አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
አባሪ፦ ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜልክ ማዘጋጀት


“አባሪ፦ ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜልክ ማዘጋጀት፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 ( እ.አ.አ)]

“አባሪ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)

አባሪ

ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜልክ ማዘጋጀት

እርሱ ስለሚወዳችሁ፣ ስለሚያምናችሁ እና ችሎታችሁን ስለሚያውቅ፣ የሰማይ አባት ልጆቻችሁን በቃል ኪዳን መንገድ ማለትም ወደ ዘለአለማዊ ህይወት ወደሚመራው መንገድ ውስጥ እንዲገቡ እና እንዲያድጉ እንድትረዱ እድሉን ሰጥቷችኋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥25–28 ይመልከቱ)። ይህ እንደ የጥምቀት ቃል ኪዳን እና በቤተመቅደስ ውስጥ የሚደረጉ ቃል ኪዳኖች የመሳሰሉ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ለማድረግ እና ለመጠበቅ እንዲዘጋጁ እነርሱን መርዳትን ያካትታል። በእነዚህ ቃል ኪዳኖች አማካኝነት ልጆቻችሁ እራሳቸውን ከአዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያስተሳስራሉ።

በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ለሚያደርጉት ለዚህ ጉዞ ልጆቻችሁን ለማዘጋጀት ብዙ መንገዶች አሉ፣ እናም እነርሱን ለመርዳት የተሻለውን መንገድ እንድታገኙ የሰማይ አባት ይረዳችኋል። መነሳሳትን ስትሹ የሚሰጡ ትምህርቶች ሁሉ ለትምህርቶቹ በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሰረት እንደማይከናወኑ አስቡ። በእርግጥ በቤት መማርን በጣም ኃያል ከሚያደርገው ነገር መካከል በቀን ተቀን የህይወት ሂደት በተፈጥሮ የሚከሰት ዓይነት በምሳሌ እና በትንሽ ቀለል ባሉ ወቅቶች የመማር እድል ነው። የቃል ኪዳን መንገድን መከተል ቀጣይነት ያለው የህይወት ሂደት እንደሆነ፣ ስለ ቃል ኪዳኑ መንገድ መማርም ቀጣይነት አለው። (“Home and Family [ቤት እና ቤተሰብ]፣” Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር] [2022 እ.አ.አ]፣ 30–31።)

ምስል
እናት ከልጅ ጋር

በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለሚያደርጉት ጉዞ ልጆቻችሁን ለማዘጋጀት ብዙ መንገዶች አሉ።

ወደተጨማሪ መነሳሳት የሚያመሩ የተወሰኑ ሃሳቦች ከታች ቀርበዋል። የመጀመሪያ ክፍል ልጆችን ለማስተማር የሚሆኑ ተጨማሪ ሃሳቦችን በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍሎች ውስጥ ከሚገኘው “ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ለእድሜልክ ማዘጋጀት” በሚለው ርዕስ ስር ለማግኘት ትችላላችሁ።

ጥምቀት እና ማረጋገጥ

ወደ ቃል ኪዳን መንገድ “የምንገባበት በር፣ ንስሃ እና በውኃ መጠመቅ” እንደሆነ ኔፊ አስተምሯል (2 ኛ ኔፊ 31፥17)። ልጆቻችሁን ለጥምቀት እና ማረጋገጫ ለማግኘት እንዲዘጋጁ የመርዳት ጥረቶቻችሁ እግሮቻቸው በዛ መንገድ ላይ እንዲጸኑ ማድረግ ይችላሉ። እነዚህ ጥረቶች በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን እና ንስሃን በማስተማር ይጀምራሉ። እንዲሁም በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባንን በመካፈል የጥምቀት ቃል ኪዳኖቻችንን እንዴት እንደምናድስ ያካትታሉ።

ሊረዷችሁ የሚችሉ ግብዓቶች እነሆ፦ 2ኛ ኔፊ 31፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “ጥምቀትtopics.ChurchofJesusChrist.org.

  • በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን እምነት የሚያጠነክር ልምድ በሚኖራችሁ ጊዜ ሁሉ፣ ለልጃችሁ አካፍሉ። እምነት እድሜ ልክ ሙሉ እያደገ ሊሄድ የሚችል ነገር እንደሆነ እንዲገነዘብ/እድትገነዘብ እርዱት ወይም እርዷት። የእናንተ ልጅ መጠመቅ በፊት በክርስቶስ ጠንካራ እምነት እንዲያዳብር ማድረግ የምትችሏቸው የተወሰኑ ነገሮች ምን ምን ናቸው?

  • ልጃችሁ የተሳሳተ ምርጫ ሲያደርግ፣ ስለንስሃ ስጦታ በደስታ ተናገሩ። እናም እናንተ የተሳሳተ ውሳኔ ካደረጋችሁ በኋላ ንስሃ ስትገቡ የሚመጣውን ደስታ አካፍሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሃጢያቶቻችን ስለተሰቃየ እና ስለሞተ የመለወጥ ኃይልን እንደሰጠን መስክሩ። ልጃችሁ ይቅርታን ሲፈልግ፣ በነፃ እና በደስታ ይቅር በሉ።

  • ስለጥምቀታችሁ ለልጃችሁ ንገሩ። ፎቶዎችን አሳዩ እንዲሁም ትውስታዎችን አካፍሉ። እንዴት እንደተሰማችሁ፣ የጥምቀት ቃል ኪዳኖቻችሁ ኢየሱስ ክርስቶስን የበለጠ እንድታውቁት እንዴት እንደረዳችሁ እና ህይወታችሁን መባረክ መቀጠላቸውን ተናገሩ። ልጃችሁ ጥያቄዎችን እንዲጠይቅ አበረታቱ።

  • በቤተሰባችሁ ወይም በአጥቢያችሁ ውስጥ ጥምቀት ሲኖር፣ ልጃችሁ እንዲየይ ውሰዱ። ልጃችሁ እና እናንተ ስላያችኋቸው እና ስለተሰማችኋቸው ነገሮች ተነጋገሩ። ከተቻለ፣ ከሚጠመቀው ግለሰብ ጋር ተነጋገሩ እንዲሁም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቁ፦ “ይህንን ውሳኔ እንዴት ነው የወሰንከው? እንዴት ነው የተዘጋጀኸው?”

  • ልጃችሁ ለማድረግ ቃል የገባውን ነገር ሲያደርግ ስትመለከቱ፣ ከልብ በሆነ ስሜት አወድሱ። ለማድረግ ቃል በገባናቸው ነገሮች መጽናት ስንጠመቅ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች እንድንጠብቅ እንድንዘጋጅ እንደሚረዳን ጠቁሙ። ስንጠመቅ ለእግዚአብሔር የምንገባው ቃል ምንድን ነው? እርሱስ ለእኛ ቃል የሚገባው ምንድን ነው? (ሞዛያ 18፥8–10፣ 13 ተመልከቱ)።

  • እናንተ እና ልጃችሁ በጋራ ቅዱስ ልምድ ሲኖራችሁ (ለምሳሌ በቤተክርስቲያን ውስጥ ቅዱሳት መጻህፍትን ስታነቡ ወይም አንድን ሰው ስታገለግሉ) ስለሚሰሟችሁ መንፈሳዊ ስሜቶች ወይም መነሳሳቶች ንገሩት/ሯት። ልጃችሁ ስለሚሰማው/ማት ነገር እንዲያካፍል/እንድታካፍል ጋብዙ። ለእናንተ በግለሰብ ደረጃ የሚናገርባቸውን መንገዶችም ጨምሮ መንፈስ ለሰዎች የሚናገርባቸውን የተለያዩ መንገዶች አስተውሉ። ልጃችሁ የመንፈስ ቅዱስን ተፅዕኖ ያየበትን/ያየችበትን ሁኔታዎች እንዲያለዩ አግዙ።

