ወጣቶች
ሰውነታችሁ ቅዱስ ነው


“ሰውነታችሁ ቅዱስ ነው፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ፣ [2022 (እ.አ.አ)] ተመልከቱ

“ውነታችሁ ቅዱስ ነው፣” ለወጣቶች ጥንካሬ

አንዲት ሴት ስትጸልይ የሚያሳይ ሥዕል።

ሰውነታችሁ ቅዱስ ነው

1 ቆሮንቶስ 6፥18–20

የእግር ኳስ የሚጫወቱ ሰዎች ምልክት

ሰውነታችሁ የሰማይ አባታችሁ ድንቅ ስጦታ ነው። እርሱን የሰጣችሁ በይበልጠ እንደ እርሱ እንድትሆኑ እንዲረዳችሁ ነው። ሰውነታችሁ መኖሩ የመምረጥ ነፃነታችሁን ለመጠቀም ተጨማሪ ኃይል ይሰጣችኋል። ዳግም የተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሰውነታችሁን በእግዚአብሔር አይን እንድታዩ ሊረዳችሁ ይችላል። ይህ ደግሞ በሰውነታችሁ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እና እንዴት እንደምትንከባከቡ በምርጫችሁ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

ዘለአለማዊ እውነቶች

ሰውነታችሁ የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳል ነውእርሱም በአጽናፈ ዓለም እጅግ የከበረ፣ ግርማ ሞገስ ያለው ፍጥረት ነው። ቅዱሳት መጻህፍት ሰውነታችንን ከቅዱስ ቤተመቅደስ ጋር ያመሳስሉታል፣ በዚህም መንፈስ ሊኖርበት ይችላል። በእርግጥም፣ ሰውነታችሁ አሁን ፍጹም አይደለም። ነገር ግን በሰውነታችሁ የሚኖሯችሁ ልምዶች አንድ ቀን ፍጹም የሆነ፣ ከሞት የተነሳ፣ ክብር ያለው አካል ለመቀበል እንድትዘጋጁ ይረዳችኋል።

ነፍሳችሁ በሰውነታችሁ እና በመንፈሳችሁ የተዋቀረች ናት። በዚህ ምክንያት፣ አካላዊ ጤንነት እና መንፈሳዊ ጤንነት በቅርበት የተሳሰሩ ናቸው። አዳኙ ሰውነታችሁን የመንከባከብ መርሆዎችን ለማስተማር እና ስጋዊ እና መንፈሳዊ በረከቶችን ለመስጠት የጥበብን ቃልን ገልጧል።

ደስተኛ ትዳርን እና ዘለአለማዊ ቤተሰቦችን ለመፍጠር ፆታ ስሜት የእግዚአብሔር እቅድ አስፈላጊ አካል ነው። እነዚህ ስሜቶች ኃጢአተኛ አይደሉም—እነርሱ የተቀደሱ ናቸው። ፆታዊ ስሜት በጣም የተቀደሰ እና በጣም ሀይለኛ ስለሆነ፣ እግዚአብሔር እንዳሰበው እነዚህን ስሜቶች እንድትጠቀሙ እንዲያዘጋጃችሁ የንፅህና ህግን ሰጥቷችኋል። የንጽሕና ሕግ ፆታዊ ግንኙነትን እግዚአብሔር የሚፈቅደው በጋብቻ ውስጥ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የብቻ እንደሆነ ይገልጻል። በዓለም ላይ ያሉ ብዙዎች የእግዚአብሔርን ህግ ችላ ይላሉ ወይም ያፌዛሉ፣ ነገር ግን ጌታ ደቀ መዛሙርቱ እንድንሆን እና ከአለም ከፍ ባለ ደረጃ እንድንኖር ይጋብዘናል።

በከተማ ጎዳና ላይ ቤተሰብ እየተራመደ።

ግብዣዎች

“የራሳችሁን—እና የሌሎችን ሠውነት—በክብር ያዙ። ስለአለባበሣችሁ፣ ስለፀጉር አሠራራችሁ እና ስለገፅታችሁ ውሳኔ በምታደርጉበት ጊዜ ‘ሠውነቴን ከእግዚአብሔር እንደተሠጠ ቅዱስ ሥጦታ እያከበርኩት ነው?’ ብላችሁ ራሣችሁን ጠይቁ። የሠማይ አባት፣ አንዳችን የሌላችንን እውነተኛ ማንነት እንድናይ ይፈልጋል፦ ሥጋዊ አካልን ብቻ ሳይሆን መለኮታዊ ዕጣ ፈንታ ያለን የተወደድን ልጆቹ መሆናችንን እንድናይ ይፈልጋል። ከእግዚአብሔር ልጅነት ማንነታችሁ ይልቅ ሥጋዊ አካላችሁን የሚያጎሉ ወይም ተገቢ ያልሆነ ትኩረትን የሚስቡ ዘይቤዎችን አስወግዱ። የስነምግባር ንጽህና እና ለእግዚአብሔር ያላችሁ ፍቅር ምርጫችሁን ይምራ። ከወላጆቻሁ ምክርን እሹ።

