2014 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ሚስኦን፥ የሰላም ልዑል
ዲሴምበር 2014


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ታህሳስ 2014 (እ.ኤ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ሚስኦን፥ የሰላም ልዑል

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደwww.reliefsociety.lds.org

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ኩዊንት ኤል ኩክ የአስራሁለት ሐዋሪያት ጉባኤ አባል እንዳሉት “አዳኝ እውነተኛ የሰላም ምንጭ ነው”። “በህይወት ፈተናዎች ውስጥም፣ በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና በእርሱ ጸጋ ምክንያት፣ የዳድቅ ኑሮ በግል ሰላም ይሸለማል።”1 ኢየሱስ ክርስቶስ የሰላም ልዑል መሆኑን መረዳት ውስጣዊ ሰላምን እንድናገኝ እና በእርሱ ያለንን እምነት እንድንጨምር ሊረዳን ይችላል።

ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ አለ፥ “በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲኖራችሁ ይህን ተናገሬአችኋለው። በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ”(ዮሐንስ 16፥33)። ያንን እውነታ በመመስከር፣ የአጠቃላይ ሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ሁለተኛ አማካሪ ሊንዳ ኤስ ሪቭስ እንዲህ አለች፥ “ጌታ ለእኔ መሀሪ ሆኗል እንዲሁም ሸክሞቼ ቀላል እንዲሆኑ አግዞኛል። ታላቅ ሰላም እንዲሰማኝ አግዞኛል።”2

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ጉባኤ አባል የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ ስካት እንዲህ አስተማሩ፥ “ለሰላም መልካም ቦታ ቢኖር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን መአከላዊ ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ ባደረግንበት በገዛ ቤቶቻችን ግድግዳዎች ውስጥ ነው።”3

ተጨማሪ ጥቅሶች

ኢሳያስ 9፥6 ሉቃስ 2፥14ዮሐንስ 14፥271 ኔፊ 13፥37ት እና ቃ 59፥23

ከቅዱሳት መጻህፍት

ኢሳይያስ ስለሰላም ልዑሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ተነበየ (ኢሳይያስ 9፥6ተመልከቱ)። በአሜሪካዎች ውስጥ ላማናውያው ሳሙኤል ከአምስት አመት በኋላ ስለሚመጡት የክርስቶስን ውልደት ምልክቶች ተናገረ ሔለማን 14፥3፣ 5 ተመልከቱ )። የተተነበየለት ቀን ሲቃረብ፣ የማያምኑ ሰዎች እነዚህ ምልክቶች ባይከሰቱ ሁሉንም ክርስቲያኖች እንደሚገድሉ አስፈራሩ። ነቢዩ ኔፊ፣ “ቀኑን በሙሉ ወደ ጌታ በኃይል ጮኸ፤ እናም እነሆ፣ የጌታ ድምፅ እንዲህ እያል ወደ እርሱ መጣ፥ በሚቀጥለውም ቀን ወደ አለም እመጣለው” 3 ኔፊ 1፥12–13)። ምልክቶቹ ታዩ፣ እናም በክርስቶስ ውልደት፣ “ሰዎቹ በድጋሚ በምድሪቱ ሰላምን ማግኘት ጀመሩ” (ቁጥር 23)።

በቤተልሔም ውስጥ፣ ማሪያም “የበኩር ልጁዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በግርግምም አስተኛችው” (ሉቃስ 2፥7)።

ማስታወሻዎች

  1. ኩዊንተን ኤል ኩክ፣ “Personal Peace: The Reward of Righteousness ፣” Liahona፣ ግንቦት 2013 (እ.አ.አ)፣ 35።

  2. ሊንዳ ኤስ ሪቭስ፣ “Claim the Blessings of Your Covenants፣” Liahona፣ ህዳር 2013 (እ.አ.አ)፣ 120።

  3. ሪቻርድ ጂ ስካት፣ “For Peace at Home፣” Liahona፣ ግንቦት 2013 (እ.አ.አ)፣ 29።

ይህን አስቡበት

አዳኝ በምን አይነት መንገድ ነው ሰላምን ወደ ሕይወታችሁ የሚያመጣው?