2010–2019 (እ.አ.አ)
የመዝጊያ ነጥቦች
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


የመዝጊያ ነጥቦች

የግለሰብ ብቁነት ይበልጥ እንደ ጌታ ለመሆን የሚደረግን የአእምሮ እና የልብ አጠቃላይ ለውጥ ይፈልጋል።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፤ ለዚህ ታሪካዊ ጉባኤ መዝጊያ ስንቃረብ፤ ጌታን ስላአነፁን ምሪቱ እና ስለ ዝማሬዎቹ እናመሰግነዋለን ፡፡ በእውነት መንፈሳዊው ድግስ አስደስቶናል፡፡

የተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ትምህርቱን ለሚሰሙ እና ለሚያዳምጡ ሰዎች ተስፋ እና ደስታን እንደሚያመጣ እናውቃለን ፡፡ እያንዳንዱ ቤት ሰላም ፣ ፍቅር እና የጌታ መንፈስ የሚኖርበት እውነተኛ የእምነት ስፍራ እንደሚሆን እናውቃለን ፡፡

በእርግጥ ፤ የተቀደሱት ቤተ፟ መቅደሶዎች የተመለስው ወንጌል አክሊል ናቸው፡፡ ቅዱስ ስርዓቶቹና ቃልኪዳኖቹ ስዎች ለአዳኛችንን ዳግም ምፃአት ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ ቁልፍ ናችው፡፡ በአሁን ወቅት 166 የተመረቁ ቤተመቅደሶች አሉን ፤ ተጨማሪም እየመጡ ነው።

የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ለእያንዳንዱ አዲስ ወይም ለታደስ ቤተ መቅደስ ከምርቃቱ ቀደም በሎ ይደረጋል፡፡ ከእኛ እምነት ያልሆኑት ብዙ ጋደኞቻችን በቤተ መቅደስ ጉብኘት ላይ በመሳተፍ ስለ ቤተ መቅደስ በርከቶች ጥቂት ይማራሉ፡፡ እናም ከነዛ ጥቂቶቹ ጎብኝዎች የበለጠ ለማወቅ ይነሳሳሉ፡፡ አንዳንዶች ከልባችው ሆነው ለነዚህ የቤት መቅደስ በርከቶች እንዴት ብቁ ሊሆኑ እንደሚቸሉ ይጠይቁ ይችላሉ፡፡

እንደ ቤተክርስቲያን አባሎች ፤ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ለመስጠት ዝግጁ መሆን አለብን ። ፤ የቤተ መቅደስ በረከቶች እራሳቸውን ለሚያዝጋጁ ለማንኛውም እና ለሁሉም ስዎች ክፍት ሆነው እንደሚገኙ ማብራራት እንችላን ፡፡ ነገር ግን የተመርቀ ቤተ መቅደስ ወስጥ መግባት ከመቻላቸው በፊት ብቁ መሆን አለባቸው፡፡ ጌታ ሁሉም ልጆቹ በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚገኘውን የዘላለም በረከት እንዲካፍሉ ይፍልጋል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቅዱሱ ቤቱ ለመግባት ብቁ ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለበት መመሪያ ሰጥቷል፡፡

እንዲህ ዓይነቱን የማስተማር እድል ለመጀመር ጥሩ ቦታ በቤተመቅደሱ ውጫዊ ክፍል ላይለተቀረፁት ቃላት ትኩረት መስጠት ነው ፤ “ቅድስና ለጌታ ፡ የጌታ ቤት” የዛሬው የፕሬዚዳንት አይሪንግ መልእክት እና ብዙ ሌሎች የበለጠ ቅዱሳን እንድንሆን አነሳስተውናል፡፡ እያንዳንዱ ቤተመቅደስ ቅዱስ ስፍራ ነው። እያንዳንዱ የቤተመቅደስ ተሳታፊ የበለጠ ቅዱስ ለመሆን ይጥራል፡፡

ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት ሁሉም መስፈርቶች ከግል ቅድስና ጋር ይዛመዳሉ። ያንን ዝግጁነት ለመገምገም ፤ በቤተመቅደሱ በረከቶች ለመደሰት የሚፈልግ እያንዳንዱ ሰው ሁለት ቃለ መጠይቆች ይኖረዋል። መጀምሪያ ከኢጲስ ቆጶሱ ፣ ከኢጲስ ቆጶሱ አማካሪ ፣ ወይም ከቅርንጫፍ ፐሬዝዳንት ፤ ሁለተኛ ከካስማው ፐሬዝዳንት ወይም ከሚሲዮን ፐሬዝዳንት ወይም ከእርሱ አማካሪዎች ከአንዱ ጋር፡፡ በእነዚህ ቃለ መጠይቆች ውስጥ ፤ ብዙ ጥያቄዎች ይጠየቃሉ፡፡

