“የቀዳሚ አመራር መልእክት፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫ የማድረግ መመሪያ [2022 (እ.አ.አ)]
“የቀዳሚ አመራር መልእክት፣” ለወጣቶች ጥንካሬ
የቀዳሚ አመራር መልዕክት
ውድ ወጣት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን
እንወዳችኋለን እንዲሁም በእናንተ እንተማመናለን። እናንተ በእውነት በዚህ ጊዜ አስፈላጊ ነገሮችን ለማድረግ ወደ ምድር ከተላኩ የሰማይ አባት ምርጥ መንፈሶች መካከል ናችሁ።
ጥንካሬ ወይም ችሎታ እንደሌላችሁ ሆኖ የሚሰማችሁ ጊዜዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ያ የተለመደ ነው። በተለይ በእነዚያ ጊዜያት፣ ወደ አዳኙ ዘወር በሉ። እርሱ “የወጣቶች ጥንካሬ” ነው።
ይህ መመሪያ በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ለመቆየት ምርጫዎችን ለማድረግ ጠንካራ የሆነ መሰረትን ለመገንባት ያግዛችኋል። ይህም በቤተመቅደስ ውስጥ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ለመግባት ለማዘጋጀት፣ ምስዮን ለማገልገል ለመዘጋጀት እና ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተል በህይወታችሁ ሁሉ ደስታን ለማግኘት ይረዳችኋል። በአዳኙ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሆናችሁ እና የእርሱን አላማዎች ለመፈጸም ከእርሱ ሀይል እንዳላችሁ ሆኖ እንደሚሰማችሁ ተስፋ እናደርጋለን።
እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ እናውቃለን። ወደ የሰማይ አባታችሁ በሚወስደው የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ጸንታችሁ እንድትቆዩ ጸሎታችን ነው። ይህን በምታደርጉበት ጊዜ፣ ወንጌልን በደስታ በማካፈል እና አለምን ለአዳኙ ዳግም ምጽአት በማዘጋጀት መልካም ተጽእኖ ታሳድራላችሁ።
ቀዳሚ አመራር