“እግዚአብሔርን ውደዱ፣ ባልንጀራችሁንም ውደዱ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫ የማድረግ መመሪያ [2022 (እ.አ.አ)]
“እግዚአብሔርን ውደዱ፣ ባልንጀራችሁንም ውደዱ፣” ለወጣትነት ጥንካሬ፡
እግዚአብሔርን ውደዱ፣ ባልንጀራችሁንም ውደዱ
ማቴዎስ 22፥37–40
ጥሩ ምርጫ እንድታደርጉ እንዲረዳችሁ፣ እግዚአብሔር ትእዛዛትን ይሰጣል። ይህን የሚያደርገው ስለሚወዳችሁ ነው። የእግዚአብሔርንም ትእዛዛት ለመታዘዝ ከሁሉ የተሻለው ምክንያት እርሱን መውደዳችሁ ነው። ፍቅር የእግዚአብሔር ትእዛዛት ማእከል ነው።
ዘለአለማዊ እውነቶች
እግዚአብሔር ይወዳችኋል። እርሱ አባታችሁ ነው። የእርሱ ፍፁም ፍቅር እርሱን እንድትወዱት ሊያበረታችሁ ይችላል። ለሰማይ አባታችሁ ያላችሁ ፍቅር በህይወታችሁ በጣም አስፈላጊው ተጽዕኖ ሲሆን፣ ብዙ ውሳኔዎች ቀላል ይሆናሉ።
እግዚአብሔርን እና ባልንጀራን ውደድ ከትእዛዛት ሁሉ የሚበልጡት ሁለቱ ትዕዛዛት እንደሆኑ ኢየሱስ አስተምሯል። ባልንጀራችሁ ማነው? ሁሉም ሰው ነው! ቅዱሳት መጻሕፍት እና ነቢያት ያስተማሩትሁሉም ነገሮች ከእነዚህ ሁለት ትእዛዛት ጋር የተያያዙ ናቸው።
በእርግጥ ከእናንተ የሚለዩ ወይም ከእናንተ ጋር የማይስማሙ ሰዎችንም ጨምሮ፣ ሁሉም ሰዎች የእናንተ ወንድሞች እና እህቶች ናቸው – ። የሰማይ አባት ልጆቹ እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ ይፈልጋል። ልጆቹን ስታገለግሉ እርሱን እያገለገላችሁ ናችሁ።
ግብዣዎች
ትእዛዛቱን በመጠበቅ ለእግዚአብሔር ያላችሁን ፍቅር አሳዩ። ለምሳሌ፣ የሰንበትን ቀን በቅድስና በመጠበቅ፣ በታማኝነት ለቅዱስ ቁርባን በመዘጋጀት እና በመካፈል፣ በሳምንት አንድ ቀን ለእርሱ ለመሰጠት ፈቃደኛ መሆናችሁን ለእግዚአብሔር ታሳያላችሁ። ስትጾሙ እና አሥራት እና በኩራትን ስትከፍሉ፣ ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የእርሱ ስራ ለእናንተ አስፈላጊ እንደሆነ ለእግዚአብሔር ታሳያላችሁ። የእግዚአብሔርን እና የክርስቶስን ስም በከንቱ ወይም በግዴለሽነት ሳይሆን በአክብሮት ስትጠቀሙ፣ እነርሱ ላደረጉላችሁ ሁሉ አመስጋኝ መሆናችሁን ታሳያላችሁ።
ሁሉንም ሰው እንደ እግዚአብሔር ልጅ እዩ። የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንደመሆናችሁ፣ ከሁሉም ዘር እና ሀይማኖቶች እና ሌሎች ቡድኖች የተወጣጡ ሰዎችን፣ በተለይ አንዳንድ ጊዜ ጎጂ ቃላት እና ድርጊቶች ተጠቂ የሆኑትን ሰዎች በማፍቀር፣ በማክበር እና በመቀበል መሪዎች መሆን ይችላሉ። ብቸኝነት የሚሰማቸውን፣ የተገለሉ ወይም አቅመ ደካማ የሆኑ ሰዎችን እርዱ። በእናንተ በኩል የሰማይ አባት ፍቅር እንዲሰማቸው እርዷቸው።
በበይነ መረብ ላይ ሆነ በአካል እየተነጋገራችሁ ቢሆንም፣ ቋንቋችሁ የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚያንፀባርቅ መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ። የሚያነሳሱ ቃላቶችን ተናገሩ— እንደቀልድ ቢሆን እንኳን ሊከፋፍል፣ ሊጎዳ ወይም ሊያስቀይም የሚችል ነገርን አትናገሩ። ቃላቶቻችሁ ሃይል ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ለበጎ ኃይል ይኑራቸው።
ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች መውደድ የሚጀምረው ከቤት ነው። በቤታችሁ ሁሉም ሰው የአዳኙ ፍቅር ሊሰማው የሚችልበት ቦታ እንዲሆን የበኩላችሁን አድርጉ።
ቃል የተገቡ በረከቶች
ትእዛዛቱን በመታዘዝ እና ከእርሱ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳኖች በመጠበቅ ፍቅራችሁን ስትገልጹ ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ግንኙነት እየጠነከረ ይሄዳል።