ከእነዚያ ጥያቄዎች መካከል አንዳንዶቹ ግልጽ እንድሆኑ በቅርብ ተስተካክለዋል፡፡ አሁን እነሱን ለእናንት መከለስ እፈልጋለሁ፡፡

  1. በዘላለም አባት እግዚአብሔር ፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ እምነት እና ምስክርነት አለህ/አለሽ?

  2. ስለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና እንደ አዳኝ እና ቤዛነት ስላለው ሚና ምስክርነት አለህ/አለሽ?

  3. ስለተመለስው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምስክርነት አለህ/አለሽ?

  4. የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዘደንትን እንደ ነብይ ፣ ባለ ራእይ እና ገላጭ እና በምድር ላይ ያሉትን ሁሉንም የክህነት ቁልፎች እንዲጠቀሙ ስልጣን የተሰጣቸው ብቸኛ ሰው እንደሆኑ ትደግፋለህ/ትደግፊያለሽ?

    የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ጉባኤ እንደ ነብያቶች ፣ ባለ ራእይዎች እና ገላጮች እንደሆኑ ትደግፋለህ/ትደግፊያለሽ ?

    ሌሎች አጠቃላይ ባለሥልጣናትን እና የአከባቢውን የቤተክርስቲያን መሪዎችን ትደግፋላችሁ?

  5. ጌታ እንዲህ ብሎአል ሁሉም ነገሮች በፊቴ “በንጽህና ይሰሩ” ፡፡ (ትምህርት እና ቃልኪዳን 42:41).

    በአስተሳሰብህ እና በባህሪህ ውስጥ ለሥነ-ምግባር ንጽህና እንዲኖርህ ትጥራለህ/ትጥሪያለሽ ?

    የንጽህናን ህግን ታከብራለህ/ታከብሪያለሽ?

  6. ለብቻህ ስትሆን እና በአደባባይ ከቤተሰብ አባላት እና ከሌሎች ጋር በምታሳየው ባህርይህ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን አስተምህሮቶች ትከተላላህ?

  7. የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን የሚቃረኑ ማንኛውንም ትምህርቶች ፣ ልምምዶች ወይም አስተምህሮቶች ትደግፋለህ ወይም ታስተዋውቃለህ?

  8. የስንበትን ቀን በቤትም ሆነ በቤተክርስቲያን ታከብራለህ ፤ ስብስባዎችን ትካፈላለህ ፤ ቅዱስ ቁርባን ተዘጋጅትህ እና በብቁንት ትወስዳለህ ፤ ህይወትህን ከወንጌል ህግጋት እና ትዕዛዛት ጋር አስማምተህ ለመኖር ትጥራለህ ?

  9. በምታደርገው ነገር ሁሉ ሐቀኛ ለመሆን ትጥራለህ?

  10. ሙሉ አስራትህን ትከፍላለህ?

  11. የጥበብ ቃልን ትረዳለህ እና ትታዘዛለህ?

  12. ለቀድሞ የትዳር አጋር ወይም ለልጆች ማንኛውም የገንዘብ ወይም ሌሎች ግዴታዎች አሉብህ?

    አዎ ከሆነ ፣ እነዚህን ግዴታዎች በዚህ ወቅት እየተወጣህ ነው ?

  13. በቤተመቅደስ ቡራኬ አስተምህሮ ላይ እንደተማርከው የቤተመቅደስ ልብስ መልበስን ጨምሮ በቤተመቅደስ ውስጥ የገባሃቸውን ቃል ኪዳኖች ትጠብቃለህ?

  14. እንደ ንስሐ አካል በመሆን በክህነት ባለስልጣናት መፈታት የሚያስፈልጋቸው ከባድ ሃጢያቶች በህይወትህ ውስጥ አሉ?

  15. ወደ ጌታ ቤት ለመግባት እና በቤተመቅደስ ስነስርዓቶች ለመሳተፍ ብቁ እንደሆክ ይሰማሃል?

