ወጣቶች
በመነሳሳት ምርጫዎችን አድርጉ


“በመነሳሳት ምርጫዎችን አድርጉ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ [2022 (እ.አ.አ)]

“በመነሳሳት ምርጫዎችን አድርጉ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ

አንዲት ወጣት በአልጋዋ ላይ እየጸለየች።

በመነሳሳት ምርጫዎችን አድርጉ

ለወጣቶች ጥንካሬ ውስጥ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን እና የነቢያቱን ትምህርቶች ታገኛላችሁ። በእነዚህ እውነቶች መመሪያነት አሁን እንዲሁም ለዘለአለም የሚባርኳችሁን የተነሳሱ ምርጫዎችን ማድረግ ትችላላችሁ።

ኢየሱስ ክርስቶስ የዘለአለም ደስታ መንገድ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ነፃነታችሁን ስትጠቀሙ፣ ወደ ዘለአለማዊ ደስታ በሚወስደው መንገድ ላይ ትሆናላችሁ። ኢየሱስ ክርስቶስን መመዘኛችሁ፣ ጠንካራ መሰረታችሁ አድርጉ። ህይወታችሁን በእርሱ ትምህርቶች ላይ ገንቡ እንዲሁም ምርጫችሁን በእነርሱ ለኩ። በጥምቀት፣ በቅዱስ ቁርባን ጊዜ እና በቤተመቅደስ ውስጥ የምትገቧቸው ቃል ኪዳኖች በክርስቶስ ላላችሁ ፅኑ መሠረት የመገንቢያ አለት ናቸው። አሁንም ቢሆን ችግሮችን እና ፈተናዎችን ትጋፈጣላችሁ፣ ነገር ግን የሰማይ አባት እና አዳኙ በሁሉም ነገሮች ይረዷችኋል።

እናንተ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር የመንፈስ ልጆች ናችሁ። የእርሱ ታላቅ የደስታ እቅድ በመንፈሳዊ መልኩ እንድታድጉ እና መለኮታዊ አቅማችሁን እንድታዳብሩ ያስችላችኋል። ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንዲሆንላችሁ የላከው ለዚህ ነው።

የሰማይ አባታችሁ ያምናችኋል። የወንጌልን ሙላት እና ከእርሱ ጋር የሚያስተሳስሩ እና ኃይሉን ወደ ህይወታችሁ የሚያመጡትን የተቀደሱ ስርአቶችን እና ቃል ኪዳኖችን ጨምሮ ታላቅ በረከቶችን ሰጥቷችኋል። ከእነዚያ በረከቶች ጋር ተጨማሪ ኃላፊነት ይመጣል። በአለም ላይ ለውጥ ማምጣት እንደምትችሉ ያውቃል፣ ይህ ደግሞ በብዙ ሁኔታዎች ከአለም የተለዩ መሆንን ይጠይቃል። ምርጫ በምታደርጉበት ጊዜ የሰማይ አባታችሁን ምሪት ፈልጉ። እርሱ በመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት በኩል ይባርካችኋል።

ለወጣቶች ጥንካሬ አላማ ሊያጋጥሟችሁ ስለሚችሉት ምርጫዎች ሁሉ “አዎ” ወይም “አይ” የሚል መልስ መስጠት አይደለም። ይልቁኑ፣ ጌታ ከፍ ባለው እና በተቀደሰው መንገድ—በራሱ መንገድ—እንድትኖሩ እየጋበዛችሁ ነው። ይህ መመሪያ ስለ መንገዱ ያስተምራችኋል። እርሱ የገለጠውን እውነት ያስረዳል። —እንደ በቤተመቅደስ ውስጥ ቃል ኪዳን መግባት እና በምስዮን ማገልገል አይነት ትልቅ ምርጫዎች፣ እንዲሁም ሰዎችን እንዴት እንደምትንከባከቡ ወይም ጊዜያችሁን እንዴት እንደምታሳልፉ አይነት ዕለታዊ ምርጫዎችን ለማድረግ እነዚህን እውነቶች የራሳችሁ መመሪያ አድርጉ።

ሌሎች ሊረዷችሁ ቢችሉም፣ መንፈሳዊ እድገታችሁ የግል ነው። ይህም በእናንተ እና በጌታ መካከል ነው። እርሱ ልባችሁን ያውቃል፣ በስተመጨረሻም የሚዳኛችሁ እሱ ብቻ ነው። በየቀኑ ለመሻሻል፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመጠበቅ እና ቃል ኪዳኖቻችሁን ለማክበር እና ሌሎች ወደ አዳኙ እንዲቀርቡ ለመርዳት የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ።

ሞዛያ 4፥29–30 (የኃጢአት መንገዶች ስፍር ቁጥር የሌላቸው ናቸው፣ ስለዚህ ራሳችንን መጠበቅ አለብን)፤ ሔላማን 5፥12 (በክርስቶስ ላይ መሠረታችሁን ገንቡ)፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥57 (መንፈስ ቅዱስን እንደ መመሪያ ውሰዱ)፤ 82፥15 (ራሳችሁን በቃል ኪዳኖች ከጌታ ጋር እስሩ) ተመልከቱ።

ሰዎች ካርታ ሲጠቀሙ የሚያሳይ ምልክት

አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክትይህ መመሪያ እንዴት ተደራጀ

እያንዳንዱ ርዕስ ሦስት ክፍሎች አሉት፦

  1. የዘለአለም እውነቶች፣ ወይም ዳግም የተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ትምህርት

  2. እነዚያን እውነታዎች ለመተግበር የሚቀርቡ ግብዣዎች

  3. በእርሱ አስተምህሮቶች ለሚኖሩ ጌታ ለመስጠት ቃል ቃል የተገቡ በረከቶች