2010–2019 (እ.አ.አ)
የተሸለ ማድረግና የተሸለ መሆን እንችላለን፡፡
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


የተሸለ ማድረግና የተሸለ መሆን እንችላለን፡፡

የክህነት ስልጣናችሁን ከእስካሁኑ በተሻለ ሁኔታ በላቀ ሃይል መጠቀም እንድትችሉ ትኩረታችሁን የህይወታችሁ ዋና በሆነው የቀን ተቀን ንስሃ ላይ አድርጉ፡፡

ውድ ወንድሞቼ፣ ይህንን እጅግ ብዙ የጌታ ክህነት ተሸካሚዎች ጉባኤ የሻለቃ ጦር መመልከት የሚያበረታታ ነው፡፡ ምን አይነት ለበጎ ታላቅ ኃይል ናችሁ ! አንወዳችሗለን። እንጸልይላችሗለን። ስለናንተ እጅግ አመስጋኝ ነን፡፡

በቅርቡ ለነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ወደተሰጠ የጌታ መመሪያ ተስቤ ራሴን አግኝቼዋለሁ— “ለዚህ ትውልድ ከንስሃ በስተቀር ምንም አትበል “1 ይህ አዋጅ በቅዱሳን መጻፍት ውስጥ ብዝሁን ጊዜ ተደጋግማል።2 ሁሉም ሰው ለምን ንስሀ መግባት ያስፈልገዋል?ይህ ግልፅ የሆነን ጥያቄ ያነሳል። መልሱ አዎን ነው።

እጅግ ብዙ ሰዎች ንስሃን እንደ ቅጣት ይመለከቱታል— በጣም አስከፊ ካልሆነ በቀር ሊርቁት እንደሚገባ ነገር፡፡ ነገር ግን ይህ ቅጣት ያስከትላል የሚለው ሰይጣን የሚያነሳሳው ስሜት ነው፡፡፡፡ ለያድነን፣ይቅር ሊለን፣ሊያጸዳን፣ሊያነጻን እና ሊቀድሰን እየፈለገ እና ተስፋ እያደረገ እጆቹን ከፍቶ ወደቆመው ወደ ኢየሱስ ክርስቶሰ እንዳንመለከት ሊገድበን ይሞክራል፡፡3 4

ንስሃየሚለው ቃል በግሪክ አዲስ ኪዳን መጻህፍት ሜየታኖዮነው፡፡ ሜታየሚለው ቅድመ ቅጥያ “ለውጥ“ ማለት ነው፡፡ ኖዮ “ሃሳብ “፣“እውቀት“፣“መንፈስ“ እና “እስትንፋስ“ ከሚሉ የግሪክ ቃላት ጋር የተዛመደ ነው፡፡5

ስለሆነም፣ኢየሱስ ክርስቶስ እኔንና እናንተን “ንስሃ“ እንድንገባ ሲጠይቀን ፣”6 ሃሳባችንን ፣ እውቀታችንን ፣ መንፈሳችንን —የምንተነፍስበትን መንገድም እንኳ እንድንቀይር እየጋበዘን ነው፡፡ የምናፈቅርበትን ፣ ጊዜያችንን የምናሳልፍበትን ፣ ሚስቶቻችንን የምንንከባከብበትን ፣ ልጆቻችንን የምናሳድግበትን እና የራሳችንን አካላት እንኳንየምንንከባከብበትን መንገድ እንድንቀይር እየጠየቀን ነው፡፡

ከዘወትር እና በየቀኑ ንስሃ ላይ ትኩረት ከማድረግ ይበልጥ ነጻ የሚያወጣ፣ይበልጥ ከፍ ወዳለ ክብር የሚያደርስ እና በግለሰብ ደረጃ ለምናደርገው እድገት ጠቃሚ የሆነ ነገር የለም፡፡ ንስሃ አንድ ጊዜ የሚደረግ ኩነት ሳይሆን ሂደት ነው፡፡። ለደስታ እና ለአእምሮ ሰላም ዋናው ቁልፍ ነው፡፡ ከእምነት ጋር ሲጣመር ንስሃ የእየሱስ ክርስቶስን የሃጥያት ክፍያ ሃይል እንድናገኝ በሩን ይከፍትልናል፡፡7

