መፅሐፈ ኢኖስ
ምዕራፍ ፩
ኢኖስ በኃይል ፀለየ እናም ለኃጢአቱ ስርየትን አገኘ—ለላማናውያን ወደፊት በሚመጣው ደህንነታቸው ተስፋ ያለው የጌታ ድምፅ ወደ አዕምሮው መጣ—ኔፋውያን ላማናውያንን ለመመለስ ጣሩ—ኢኖስ በቤዛው ይደሰታል። ከ፬፻፳ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እነሆ፣ እንዲህ ሆነ እኔ ሀኢኖስ ለአባቴ ፃድቅ ሰው እንደነበር ስለማውቅ—በራሱም ቋንቋ እናም ደግሞ በጌታ ሐአስተዳደግና ተግሳፅ መስላስተማረኝ፣ እናም ለዚህ የአምላኬ ስም የተባረከ ይሁን—
፪ እናም ሀለኃጢአቴ ስርየትን ከማግኘቴ በፊት በእግዚአብሔር ፊት ስለነበረኝ ለትግል እነግራችኋለሁ።
፫ እነሆ፣ አራዊትን ለማደን ወደጫካው ሄድኩ፤ እናም አባቴ ዘለዓለማዊ ህይወትንና የቅዱሳንን ሀደስታ በተመለከተ ሁልጊዜ ሲናገር የምሰማቸው ቃላት ወደልቤ ለጠልቀው ገቡ።
፬ እናም ነፍሴ ሀተራበች፤ በፈጣሪዬም ፊት ለተንበረከክሁ፣ እናም ለነፍሴ በሀይለኛ ሐፀሎትና ልመና ወደእርሱ ጮህኩኝ፣ እናም ቀኑን ሙሉ ወደ እርሱ ጮህኩኝ፤ አዎን፣ ምሽቱ ሲመጣ ድምፄን ሰማይ እስከሚደርስ ከፍ አደረግሁት።
፭ እናም ሀድምፅ ወደእኔ መጣ፣ እንዲህም አለኝ፥ ኢኖስ ኃጢያትህ ይቅር ተብሎልሃል እናም አንተ ትባረካለህ።
፮ እናም እኔ ኢኖስ እግዚአብሔር ሊዋሽ እንደማይችል አውቃለሁ፤ ስለሆነም፣ በደሌ ተወግዶልኛል።
፯ እናም ጌታ፣ ይህ እንዴት ሆነ? አልኩት።
፰ እናም እርሱም አለኝ፥ ባላየኸውና ሰምተህ በማታውቀው በክርስቶስ ባለህ ሀእምነት ምክንያት ነው። እናም እራሱን በአካል ከመግለፁ በፊት ብዙ አመታት ያልፋሉ፤ ስለሆነም፣ ሂድ እምነትህ ለአድኖሃል።
፱ አሁን፣ እንዲህ ሆነ እነዚህን ቃላት በምሰማ ጊዜ ለኔፋውያን ወንድሞቼ ደህንነት ሀማሰብ ጀመርኩ፤ ስለሆነም፣ ለእነርሱ ነፍሴን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ለአፈሰስኩ።
፲ እናም እንደዚህ በመንፈስ በምታገልበት ጊዜ፣ እነሆ፣ የጌታ ድምፅ ሀበአዕምሮዬ በድጋሚ መጥቶ እንዲህ አለኝ፤ ወንድሞችህ ትዕዛዛቴን ለመጠበቅ ባላቸው ትጋት መሰረት እጎበኛቸዋለሁ። ለእነርሱም ይህን ምድር ለሰጥቻቸዋለሁ፣ ይህችም ቅዱስ ምድር ናት፤ በክፋት የተነሳ ካልሆነ በቀር ሐአልረግማትም፤ ስለሆነም፣ በተናገርኩት መሰረት ወንድሞችህን እጎበኛቸዋለሁ፤ እናም መተላለፋቸውን በራሳቸው ላይ በሀዘን አወርዳለሁ።
