ቅዱሳት መጻህፍት
ሔለማን ፲፮


ምዕራፍ ፲፮

ሳሙኤልን የሚያምኑ ኔፋውያን በኔፊ ተጠመቁ—ሳሙኤል ንስሃ ባልገቡ ኔፋውያን ቀስቶች እንዲሁም ድንጋይ ሊገደል አልቻለም—ጥቂቶች ልባቸውን አጠጠሩ እናም ሌሎች መላዕክቶችን ተመለከቱ—የማያምኑት፣ በክርስቶስ እናም በኢየሩሳሌም ስለመምጣቱ ማመን ትርጉም የለውም አሉ። ከ፮–፩ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንግዲህ፣ እንዲህ ሆነ በከተማዋ ግንብ ሳሙኤል ላማናዊው ሲናገር ቃሉን ያዳመጡት ብዙዎች ነበሩ። በቃሉ ያመኑ ሁሉ ሄዱና ኔፊን ፈለጉት፤ እናም በመጡና እርሱን ባገኙት ጊዜ፣ በጌታም ለመጠመቅ ፈልገው፣ ኃጢአታቸውን ለእርሱ ተናዘዙ፣ እናም አልካዱም።

ነገር ግን የሳሙኤልን ቃላት የማያምኑ ሁሉ በእርሱ ተቆጥተው ነበር፤ እናም በግንቡም ላይ ድንጋይ ወረወሩበት፣ እናም ደግሞ በግንቡ ላይ ቆሞ ሳለ ቀስቶቻቸውን ወረወሩበት፤ ነገር ግን በድንጋዮቻቸው ሆነ በበቀስቶቻቸው ሊመቱት እስከማይችሉ ድረስ የጌታ መንፈስ ከእርሱ ጋር ነበር።

እንግዲህ እርሱን መምታት እንዳልቻሉ በተመለከቱ ጊዜ፣ በኔፊ ለመጠመቅ እስከሚሄዱ ድረስ በቃሉ ያመኑ ብዙዎች ነበሩ።

እነሆም፣ ክርስቶስ በቅርቡ መምጣቱን ያውቁ ዘንድ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን በማሳየት፣ ኔፊ አጥምቋልም፣ ተንብዮአልም፣ እናም ሰብኳል፤ በመጮህም ንስሃን ለህዝቡ ተናግሯል፤ በህዝቡም መካከል ተዓምራቶች ሰርቷል—

በቅርቡ ስለሚመጡትም ነገሮች ለእነርሱ በመንገር፣ እንዲያምኑ ባለው አላማ ምክንያት በሚመጡበት ጊዜም ቀደም ብለውም እንዲያውቁት ተደርጎ እንደነበር እንዲያውቁ እና እንዲያስታውሱ ዘንድ አሳይቶአቸዋል፤ ስለዚህ የሳሙኤልን ቃላት ያመኑት ሁሉ ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሄዱ፤ ንስሃ በመግባት፣ እና ኃጢአታቸውንም በመናዘዝ መጥተዋልና።

ነገር ግን ብዙዎቹ የሳሙኤልን ቃላት አያምኑም ነበር፤ ስለዚህ በድንጋይ እንዲሁም በቀስታቸው እርሱን ለመምታት አለመቻላቸውን በተገነዘቡ ጊዜ፣ ወደ ሻምበሎቻቸው እንዲህ በማለት ጮሁ፥ ይህንን ሰው ውሰዱትና እሰሩት፣ የዲያብሎስ መንፈስ አለበትና፤ እናም በውስጡ ባለው የዲያብሎስ ኃይልም በድንጋይም ሆነ በቀስት ልንመታው አልቻልንም፤ ስለዚህ ያዙትና እስሩት፣ እናም ወዲያ ውሰዱት።

እናም እጃቸውን ሊጭኑበት በሄዱ ጊዜም፣ እነሆ፣ እራሱን ከግንቡ ላይ ዘለለና፣ ከምድራቸው ሸሸ፤ አዎን ወደ ራሱም ሃገር ሸሸ፣ እናም በራሱ ህዝብ መካከልም መስበክና መተንበይ ጀመረ።

እናም እነሆ፣ ከዚህም በኋላ ኔፋውያን ምንም ስለእርሱ አልሰሙም፤ እናም የህዝቡ ጉዳዮች ይኸው ነበሩ።

እናም በኔፊ ህዝብ ላይ የመሣፍንቱ ሰማንያ ስድስተኛ የንግስና ዘመን ተፈፀመ።

እናም አብዛኞቹ ሰዎችም ከነኩራታቸው እንዲሁም ኃጢአታቸው እየቀሩ፤ እናም ጥቂቶቹ ክፍሎች በእግዚአብሔር ፊት በጥንቃቄ እየተራመዱ፣ የመሣፍንቱ ሰማንያ ሰባተኛ የንግሥና ዘመን ደግሞም እንደዚህ ተፈፀመ።

