2010–2019 (እ.አ.አ)
የማስታረቅ አገልግሎት
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


የማስታረቅ አገልግሎት

በአለም አዳኝ በተሰጠኝ ሐዋርያዊ ስልጣን፣ ለመፈለግ የዋሆች እና ደፈሮች ከሆናችሁ ከእግዚኣብሄር እና እርስ በርስ ጋር በመታረቅ የሚመጣውን የነፍስ መረጋጋት እመሰክራለሁ።

ባለፈው ሚያዝያ፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን የአገልግሎትን ጽንሰ-ሀሳብ በሚሰጡበት ጊዜ፣ እግዚአብሔርን የመውደድ እና እርስ በእርስ የመዋደድን ታላላቅ ትእዛዛት የሚጠበቅበት እንደ አንድ መንገድ እንደሆነ አረጋግጠዋል።1 እኛ፣ እንደ ቤተክርስቲያኗ ባለስልጣናት፣ ያን በሚመለከት በጀመራችሁት ታላቅ መልስ እናጨበጭብላችኋለን እናም መልካም ስራ እንላችኋለን። በዚህ አስደናቂ ጥረት ውድ ነቢያችንን በመከተላችሁም እናመሰግናችኋለን እናም ለተጨማሪ ብዙ መመሪያዎች እንዳትጠብቁም ሀሳብ እናቀርብላችኋለን። ወደ ገንዳው ውስጥ ዝለሉ እናም ዋኙ። እርዳታ ወደሚፈልጉትም ሂዱ። በጀርባችሁ ወይም በደረታችሁ መዋኘት እንደለባችሁ በማሰብ አትባዝኑ። የተማርነውን መሠረታዊ መርሆችን ከተከተልን፣ ከክህነት ቁልፎች ጋር ከስተካከልን እናም እና መንፈስ ቅዱስ እንዲመራን ከፈለግን፣ ልንወድቅ አንችልም።

በዚህ ጠዋት፣ ሥራ መደብ የሌለው፣ የተቀናጀ ቃለ መጠይቅ የማያካትት፣ እናም ከሰማይ በስተቀር ምንም ሪፖርት ማድረጊያ መስመር የሌለው የግል የአገልግሎት ገፅታን በበለጠ መናገር እፈልጋለሁ። እንደዚያ አይነት አገልግሎት አንድ ቀላል ምሳሌ ላከፍላችሁ።

ግራንት ሞሬል ቦወን ታታሪ ሠራተኛ፣ ታማኝ ባለትዳር እና አባት ነበር፣ እንደ አብዛኞቹ ገቢያቸውን በእርሻ የደረጉ ነዋሪዎች የአካባቢው ድንች ምርት ድካማ በሆነበት ጊዜ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል አጋጥሞት ነበር። እሱና ባለቤቱ ኖርማ ሌላ ሥራ መስራት ጀመሩ፣ በመጨረሻም ወደ ሌላ ከተማ ተዛወሩ፣ እናም ወደ ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ወደላይ መጓዝ ጀምረው ነበር። ይሁን እንጂ፣ በጣም አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ፣ በቤተመቅደስ መግቢያ ቃለ መጠይቅ ወቅት፣ ኤጲስ ቆጶስ የሞሬል ሙሉ አስራት የመክፈሉን መግለጫ ትንሽ በመጠረጠሩ ወንድም ቦወን በጣም አዝኖ ነበር።

ከእነዚህ ሰዎች የትኛው ይበልጥ ትክክለኛ እውነታ እንደለው አላውቅም፣ ግን እህት ቦወን ከቃለ መጠይቁ የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ ከርድ ይዛ ስቶጣ፣ ወንድም ቦወን ለአስራ አምስት አመታት ከቤተክርስቲያኗ የሚያሪቀውን ቁጣ ይዞ ሄደ።

ስለ አስራቱ ማንም ትክክለኛ ቢሆን፣ ሞሬል እና ኤጲስ ቆጶሱ “ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ”2 የሚለውን የአዳኙን ትዕዛዝ እና “በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ”3 የሚለውን የጳውሎስን ምክር ረስተዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን አልተስማሙም፣ እና በወንድም ቦውን ቁጣ የተነሰ ለብዙ ቀናት፣ ከዚያም ሳምንታት፣ እና ከዚያ አመታት ፀሀይ ወረደች፣ “ቁጣ፣ ካልተገደበ፣ በተደጋጋሚ ከበሰጨው ይልቅ [አጥፊ] ነው”4 ተብሎ በጥንቱ ሮማውያን ጥበበኛ የሆነ አንድ ሰው የተናገረውን ነጥብ አረጋገጠ። ግን የእርቅ ተአምር ሁልጊዜ ለእኛ ይገኛል፣ እናም ለቤተሰቦቹ እና እውነት መሆኖን ለምያውቀው ቤተክርስቲያን ካለው ፍቅር የተነሳ፣ ሞሬል ቦወን ወደ ሙሉ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ ተመለሰ። ይሄ እንዴት እንደሚሆን ልንገራችሁ።

