2010–2019 (እ.አ.አ)
ምሳሌያዊ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆን
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


ምሳሌያዊ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆን

የጌታን ቃል እንድትመገቡ እና የእርሱን ትምህርቶች በግል ሕይወታችሁ ውስጥ ተግባራዊ ተደርጉት ዘንድ ፍቅሬን እና በረከቴን እሰጣችኋለሁ።

ይህ የሚያነሳሳ ታሪካዊ ጉባኤ ነበር። የወደፊቱን በጉጉት እንጠብቃለን። የተሻለ እንድናደርግ እና የተሻለ እንድንሆን ትነሳስተናል። በአጠቃላይ ባለስልጣኖች እና በአጠቃላይ ሀላፊዎች ከዚህ መስበኪያ የተሰጡት አስደናቂ መልእክቶች እና መዝሙሮች ልብ የሚማርኩ ናቸው። በዚህ ሳምንት ጀምሮ እነዚህን መልእክቶች እንድታጠኑ አበረታታችኋለሁ።1 እነዚህ ዛሬ ጌታ ለህዝቡ ያለውን ሀሳብ እና ፍላጎት ይገልጻሉ።

እያንዳንዱ ቤተሰብ በጥንቃቄ በመከተል ቤተሰቦቻቸውን ወደ እምነት መቅደስ ይለውጡት ዘንድ አዲሱ በቤት-መሰረት የሆነው በቤተክርስቲያኗ የሚደገፈው ትምህርት የቤተሰቦች ሀይልን ለመፍታት ችሎታ አለው። ቤታችሁን እንደ ወንጌል መማሪያ ክፍል ለመለወጥ በትጋት ስትሰሩ፣ ከጊዜ በኋላ የሰንበት ቀኖቻችሁ ደስተኖች ይሆናሉ። ልጆቻችሁ የአዳኝን ትምህርት ለመማር እና ለመኖር ይደሰታሉ፣ እናም ጠላት በህይወታችሁ እና በቤታችሁ ውስጥ ያለው ተፅዕኖ ይቀንሳል። በቤተሰባችሁ ውስጥ ያለው ለውጥ ታላቅ እና የሚቀጥል ይሆናል።

በዚህ ጉባኤ ቤተክርስቲያኑን በምንጠራበት በእያንዳንዱ ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማክበር አስፈላጊ የሆነውን ጥረት ለማከናወን ያለን ውሳኔ ተጠናክሯል። የአዳኙን ቤተክርስትያንና አባላቶቿን በትክክለኛ ስም ለመጠቀም ጠንቃቃ ትኩረት ማድረጋችን ለቤተክርስትያኑ አባላት ታላቅ የመንፈሳዊ ሀይልን የሚያገኙበት ተጨማሪ እምነት እንደሚመራችሁ ቃል እገባላችኋለሁ።

አሁን ወደ ቤተመቅደስ ርዕስ እንዙር። በቤተመቅደስ ውስጥ የምናሳልፋቸው ጊዜዎች ለእኛና ለቤተሰቦቻችን ደህንነት እና ከፍ ለመደረግ አስፈላጊ እንደሆኑ እናውቃለን ።።

የራሳችንን የቤተመቅደስ ስነስርዓቶች ከተቀበልን እና ከእግዚአብሔር ጋር ቅዱስ ቃል ኪዳኖች ከገባን በኋላ፣ በጌታ ቤት ብቻ ልገኝ የሚቻለውን ቀጣይ መንፈሳዊ ጥንካሬ እና ጥናት እያንዳንዳችን ያስፈልጉናል። እናም ቅድመ አያቶቻችን ለእነርሱ ተተኪ ሆነን እንድናገለግል ይፈልጉናል።

የአለም መሰረት ከመፈጠሩ በፊት፣ የወንጌልን እውቀት ሳያውቁት ለሞቱ ሰዎች የቤተመቅደስ በረከቶችን ለመስጠት መንገድ የዘጋጀውን የእግዚአብሔር ምሕረት እና ቅንነት አስቡ። እነዚህ ቅዱስ የቤተመቅደስ ስርዓቶች የጥንት ናቸው። ለእኔ ይህ ጥንታዊነት አስደሳች እናም የእነዚህ እውነተኛነት ማስረጃ ነው።2

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ የጠላት ጥቃቶች፣ በትልቅነት እና በልዩነት፣ በብዙ እጥፍ እያደጉ ናቸው።3 በቤተመቅደስ ውስጥ በየጊዜው ለመገኘት ያለን ፍላጎት ከዚህ በፊት ከነበረው በላይ ታላቅ ነው። ጊዜአችሁን እንዴት እንድምታሳልፉበት በጸሎት እንድትመለከቱት እለምናችኋለሁ። ለወደፊታችሁ እናም ለቤተሰቦቻችሁ ጊዜ ስጡ። ወደ ቤተመቅደስ ለመድረስ የምትችሉ ከሆናችሁ፣ በእርሱ ቤት ለመገኘት፣ ከጌታ ጋር ዘወትር ቀጠሮ እንድትዙ፣ ከዚያም ይህን ቀጠሮ በትክክል እና በደስታ እድትጠብቁ አበረታታችኋለሁ። በቤተመቅደሶቹ ውስጥ ለማገልገል እና ለማምለክ መስዋዕቶች ስታደርጉ፣ ጌታ እናንተ እንደሚያስፈልጋችሁ የሚያውቀውን ታዕምራት እንደሚያመጣ ቃል እገባላችኋለሁ።

