2010–2019 (እ.አ.አ)
በንስሐ መንጻት፤
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


በንስሐ መንጻት፤

በእግዚያብሄር እቅድና በእየሱስ ክርስቶስ የሃጥያት ክፍያ ምክንያት በንስሃ ሂደት ልንነጻ እንችላለን፡፡

በስጋዊ ህይወት ለሰውና ለእግዚያብሄር ህግ ተገዢዎች ነን፡፡ በነዚህ በሁለቱ ህጎች ስር የሆኑ ከባድ የስነምግባር ግድፈቶችን የመዳኘት ለየት ያለ ልምድ አግኝቼ ነበር—በመጀመሪያ በዩታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኜ ሳገለግል እና አሁን ደግሞ እንደ ቤተክርስቲያኗ ቀዳሚ አመራር አባልነቴ፡፡ በሰውና በእግዚያብሄር ህጎች መካከል ባለው ልዩነት ላይ ያገኘሁት ተመክሮ በእየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ሃይል እና እውነተኛነት ላይ ያለኝን አድናቆትት አሳድጎልኛል፡፡ በሰዎች ህግ እጅግ በጣም ከባድ በሆነ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ሰው ያለአመክሮ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ሊፈረድበት ይችላል፡፡ ነገር ግን በአፍቃሪ ሰማያዊ አባታችን የምህረት እቅድ ዘንድ ሁኔታው ይለያል፡፡ በአዳኛችን የሃጢያት ክፍያ መስዋእትነት ምክንያት “የተሰበረ እና የተጸጸተ ልብ ላላቸው ሁሉ” እነዚሁ ከባድ ሀጢያቶች በዚህ ህይወት ይቅር ሊባሉ እንደሚችሉ አይቻለሁ፡፡(2ኛ ኔፊ 2፧7). ክርስቶስ ይዋጀናል ፤የሃጥያት ክፍያ መስዋእቱም እውን ነው፡፡

የአዳኛችን ሩህሩህ አፍቃሪነት አሁን በመዘምራኑ በቀረበው ታላቅ መዝሙር ተገልጿል፡፡

ወደ ክርስቶስ ኑ; እርሱ ሁሌም ይሰማችኋል,

ምንም እንኳን በጨለማ ብትጠፉም .

እርሱ ይወዳችኋል ፈልጎም ያገኛችኋል ይመራችኋልም

ከጨለማ ለሊት ወደ ቀን፡፡.1

የእየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ መስዋእትነት “ንስሃ ለሚገቡ እና ወደ እርሱ ለሚመጡ“ ሁሉ በሩን ይከፍታል፡፡ (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 18፧11፤ ደግሞም ማርቆስ 3፧281ኛ ኔፊ 10፧18; አልማ 34፧8,16)፡፡ የአልማ መጽሃፍ ክፉዎችና ደም የተጠሙ የነበሩ ሰዎችእንኳ ስለገቡት ንስሃ እና ስለተደረገላቸው ይቅርታ ይናገራል፡፡ (አልማ 25፧1627፧27, 30)ን ይመልከቱ፡፡ ዛሬ የኔ መልእክት በመወገድ የቤተክርስቲያን አባልነታቸውን ያጡትን ወይም ስማቸው የተሰረዙትንን ጨምሮ ለሁላችንም ተስፋ ነው፡፡ ሁላችንም በንስሃ መንጻት የምንችል ሃጢያተኞች ነን፡፡ ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ “ ሃጢያትን መናዘዝ ቀላል አይደለም ፤ነገር ግን ሽልማቱ የምንከፍለውን ዋጋ ተገቢ ያደርገዋል፡፡“ ሲል አስተምሯል ሽማግሌ ኔልሰን፡፡2

ንስሀ

ንስሃ በአዳኛችን ይጀምራል፤ ሸክም ሳይሆን ደስታ ነው፡፡ ፕሬዚደንት ራስል ኤም ኔልሰን ባለፈው የገና ዲቮሽናል “እውነተኛ ንስሃ የአንድ ጊዜ ሁነት አይደለም“ሲል አስተምሯል ፡፡ የማያልቅ ልዩ መብት ነው፡፡ ለማደግ እና ለአእምሮ ሰላም፣ ለምቾት እንዲሁም ለደስታ መሰረታዊ ነው፡፡.”3