  • በወንጌል ቤተ መጻህፍት ስብስቦች ውስጥ “እርሱን ስሙት!“ በሚል ርዕስ ስር ያሉትን የተወሰኑ ቪዲዮዎች በጋራ ተመልከቱ። የጌታ አገልጋዮች እርሱን ስለሚሰሙባቸው የተለያዩ መንገዶች ተነጋገሩ። ልጃችሁ የአዳኝን ድምፅ እንዴት እንደሚሰማ/እንደምትሰማ ስዕል እንዲስል/እንድትስል ወይም ቪድዮ እንዲሰራ/እንድትሰራ ጋብዙ።

  • የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል መሆን እንዴት እንደባረካችሁ ተናገሩ። ሌሎችን ስታገለግሉ እና ሌሎች እናንተን ሲያገለግሉ ወደ የሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መቅረብ የቻላችሁት እንዴት ነው? እንደ የቤተክርስቲያን አባል ልጃችሁ ሌሎችን ለማገልገል እና ለማጠንከር የሚችልባቸውን መንገዶች እንዲያስብ አግዙ።

  • ቅዱስ ቁርባንን በቤተሰባችሁ ውስጥ የተቀደሰ እና አስደሳች ክስተት አድረጉት። በቅዱስ ቁርባን ወቅት ልጃችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ለማተኮር የሚችልባቸውን መንገዶች እንዲያቅድ አግዙ። ቅዱስ ቁርባን ለእኛ ቅዱስ እንደሆነ የምናሳየው እንዴት ነው?

  • የጓደኛ መጽሔት እትም በአብዛኛው ጊዜ ልጆች ለጥምቀት እና ማረጋገጫ ለማግኘት እንዲዘጋጁ ለመርዳት የታሰቡ ፅሁፎችን፣ ታሪኮችን እና እንቅስቃሴዎችን ያካትታል። ልጆቻችሁ የተወሰነ መርጠው ከእናንተ ጋር እዲያነቡ እና እንዲደሰቱ ፍቀዱላቸው። (በተጨማሪም በወንጌል ቤተ መጻህፍት የልጆች ክፍል ውስጥ “ለጥምቀት መዘጋጀት” በሚለው ስር ያሉትን ስብስቦች ተመልከቱ።)

    ምስል
    ወንድ ልጅ ሲጠመቅ

    ወደ ቃል ኪዳን መንገድ “የምንገባበት በር፣ ንስሃ እና በውኃ መጠመቅ” እንደሆነ ኔፊ አስተምሯል (2 ኛ ኔፊ 31፥17)።

ልጆቻችሁን ስለ ክህነት ማስተማር

ክህነት እግዚአብሔር ልጆቹን የሚባርክበት የእርሱ ስልጣን እና ኃይል ነው። የእግዚአብሔር ክህነት ዛሬ በምድር ላይ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አለ። ቃል ኪዳናቸውን የሚጠብቁ ሁሉም የቤተክርስቲያን አባላት በቤታቸው ውስጥ እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ለማጠንከር በእግዚአብሔር የክህነት ኃይል ይባረካሉ (General Handbook: Serving in The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints [አጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል]3.5 ይመልከቱ ChurchofJesusChrist.org). ይህ ኃይል አባላቶች በግል እና በቤተሰቦቻቸው ህይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን የደህንነት እና በዘለአለም ህይወት ከፍ የመደረግ ስራን ሲሰሩ ይረዳል (General Handbook [አጠቃላይ መጽሐፍ]2.2 ይመልከቱ)።

በክህነት ስልጣን አማካኝነት ስርዓቶችን እንቀበላለን። ወንዶች እና ሴቶች በቤተክርስቲያን ጥሪዎች ውስጥ ሲያገለግሉ የክህነት ቁልፎችን በያዙ ሰዎች ምሪት ስር በመሆን በክህነት ስልጣን አማካኝነት ያገለግላሉ። ሁሉም የሰማይ አባት ልጆች—ወንድ ልጆቹም እና ሴት ልጆቹም—ክህነትን የበለጠ ለመረዳት ሲመጡ ይባረካሉ።

ስለክህነት የበለጠ ለመማር፣ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “መንፈሳዊ ሀብቶች፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2019 (እ.አ.አ)፣ 76–79፤ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የክህነት ኃይል ዋጋ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 66–69፤ “Priesthood Principles [የክህነት መርሆዎች]፣” ምዕራፍ 3 በ General Handbook [አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ] ውስጥ ይመልከቱ።