ነገ ፣ እነዚህ የተከለሱ የቤተመቅደስ መግቢያጥያቄዎች በዓለም ዙሪያ ላሉት የቤተክርስቲያን መሪዎች ይሰራጫሉ።

ለእነዚህ ጥያቄዎች በሐቀኝነት ከመመለስ በተጨማሪ፣እያንዳንዱ ጎልማሳ የቤተመቅደስ ተሳታፊ ከመደበኛ ልብሱ በታች የክህነት ቅዱስ ልብሱን እንደሚለብስ ግልጽ ነው። ይህ ጌታን በይበልጥ ለመምስል በየቀኑ ለሚደረግ ጥረት ውስጣዊ ቁርጠኝነት ምሳሌ ነው። ደግሞም ለተደረጉት ቃል ኪዳኖች በየቀኑ ታማኝ እንድንሆን እና በየቀኑ ከፍ ባለና ንጹህ በሆነ መንገድ በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ እንድንመላለስ ያስታውሰናል።

አሁን፣ለአፍታ ፤ ለወጣቶቻችን መናገር እፈልጋለሁ ፡፡ ለተወሰነ የቤተመቅደስ አገልግሎት መግቢያ ፍቃድ ብቁ እንድትሆኑ እናበረታታችኃለን ፡፡ ለውክልና ጥምቀት እና ማረጋገጫ ስነስርዓት ስትዘጋጁ እናንተን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ብቻ ነው የምትጠየቁት ፡፡ በዚያ በቅዱስ ቤተመቅደስ ስራ ውስጥ ለመሳተፍ ብቁነታችሁ እና ፈቃደኛነታችሁ በጣም አመስጋኞች ነን። እናመስኛችኃለን ፡፡

ወደ ጌታ ቤት ለመግባት የግለሰብ ብቁነት ብዙ ግለሰባዊ መንፈሳዊ ዝግጅት ይጠይቃል። በጌታ እርዳታ ግን ምንም የማይቻል ነገር የለም ፡፡ በአንዳንድ መንገዶች ፤ ለቤተመቅደስ ዝግጁ የሆነን ህዝብ ከመገንባት ይልቅ ቤተመቅደስ መገንባት ቀላል ነው። እንደ ጌታ የበለጠ ለመምስል ፣ ሐቀኛ ዜጋ መሆን ፣ የተሻለ ምሳሌ ለመሆን ፣ እና ቀናተኛ ሰው ለመሆን የግለሰብ ብቃት የአእምሮ እና የልብ አጠቃላይ ለውጥ ይጠይቃል ፤

የቤተሰባችሁን ለዘላለም “በማያቋርጥ ደስታ ውስጥ “ መቀጠልን ጨምሮ እንደዚህ ዓይነቱ የዝግጅት ስራ በዚህ ህይወት ውስጥ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን በረከቶች እና ለመጪው ሕይወት ሊታሰቡ የማይችሉ በረከቶችን እንደሚያመጣ እመሰክራለሁ።1

አሁን ወደ ሌላ ርዕስ መሄድ እፈልጋለሁ - የመጪው አመት እቅዶች ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2020 የፀደይ ወቅት ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ያ የምናውቀውን (የመገለጥን) ልምድ የመጀመሪያውን ራእይ ያካበተበት ፤ በትክክል 200ኛ ዓመት ይሆናል ፡፡ እግዚአብሔር አብ እና የተወደደው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ለ14 አመቱ ወጣት ለዮሴፍ ታዩ። ይህ ክስተት የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በዳግም መመለሱን እንደ መጀመሩ ምልክት ተደርጎበታል።በትክክል በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ እንደተተነበየው።2

ከዚያ የሰማይ መልእክቶች ለተከታታይ ጉብኝቶች መጡ ፤ ሞሮኒን ፣ መጥምቁ ዮሐንስን ፣ እና የመጀመሪያዎቹን ሐዋርያት ጴጥሮስ ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስን ጨምሮ ፡፡ ሙሴን ፣ ኤልያስን እና ኤልያስን ጨምሮ ሌሎች ተከተሏቸው ፡፡ እያንዳንዳቸው በምድር ላይ ያሉትን የእግዚአብሔር ልጆች እንደገና ለመባረክ መለኮታዊ ስልጣንን አመጡ ፡፡