በቃልኪዳን መንገድ በብርታት እየተጓዛችሁ ያላችሁም ቢሆን፤ አዳልጧችሁ ወይም ከመንገዱ ወጥታችሁም ቢሆንወይም የቃልኪዳኑን መንገድ ጭራሹን ማየት ያልቻላችሁ ቢሆን ንስሃ እንድትገቡ እማጸናችኋለሁ፡፡ በየቀኑ የሚደረግ ንስሃ ያለውን የማበርታት ሃይል ተለማመዱ—በየቀኑ ትንሽ ሻል ያለ ነገር የማድረግን እና የመሆንን፡፡

ንስሃ ለመግባት ስንመርጥ መለወጥን እንመርጣለን! አዳኛችን ልንሆን ወደምንችለው ምርጥ እኛነታችን እንዲለውጠን እንፈቅድለታለን፡፡ በመንፈስ ለማደግ እና ደስታን ለመቀበል እንመርጣለን—በእርሱ ነጻ የመውጣት ደስታ፡፡8 ንስሃ ለመግባት በምንመርጥበት ጊዜ ይበልጥ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆንን እንመርጣለን!9

ወንድሞች የተሸለ ማድረግ እና መሆን አለብን ምክንያቱም በውጊያ ውስጥ ነን፡፡ ከሃጥያት ጋር የሚደረገው ትግል እውን ነው፡፡ ጠላት ምስክርነቶችን ለማጥፋት እና የጌታን ስራ ለማስተጓጎል ጥረቶቹን በአራት እጥፍ እያሳደገ ነው፡፡ የጌታን ደስታ እና ፍቅር ከመቋደስ ለመከልከል ተከታዮቹን አቅም ባላቸው መሳሪያዎች እያስታጠቀ ነው፡፡10

ንስሃ ጠላት የሚያስቀምጠውን የመከራ ወጥመድ ለማስወገድ ቁልፍ ነው፡፡ በዚህ የዘላለማዊ እድገታችን ነጥብ ላይ ሳለን ጌታ ከእኛ ፍፁምናን አይጠብቅም፡፡ ነገር ግን ከፍ ባለ ንፅህና እንድንመላለስ ይጠብቅብናል፡፡ በየቀኑ የሚደረግ ንስሃ የንጽህና መንገድ ነው ንጽህናም ሃይልን ያስገኛል፡፡ ግላዊ ንጽህና በእግዚያብሄር እጅ ሃይለኛ መሳርያ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ንስሃችን—ንጽህናችን—የእስራኤልን መሰብሰብ እንድንረዳ አቅም ያላብሰናል፡፡

“የክህነት መብቶች እና የሰማይ ኃይላት የማይነጣጠሉ ናቸው፣ እና የሰማይ ኃይላት በፅድቅ መሰረታዊ መርሆች የሚካሄድ ካልሆነ በስተቀር ሊቆጣጠሯቸው እና ሊጠቀሙባቸውም ዘንድ አይቻልም።“ ሲል ጌታ ጆሴፍ ስሚዝን አስተምሮታል፡፡11

የሰማይን ኃይልን ለማግኘት ታላቅ መንገድ የሚሰጠን ምን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ እድገታችንን ምን እንደ ሚገታው እናውቃለን—የሰማይን ሃይልን ይበልጥ ለማግኘት ማድረግ ማቆም ያለብንን፡፡ ወንድሞች ፣ንስሃ እንዳትገቡ መንገዱን የዘጋባችሁ ምን እንደሆነ ለመረዳት በጸሎት መንፈስ ጠይቁ፡፡ ንስሃ ከመግባት ምን እንደሚገታችሁለዩ፡፡ እናም ከዚያም ተለወጡ! ንስሀ ግቡ! እስከዛሬ ካደረግነው እና ከሆንነው በላይ ሁላችንም የተሸለ ማድረግና የተሸለ መሆን እንችላለን፡፡12