ስለንስሃ የሚናገሩ አንዳንድ ታላላቅ ትምህርቶች የሚገኙት በመጽሃፈ ሞርሞን የአልማ ምሳሌዎች ውስጥ በኋላ እርሱ “ በብዙ አለማመን “ ፣ “በኩራት ከፍ ያሉ“ እና ልባቸውን “ በሃብት እና በአለም ከንቱ ነገሮች “ላይ ያሳረፉ አንደነበሩ ለገለጻቸው የቤተክርስቲያን አባላት የተጻፈ ነበር፡፡ (አልማ 7፧6፡፡) እያንዳንዱ የተመለሰችው ቤተክርስቲያን አባል ከዚህ ቀስቃሽ ትምህርት ብዙ መማር ይገባዋል፡፡

በእየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጀምራለን፤ ምክንያቱም “የዓለምን ኃጢያት ሊወስድ የሚመጣው እርሱ ነው፡፡ “ (አልማ 5፧48፡፡) ንስሃ መግባት አለብን ምክንያቱም፣ አልማ እንዳስተማረው “ ንስሃ ካልገባችሁ በምንም መንገድ የእግዚአብሔርን መንግስት ልትወርሱ አትችሉም።“” (አልማ 5፧51፡፡) ንስሃ አስፈላጊ የእግዚአብሔር እቅድ ክፍል ነው። በስጋዊ ልምምድ ሁሉም ሃጥያትን ስለሚሰራ እና ከእግዚያብሄር ፊትም ስለሚነጠል ሰው ያለንስሃ ”ሊድን ”አይችልም፡፡(አልማ 5፧31; see also ሄለማን 12፧22).

ከመጀመሪያ ጀምሮ ይህ ትምህርት እየተሰጠ ነበር፡፡ እግዚአብሄር አዳምን እንዲህ ሲል አዘዘው” ስለዚህ በየትም ያሉ ሁሉም ሰዎች ንስሀ መግባት እንደሚገባቸው ልጆችህን አስተምራቸው፣ አለዚያም የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ በምንም አይችሉም፣ ምንም እርኩስ ነገር በዚያ ወይም በእርሱ ፊት መኖር አይችልምና፤” (Moses 6፧57). ሃጥያቶቻችንን በሙሉ—የእግዚያብሄርን ትእዛዛት በመቃረን ስላደረግናቸው ወይም ስላላደረግናቸው ነገሮች በሙሉ ንስሃ መግባት አለብን፡፡ ከዚህ ነጻ የሆነ ማንም ሰው የለም። ትናንት ምሽት ፕሬዚደንት ኔልሰን “ወንድሞች ፣ሁላችንም ንስሃ ያስፈልገናል፡፡“ ሲል ጠይቆን ነበር፡፡.”4

በእምነት ወደ ክርስቶስ ስንመጣ ሃጥያታችንን ከተውን ፣ ለጌታ እና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜም ለስጋዊ ዳኛ ከተናዘዝናቸው ከሃጥያታችን ለመንጻት እንችላለን፡፡ ( ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 58፧43ን ይመልከቱ፡፡) በተጨማሪም ወደ እየሱስ ክርስቶስ ስንመጣ “የጽድቅ ስራ ማቅረብ” እንዳለብን አልማ አስተምሯል፡፡ (አልማ 5፧35፡፡) እነዚህ ሁሉ ወደክርስቶስ እንድንመጣ የቅዱሳን ጽሁፎች ተደጋጋሚ ግብዣዎች አካል ናቸው፡፡