፲፩ እናም እኔ ኢኖስ፣ እነዚህን ቃላት ከሰማሁ በኋላ እምነቴ በጌታ የማይናወጥ ሆነ፤ እናም ለወንድሞቼ ላማናውያን በብዙ ረጅም ትግል ወደ እርሱ ፀለይኩ።
፲፪ እናም እንዲህ ሆነ ባለኝ በሙሉ ትጋት ከሰራሁና ሀከፀለይኩ በኋላ፣ ጌታም አለኝ፥ በእምነትህ የተነሳ ለእንደተመኘኸው መሰረት እሰጥሀለሁ።
፲፫ እናም አሁን እነሆ፣ ከእርሱ የፈለግሁት ፍላጎት ይህ ነበር—የእኔ ህዝብ ኔፋውያን በመተላለፋቸው መውደቅ ካለባቸውና በምንም አይነት ሀመጥፋትም ቢኖርባቸው፣ ላማናውያንም መጥፋት ከሌለባቸው፣ ጌታ አምላክ የህዝቤን የኔፋውያን ታሪክ ለእንዲጠብቅ ዘንድ፤ እንዲሁም፣ በቅዱስ ክንዱ ኃይልም እንኳን ቢሆን፣ ይህም ወደፊት አንድ ቀን ለላማናውያን ሐይመጡ ዘንድ፣ ምናልባት ወደ ደህንነት መይመጡ ዘንድ—
፲፬ ለጊዜው እነርሱን ወደ እውነተኛው እምነት የመመለሱ ትግል ሀከንቱ ነበር። እናም ታሪካችንና እኛን፣ ደግሞም የአባቶቻችንን ባህል ሁሉ የሚቻላቸው ከሆነ ለያጠፉ ዘንድ በቁጣቸው ማሉ።
፲፭ ስለሆነም፣ ጌታ እግዚአብሔር ታሪካችንን ሀማስቀመጥ እንደሚቻለው ስለማውቅ፣ ያለማቋረጥ ወደ እርሱ ጮህኩኝ፣ እርሱም እንዲህ ብሎኛልና፥ በክርስቶስ ስም እንደምትቀበል ካመንህ ምንም ነገር በእምነት ብትጠይቅ ትቀበላለህ።
፲፮ እናም እኔ እምነት ነበረኝ፣ እናም ሀመዝገቦቹን ለእንዲያስቀምጥ ወደ እግዚአብሔር ጮህኩ፤ በእርሱ ዘመን ለላማናውያን ሐእንደሚያመጣውም ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን ገባ።
፲፯ እናም እኔ ኢኖስ፣ በገባው ቃል ኪዳን መሰረት እንደሚሆን አውቃለሁ፤ ስለዚህ ነፍሴም እረፍትን አገኘች።
፲፰ እናም ጌታ አለኝ፥ አባቶችህም ደግሞ ስለዚህ ነገር ከእኔ ይፈልጉ ነበር፤ እናም ለእነርሱ እንደእምነታቸው ይደረግላቸዋል፤ እምነታቸው ልክ እንደአንተው ነበርና።
፲፱ እናም አሁን እንዲህ ሆነ እኔ ኢኖስ፣ የሚመጡትን ነገሮች በመተንበይ በኔፋውያን ህዝብ መካከል ተጓዝኩ፣ እናም የሰማኋቸውንና ያየኋቸውን ነገሮች መሰከርኩ።