የወንድም ቦወን ወንድ ልጅ ብራድ በደቡባዊ አይዳሆ ውስጥ ታማኝ ሰባዎቹ የአካባቢ እያገለገለ ያለ መልካም ጓደኛችን ነው። በዚህ ክስተት ወቅት ብራድ የአስራ አንድ ዓመት ልጅ ነበር፣ እና ለአስራ አምስት ዓመታት የአባቱ ሃይማኖታዊ ታማኝነት እያሽቆለቆለ ሲሄድ ተመለከተ፣ ቁጣና አለመግባባት ሲዘራ ለተመራተው አስከፊው ምርት ምስክር ነበር። አንድ ነገር መደረግ ነበረበት። ስለዚህ የምስጋና ቀን በዓል እ.ኤ.አ. በ 1977 ስመጣ፣ የ26 ዓመቱ የብርገም ያንግ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ብራድ ፤ ሚስቱ፣ ቫለሪ ፤ እና ህጻኑ ሌጅ፣ ሚክ፣የተማሪ ስሪት መኪናቸውን ጭነው እና፣ ምንም እንኳን መጥፎ የአየር ሁኔታ ቢኖርም ወደ ቢልንግስ፣ ሞንታና ተጓዙ። በዌስት ዬሎስቶን አቅራቢያ በሚገኝ የበረዶ ማጠራቀሚያ ላይ የነበረው ግጭት እንኳ እነዝን ሶስት ሰዎች ለወንድም ቦውን የአገልግሎት ግንኙነት ከማድረግ አልገደባቸውም።

እንደደረሱ፣ብራድ እና እህቱ ፓም ከአባታቸው ጋር ብቻቸውን መሆን እንደምፈልጉ ጠየቁ። “አንተ ድንቅ አባት ነህ” ብራድ ስሜት ውስጥ ሆኖ ጀመረ፣ “ምን ያህል እንደምትወደን ሁሌም እናውቀለን። ነገር ግን የሆነ ችግር አለ፣ እና ለረዥም ጊዜ ቆይቷል። አንድ ጊዜ ስለተጎደክ፣ ይህ ቤተሰብ በብዙዓመታት ሲጎዳ ቆይቷል። እኛ ተሰብረናል፣ አንተ ብቻ ነህ ልትጠግነን የምትችለው። እባክህን፣ እባክህን፣ ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ፣ ከኤጲስ ቆጶስ ጋር የነበረህን መጥፎ አጋጣሚ ለመተው በልብህ ፈለገህ እንደ በፊቱ ይህንን ቤተሰብ በወንጌል ውስጥ መመራት ትችላለህ?”

በመከከላቸው ዝምታ ነገሰ። በመቀጠልም ወንድም ቦወን የአጥንቱ አጥንት እና የሥጋው ሥጋ፣5 የነበሩትን ሁለቱ ልጆቹን ወደላይ ተመለክቶ፣ በፀጥታ ተናገረ፣ “እሺ። አዎ፣ አደርገለው።”

ባልጠበቀው መልስ ተደንቆ፣ ብራድ ቦወን እና ቤተሰቦቹ አባታቸው በህይወቱ ውስጥ ነገሮችን ለማስተካከል በማታረቅ መንፈስ ወደ ጳጳሱ ስሄድ ተመለከከቱ። ለዚህ ደፈር ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ላልተጠበቀ ጉብኝት ፍፁም ምላሽ፣ ወንድም ቦውን ተመልሶ እንድመጣ በተደጋጋሚ ግብዣዎችን ስልክ የነበረው፣ በሞሬል ዙሪያ እጆቹን ዘርግቶ እቅፍ አድርጎ ያዘው—ለበጣም ረጅም ጊዜም አቀፈው።