በተአምራዊ ሁኔታ ፤ እኛ ደግሞ መፅሐፈ ሞርሞንን ተቀበልን: - ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ተጓዳኝ መፅሐፈ፡፡ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች እና የታላቁ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ የታተሙት ራዕዮች ፡ በተጨማሪም ስለእግዚአብሄር ትእዛዛት እና ዘላለማዊ እውነት ያለንን መረዳት በጣም አበርክተውልናል።

የሐዋርያትን ፣ የሰባዎችን ፣ የፓትርያርክን ፣ የሊቀ ካህንን ፣ የሽማግሌን ፣ የኢጲስ ቆጶስን ፣ የካህንን ፣ የመምህርን እና የዲያቆንን ጨምሮ የክህነት ቁልፎች እና ክፍሎች ተመልሰዋል ፡፡ እናም ጌታን የሚወዱ ሴቶችም በድፍረት በሴቶች መረዳጃ ማህበር ፣ በህጻናት ክፍል ፣ በወጣት ሴቶች ፣ በስንበት ትምህርት እና ሙሉ ሆኖ በተመለስው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በሁሉም አስፈላጊ ክፍሎች ውስጥ ፤ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ጥሪዎች ውስጥ ያገለግላሉ ።

ስለዚህ እ.ኤ.አ. 2020 ዓመት እንደ ሁለት መቶኛው ዓመት ሆኖ ይሰየማል ፡፡ የሚቀጥለው ሚያዝያ አጠቃላይ ጉባኤ ከየትኛውም ቀደምት ጉባኤዎች የተለየ ይሆናል ፡፡ በሚቀጥሉት ስድስት ወራቶች ውስጥ ፤ እያንዳንዱ አባል እና እያንዳንዱ ቤተሰብ ለልዩ ስብሰባ እንደሚዘጋጁ ተስፋ አደርጋለሁ ይህም እንደገና የተመለሰውን ወንጌል መሰረቶች ያስታውሰናል፡፡

ዝግጅታችሁን በታላቅ ዋጋ ዕንቁ የተመዘገበውን የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ ራዕይ በማንበብ መጀመር ትችላላችሁ፡፡ ለሚቀጥለው ዓመት የኑ ፤ ተከተሎኝትምህርት ጥናታችን መጽሃፈ ሞርሞን ነው፡፡ “ከመጸሃፈ ሞርሞን ያገኘሁት እውቀት በድንገት ቢወሰድብኝ ህይወቴ እንዴት ይለወጣል?” ወይም “የመጀመሪያውን ራእይ ተከትለው የመጡት ክስተቶች ለእኔ እና ለምትወዳቸው ሰዎች ለውጥ ያመጡት እንዴት ነው?” በሚሉ እና በመሰሳሰሉ ጠቃሚ ጥያቂዎች ላይ ልታሰላስሉ ትወዱ ይሆናል፡፡ እንዲሁም፤ የመጸሃፈ ሞርሞን ቪዲዮዎች አሁን ስለሚገኙ፤ በግል እና በቤተሰብ ጥናታችሁ ላይ ልታካትቷቸው ትወዱ ይሆናል።

የራሳችሁን ጥያቄ ምረጡ። የራሳችሁን እቅድ ንደፉ። እራሳችሁን አስደናቂ ወደሆነው ዳግም በተመለሰው ብርሃን ጥመቁ። ይህን ስታደርጉ፤ የሚመጣው ሚያዚያ አጠቃላይ ጉባኤ የሚታወስ ብቻ ሳይሆን፤ የማይረሳ ይሆናል።

አሁን እንደ ማጠቃለያ፤ ፍቅሬን እና በረከቴን እተውላችኋለው፤ እያንዳንዳችሁ በያንዳንዷ ቀናት ሁሉ ይበልጥ ደስተኛ እና ቅዱስ እንድትሆኑ። እስከዚያ ድረስ፤ በጌታ መሪት “የእግዚአብሔር እቅድ እስከሚከናወን፣ እና ታላቁ ያህዌ ስራው ተፈፅሟል እስከሚል”3ድረስ ራዕይ በቤተክርስቲያን እንደሚቀጥል እባካችሁ እርግጠኛ ሆኑ።

እንዲህም እባርካችኋለሁ፤ ለእናንተ ያለኝን ፍቅር በድጋሚ እያረጋገጥኩ ምስክርነቴ እግዚአብሔር ህያው ነው! ኢየሱስ ክርስቶስ ነው! ይህች የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት እና እኛም ህዝቡ ነን።” በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።