቆሰሉ በጥልቅ ቁስልም ተበሱ።