በጥቂት ሳምንታት ብቻ፣ ብዙ ጊዜም አይወስድም፣ ወንድም ቦወን እንደገና ሙሉ በሙሉ በቤተክርስቲያኗ እንቅስቃሴ ውስጥ ሙሉ ተሳታፊ ሆነ እናም ወደ ቤተመቅደስ ለመመለስ ብቁ ሆነ። ብዙም ሳይቆይ በትግል ላይ የለውን ትንሽ የ25 አባለት ቅርንጫፍ ለመምራት ጥሪ ተቀበለ እናም ቁጥሩ ከ100 በላይ በሚሆኑ ጉባኤዎች አደገ። ይህ ሁሉ የተካሄደው ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት ነው፣ ነገር ግን አንድ ወንድ እና ሴት ልጅ ለአባታቸው ያቀረቡትን የአገልግሎት ጥሪ እና እና የአባታቸው ይቅር ለማለት እና የሌሎች ድክመቶች ቢኖርም ወደፊት ለመሄድ ፈቃደኛ የመሆነ ውጤት ወደ ቦውን ቤተሰብ አሁንም ድረስ በረከቶችን እያመጣ ነው—ለዘለአለምም ይመጣል።

ወንድሞች እና እህቶች፣ “በፍቅር አብረን እንድንኖራር”6 ኢየሱስ ጠይቆናል “በመካከላችሁ ምንም ፀብ ሳይኖር።”7 “የፀብ መንፈስ ያለበት ከእኔ አይደለም፣” በማለት ኔፋውያንን አስጠነቀቀ።8 በእርግጥም፣ በከፍተኛ ደረጃ፣ ከክርስቶስ ጋር ያለን ግንኙነት እርስ በርሳችን ባለን ግንኙነት መሰረት ይወሰናል ወይም ቢያንስ ይጎዳል።

“ወደእኔ ለመምጣት የምትፈልጉ ከሆነ፣” እሱም አለ፣ “እናም ወንድማችሁ በእናንተ ላይ አንድ ነገር እንዳለው ካስታወሳችሁ—

“ወደ ወንድማችሁም ሂዱ፣ እናም በመጀመሪያ ከወንድማችሁ ጋር ተስማሙ፤ እናም ልባችሁን በዓላማ ሞልታችሁ ወደእኔ ኑ፣ እናም እኔ እቀበላችኋለሁ።9

በእርግጥም እያንዳንዳችን አሁንም በአንድ ሰው ልብ ወይም ቤተሰብ ወይም ጎረቤት ውስጥ ያለውን ሰላም የምያበላሹ ማለቂያ የሌለው የድሮ ጠባሳዎች ስብስብ እና ሀዛኖችእና መጥፎ ትዝታዎችን መጥቀስ እንችላለን። ያንን ሕመም ያመጣነው ወይንም የተቀበልነው ብንሆን፣ ሕይወት ልክ እግዚአብሔር እንደፈቀደው የሚክስ እንድሆን እነዚህ ቁስሎች መፈወስ ይኖርባቸዋል። ልክ የልጅ ልጆቻችሁ እናንተን ወክለው በጥንቃቄ በማቀዝቀዣ እንዳስቀመጡት ምግብ፣ እነዚህ የረጁ ቅሬታዎች የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜያቸው ከለፈ ሰንብቶል። እባካችሁ በነፍሳችሁ ውስጥ ከእንግዲህ ወዲያ የከበረ ቦታ አትስጧቸው። ፕሮስፔሮ The Tempest ለተፀፃቹ አሎንሶ እንዳለው “ባለፈው ከባድ ሸክም ጊዜያትን አናስታውስ።”10

“ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ፣”11 በማለት ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ አስተማረ። እናም በእኛም ዘመን እንድ አለ፣ “እኔ ጌታ ይቅር የሚለውን እኔ እለዋለሁ፣ አንተን ግን ሁሉንም ሰው ይቅር ማለት አለባችሁ።”12 ይሁን እንጂ፣ ለአንዳንድ በጭንቀት ውስጥ ለሚኖር ሰው ተናገረውን ሳይሆን ያደረገውን መገንዘብ አስፈላጊ ነው። “በሰው እጅ ከገጠመችሁ አሳዛኝ ክስተት በተቃራኒ እውነተኛ ስቃይ ወይም እውነተኛ ሀዘን እንዲሰማችሁ አልተፈቀደላችሁም፣” ብሎ አልተናገረም። “ሙሉ በሙሉ ይቅር ለማለት መርዛማ ግንኙነት መፍጠር ወይም ወደ አስነዋሪ እና አጥፊ ሁኔታ መመለስ አለበችሁ” አላለም። ምንም እንኳን የሚመጡብን በጣም አስከፊ የሆኑ የወንጀል ድርጊቶች ቢኖሩም እንኳን፣ ከስቃያችን በላይ ከፍ ልንል የምንችለው በእውነተኛው ፈውስ መንገድ ላይ እግሮቻችንን ስናስቀምጥ ብቻ ነው። ያም ለእያንዳንዳችንን “ኑ ተከተሉኝ”13 ብሎ በሚጠራንን በናዝሬቱ ኢየሱስ የተራመረበት የይቅርታ መንገድ ነው።