፳ እናም የኔፊ ህዝብ ላማናውያንን ወደ እውነተኛው የእግዚአብሔር እምነት እንዲመልሱ በትጋት እንደሚመክሩ እመሰክራለሁ። ነገር ግን ሀስራችን ከንቱ ነበር፤ ጥላቻቸው የፀና ነበር፣ እናም በመጥፎ ተፈጥሮአቸው ተመርተው ስለነበር አረመኔ፣ አስፈሪም፣ ለደም የተጠማ ህዝብና፣ ሐጣኦትን አምላኪና ርኩሳን ሆኑ፤ የታደኑ አውሬዎችን በመመገብ፤ በድንኳን መኖርና፣ በምድረበዳ ውስጥ አጭር የቆዳ ግልድም አገልድመው እራሳቸውን ተላጭተው ተዘዋወሩ፤ እናም ችሎታቸውም መስለቀስትና ደጋን እንዲሁም ምሳር ነበር። እናም ብዙዎች ከጥሬ ስጋ በስተቀር ምንም አይበሉም ነበር፤ እናም እነሱ ያለማቋረጥ እኛን ለማጥፋት ይፈለጉ ነበር።
፳፩ እናም እንዲህ ሆነ የኔፊ ህዝብ መሬትን ያርሱ ነበር፣ እናም ሁሉንም አይነት እህልና ፍራፍሬ ሀያበቅሉ፣ የከብት መንጋዎችን፣ ከሁሉም የከብት አይነት መንጋዎችን፣ ፍየሎችን፣ የሜዳ ፍየሎችን፣ እናም ደግሞ ብዙ ፈረሶችን ያረቡ ነበር።
፳፪ እናም ከእኛ መካከል እጅግ ብዙ ሀነቢያት ነበሩ። እናም ህዝቡ ለመረዳት የሚያስቸግር ለአንገተ ደንዳና ነበር።
፳፫ እናም እጅግ ሀአስከፊ ከሆነው የጦርነት ለሰበካና ትንቢት፣ እናም ፀብና ጥፋት፣ እንዲሁም ያለማቋረጥ ሞትን ሐከሚያስታውሳቸውና፣ ከዘለዓለማዊ ጊዜ፣ ፍርድና ከእግዚአብሔር ኃይል፣ በጌታ ፍርሃት መያለማቋረጥም ይጠበቁ ዘንድ ካነሳሳቸው በስተቀር ምንም የለም። ከእነዚህ ነገሮችና እጅግ ታላቅ የሆነው ግልፅ ንግግር በስተቀር ወደ ጥፋት በፍጥነት ከመሄድ የሚጠብቃቸው ምንም ነገር አልነበረም እላለሁ። እናም በእንደዚህ አይነት እነሱን በተመለከተ እፅፋለሁ።
፳፬ እናም በጊዜዬ በኔፋውያንና በላማናውያን መካከል ጦርነቶችን ተመልክቻለሁ።
፳፭ እናም እንዲህ ሆነ እየሸመገልኩ ሄድኩ፣ እናም አባታችን ሌሂ ኢየሩሳሌምን ሀለቆ ከወጣ አንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ አመታት አለፉ።
፳፮ እናም በእግዚአብሔር ኃይል ለዚህ ህዝብ መስበክና እንድተነብይ፣ እናም በክርስቶስ ባለው እውነት መሰረት ቃሉን እንድናገር እንደተገፋፋሁ በቶሎ ወደ መቃብሬ መሄድ እንዳለብኝ ተመለከትኩ። እናም በዘመኔ ሁሉ ተናግሬዋለሁ፣ በዚህም ከዓለም በላይ ተደስቼበታለሁ።
፳፯ እናም ከቤዛዬ ጋር ወደሆነው ሀማረፊያዬ በቶሎ እሄዳለሁ፤ በእርሱ እንደማርፍ አውቃለሁና። እናም ለየሚሞተው ሐየማይሞተውን በሚተካበትና፣ በእርሱ ፊት በምቆምበት ቀን እደሰታለሁ፤ ከእዚያም ፊቱንም በደስታ አያለሁ፣ እርሱም ይለኛል፥ የተባረከው ወደ እኔ ና፣ በአባቴም መቤት የተዘጋጀልህ ቦታ አለ። አሜን።