ልንሻሻል የምንችልባቸው ልዩ መንገዶች አሉ፡፡ ሰውነታችንን የምንንከባከብበት መንገድ አንዱ ነው፡፡ የሰው አካላት ተአምር በአድናቆት ያፈዘኛል፡፡ አስደናቂ ፈጠራ ነው፤ቀስ በቀስ ወደመጨረሻው መለኮታዊ አቅማችን ለመድረስ ለምናደርገው የከፍታ ጉዞ አስፈላጊ ነው ፡፡ ያለ እርሱ ማደግ አይቻለንም፡፡፤ የአካል ስጦታ በመስጠት እግዚአብሔር ይበልጥ እንደ እሱ እንድንሆን ወሳኝ እርምጃ እንድንወስድ ፈቅዶልናል፡፡

ሰይጣን ይህንን ያውቃል፡፡ የቅድሞ ህይወቱ ክህደት እውነታ ለዚህ ስጦታ በዘላቂነት ሙሉ በሙሉ እንዳያሟላ ስለሚያደርገው ያበሳጨዋል፡፡ይህም በቋሚ የምቀኝነት እና የቁጣ ስሜት ውስጥ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ባይሆኑም፤ ብዙዎቹ፤ በመንገዳችን የሚያስቀምጣቸው ፈተናዎች የራሳችንን ወይም የሌሎች ሰዎችን አካላት እንድንጎዳ ምክንያት ሊሆኑብን ይችላ.ል፡፡ ሰይጣን አካል አልባ በመሆኑ ምክንያት ደስተኛ ስላልሆነ እኛም በአካላችንምክንያት ደስተኞች እንዳንሆን ይፈልጋል፡፡ 13

አካላችሁ የዘላለማዊ መንፈሳችሁ ማደሪያ የግል ቤተመቅደሳችሁ ነው፡፡14 ቤተመቅደሱን መንከባከባችሁ አስፈላጊ ነው፡፡ ወንድሞች እጠይቃችኋለሁ፡ እግዚያብሄርን ከማስደሰት ይልቅ በሰውነታችሁ አልባሳት እና ንጽህና በአለም ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ነው ይበልጥ ፍላጎታችሁ? የምትመልሱት መልስ እርሱ ለናንተ ስለሰጣችሁ ድንቅ ስጦታ ያሏችሁ ስሜቶች ቀጥተኛ መልእክት ይልክለታል ፡፡ ለአካላታችን በምንሰጠው በዚህ ክብር ፤ ወንድሞች፤ የተሻለ የምናደርግና የተሻለ የምንሆን ይመስለኛል፡፡

የተሻለ የምናደርግበትና የተሻለ የምንሆንበት ሌላው መንገድ በህይወታችን ውስጥ ከሚስቶቻችን እና ከሴት ልጆቻችን ፣ከእናቶቻችን እና ከእህቶቻችን ጀምረን ሴቶችን የምናከብርበት መንገድ ነው፡፡ 15

ከወራት በፊት ከአንዲት ውድ እህት ልብ የሚሰብር ደብዳቤ ደረሰኝ፡፡ እንዲህ ስትል ጻፈችልኝ “[ሴት ልጆቼ እና እኔ] የባሎቻችንን እና የወንድ ልጆቻችንን ያልተከፋፈለ ትኩረት ለማግኘት ማለቂያ የሌለው ውድድር ውስጥ እንዳለን ይሰማናል ከ24/7ሁሉም ሰው ሰአት ትኩስ የስፖርት መረጃ ዘገባ ፣ ከሰቶክ ገበያ ትኩስ መረጃ እና ማባሪያ ከሌለው ትንተና እና እያንዳንዱን ፕሮፌሽናል የስፖርት ጨዋታዎች ከመመልከት ጋር፡፡ [ከስፖርት እና ከጨዋታዎች] ጋር ባላቸው የቀን ተቀን የጠበቀ ቁርኝት ምክንያት ከባሎቻችን እና ከወንድ ልጆቻችን ጋር ያለንን ጥብቅ ግንኙነት እያጣነው ይመስላል፡፡16

