ወጣቶች
እውነትም አርነት ያወጣችኋል


“እውነትም አርነት ያወጣችኋል፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫ የማድረግ መመሪያ [2022 (እ.አ.አ)]

“እውነት ነጻ ያደርጋችኋል፣” ለወጣቶች ጥንካሬ

አንዲት ወጣት ሴት ሻማ ይዛ ወደ ሰማይ ስትመለከት ሚያሳይ ሥዕል።

እውነት ነጻ ያደርጋችኋል

ዮሐንስ 8፥32

የሰማይ አባታችሁ የእውነት አምላክ ነው። እርሱ ሁሉን አዋቂ ነው። እውነት ሁሉ ከእርሱ ዘንድ መጥቶ ወደ እርሱ ይመራል። መማር ስትፈልጉ፣ በታማኝነት ስትኖሩ እና ምንም እንኳን ብቻችሁን ልትቀሩ ብትችሉም ትክክል እንደሆነ ለምታውቁት ነገር በጀግንነት ስትቆሙ፣ ለእውነት ቦታ እንዳላችሁ ታሳያላችሁ።

ፈገግ የሚል ወጣት።

ዘለአለማዊ እውነቶች

የሰማይ አባት ሴት ልጆቹ እና ወንዶች ልጆቹ ሁል ጊዜ እንዲማሩ ይፈልጋል። ትምህርትን ለመፈለግ እና ለመውደድ ምድራዊ እና መንፈሳዊ ምክንያቶች አሏችሁ። ትምህርት ገንዘብ ስለማግኘት ብቻ አይደለም። የሰማይ አባትን የመምሰል የዘለአለም ግባችሁ አካል ነው።

በቅንነት መኖር ማለት እውነትን በሙሉ ልባችሁ መውደድ—እንዲሁም የግል ምቾት፣ ታዋቂነትን ወይም መደላደልን ከምትወዱት በላይ መውደድ ማለት ነው። ትክክል ስለሆነ ብቻ ትክክል የሆነውን ማድረግ ማለት ነው።

እናንተ የምታካፍሉት ውድ ነገር አላችሁ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የህይወት ጥያቄዎችን መልሶች ይዟል። የሰላም እና የደስታ መንገድ ነው። ሁሉንም ነገር ላታውቁ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ሌሎች ሰዎች እውነተኛ የሆኑ ዘለአለማዊ መርሆዎችን እንዲረዱ እና ዋጋ እንዲሰጡ ለመርዳት በቂ እውቀት አላችሁ።

ግብዣዎች

ሁል ጊዜ ተማሩ። አእምሯችሁን እና ክህሎቶቻችሁንን ለማሳደግ እድሎችን ፈልጉ። እነዚህ እድሎች የትምህርት ቤት መደበኛ ትምህርት ወይም የሙያ ስልጠና እንዲሁም ከምታምኗቸው ምንጮች መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን ሊያካትቱ ይችላሉ። በጥረታችሁ ውስጥ ጌታን አሳትፉት፣ እርሱም ይመራችኋል። በዙሪያችሁ ስላለው ዓለም ስትማሩ፣ ዓለምን ስለፈጠረው አዳኝም ተማሩ። የእርሱን ህይወት እና አስተምህሮት አጥኑ። ሴሚናሪ፣ ኢንስቲትዩት እና የግል የወንጌል ጥናት የህይወት ዘመናችሁ ትምህርት አካል አድርጉ።

እውነትን በጣም ውደዱ፣ እንዲህም በመሆን በሁሉም ቦታ—በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ፣ በበይነ መረብ ላይ—በምንም መንገድ ለመስረቅ፣ ለመዋሸት፣ ለማጭበርበር ወይም ለማታለል ፈጽሞ አትፈልጉ። በግልጽ እንዲሁም በግል ተመሳሳይ የሆናችሁ የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ተከታዮች ሁኑ።

ለሌሎች ብርሃን ሁኑ። ንግግራችሁ እና ድርጊታችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት ያንጸባርቅ። እንደ ሚስዮናዊ እና በህይወታችሁ ሁሉ የእርሱን የክብር ወንጌል ለማካፈል ለሚኖራችሁ የወደፊት እድሎች አሁን ተዘጋጁ። እንዲሁም ስለሚሰማችሁ ተስፋ እና ደስታ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ ለመንገር ዝግጁ ሁኑ።