ሞቃታማ በሆነ አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ሁለት ወጣቶች።

ሰውነታችሁን የሚያጠናክር ነግሮች አግረጉ— የሚጎዳውን ወይም የሚያበላቸውን አታድርጉ። እግዚአብሔር ባዘጋጃቸው ብዙ መልካም ነገሮች በአመስጋኝነት ተደሰቱ። ነገር ግን አልኮል፣ ትምባሆ፣ ቡና፣ ሻይ እና ሌሎች ጎጂ እጾች እና ንጥረ ነገሮች ለሰውነታችሁ ወይም ለመንፈሳችሁ እንደማይጠቅሙ አስታውሱ። ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን፣ ለምሳሌ በሀኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች፣ እንኳን በትክክል ካልተጠቀማችሁ ጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ።

ፆታዊ ግንኙነትን እና ፃታዊ ስሜትን የተቀደሱ አድርጉ። እነርሱም የቀልድ ወይም የመዝናኛ ርዕሰ ጉዳይ መሆን የለባቸውም። በወንድና በአንዲት ሴት መካከል ካለ ከጋብቻ ውጪ፣ የሌላን ሰው ግላዊ፣ ቅዱስ የአካል ቦታዎችን በልብስ በላይ ቢሆንምመንካት ስህተት ነው። የምታደርጉትን፣ የምትመለከቱትን፣ የምታነቡትን፣ የምታዳምጡትን፣ የምታስቡትን፣ የምትለጥፉትን ወይም የምትጽፉትን በምትመርጡበት ጊዜ በሌሎች ወይም በራሳችሁ ላይ ሆን ተብሎ ጾታዊ ስሜት የሚቀሰቅስ ማንኛውንም ነገር አስወግዱ። ይህም ማንኛውንም አይነት የብልግና ምስሎችን ያካትታል። ሁኔታዎች ወይም ተግባሮች ፈተናን የበለጠ እንደሚያጠናክሩ ካወቃችሁ ራቋቸው። እነዚህ ሁኔታዎች እና ተግባሮች ምን እንደሆኑ ታውቃላችሁ። እርግጠኛ ካልሆናችሁ፣ መንፈስ፣ ወላጆቻሁ እና መሪዎቻችሁ ለማወቅ ሊረዷችሁ ይችላሉ። ህይወትን የመፍጠር ቅዱስ ኃይልን አንደምታከብሩ ለሰማይ አባታችሁ አሳዩ።

ቤተሰብ በአንድ ላይ ምግብ እያበሰለ

ቃል የተገቡ በረከቶች

በባህሪያችሁ፣ በመልካችሁ እና በአለባበሳችሁ ሰውነታችሁን ስታከብሩ ለራሳችሁ እና ለሌሎች ያላችሁ ክብር ይጨምራል

የጥበብን ቃል ለሚጠብቁት እግዚአብሔር ታላቅ የእውቀትን ሀብት ቃል ገብቷል። ከሱስ የጸዳ ጤናማ አካል፣ የግል መገለጥን የመቀበል፣ በግልፅ የማሰብ እና ጌታን የማገልገል ችሎታን ይጨምራል።

የንጽሕና ሕግን በማክበር መኖር የእግዚአብሔርን ሞገስ እና የግል መንፈሳዊ ኃይል ያስገኛል። በትዳር ውስጥ ስትሆኑ፣ ይህ ህግ ለትዳራችሁ የበለጠ ፍቅርን፣ መተማመንን እና አንድነትን ያመጣል። ይህንን ህግ ማክበር ለዘለአለም እድገትእንዲኖራችሁ እና የሰማይ አባታችሁን እንድትመስሉ ያስችላችኋል። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር በመሆን ስትኖሩ እምነታችሁ ያድጋል።

ኢየሱስ ማርያምንና ማርታን ሲያስተምር የሚያሳይ ሥዕል።
የጥይቄዎች እና መልሶች ምልክት

ጥያቄዎች እና መልሶች

ጌታ ስለአለባበስ፣ ስለአጋጌጥ፣ ስለንቅሳት እና ስለመበሳት ያለው መስፈርት ምንድን ነው? ከአለም የተለያችሁ መሆን ማለት ቢሆንም፣ የጌታ መስፈርት የሰውነታችሁን ቅድስና ማክበር ነው። ውሳኔዎችን፣ በተለይ በሰውነታችሁ ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ያላቸውን ውሳኔዎች፣ በምታደርጉበት ጊዜ ይህ እውነት እና ቅዱስ መንፈስ መሪያችሁ ይሁን። ብልህ እና ታማኝ ሁኑ፣ እንዲሁም ከወላጆቻችሁ እና ከመሪዎቻችሁ ምክር ፈልጉ።