ወንድሞች፣ እንደ ክህነት ስልጣን ተሸካሚ የመጀመሪያው እና ዋነኛው ሀላፊነታችሁ ሚስቶቻችሁን ማፍቀር እና መንከባከብ ነው፡፡ ከእርሷ ጋር አንድ ሁን፡፡ ባልደረባዋ ሁን፡፡ የአንተ ለመሆን መፈለግን ቀላል አድርግላት፡፡ ከእርስዋ ጋር ዘላለማዊ ጥምረትን ከመገንባት የበለጠ በህይወትህ ምንም ሌላ ፍላጎት ቅድሚያ ማግኘት የለበትም፡፡ ምንም የቴሌቪዥን ፕሮግራም ፣ ስልክ ወይም ኮምፒተር ከእርሷ ደህንነት በላይ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ጊዜያችሁን እንዴት እንደምታሳልፉ እና ጉልበታችሁን የት እንደምታፈሱት ጥናት አድርጉ፡፡ ያ ልባችሁ የት እንደሆነ ይነግራችኋል፡፡ ልባችሁ ከሚስታችሁ ልብ ጋር እንዲጣጣም ጸልዩ፡፡ ደስታን እንድታመጣላት ፈልግ፡፡ ምክሯን ጠይቅ እናም አዳምጥ፡፡ የእርሷ ግብአት የአንተን ውጤት ያሻሽለዋል፡፡

በቅርባችሁ የሚገኙ ሴቶችን አሳዝናችሁ ንስሃ የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ አሁኑኑ ጀምሩ፡፡ በተጨማሪም አስታውሱ ሴቶች የጌታን የንጽህና ህግ ከመኖር የሚገኘውን በረከት እንዲቀበሉ መርዳት የናንተ ሃላፊነት ነው፡፡ አንዲት ሴት የቤተመቅደስ በረከቶቿን መቀበል የማትችልበት ምክንያት እንዳትሆኑ፡፡

ወንድሞች፣ሁላችንም ንስሃ መግባት ያስፈልገናል፡፡ ከሶፋው ላይ መነሳት፣ሪሞቱን ማስቀመጥ እና ከመንፈሳዊ እንቅልፋችን መንቃት ያስፈልገናል፡፡ በምድር እጅግ አስፈላጊ በሆነው ስራ ውስጥ መሳተፍ እንድንችል የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ትጥቅ የመልበሻ ሰዓት አሁን ነው ፡፡ “በማጭዶቻችሁ ለማጨድ፣ እናም በሙሉ ኃይላችሁ፣ አዕምሮአችሁ፣ እናም ጉልበታችሁ ለመሰብሰብ“ ሰአቱ አሁን ነው፡፡17 የክፋት ሃይሎች ከዛሬ በበለጠ በብዙ ሃይል ተቆጥተው አያውቁም፡፡ እንደ ጌታ አገልጋዮች ፣ይህ ውጊያ እየተፋፋመ መተኛት አንችልም፡፡

ቤተሰባችሁ የናንተን አመራር እና ፍቅር ይፈልጋል፡፡ የሽማግሌዎች ሸንጓ እና በዋርዳችሁ ወይም በቅርንጫፋችሁ ያሉ የናንተን ጥንካሬ ይፈልጋሉ፡፡ እናም የሚያገኟችሁ ሁሉ እውነተኛ የጌታ ደቀመዝሙር ምን እንደሚመስል እና እንዴት እንደሚሰራ ማወቅ አለባቸው፡፡

