ምዕራፍ ፱
ሞሮኒ በክርስቶስ ለማያምኑት ንሰሃ እንዲገቡ ጠራቸው—ራዕይ ስለሚሰጠው እናም ለታማኞችም ራዕዮችን እናም ምልክቶችን ስለሚሰጠው የተአምራት እግዚአብሔር አወጀ—ተአምራቶች የቆሙት እምነት ባለመኖሩ ነው—ያመኑትን ምልክቶች ይከተሉአቸዋል—ሰዎች ብልህ እንዲሆኑና ትዕዛዛቱን እንዲጠብቁ ይመከራሉ። ከ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እናም አሁን፣ ደግሞ በክርስቶስ ስለማያምኑት እናገራለሁ።
፪ እነሆ፣ በመጎብኘታችሁ ቀን ታምናላችሁን—እነሆ፣ ጌታ ሲመጣ፣ አዎን በዚያ፣ ሀበታላቁ ቀን ለመሬት እንደ ጥቅልል በምትጠቀለልበት ጊዜ እናም አለቶችም በታላቅ ሙቀት ሐበሚቀልጡበት ጊዜ፣ አዎን፣ በዚያ ታላቅ ቀን በእግዚአብሔር በግ ፊት በምትቆሙ ጊዜ—እግዚአብሔር የለም ትላላችሁን?
፫ ክርስቶስን መካዳችሁን ትቀጥሉበታላችሁ፣ ወይንም የእግዚአብሔርን በግ ለማየት ይቻላችኋል? ጥፋታችሁን እያወቃችሁ ከእርሱ ጋር ለመኖር ታስባላችሁን? ህጉን በማንኛውም እንደጣሳችሁ ነፍሳችሁ አውቃ በምትቆስል ጊዜ ከቅዱሱ ጋር በመኖር ደስተኛ መሆን እንደምትችሉ ታስባላችሁን?
፬ እነሆ፣ የተበከለ ህሊና በፊቱ እያላችሁ ከቅዱስ እና ፍትህ እግዚአብሔር ጋር መኖር ሀከተኮነኑት ነፍሳት ጋር ለበሲዖል ከመኖር በላይ አሰቃቂ ነው እላችኋለሁ።
፭ እነሆም፣ በእግዚአብሔር ፊት ሀራቁታችሁን መሆናችሁን፣ እናም ደግሞ የእግዚአብሔር ክብርና፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስነት ለማየት በምትመጡበት ጊዜ፣ በእናንተ ላይ የማይጠፋን እሳት ያቀጣጥላል።
፮ እናንተ ሀየማታምኑ ሆይ፣ ወደ ጌታ ለተመለሱ፤ ምናልባት በመጨረሻውና በዚያ በታላቁ ቀን እንከን የሌላችሁ፣ ሐንፁህ፣ መልካም፣ እናም መበበጉ ደም የፀዳችሁ ሆናችሁ ትገኙ ዘንድ ወደ አብ በኢየሱስ ስም በኃይል ጩሁ።
፯ እናም እናንተ የእግዚአብሔርን ራዕይ ሀለካዳችሁና፣ እነርሱ ተፈፅመዋል፣ ራዕዮች፣ ትንቢቶች፣ ስጦታዎችም ሆነ፣ መፈወስ፣ እናም በልሳን መናገርም ሆነ፣ በልሳን የሚናገሩትን ለመተርጎም ቆሟል የምትሉትን በድጋሚ እናገራችኋለሁ፤
፰ እነሆ እኔ እንዲህ እላችኋለሁ፣ እነዚህን ነገሮች የሚክድ የክርስቶስን ሀወንጌል አያውቅም፤ አዎን፣ ቅዱሳን መጽሐፍትንም አላነበበም፣ ይህም ቢሆን እንኳን ለአልተረዱትም።
፱ እግዚአብሔር ሀትናንትና፤ ዛሬም እንዲሁም ለዘለዓለም አንድ እንደሆነ እናም በእርሱም የመቀያየርም ሆነ የመለወጥ ጥላ አለመኖሩን አላነበብንምን?