በእያንዳንዱ የሰንበት ቀን ከቅዱስ ቁርባኑ መካፈል አለብን፡፡ በዚያ ስርዐት ቃልኪዳን እንገባለን በረከቶችንም እንቀበላለን አዳኛችን እንድንደርስበት ከጋበዘው ፍጽምና እንዳንደርስ የሚያደርጉንን ሁሉንም ድርጊቶች እና ፍላጎቶች መቋቋም የሚያስችለንን ቃልኪዳን እንገባለን በረከቶችንም እንቀበላለን፡፡ ( ማቴዎስ 5:483ኛ ኔፊ 12፧48 ይመልከቱ)፡፡ ”ለራሳችን ሃጢአተኝነትን በሙሉ ከካድን እናም በሙሉ ሃይላችን ፣ አእምሮአችን እና ጉልበታችን እግዚአብሄርን ከወደድን“ “በክርስቶስ ፍጹም እንሆናለን“ እናም ደሙ በመፍሰሱ ምንም “እንከን የሌለብን ቅዱስ“ እንሆናለን፡፡ (ሞሮኒ 10፧32–33). እንዴት ያለ ተስፋ ነው! እንዴት ያለ ተአምር ነው! እንዴት ያለ በረከት ነው!

II. ተጠያቂነት እና ስጋዊ ፍርድ

የዚህ ስጋዊ ህይወት የእግዚአብሄር እቅድ አንድ አላማ ” [የእኛ ]ጌታ እግዚአብሄር የሚያዘንን ነገሮች በሙሉ እንደምንፈጽም ለማየት” እና ”ለማረጋገጥ ” ነው፡፡(አብራሃም 3፧25). እንደ እቅዱ አካል፣ እኛ በእግዚአብሄር እና በተመረጡ አገልጋዮቹ ተጠያቂዎች ነን እናም ተጠያቂ የምንሆንባቸው ነገሮች የስጋዊ እና የመለኮታዊ ፍርድን ያካትታሉ፡፡

በጌታ ቤተክርስቲያን ለአባላት እና ለእጩ አባላት ስጋዊ ፍርዶች የሚሰጡት መለኮታዊ መመሪያ በመጠየቅ በመሪዎች አማካኝነት ነው፡፡ የሃጥያት ክፍያ መስዋእቱን ሃይል ለመቀበል በቃልኪዳኑ መንገድ ለዘላለም ህይወት ወደክርስቶስ ለመምጣት የሚሹትን ሰዎች መለየት የእነሱ ሃላፊነት ነው፡፡ ስጋዊ ፍርድ አንድ ሰው ለንስሃ ዝግጁ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ይወስናሉ፡፡ አንድ ሰው በቤተመቅደስ ለመሳተፍ ፈቃድ ለማግኘት ብቁ ነውን? አንድ ከቤተክርስቲያን መዝገብ ውስጥ ስሙ የተሰረዘ ሰው በእየሱስ ክርስቶስ የሃጥያት ክፍያ በጥምቀት ቤተክርስቲያኗን ለመቀላቀል በበቂ ሁኔታ ንስሃ ገብቷልን?

አንድ በእግዚአብሄር የተጠራ የስጋዊ ህይወት ዳኛ ለአንድ ሰው እንደ ቤተመቅደስ መብቶች ያሉ ቀጣይ እድገቶችን ሲፈቅድ ሰውየውን ንጹህ አድርጎ አይደለም እንዲሁም ምንም ሃጥያት ይቅር እያለለትም አይደለም፡፡ ሽማግሌ ስፔንሰር ደብልዩ ኪምባል ስጋዊ “ ቅጣቶች ከቀሩ “ በኋላ ሰውየው “ከሰማይ አምላክ የመጨረሻ ንስሃ መሻት እና ማግኘት አለበት ያኔም ነው የሚነጻው ሲል አስተምሯል፡፡”5 እንዲሁም የሃጥያት ተግባራት እና ፍላጎቶች እስከ መጨረሻው ፍርድ ንስሃ ካልተገባባቸው ንስሃ ያልገቡት ሰዎች ከነሃጥያታቸው ይቀራሉ፡፡ የመጨረሻው የንስሃ ንጽህና በእያንዳንዳችን እና በእግዚአብሄር መካከል ነው፡፡