  • የክህነት ስርዓቶችን ቀጣይነት ያላቸው የህይወታችሁ ክፍሎች አድርጓቸው። ለምሳሌ፣ ልጃሁን በየሳምንቱ ለሚደረገው የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ በመንፈስ እንዲዘጋጅ እርዱ። ሲታመም/ስትታመም ወይም መፅናናት ወይም አቅጣጫ ሲያስፈልገው/ጋት፣ ልጃችሁ የክህነትን በረከቶች እንዲሻ/እንድትሻ አበረታቱ። ጌታ በክህነት ኃይል ቤተሰባችሁን እየባረከ ያለበትን መንገዶች መጠቆምን ልምድ አድርጉ።

  • ቅዱሳት መጻህፍትን በጋራ ስታነቡ፣ እግዚአብሔር ህዝቡን በኃይሉ አማካኝነት እንዴት እንደሚባርክ ለመወያየት እድሎችን ፈልጉ። እግዚአብሔር በክህነቱ አማካኝነት እናንተን የባረከበትን ልምዳችሁን አካፍሉ። በክህነት አማካኝነት ከእግዚአብሔር ስለምንቀበላቸው በረከቶች ምሳሌዎች General Handbook [አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ]3.23.5 ይመልከቱ።

  • በቤተሰባችሁ ውስጥ የአንድ ሰውን የክህነት ስልጣን መስመር ተማሩ። (የመልከጸዴክ ክህነት ተሸካሚዎች የስልጣን መስመር ቅጂ ኢሜልን ለሚከተለው በመላክ መቀበል ትችላላችሁ LineofAuthority@ChurchofJesusChrist.org፤ እንዲሁም “የክህነት የመስመር ስልጣን መጠይቅ [Request a Priesthood Line of Authority]” በእርዳታ ማዕከል ውስጥ ይመልከቱ ChurchofJesusChrist.org.) የክህነት ስልጣን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከራሱ እንደሚመጣ ማወቅ ለምን ጠቃሚ እንደሆነ ተናገሩ። እርሱን ለእኛ ይህን የሚያጋራው ለምንድን ነው?

  • ከጥምቀት በኋላ ልጆቻችሁ የጥምቀትን ቃል ኪዳን በመጠበቅ የክህነት ኃይልን መቀበል እንደሚችሉ አስተምሩ። የፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን መልዕክትን “መንፈሳዊ ሀብቶች፣” በጋራ ከልሱ (ሊያሆና፣ ህዳር 2019 (እ.አ.አ)፣ 76–79 ይመልከቱ)። የክህነት ስርዓቶች የእግዚአብሔርን ሃይል ወደ ህይወታችሁ እንዴት እንዳመጡ ለልጆቻችሁ ንገሩ። በክህነት ኃይል ስለምንባረክባቸው የተወሰኑ መንገዶች ዝርዝር ለማግኘት General Handbook [አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ]3.5 ይመልከቱ።

  • “የጌታ አገልጋይ ምን ዓይነት ነው?” የሚለውን ጥያቄ ተወያዩበት። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥36–42 በጋራ አንብቡ እና መልሶችን ፈልጉ። ልጆቻችሁ (ወይም ሌላ ሰው) በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ካሉት አንዱን መርህ ባህርይ ተግባራዊ ሲያደርጉ ስትመለከቱ ጠቁሙ።

  • እናንተ ወይም ልጃችሁ በርን ለመክፈት ወይም መኪናን ለማስነሳት ቁልፍን ሲጠቀም፣ የክህነት መሪዎች ከያዙት ቁልፎች ጋር ለማነጸጸር የአፍታ ጊዜ ውሰዱ። (ለክህነት ቁልፎች ትርጉም General Handbook [አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ]3.4.1 ይመልከቱ)። የክህነት ቁልፎች ለእኛ “የሚከፍቱት” ወይም “የሚያስነሱት” ምንድን ነው? እንዲሁም ጌሪ ኢ. ስቲቭንሰን፣ “የክህነት ቁልፎች እና ስላጣን የት ናቸው?፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 29-32፤ “ቁልፎቹ የት ናቸው?” (ቪዲዮ) ChurchofJesusChrist.org.