ፈተናዎችን እና መጥፎ ልማዶችን እንዴት ማሸነፍ እችላለሁ? የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተን ለመርዳት ኃይል አላቸው። እንደ ጸሎት፣ የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና ሌሎች፣ በማገልገል አይነት ያን ሃይል ወደ ህይወታችሁ በሚጋብዙ ነገሮች ህይወታችሁን ሙሉ። ኢየሱስ ክርስቶስን እና ወደ ወንጌሉን ስትቀበሉ ድክመቶች ጥንካሬዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ትገነዘባላችሁ። እንደ አስፈላጊነቱ ከወላጆች፣ ከመሪዎች እና ከባለሙያዊ አማካሪዎች እርዳታ ጠይቁ። በሱስ ለሚሰቃዩት፣ ቤተክርስቲያኗ ከሱስ የማገገሚያ ፕሮግራም አላት። እነዚህም የአዳኙ ቤተክርስቲያን ህይወታችሁን እንድትቆጣጠሩ ለመርዳት የምታቀርባቸው በረከቶች ናቸው። ይህም ጊዜ ስለሚወስድ፣ ታገሱ እንዲሁም በምንም ተስፋ አትቁረጡ።

አንዲት ልጅ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስታነብ።

ተመሳሳይ ጾታ ያላቸውን ሰዎች ይስቡኛል። እነዚህን መስፈርቶች እንዴት ተግባራዊ አደርጋለሁ? በተመሳሳይ ጾታ መሳብ ኃጢአት አይደለም። እነዚህ ስሜቶች ካሏችሁ እና እዚህን ስሜቶች ካልተከተላችሁ ወይም ካላደረጋችሁ፣ የሰማይ አባትን የንጽህና ህግ አልጣሳችሁም። እናንተ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች እና የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ናችሁ። አዳኙ ያጋጠማችሁን ሁሉ እንደሚረዳ አስታውሱ። ከእርሱ ጋር ባላችሁ የቃል ኪዳን ግንኙነት፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመጠበቅ እና ቃል የገባላችሁንን በረከቶች ለመቀበል ብርታት ታገኛላችሁ። በእርሱ እና በወንጌሉ እመኑ።

ጥቃት ደርሶብኛል፣ እንዲሁም ሃፍረት ይሰማኛል። እኔ እንደ ኃጢአተኛ እቆጠራለሁ? የማንኛውም ጥቃት ወይም ጉዳት ሰለባ መሆን ኃጢአተኛ አያደርግም። እባካችሁ የጥፋተኝነት ስሜት ወይም እፍረት አይሰማችሁ። አዳኙ ይወዳችኋል። ሊረዳችሁ፣ ሊፈውሳችሁ እና ሰላም ሊሰጣችሁ ይፈልጋል። ባለሙያዊ አማካሪዎች፣ የቤተሰብ አባላቶቻችሁ እና መሪዎቻችሁ እንዲሁ ሊረዷችሁ ይችላሉ።

ዘፍጥረት 1፥27 (የተፈጠርነው በእግዚአብሔር መልክ ነው)፤ ዮሐንስ 14፥18 (አዳኙ መጽናኛን ቃል ገብቷል)፤ ፊልጵስዩስ 4፥7 (የእግዚአብሔር ሰላም ማስተዋልን ያልፋል ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥15 (መንፈስ እና ሥጋ ነፍስ ናቸው)፤ 89 (የጥበብ ቃል)፤ 121፥45 (ምግባረ በጎነት አስተሳሰብን ያሳምር) ተመልከቱ።

የቤተመቅደስ ምልክት

የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ጥያቄዎች

ጌታ እንዲህ ብሏል ሁሉም ነገሮች በፊቴ “በንጽህና ይሰሩ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥41). በአስተሳሰብህ/ሽ እና በባህሪህ/ሽ ውስጥ የሥነ–ምግባር ንጽህና እንዲኖርህ/ርሽ ጥረት ታደርጋለህ/ታደርጊያለስሽ? የንጽህና ህግን ታከብራለህ/ታከብሪያለሽ?

የጥበብ ቃልን ትረዳለህ/ትረጃለሽ እና በዚህም ትታዘዛለህ/ትታዘዣለሽ?