III. ትንሳኤ እና የመጨረሻው ፍርድ

በቅዱሳን ጽሁፎች በተለምዶ ይበልጥ የተጠቀሰው ፍርድ ከትንሳኤ በኋላ የሚመጣው የመጨረሻው ፍርድ ነው፡፡ (2ኛ ኔፊ 9፧15)ን ይመልከቱ፡፡ ብዙ ቅዱሳን ጽሁፎች “በስጋዊ አካል እንደተሰሩት ስራዎች ለመዳኘት“ “በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እንደምንቆም“ ይገልጻሉ፡፡ (ሮሜ 14፧10፤ ደግሞም 2 ኛ ኔፊ 9፧15ሞዛያ 27፧31) (አልማ 5፧15፧ ደግሞም ራእይ 20፧12አልማ 41፧33ኛ ኔፊ 26፧4፧ የዮሃንስ )ን ይመልከቱ፡፡ ሁሉም “እንደየስራው“ (3ኛ ኔፊ 27፧15) “እናም በልባቸው ፍላጎቶች መሰረት“ ይዳኛሉ፡፡( ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 137፧9፤ ደግሞም አልማ 41፧6)ይመልከቱ፡፡

የመጨረሻው ፍርድ አላማ አዲስ ፍጥረታት በመሆን “ከእንግዲህ ሃጥያት ለመፈጸም ምንም ፍላጎት የለንም ነገር ግን ያለማቋረጥ መልካምን መስራት እንጂ፡፡“ ሲል አልማ የገለጸውን “ታላቅ የልብ ለውጥ“ አድርገን እንደሆነ ለመወሰን ነው፡፡ ( አልማ 5፧14, 26) ን ይመልከቱ፣(ሞዛያ 5፧2). የዚህ ዳኛ አዳኛችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ( ዮሃንስ 5፧222ኛ ኔፊ 9፧41) ን ይመልከቱ፡፡ ከፍርዱ በኋላ ሁላችንም ”ፍርዱ ትክክል እንደሆነ” እንናዘዛለን፤(ሞዛያ 16፧1; 27:31አልማ 12፧15), ምክንያቱም ሁሉን ነገር ለማወቅ መቻሉ (2ኛ ኔፊ 9፧15, 20)ን ይመልከቱ ጽድቅ ስለሆኑት ወይም ንስሃ ስለገባንባቸውም እና ጽድቅ ስላልሆኑ ንስሃ ስላልገባንባቸውም ወይም ስላልተቀየሩት ስለሁሉም ድርጊቶቻችን አና ፍላጎቶቻችን የተሟላ እውቀት ይሰጠዋል፤ ፡፡

ቅዱሳን ጽሁፎች የዚህን የመጨረሻ ፍርድ ሂደት ይገልጻሉ፡፡ የአፍቃሪ አምላክ ፍርድ “ሁሉም ነገሮች ወደ ተገቢው ስርአት እንዲመለሱ “ይፈልጋል ሲል አልማ ያስተምራል፡፡ (አልማ 41፧2). ይህ ማለት “ በዚህ ህይወት ስራቸው መልካም ከሆነና፣ የልባቸው ፍላጎት መልካም ከሆነ፣ ...በመጨረሻው ቀን ደግሞ መልካም ወደሆነው መመለስ አለባቸው።” (አልማ 41፧3). በተመሳሳይም “ስራቸው[ወይም ፍላጎታቸው] መጥፎ ከሆነ በእነርሱ ላይ ለመጥፎ ይመለሱባቸዋል፡፡” (አልማ 41፧4–5; ደግሞም ሄለማን 14፧31)ን ይመልከቱ፡፡ ስለዚህም ነብዩ ያዕቆብ በመጨረሻው ፍርድ “ ጻድቅ የሆኑት አሁንም ጻድቅ ይሆናሉ እናም የረከሱት አሁንም እርኩሳን ይሆናሉ “ ሲል አስተምሯል፡፡l” (2ኛ ኔፊ 9፧16; ደግሞም ሞርሞን 9፧141ኛ ኔፊ 15፧33)ን ይመልከቱ፡፡ ያ ሞሮኒ “ዘለዓለማዊ ዳኛ በሆነው በታላቁ ያህዌህ የህያዋን እና የሙታን አስደሳቹ የፍርድ ወንበር ፊት “ ካለው በፊት ያለ ሂደት ነው፡፡(ሞሮኒ10፧34፤ ደግሞም 3ኛ ኔፊ 27፧16) ይመልከቱ፡፡