የእርሱ ደቀ መዝሙር እንዲሆኑ እና እርሱ የደረገውን የቻልነውን ለማድረግ በቀረበው ግብዣ፣ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች እንደገለፀው “በማስታረቅ አገልግሎት“ “ለክርስቶስ አምባሳደሮች” እንድንሆን ኢየሱስ የእርሱ ፀጋ መሳሪያ እንድንሆን እየጠየቀን ነው።14 የቁስሎች ሁሉ ፈዋሽ፣ በደልን ሁሉ የሚያስተካክል፣ በአለም ውስጥ በሌላ መንገድ በማይገኘው አስቸጋሪ በሆነው በማስታረቅ ተግባር ውስጥ ከእሱ ጋር አብረን እንድንሰራ ይጠይቀናል።

ስለዚህ፣ ፊሊፕስ ብሩክስ እንደጻፈው፥ “አንድ ቀን እናስወግደለን በማለት፣ አሰቃቂ አለመግባባቶች ከአመት ወደ አመት እንዲሻገሩ የምትፈቅዱ ፥ ኩራታችሁን መስዋእት ለማድረግ እና ለማረጋጋት አሁን ቀኑ መሆኑን አእምሮአችሁን ማሳመን በለመቻላችሁ ምክንያት መጥፎ ክርክርን በህይወት እያቆያችሁ የላችሁ ፥ በማይረባ ጥፋታቸው ምክንያት … ፣ በመንገድ ላይ ስትሄዱ በብስጭት ሰዎችን የምታልፉ፥ አንድ ቀን እሰጣለው … በማለት፣ ለአድናቆት ወይም ለደግነት ቃል በአንድ ሰው የልብ ውስጥ ሕመም የምትፈቅዱ፣ … ወዲያ በፍጥነት ሂዱ እናም ልታደርጎቸው ሌላ አጋጣሚ ፈፅሞ ሊገኝ የማይቻለውን ነገር አድርጉ።”15

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የድሮ ወይም አደድስ፣ጥፋቶችን ይቅር ማለት እና መተው፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ታላቅነት ማዕከላዊ መሆኑን እመሰክራለሁ። እንዲህ ዓይነቱ መንፈሳዊ ጥገና ሊመጣ የሚችለው “በክንፎቹ ፈወስ”16 እኛን ለመርዳት በሚፈጥነው መለኮታዊ መድኃኒታችን ብቻ መሆኑን እመሰክራለሁ። እናመሰግናዋለን፣ እሱን የላከውን የሰማይ አባታችንንም እናመሰግናለን፣ ያንን ማደስ እና ዳግም መወለድ፣ ከድሮው ሀዘኖች እና ያለፉት ስህተቶች ወደፊት ነፃ መሆን፣ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ብቻ ሰይሆኑ፣ ግን ቀድሞውኑ የተገዙ እና በጣም ውድ የሆነ ዋጋ በፈሰሰው በበጉ ደም ተከፍሏል።

በአለም አዳኝ በተሰጠኝ ሐዋርያዊ ስልጣን፣ ለመፈለግ የዋሆች እና ደፈሮች ከሆናችሁ ከእግዚኣብሄር እና እርስ በርስ ጋር በመታረቅ የሚመጣውን የነፍስ መረጋጋት እመሰክራለሁ። “እርስ በእርሳችው መከራከር አቁሙ፣”17 ብሏል አዳኝ። የቆየ ጉዳት እንዳለ ካወቃችሁ፣ ጠግኑት። እርስ በርሳችሁ በፍቅር ተንከበከቡ።

ውድ ጓደኞቼ፣ በጋራ ባለን የመታረቅ አገልግሎታችን ውስጥ፣ ሰላም ሰሪዎች እንድንሆን—ሰላምን እንድንወድ፣ እላምን እንድንፈልግ፣ ሰላምን እንድንፈጥር፣ ሰላምን እንድናፈቅር—እጠይቃለሁ። ያንን ይግባኝ በሰላም ልዑል ስም፣ ስለ የዋሕነት እና ኢፍትሃዊነት፣ በሐሰት ክሶች እና “በጓደኞቹ ቤት ስለመቁሰል”18 ሁሉንም ነገር በሚያውቀው፣ ነገር ግን አሁንም ይቅር ለማለት እና ለመርሳት—እና ለመፈወስ—እና ደስተኛ ለመሆን የሚያስችል ጥንካሬን ያገኝ። ለዚያ፣ ለእናንተ እና ለእኔ፣ የምጸልየው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ አሜን።