አሁን ወቅት የተቀደሱ 159 ቤተመቅደሶች አሉን። እነዚያ ቤተመቅደሶችን በትክክል መንከባከብ ለኣ በጣም አስፈላጊ ነው። ጊዜ ሲያልፍም፣ ቤተመቅደሶች መታደስ እና መጸዳት ያስፈልጋቸዋል። በዚህም ምክንያት፣ የሶልት ሌክ ቤተመቅደስን እና ሌሎች በፈር ቀዳጆች የተሰሩ ቤተመቅደሶችን ለማሻሻል እና ለማደስ እቅዶ እየተሰሩ ናቸው። ስለእነዚህ የስራ እቅዶች ዝርዝር በሚመሰረቱበት ጊዜ እንካፈላቸዋለን።

ዛሬ ስለሚገነቡ 12 ተጨማሪ ቤተመቅደሶች ማሳወቃችን ደስ ይለናል። እነዚያ ቤተመቅደሶች በሚቀጥሉት ቦታዎች ይገነባሉ፥ መንዶዛ፣ አርጀንቲና፤ ሳልቫዶር፣ ብራዚል፤ ዩባ ስቲ፣ ካሊፎርኒያ፤ ፈኖም ፔን፣ ካምቦዲያ፤ ፕሬያ፣ ኬፕ ቬርዴ፤ ዪጎ፣ ጉዋም፤ ፑዌብሎ፣ ሜክሲኮ፤ አክላንድ፣ ኒው ዚላንድ፤ ሌጎስ፣ ናይጄሪያ፤ ዳቮ፣ ፊሊፒንስ፤ ሳን ሁዋን፣ ፖርቶ ሪኮ፤ እና ዋሽንግተን አውራጃ፣ ዩታ።

ቤተመቅደሶች መገንባት እና መንከባከብ ህይወታችሁን ላይቀይር ይችላል ፣ ነገር ግን በቤተመቅደስ ውስጥ የምታሳልፉት ጊዜ ግን በእርግጥም ለውጥ ይኖረዋል። ከቤተመቅደስ ለረዥም ጊዜ ለቀሩት፣ በተቻለ መጠን ቶሎ ብለው እንዲዘጋጁ እና እንድመለሱ አበረታታችኋለሁ። እናም ይህን ቅዱስ እና እድሜ የለሽ ስራን እንደሚመራ የራሳችሁ ምስክርነትን ታገኙ ዘንድ፣4 በቤተመቅደስ ውስጥ እንድታመልኩ እና አዳኙን ስለእናንተ ያለውን የማያልቅ ፍቅር በጥልቅ እንዲሰማችሁ እንድትፀልዩ እጋብዛችኋለሁ።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ለእምነታችሁ እና ለድጋፌአችሁ አመሰግናችኋለው። የጌታን ቃል እንድትመገቡ እና የእርሱን ትምህርቶች በግል ሕይወታችሁ ውስጥ ተግባራዊ ተደርጉት ዘንድ ፍቅሬን እና በረከቴን እሰጣችኋለሁ። ራዕይ በቤተክርስቲያኗ እንደሚቀጥል እና “የእግዚአብሔር እቅድ እስከሚከናወን፣ እና ታላቁ ያህዌ ስራው ተፈፅሟል እስከሚል”5 ድረስ እንደሚቀጥል አረጋግጥላችኋለሁ።

በህይወትዎ ውስጥ ያጋጠሙዎትን የግል ተግዳሮቶች ለመቋቋም እምነት እና መፅናኛ እያላችሁ፣ በእርሱ እና በቅዱስ ስራው በሚኖራችሁ በሚያድግ እምነት እባርካችኋለሁ። ምሳሌአዊ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን እድትሆኑም እባርካችኋለሁ። እንዲህም እባርካችኋለሁ እናም እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ ምስክሬን እሰጣችኋለሁ! ኢየሱስ ክርስቶስ ነው! ይህች የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት። እኛም የእርሱ ህዝብ ነን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜል።

ማስታወሻዎች

  1. የአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶችን በኢንተርኔት LDS.org and on the Gospel Library app ይመልከቱ። ይህም በ Ensign እና Liahona ይታተማሉ። በፖስታ የሚደርሱት ወይም በኢንተርኔት ሊወርዱ የሚችሉት የቤተክርስቲያኗ መፅሔቶች፣ እንዲሁም New Era እና Friend፣ በቤት-መሰረት የወንጌል ትምህርታችሁ ውስጥ አስፈላጊ ክፍል ያላቸው ናቸው።

  2. ለምሳሌ፣ ዘጸአት 2829ዘሌዋውያን 8 ይመልከቱ።

  3. ሞዛያ 4፥29 ይመልከቱ።

  4. See Wilford Woodruff, “The Law of Adoption,” discourse delivered at the general conference of the Church, Apr. 8, 1894. ፕሬዘደንት ውድረፍ እንዳሉት፥ “ራዕዮችን ገና አልፈጸምንም። የእግዚአብሔርን ስራ ገና አልፈጸምንም። … ፍጹም እስከሚሆን ድረስ ለዚህ ስራ ምንም መጨረሻ የለም” (Deseret Evening News, Apr. 14, 1894, 9)።

  5. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (2007), 142.