፲ እናም አሁን፣ ለራሳችሁ የሚለዋወጥና በእርሱም የመለዋወጥ ጥላ ያለበትን አምላክ የምታስቡ ከሆነ፣ የተአምራት አምላክ ያልሆነውን አምላክ ለራሳችሁ አስባችኋል።
፲፩ ነገር ግን እነሆ፣ ለእናንተም የተአምራት አምላክ፣ እንዲሁም የአብርሃምን አምላክ፣ እናም የይስሃቅን አምላክ፣ እናም የያዕቆብን አምላክን አሳያችኋለሁ፤ እርሱም ሰማይና ምድርን፣ እናም በውስጡም ያሉትን ነገሮች ሁሉ የፈጠረ ሀአምላክ ነው።
፲፪ እነሆ፣ እርሱ ሀአዳምን ፈጠረና፣ በአዳም ምክንያት የሰው ልጅ ለውድቀት መጣ። እናም በሰው ልጅ መውደቅ የተነሳ፣ አብና ወልድ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ፤ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነትም ለሰው ልጅ ሐቤዛነት መጣ።
፲፫ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ለሰዎች ቤዛነት በመምጣቱ፣ ወደ ጌታም ፊት ተመልሰዋል፤ አዎን፣ ሁሉም ሰዎች የዳኑበት በዚህም ነው፥ የክርስቶስ ሞት ሀትንሣኤን አመጣ፣ ይህም መጨረሻ ከሌለው እንቅልፍ ቤዛነት አመጣ፣ መለከቱ ሲነፋ ሰዎች ሁሉ ከዚህ ለእንቅልፍ በእግዚአብሔር ኃይል ይነቃሉ፣ እናም ትልልቆችም ሆኑ ትንንሾች የሆኑት ይመጣሉ፣ እናም ዘላለማዊ ከሆነው የሞት ሐሰንሰለት በመዳንና በመፈታት፣ ይህም ሞት ጊዜአዊው ሞት ነው፣ በፍርዱ ወንበር ፊት ሁሉም ይቆማሉ።
፲፬ እናም የቅዱሱ ሀፍርድ በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ ለንፁህ ያልሆነውም አሁን ንፁህ ሳይሆን የሚቀርበት ጊዜ ይመጣል፤ እናም ፃድቅ የሆነው አሁንም ፃድቅ ይሆናል፤ ደስተኛ የነበረውም አሁን ደስተኛ ይሆናል፤ እንዲሁም ደስተኛ ያልነበረው አሁንም ደስተኛ አይሆንም።
፲፭ እናም አሁን፣ እናንተ ለራሳችሁ ሀምንም ተአምራትን መስራት የማይችል አምላክን ያሰባችሁ ሁሉ፣ እንዲህ ስል እጠይቃችኋለሁ፥ እኔ የተናገርኳቸው እነዚህ ነገሮች ሁሉ አልፈዋልን? መጨረሻው መጥቷልን? እነሆ አይደለም እላችኋለሁ፤ እናም እግዚአብሔር የተአምራት አምላክ መሆኑን አላቆመም።
፲፮ እነሆ፣ እግዚአብሔር የሰራቸው በዐይናችን ድንቅ አይደሉምን? አዎን፣ እናም ድንቅ የሆነውን የእግዚአብሔር ሀሥራዎች የሚገባው ማነው?
፲፯ ሀበቃሉ ሰማይና ምድር ለመፈጠሩ፤ እናም ቃሉ ባለው ኃይል የሰው ልጅ ከመሬት ሐአፈር መፈጠሩ፤ እናም በቃሉ ኃይል ተአምራት መሠራቱ ተአምር አይደለም የሚል ማነው?