በእግዚያብሄር ፊት ንጹህ እንደምንሆን ለማረጋገጥ ከመጨረሻው ፍርድ በፊት ንስሃ መግባት አለብን፡፡ አለብን፡፡( ሞርሞን 3፧22) ይመልከቱ፡፡ አልማ ሃጥያተኛ ልጁን በእግዚያብሄር ፊት ሃጥያታችንን መደበቅ አንችልም ፤ “እናም ንስሃ ካልገባህ በመጨረሻው ቀን በአንተ ላይ ለምስክርነት ይቆማሉ።“ሲል ነግሮታል ፡፡ (አልማ 39፧8፤ አትኩሮት ተጨምሯል፡፡) የእየሱስ ክርስቶስ የሃጥያት ክፍያ የሚፈለገው መንጻት ላይ ለመድረስ ያለውን ብቸኛ መንገድ ንስሃን ይሰጠናል ፤ እናም ይህ ስጋዊ ህይወት ያንን ማድረጊያ ጊዜ ነው፡፡ ምንም እንኳን አንዳንድ ንስሃ በመንፈሳዊው አለም እንደሚደረግ የተማርን ቢሆንም (see ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 138፧31, 33, 58)፣ያ የተረጋገጠ አይደለም፡፡ ሽማግሌ ሜልቪን ጄ ባላርድ ሲያስተምር “ ስጋና መንፈስ አንድ ላይ ተጣምረው እያሉ ሃጥያትን ማሸነፍ እና ጌታን ማገልገል ይበልጥ ቀላል ነው፡፡ ይህ ሰዎች ይበልጥ መለወጥ የሚችሉበት እና ተጋላጭ ...የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ የንስሃ ጊዜ ነው፡፡”6

ንስሃ ስንገባ ሃጥያቶቻችን ድርጊቶቻችንን እና ፍላጎቶቻችንን ጨምሮ ፣ እንደሚታጠቡ እና ይቅር ባዩ የመጨረሻ ዳኛችን “በድጋሚ እንደማያስታውሳቸውምየጌታ ማረጋገጫ አለን፡፡ “(ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 58፧42፤ ደግሞም ኢሳይያስ 1፧18; ኤርምያስ 31፧34ዕብራውያን 8፧12አልማ 41፧6ሄለማን 14፧18–19)ን ይመልከቱ፡፡ በንስሃ በመንጻት ንጉስ ቤንጃሚን“በማያልቀው ደስታ ከእግዚያብሄር ጋር ይኖራሉ “ሲል የገለጸውን የዘላለም ህይወት መስፈርቶች እናሟላለን፡፡፡፡” (ሞዛያ 2፧41፤ ደግሞምትምህርት እና ቃልኪዳኖች 14፧7)ን ይመልከቱ፡፡

እንደ ሌላ የእግዚያብሄር ”የመመለስ እቅድ” አካል (አልማ 41፧2) ትንሳኤ ”ሁሉንም ነገር ...ወደ ተገቢው እናም ትክክለኛ አቋሙ ”ይመለልሳል፡፡ (አልማ 40፧23). ስለዚህ በዚህ ህይወት ያሉብን አካላዊ ጉዳቶችና እንከኖች በውልደት ወይም በአደጋ ወይም በበሽታ ምክንያት የተከሰቱትን ጨምሮ ወደ ትክክለኛ አቋማቸው ይመለሳሉ፡፡

ይህ መመለስ በመንፈሳዊ ንጹህ አለመሆናችንን ወይም ያላሸነፍናቸውን ፍላጎቶች ወይም ሱሶች ሊያነጻልንና ወደ ትክክለኛ አቋማቸው ሊመልስልን ይችላል? ያ ሊሆን አይችልም፡፡ በፍላጎታችንና በተግባራችን ልክ እንደሚፈረድብን ከዚህ ዘመን መገለጦች እናውቃለን፡፡፤ (አልማ 41፧5ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 137፧9)ን ይመልከቱ፡፡ እናም የገዛ ሃሳባችንም ይወቅሰናል፡፡ (አልማ 12፧4)ን ይመልከቱ፡፡ እስከ ሞት ድረስ “የንስሃችንን ቀን ማስረዘም“ የለብንም (አልማ 34፧33) ምክንያቱም፣ በዚህ ህይወት እኛን የሚወርሰው ይሀው መንፈስ —የጌታም ይሁን የዲያብሎስ” በዘላለማዊው ዓለም እኛን የእራሱ ለማድረግ ስልጣን ይኖረዋል” ሲል አሙሌክ አስተምሯል፡፡ (አልማ 34፧34). አዳኛችን ሃይል አለው፤ ከክፉ ሊያድነንም ዝግጁ ነው፡፡ ከክፋታችን ወይም ተገቢ ካልሆነ ምኞታችንና ሃሳቦቻችን ንስሃ ለመግባት እርዳታ የምንጠይቀውእና በመጨረሻው ቀን በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ዝግጁ መሆን የምንችልበት ጊዜው አሁን ነው፡፡