ውድ ወንድሞቼ፣ከዚህ ስጋዊ ህይወት በፊት በነበራችሁ መንፈሳዊ ጥንካሬ ምክንያት በዚህ አስፈላጊ ሰዓት ወደ ምድር እንድትመጡ በአባታችን ተመርጣችኋል፡፡ እናንተ እስከዛሬ ወደ ምድር ከመጡት እጅግ ደፋር፣ እጅግ ምርጥ ከተባሉት ውስጥ ናችሁ ፡፡ ሰይጣን ከዚህ ስጋዊ ህይወት በፊት ማን እንደነበራችሁ ያውቃል እንዲሁም አዳኛችን ከመመለሱ በፊት መስራት የሚገባውን ስራ ያውቃል፡፡ እናም ከሺህ አመታት የማጭበርበር ልምምድ በኋላ ጠላት ባለብዙ ልምድ እና የማይታረም ነው፡፡

ምስጋና ይግባው፤ የተሸከምነው የክህነት ከጠላት ማጭበርበሪያዎች እጅግ ጠንካራ ነው፡፡ ጌታ የሚፈልገውን ወንዶች እና ወጣት ወንዶች እንድትሆኑ እማጸናችኋለሁ፡፡። የክህነት ስልጣናችሁን ከእስካሁኑ በተሻለ ሁኔታ በላቀ ሃይል መጠቀም እንድትችሉ ትኩረታችሁን የህይወታችሁ ዋና በሆነው የቀን ተቀን ንስሃ ላይ አድርጉ፡፡ ይህ ራሳችሁን እና ቤተሰባችሁን ከመጪው አስቸጋሪ ጊዜ በመንፈስ የምትጠብቁበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡

ጌታ የራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ የሌሎችን ደህንነት ከራሳቸው በፊት የሚያስቀድሙ ሰዎችን ይፈልጋል፡፡ የመንፈስን ድምጽ በግልጽ ለመስማት ሆነ ብለው የሚሰሩ ሰዎችን ይፈልጋል፡፡ ቃልኪዳናቸውን በሃቀኝነት የሚጠብቁ የቃልኪዳን ሰዎችን ይፈልጋል፡፡ ጾታዊ ንጽህናቸውን ለመጠበቅ ቁርጠኛ የሆኑ ሰዎችን ይፈልጋል—በንጹህ ልብ ፣በንጹህ አእምሮ፣እና በፈቃደኛ እጆች በረከትን ለመስጠት በቅጽበት ማስታወቂያ ሊጠሩ የሚችሉ ብቁ ሰዎች ይፈልጋል፡፡ ጌታ ንስሃ ለመግባት ጉጉ የሆኑ ወንዶችን ይፈልጋል—ለማገልገል ቅንነት ያላቸው እና ብቁ የክህነት ተሸካሚ የጌታ ሻለቃ ጦር አካል የሚሆኑ፡፡

እነዚህን ወንዶች እድትሆኑ እባርካችኋለሁ።። በየቀኑ ንስሃ ለመግባት ድፍረት እንድታገኙ እና ሙሉ የክህነት ስልጣንን እንዴት እንደምትጠቀሙ እንድትማሩ እባርካችኋለሁ፡፡ የአዳኛችንን ፍቅር ለሚስቶቻችሁ እና ለልጆቻችሁ እንዲሁም ለሚያውቋችሁ ሁሉ ትሰጡ ዘንድ እባርካችኋለሁ፡፡ የተሻለ እንድታደርጉ እና የተሻለ እንድትሆኑ እባርካችኋለሁ፡፡ ደግሞም እባርካችኋለሁ ይህንን ጥረት ስታደርጉ በህይወታችሁ ተአምራት ታያላችሁ፡፡

በሁሉን ቻይ በእግዚአብሔር ስራ ተጠምደናል፡፡። ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው። እኛ የእነርሱ አገልጋዮች ነን። ስለዚህ እመሰክራለሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።