፲፰ እናም ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ሀተአምራትን አልሰራም የሚለው ማነው? እናም በሐዋርያቶቹ እጅ ብዙ ተአምራት ተሰርተው ነበር።
፲፱ እናም በዚያ ጊዜ ሀተአምራቶች ተደርገው ከሆነ፣ እግዚአብሔርስ የተአምራት አምላክ መሆኑን ለምን ያቆማል እናም ግን የማይለወጥ አምላክ ሊሆን ይችላል? እንዲሁም እነሆ እላችኋለሁ እርሱ አይለወጥም፣ የሚለወጥ ከሆነ አምላክነቱን ያቆማል፣ እናም አምላክነቱን አያቆምም፣ የተአምራትም አምላክ ነው።
፳ እናም በሰው ልጆች መካከል ሀተአምራት መስራቱን ያቆመበት ምክንያት እነርሱ እምነት አጥተው በመመንመናቸው፣ እናም ከትክክለኛው መንገድ በመራቃቸውና፣ ለየሚያምኑበትን አምላክ ባለማወቃቸው ነው።
፳፩ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ ምንም ባለመጠራጠር በክርስቶስ የሚያምን፣ በክርስቶስ ስም አብን ሀማንኛውንም ነገር ከጠየቀ ለእርሱ ይሰጠዋል፤ እናም ይህ ቃል ኪዳን ለሁሉም፣ እንዲሁም እስከ አለም ዳርቻ እንኳን ነው።
፳፪ እነሆም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እስከምፅአቱ ለሚቆዩትም ደቀ መዛሙርቱ፣ አዎን፣ እናም ደግሞ ለሁሉም ደቀመዛሙርት ህዝቡ እየሰሙት እንዲህ ሲል ተናገራቸው፥ ወደ ዓለም ሁሉ ሀሂዱና፣ ለፍጥረት ሁሉ ወንጌልን ስበኩ።
፳፫ እናም ያመነና የተጠመቀም ይድናል፤ ያላመነ ግን ሀይኮነናል፤
፳፬ እናም ያመኑትን እነዚህ ሀምልክቶች ይከተሏቸዋል—በስሜ ለአጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ልሳንም ይናገራሉ፤ መርዛማ እባቦችንም ያነሳሉ፤ እናም የሚገድልን ነገር ቢጠጡም አይጎዳቸውም፤ ሐእጃቸውን በህመምተኞች ላይ ይጭናሉና ያድኗቸዋል፤
፳፭ እናም ምንም ሳይጠራጠር በስሜ የሚያምን ቢኖር፣ ለእርሱ እስከ ዓለም ዳርቻ ቃሌን ሁሉ ሀማረጋገጫ አደርግለታለሁ።
፳፮ እናም እንግዲህ፣ እነሆ፣ የጌታን ሥራ የሚቃወም ማን ነው? ንግግሩንስ የሚክድ ሀማን ነው? ሁሉን ቻይ በሆነው በጌታ ኃይል ላይ የሚነሳስ ማን ነው? የጌታን ሥራ የሚንቅ ማን ነው? የክርስቶስን ልጆች የሚንቅስ ማን ነው? እነሆ፣ የጌታን ሥራ ለየምትንቁ ሁሉ፣ ትገረማላችሁ እናም ትጠፋላችሁ።
፳፯ አቤቱ አትናቁና አትገረሙ፤ ነገር ግን የጌታን ቃላት አድምጡት፣ እናም፣ በስሙም የምትፈልጉትን ነገር አብን በኢየሱስ ስም ጠይቁት። አትጠራጠሩ፣ ነገር ግን የምታምኑ ሁኑ፣ በጥንት ጊዜ እንደነበሩት ሰዎች በእምነት ጀምሩ፤ እናም በሙሉ ሀልባችሁ ሆናችሁ ወደ ጌታ ለኑ፤ እናም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በፊቱ የራሳችሁን መዳን ሐፈፅሙ።