የምህረት እጆች

ሁሉን አቀፉ የእግዚያብሄር እቅድ እና ትእዛዛቶቹ ሁሉ “ ከሁሉ ነገሮች በላይ አስፈላጊ …እና ለነፍስ እጅግ አስደሳች “የሆነው ለያንዳንዳችን ያለው ፍቅር ነው፡፡” (1ኛ ኔፊ 11፧22–23) ነብዩ ኢሳያስ ክፉ ሰው “ ወደ እግዚአብሔር ቢመለስ እርሱም ይምረዋል እናም ይቅርታውም ብዙ ነው“ ሲል አረጋግጧል (ኢሳይያስ 55፧7)፡፡ “እነሆ፣ ለሰው ሁሉ ግብዣን ልኳል፣ የምህረት ክንድ ወደ እነርሱ ተዘርግቷልና።“ ሲል አስተምሯል አልማ፡፡ (አልማ 5፧33፤ ደግሞም 2ኛ ኔፊ 26፧25–33)ን ይመልከቱ፡፡ የተነሳው ጌታ ለኔፋውያን ፣ “የምህረት ክንዴ ወደ እናንተ ተዘርግታለች፣ እናም ማንም ቢመጣ እቀበለዋለሁ” ብሏቸዋል፡፡ (3 ኔፊ 9፧14)። ከዚህ እና ከሌሎች ቅዱስ ጽሁፋዊ አስተምህሮቶች በመነሳት አፍቃሪ የሆነው አዳኛችን ሁሉንም ወንዶችና ሴቶች እጆቹን ዘርግቶ በመቀበል እሱ ባዘዘላቸው እና እግዚያብሄር ለልጆቹ ባለው ታላላቅ በረከቶች እንዲደሰቱባቸው እንደሆነ እናውቃለን፡፡ 7

በእግዚያብሄር እቅድና በእየሱስ ክርስቶስ የሃጥያት ክፍያ ምክንያት አግዚያብሄር እንደሚወደን እና በንስሃ ሂደት ልንነጻ እንደምንችል ከ“ፍጹም ብሩህ ተስፋ“ጋር እመሰክራለሁ፡፡ “ የክርስቶስን ቃል በመመገብ፣ እናም እስከመጨረሻው በመፅናት የምንቀጥልከሆነ፣ እነሆ አብ እንዲህ ይላል፧ የዘለዓለም ህይወት ይኖራችኋል“2 ኔፊ 31፧20 የሚል ቃል ተገብቶልናል። ሁላችሁም እንዲሁ እንድታደርጉ የምማጸነው እና የምለምነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “Come unto Jesus,” መዝሙር ቁጥር 117።

  2. ሩሴል ኤም ኔልሰን፣ “Repentance and Conversion፣” Liahona፣ ግንቦት 2007 (እአአ)፣ 102።

  3. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Four Gifts that Jesus Christ Offers to You,” 2018 የቀዳሚ ፕሬዚደንት የገና ዲቮሽናል፣www.lds.org/broadcasts.

  4. ረስል ኤም ኔልሰን “We Can Do Better and Be Better,” ኢንሳይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 47።

  5. የስፔንሰር ደብሊው ኪምቦል አስተምህሮ, ed. እድዋርድ ኤል ኪምባል(1982 እኤአ), 101

  6. ሜልቪል ጄ. ባላርድ፣ በሜልቪል አር.ባላርድ ፣ ሜልቪል ጄ. ባላርድ: Crusader for Righteousness (1966), 212–13.

  7. ታድ አር. ካሊስተር The Infinite Atonement (2000)፣ 27–29 ይመልከቱ፡፡