በክርስቶስ ዓይነት አገልግሎት ፍቅራችሁን ስትገልጹ ከሌሎች ጋር ያላችሁ ግንኙነት እየጠነከረ ይሄዳል። ዓለምን የበለጠ ተወዳጅ ቦታ በማድረግ ደስታን ታገኛላችሁ።
ጥያቄዎች እና መልሶች
የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት ሊሰማኝ ይችላል? የሰማይ አባት ፍቅር ሁልጊዜም አለ። በፀሎት አማካኝነት አዘውትራችሁ ከእርሱ ጋር ተነጋገሩ። ስሜታችሁን ለእርሱ አካፍሉ እንዲሁም ከእርሱ የሚመጡትን ግንዛቤዎች አዳምጡ። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የሚገኙት ቃላቶቹን አንብቡ። እርሱ ያደረገላችሁን ነገር ሁሉ አስቡ። መንፈሱ በሚገኝበት ቦታ እና ተግባር ጊዜ አሳልፉ።
ጌታ መጥፎ የሚያደርጉኝንም ጨምሮ ሁሉንም ሰው እንድወድ ይጠብቃል? ጌታ ጠላቶቻችሁን እንድትወዱ እና ለሚበድሏችሁ እንድትጸልዩ ይጠብቅባችኋል። ሆኖም፣ ያ ማለት ስሜታዊ፣ አካላዊ ወይም መንፈሳዊ ጉዳት በሚያደርስባችሁ ሁኔታ ውስጥ መቆየት አለባችሁ ማለት አይደለም። እራሳችሁን ለመጠበቅ ጤናማ ገደቦችን አዘጋጁ። በደል ወይም ጥቃት እየደረሰባችሁ ከሆነ—ወይም ይህ በሌላ ሰው ላይ እየደረሰ እንደሆነ ካወቃችሁ—ታማኝ የሆነ አዋቂን አነጋግሩ።
ከተቃራኒ ጾታ አባላት ጋር መተዋወቅ ያለብኝ መቼ እና እንዴት ነው? ከሌሎች ጋር ለመተዋወቅ ከሁሉ የተሻለው መንገድ እውነተኛ ጓደኝነት ነው። በወጣትነታችሁ ጊዜ ከብዙ ሰዎች ጋር ጥሩ ጓደኝነት ፍጠሩ። በአንዳንድ ባሕሎች ወጣቶች ከተቃራኒ ጾታ ጋር የሚተዋወቁት ጤናማ በሆኑ የቡድን ተግባሮቶች ላይ ነው። ለስሜታዊ እና መንፈሳዊ እድገታችሁ እና ደህንነታችሁ፣ አንድ ለአንድ ተግባሮች እናንተ ብስለት እስኪኖራችሁ ድረስ መተላለፍ ይባቸዋል—16 አመት ጥሩ መመሪያ ነው። ከወላጆቻችሁ እና ከመሪዎቻችሁ ጋር ተመካከሩ። ልዩ ግንኙነቶችን እድሜያችሁ ከፍ ለሚልበት ጊዜ አቆዩ። ለኢየሱስ ክርስቶስ የገባችሁትን ቃል እንድትጠብቁ ከሚረዷችሁ ጋር ጊዜ አሳልፉ።
ቤቴ ፍቅር የሰፈነበት ቦታ ካልሆነ ምን ማድረግ እችላለሁ? አዳኛችሁ ሁኔታችሁን ያውቃል፣ እንዲሁም ይወዳችኋል። ታጋሽ ሁኑ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ጠብቁ፣ ለቤተሰባችሁም ጥሩ ምሳሌ ሁን። በአጥቢያ ቤተሰባችሁ ውስጥ ግንኙነቶችን ገንቡ። በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ላይ የተመሰረተ የራሳችሁን ቤተሰብ ለመገንባት አሁን ተዘጋጁ።
ኢሳይያስ 58፥3–11 (የጾም ዓላማዎች)፤ 58፥13–14 (ሰንበትን የማክበር በረከቶች)፤ ሚልክያስ 3፥8–10 (አሥራት የመክፈል በረከቶች)፤ ሉቃስ 6፥27–28 (ጠላቶቻችሁን ውደዱ)፤ 10፥25–37 (ባልንጀራዬ ማን ነው?) ዮሐንስ 3፥16–17 (እግዚአብሔር ወዶናልና ልጁን ላከ)፤ 14፥15 (እግዚአብሔርን ስለምንወደው ትእዛዛትን እንጠብቃለን)፤ 1 ዮሐንስ 4፥19 (እግዚአብሔርን የምንወደው እርሱ ስለሚወደን ነው)፤ ሞዛያ 2፥17 (ሌሎችን ስናገለግል እግዚአብሔርን እናገለግላለን) ተመልከቱ።
የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ጥያቄዎች
በግል እንዲሁም በህዝብ ፊት በምታሳየው/በምታሳዪው ባህርይ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን አስተምህሮቶች ትከተላላህ/ትከተያለሽ?
የሰንበትን ቀን በቤትም ሆነ በቤተክርስቲያን ቅዱስ አድርጎ ለመጠበቅ፤ በስብስባዎች ለመገኘት፤ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ለመዘጋጀት እና በብቁነት ለመውሰድ፤ እንዲሁም ህይወትህን/ህይወትሽን ከወንጌል ህግጋት እና ትዕዛዛት ጋር አስማምተህ/ሽ ለመኖር ትጥራለህ/ትጥሪያለሽ?
ሙሉ አስራት ትከፍላለህ/ትከፍያለሽ?