ቃል የተገቡ በረከቶች

ትምህርት ጌታን የማገልገል ችሎታችሁን ይጨምራል። ሌሎችን እንድትባርኩ፣ በተለይም ቤተሰባችሁን እንድትባርኩ ኃይል ይሰጣችኋል። የበለጠ በተማራችሁ ቁጥር፣ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት እና በአለም ላይ በጎ ተጽዕኖ ለማሳደር የበለጠ ትረዳላችሁ።

ታማኝነት ሰላምን እና ራስን ማክበርን ያመጣል። ቃላቶቻችሁ እና ድርጊቶቻችሁ ከእውነት ጋር ሲጣጣሙ፣ በሌሎች ሰዎች እና በጌታ—እናንተ እምነት ሊጣልባችሁ እንደምትችሉ ያሳያሉ።

ለኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ታማኝ ስትሆኑ እርሱም በጎናችሁ ይገኛል። ሌሎች ከእናንተ ጋር ላይስማሙ ይችላሉ፣ ነገር ግን ድፍረታችሁ እና ቅንነታችሁ ይስተዋላል። ሌሎች የእናንተን አርአያ ቢከተሉም ባይከተሉ፣ በክርስቶስ ላይ ያለው የእናንተ ምስክርነት፣ ልበ ሙሉነት እና እምነት ያድጋል።

የጥይቄዎች እና መልሶች ምልክት

ጥያቄዎች እና መልሶች

ስለ ቤተክርስቲያኗ ጥያቄ ማንሳት ስህተት ነው? መልሶችን እንዴት ማግኘት እችላለሁ? ጥያቄ መኖሩ የድክመት ወይም የእምነት ማነስ ምልክት አይደለም። እንዲያውም ጥያቄዎችን መጠየቅ እምነትን ለመገንባት ሊረዳ ይችላል። የወንጌል ዳግም መመለስ የጀመረው የ14 አመቱ ጆሴፍ ስሚዝ ጥያቄዎችን በእምነት በመጠየቁ ነበር። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ፣ በእግዚአብሔር ነቢያት ቃላት፣ ከመሪዎቻችሁ፣ ከታማኝ ወላጆቻችሁ፣ እና ከእግዚአብሔር ከራሱ መልስ ፈልጉ። መልሶች ወዲያውኑ የማይመጡ ከሆነ በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝን እንደምትማሩ እርግጠኛ ሁኑ። በምታውቁት ነገር መመላለሳችሁን ቀጥሉ፣ እንድሁም እውነትን መፈለጋችሁን ቀጥሉ።

ጆሴፍ ስሚዝ በቅዱስ ጫካ ውስጥ በእግዚአብሔር አብ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ተንበርክኮ የሚያሳይ ሥዕል።

የተለያየ እምነት ያላቸውን ሰዎች ሳላስቀይም ለትክክለኛው ነገር እንዴት ታማኝ መሆን እችላለሁ? መጀመር የምትችሉት ንግግራችሁና ድርጊታችሁ ለእግዚአብሔር እና ለልጆቹ ባላችሁ ፍቅር የተነሳሳ መሆኑን በማረጋገጥ ነው። ወንጌልን ማካፈል የሚቻለው በክርክር መንፈስ ሳይሆን ግልጽነትን፣ ትህትናን እና ደግነትን በማሳየት መሆን ይኖርበታል። በእነርሱ አመለካከት ባትስማሙም እንኳ ለሌሎች ፍቅር ማሳየት ትችላላችሁ።

ማቴዎስ 5፥14–16 (ብርሃንናችሁይብራ)፤ ዮሐንስ 14፥6 (ኢየሱስ እውነት ነው)፤ 1 ጴጥሮስ 3፥15 (በክርስቶስ ያላችሁን ተስፋ ለማካፈል ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ)፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥77–80 (ጌታ እንድንማር የሚፈልጋቸውን ነገሮች)፤ 93፥36 (የእግዚአብሔር ክብር የመረዳት ችሎታ ነው)፤ 124፥15 (ታማኝነት ማለት ትክክለኛ የሆነውን ነገር ማፍቀር ነው)፤ 130፥18 (የመረዳት ችሎታችን ከሞት ስንነሳ አብሮን ይነሳል)።

የቤተመቅደስ ምልክት

የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለማግኘት የሚጠየቅ ጥያቄ

በምታደርገው/ጊው ነገር ሁሉ ሐቀኛ ለመሆን ትጥራለህ/ሪያለሽ?