መፅሐፈ ጄረም
ምዕራፍ ፩
ኔፋውያን የሙሴን ህግ ጠበቁ፣ የክርስቶስንም መምጣት ጠበቁ፣ እናም በምድሪቱ ላይ በለፀጉ—ብዙ ነቢያት ሕዝቡን በእውነት ጎዳና ለመጠበቅ ጣሩ። ከ፫፻፺፱–፫፻፷፩ ም.ዓ. ገደማ።
፩ አሁን እነሆ፣ እኔ ጄረም፣ በአባቴ፣ ኢኖስ ትዕዛዝ መሰረት የእኛ ሀየትውልድ ሐረግ ይጠበቅ ዘንድ ጥቂት ቃላት እፅፋለሁ።
፪ እናም ሀእነዚህ ሰሌዳዎች ለትንሽ ቦታ ያላቸው በመሆኑ፣ እና እነዚህ ነገሮች ሐየሚፃፉት ለወንድሞቻችን መላማናውያን ጥቅም ስለሆነ፣ በመሆኑም ጥቂት መፃፌ አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን የእኔን ትንቢትም ሆነ ራዕይ አልፅፍም። አባቶቼ ከጻፉትስ የበለጠ ምን መፃፍ ይቻለኛል? እነርሱ የደህንነትን ዕቅድ አልገለጹምን? እኔ እላችኋለሁ፣ አዎን፣ እናም ይህ ለእኔ ብቁ ነው።
፫ እነሆ፣ በልባቸው ጠጣርነትና፣ በጆሮአቸው መደንቆር፣ እናም በአዕምሮአቸው መታወርና፣ ሀበአንገተ ደንዳናነታቸው ምክንያት፤ በዚህ ህዝብ መካከል ብዙ መስራቱ አስፈላጊ ነው፤ ይሁን እንጂ፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ እጅግ መሀሪ ነው፣ እናም እስከአሁንም ከምድረ ገፅ ለአላጠፋቸውም።
፬ እናም ብዙ ሀራዕይ ያላቸው ብዙዎች በመካከላችን አሉ፤ ምክንያቱም ሁሉም አንገተ ደንዳና አይደሉምና። እናም አንገተ ደንዳና ያልሆኑና እምነት ያላቸው ሁሉ፤ እንደ እምነታቸው፣ ለሰው ልጆች ነገሮችን ከሚገልፀው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ለህብረት አላቸው።
፭ እናም አሁን፣ እነሆ፣ ሁለት መቶ ዓመታት አለፉ፣ የኔፊ ህዝቦች በምድሪቷ ላይ በረቱም። የሙሴን ህግና ሀየሰንበትን ቀን ለጌታ ቅዱስ አድርገው ለበመጠበቅ አስተዋሉ። ኃይማኖትንም ሐአላረከሱም፤ ወይም መአይሳደቡም። እናም የምድሪቷን ህጎች እጅግ የጠበቁ ነበሩ።
፮ እናም እነርሱና፣ ላማናውያን ደግሞ በምድሪቱ ገፅ ላይ በብዛት ተበታትነው ነበር። እናም ከኔፋውያን ይበልጥ እጅግ ብዙ ነበሩ፤ እናም ሀመግደል ይወዱ ነበርና፣ የዓራዊትን ደም ይጠጡ ነበር።
፯ እናም እንዲህ ሆነ፣ ከእኛ ከኔፋውያን ጋር ለመዋጋት ብዙ ጊዜ መጥተው ነበር። ነገር ግን ሀነገሥታቶቻችንና መሪዎቻችን በጌታ እምነት ኃያል ሰዎች ነበሩ፤ እናም ህዝቡን የጌታን መንገድ አስተማሩ፤ ስለሆነም፣ እኛ ላማናውያንን ተቋቋምን፣ እንዲሁም ለከምድራችን አስወገድናቸው፣ እናም ለከተሞቻችን ወይም የውርሳችን ቦታ የሆነውን ማንኛውንም መከላከያ መስራት ጀመርን።
፰ እናም እጅግ ተባዛንና፣ በምድሪቱ ገፅ ላይ ተሠራጨን፣ እናም በወርቅና በብር እንዲሁም በከበሩ ነገሮችና፣ በመልካም የእንጨት ጥበብም፣ በመገንባትም፣ በማሽኖችም፣ እንዲሁም ደግሞ በብረትና መዳብ፣ እንዲሁም በነሀስ ምድሩን ለማረስ የሚያስችሉ መሳሪያዎችን እንዲሁም ሀየጦር መሳሪያዎች በመስራት፣ አዎን ሹል ጫፍ ያለው ቀስትና፣ ሰይፍ፣ ጦር እናም ለጦርነት ሁሉንም አይነት ዝግጅት በማድረግ እጅግ ሀብታም ሆንን።
፱ እናም ላማናውያንን ለመገናኘት እንደዚህ እየተዘጋጀን እያለን፣ እነርሱ በእኛ ላይ ሊያይሉብን አልቻሉም። ነገር ግን ለአባቶቻችን እንዲህ በማለት የተናገረው የጌታ ቃል ተረጋግጦ ነበር፥እናንተ የእኔን ትዕዛዛት እስከጠበቃችሁ ድረስ በምድሪቱ ላይ ትበለፅጋላችሁ።
፲ እናም እንዲህ ሆነ የጌታ ነቢያት በእግዚአብሔር ቃል መሰረት እነርሱ ትዕዛዛትን ካልጠበቁ፣ ነገር ግን ወደ መተላለፍ ከወደቁ፣ ከምድር ፊት ሀመጥፋት እንዳለባቸው የኔፊን ህዝብ አስፈራርተው ነበር።
፲፩ ስለሆነም በነቢያትና፣ ካህናትና፣ መምህራን ህዝቦችን የሙሴን ሀህግጋትና የተሰጠበትን አላማ በማስተማር፣ ወደመሲህ ወደፊት ለእንዲመለከቱና እርሱ ሐእንደመጣም አይነት እንደሚመጣ እንዲያምኑ በትእግስት አጥብቀው በመምከር በትጋት አገለገሉ። እናም በዚህ ሁኔታ አስተምረዋቸው ነበር።
፲፪ እናም እንዲህ ሆነ ይህን በማድረግ ከምድር ፊት ሀእንዳይጠፉ ጠበቋቸው፤ ልባቸውንም በቃላት ለወቀሱት፣ በማከታተልም ለንስሀ አነሳሷቸው።
፲፫ እናም እንዲህ ሆነ ለብዙ ጊዜ ከነበረው የጦርነትና ግጭት እንዲሁም የፀብ ሁኔታ ሁለት መቶ ሠላሳ ስምንት ዓመታት አለፉ።
፲፬ እናም እኔ ጄረም፣ ሰሌዳዎቹ ትንሽ በመሆናቸው፣ ከዚህ የበለጠ አልፅፍም። ነገር ግን እነሆ፣ ወንድሞቼ፣ ወደ ሀሌላኛው የኔፊ ሰሌዳዎች መሄድ ትችላላችሁ፤ እነሆ፣ በእነርሱ ላይ ይፃፉ ዘንድ ባደረጉት፣ ወይም እንደ ነገሥታቱ አፃፃፍ የጦርነት ታሪኮች ተቀርፀዋል።
፲፭ እናም እንደ አባቶቼ ሀትዕዛዛት መሰረት ይጠበቁ ዘንድ እነዚህን ሰሌዳዎች ለወንድ ልጄ፣ ለኦምኒ፣ አስረክባለሁ።