፳፰ በሙከራ ጊዜያችሁም ሀብልህ ሁኑ፤ የጎደፉ ነገሮችን በሙሉ ከላያችሁ ላይ አራግፉ፤ ለለምኞቶቻችሁ ማስፈፀሚያ በክፉ አትጠይቁ፤ ነገር ግን ወደ ፈተና እንዳትገቡ ዘንድ፣ ነገር ግን እናንተ እውነተኛውን እናም ሐህያውን እግዚአብሔር ታገለግሉ ዘንድ በማይነቃነቀው ፅናታችሁ ጠይቁ።
፳፱ ሀብቁ ሳትሆኑ እንዳትጠመቁም ተጠንቀቁ፤ የክርስቶስንም ቅዱስ ቁርባን ለብቁ ሳትሆኑ ላለመቁረስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ሁሉንም ነገሮች ስታደርጉ ሐበብቁነት ማድረጋችሁን ተመልከቱ፣ ስታደርጉም በህያው እግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አድርጉት፤ እናም ይህን ካደረጋችሁና፣ እስከመጨረሻ ፅኑ ከሆናችሁ በምንም ዓይነት እናንተ አትጣሉም።
፴ እነሆ፣ ሙታን ሆኜ እንደምናገረው ሀእናገራችኋለሁ፤ ምክንያቱም እናንተ የእኔ ቃል እንደሚኖራችሁ አውቃለሁ።
፴፩ ሀበጉድለቶቼ ምክንያት አትኮንኑኝ፣ አባቴንም በጉድለቶቹ አትኮንኑት፣ ከእርሱም በፊት ሲጽፉ የነበሩትንም አትኮንኑአቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እኛ ከነበርነው የበለጠ ብልህ ለመሆን ትማሩ ዘንድ ፍፁም አለመሆናችንን ስለገለፀላችሁ ምስጋና አቅርቡለት እንጂ።
፴፪ እናም አሁን፣ እነሆ፣ በመካከላችን በንግግራችን ስርዐት መሰረት የተላለፉልንና የቀየርናቸው ሀየተለወጡ ግብፃውያን ተብለው በሚጠሩት ፊደላት እንደችሎታችን ይህንን መዝገብ ፅፈናል።
፴፫ እናም ሰሌዳዎቻችን በበቂ ሁኔታ ትልቅ ቢሆኑ ኖሮ በዕብራውያን እንፅፈው ነበር፤ ነገር ግን ዕብራውያንም ደግሞ በእኛ ተለውጧል፤ እናም በዕብራውያን መፃፍ ብንችል ኖሮ፣ እነሆ፣ በመዛግብቶቻችን ውስጥ ስህተት አታገኙም ነበር።
፴፬ ነገር ግን ጌታ የፃፍናቸውን ነገሮች ያውቃል፣ እናም ደግሞ ማንም ሌላ ሰው ቋንቋችንን አያውቅም፤ እናም ምክንያቱም ማንም ሌላ ሰው ቋንቋችንን ባለማወቁ፣ ስለዚህ እርሱም የሚተረጉምበትን ሀመንገድ አዘጋጅቷል።
፴፭ እናም እነዚህ ነገሮች ሀእምነት አጥተው የመነመኑትን ወንድሞቻችንን ደም ከልብሶቻችን ላይ እናነፃ ዘንድ የተፃፉ ናቸው።
፴፮ እናም እነሆ፣ ወንድሞቻችንን በተመለከተ እነዚህን ነገሮች፣ አዎን፣ ክርስቶስን ወደማወቅ ይመለሱ ዘንድ፣ ሀየፈለግናቸው በምድሪቱ ይኖሩ በነበሩት ቅዱሳን ሁሉ ፀሎት መሰረት ነው።
፴፯ እናም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ፀሎታቸው እንደ እምነታቸው እንዲመለስላቸው ያድርግ፤ እግዚአብሔር አብም ከእስራኤል ቤት ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ያስታውስ፤ እናም በክርስቶስ ስም ባላቸው እምነት በኩል ለዘለዓለም ይባርካቸው። አሜን።