፲፩ እናም ደግሞ በመሣፍንቱ ሰማንያ ስምንተኛ የንግስና ዘመን ሁኔታዎቹ እነዚህ ነበሩ።

፲፪ እናም ነገር ግን በመሣፍንቱ ሰማንያ ዘጠነኛ ዓመት የንግስና ዘመን በክፋት ይበልጥ ከመጠጠራቸው፣ እናም በይበልጥ ከእግዚአብሔር ትዕዛዛት ተቃራኒ የሆኑትን በተጨማሪ ከሚሰሩት በስተቀር በሰዎች ጉዳዮች ላይ ትንሽ የሚሆን ለውጥ አልነበረም።

፲፫ ነገር ግን እንዲህ ሆነ በመሣፍንቱ ዘጠናኛ የንግስና ዘመን፣ ለህዝቡ ታላቅ ምልክቶች፣ እና ድንቆች፣ ተሰጥተዋቸው ነበር፤ እናም የነቢያቱ ቃላትም መፈፀም ጀምረው ነበር።

፲፬ እናም መላዕክት ለሰዎች ጠቢብ ለሆኑ ሰዎችም ታዩአቸው፣ እናም እነርሱ የታላቁ ደስታ የምስራችን ነገሩአቸው፤ በዚህም ዓመት የቅዱሳት መጻሕፍት ትንቢቶችም እንዲህ መፈፀም ጀመሩ።

፲፭ ይሁን እንጂ፣ ኔፋውያንና ደግሞ ላማናውያን ከሆኑት፣ ከሁሉም በላይ ከሚያምኑት በቀር ሰዎች ልባቸውን ማጠጠር ጀመሩ፤ እናም በጉልበታቸውና በጥበባቸው እንዲህ በማለት መመካትም ጀመሩ፥

፲፮ ከብዙዎች መካከል ጥቂት ነገሮችን በትክክል ገምተዋል፤ ነገር ግን እነሆ፣ የተነገሩት እነዚህ ታላቅ እንዲሁም ድንቅ ስራዎች ሁሉ እንደማይመጡ እናውቃለን።

፲፯ እናም ምክንያት በማቅረብምና እርስ በእርሳቸው እንዲህ በማለት መጣላት ጀመሩ፥

፲፰ እንዲህ ያለ ክርስቶስ የሚባል ፍጡር ይመጣል ማለት ተገቢ አይደለም፤ ይህም ከሆነ፣ እናም እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ፣ እንደተባለውም የሰማይና የምድር አባት ከሆነ በኢየሩሳሌም ላሉት እንደሚያደርገው ለምን እራሱን ለእኛም አይገልፅም?

፲፱ አዎን፣ በኢየሩሳሌም ምድር እንደሚያደርገው እራሱን ለምን በዚህች ምድርም አያሳይም?

ነገር ግን እነሆ፣ ይህ በእኛ መካከል ሳይሆን ነገር ግን ራቅ ባለ ምድር፣ በማናውቀው ምድር በሚመጣው ታላቅ እና አስገራሚ ነገር እንድናምን የሚያደርግ በአባቶቻችን የተላለፈልን ክፉ ወግ እንደሆነ እናውቃለን፤ ስለዚህ እውነት መሆናቸውን በዓይናችን ለመመስከር ስለማንችል፣ ባለማወቅ እንድንቆይ ማድረግ ይችላሉ።

፳፩ እናም ቃልን እንዲያስተምሩን በእነርሱ ስለምንመካ፣ በጮሌነትና፣ በክፉው ሚስጥራዊ ጥበብ፣ እኛን ለቃላቶቻቸው አገልጋዮች እንድንሆንና፣ እንድናገለግላቸው ዝቅ አድርጎ የሚያስቆየን፣ እኛ ልንረዳው የማንችለውን ታላቅ ሚስጥር ይሰራሉ፤ እናም በህይወት ዘመናችን ሁሉ እራሳችንን ለእነርሱ አሳልፈን ከሰጠን እንደዚህ በድንቁርና ያቆዩናል።

፳፪ እናም ህዝቦች የማይረቡና ከንቱ በሆኑት ልባቸው ከዚህ የበለጡ ብዙ ነገሮችን ገመቱ፤ እናም ሰይጣን ያለማቋረጥ ክፋት እንዲሰሩ ስለሚበጠብጣቸው ይበልጥ ተረብሸው ነበር፤ አዎን፣ እርሱም መልካም በነበሩት እና በሚመጣው ላይ ልባቸውን ያጠጥሩ ዘንድ አሉባልታንና፣ ፀብን በምድሪቱ ገፅ ሁሉ ላይ ለማሰራጨት ሄዷል።

፳፫ እናም በጌታ ህዝቦች መካከል ምልክቶችና አስገራሚ ስራዎች ቢከናወኑም፣ እናም ብዙ አስደናቂ ነገሮችን ቢያደርጉም፣ ሰይጣን በምድር ገፅ ላይ ሁሉ ባሉ የሰዎች ልብ ታላቅ ሥፍራን ይዟል።

፳፬ እናም በኔፊ ህዝብ ላይ የመሣፍንቱ ዘጠናኛው የንግሥ ዘመን እንደዚህ ተፈፀመ።

፳፭ እናም በሔለማንና በወንድ ልጆቹ ዘገባ መሰረት የሔለማን መጽሐፍ እንዲህ ተጠናቀቀ።