  • ለጥሪ ስትለዩ የሚቻል ከሆነ ልጃችሁ እንዲገኝ ጋብዙ። ልጃችሁ ጥሪያችሁን ስታሟሉ እንዲያይ አድርጉ። ልጆቻችሁ ሊያግዟችሁ የሚችሉበትን ተገቢ መንገዶች መፈለግም ትችላላችሁ። የጌታን ኃይል በጥሪያችሁ ውስጥ እንዴት እንደሚሰማችሁ ግለፁ።

ወደ ቤተመቅደስ መሄድ—ለሙታን ጥምቀቶች እና ማረጋገጫዎች

ቤተመቅደሶች የሰማይ አባት ለልጆቹ ያለው ዕቅድ አካል ናቸው። ሁሉም ነገሮች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚጠቁሙበት በቤተመቅደስ ውስጥ፣ በቅዱስ ስርዓቶች ስንሳተፍ ከሰማይ አባት ጋር ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን እናደርጋለን። የሰማይ አባት በዚህ ህይወት ስርዓቶቹን ያልተቀበሉትን ጨምሮ ሁሉም ልጆቹ ቃል ኪዳኖችን እዲገቡ እና በስርዓቶች እንዲሳተፉ መንገድን ሰጥቷል። ልጃችሁ 12 ዓመት በሚሆንበት/በምትሆንበት የዓመቱ መጀመሪያ ላይ፣ ልጃችሁ በቤተመቅደስ ውስጥ ለሞቱ ቅድመ ዓያቶች ለመጠመቅ እና ማረጋገጫ ለማድረግ በቂ ነው።

ስለሙታን ጥምቀቶች እና ማረጋገጫዎች የበለጠ ለመማር “ስለ ውክል ጥምቀት እና ማረጋገጫ [About Proxy Baptism and Confirmation]፣” ይመልከቱ። temples.ChurchofJesusChrist.org.

  • ሁኔታችሁ በሚፈቅዱላችሁ ጊዜ ሁሉ ደጋግማችሁ በቤተመቅደስ ተሳተፉ። ቤተመቅደስ ለምን እንደምትሄዱ እና ወደ ሰማይ አባት እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመቅረብ እንዴት እንደሚረዳችሁ ለልጃችሁ ተናገሩ።

  • የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ጥያቄዎችን በጋራ ከልሱ እንዲሁም ተወያዩ። በቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ቃለ መጠይቅ ወቅት ስለሚሆነው ነገር ለልጃችሁ ተናገሩ። ለእናንተ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ መያዝ ለምን ለእናንተ አስፈላጊ እንደሆነ አካፍሉ።

  • ሚልክያ 4፥6ን በጋራ አንብቡ። ልቦቻችሁ ወደ ቅድመ ዓያቶቻችሁ እንዴት እንደሚመለስ ተናገሩ። የቤተሰብ ታሪካችሁን በጋራ በመፈለግ ስለቅድመ ዓያቶቻችሁ የበለጠ ተማሩ FamilySearch.org. መጠመቅ እና ማረጋገጫ መቀበል የሚያስፈልጋቸውን የቅድመ ዓያቶች ፈልጉ። የአጥቢያ የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ አማካሪ ሊረዳችሁ ይችላል።

  • በወንጌል ቤተ መጻህፍት የልጆች ክፍል ውስጥ “ቤተመቅደስ” በሚለው ርዕስ ስር ካሉት ስብስቦች ውስጥ የተወሰኑትን ግብዓቶች በጋራ ከልሱ። (ደግሞም “ለቤተመቅደስ ጥምቀቶች እና ማረጋገጫዎች ልጆቻችሁን ማዘጋጀት” የሚለውን በ ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ።)

የፓትርያርክ በረከትን መቀበል

የፓትርያርክ በረከት የምሪት፣ የመፅናናት እና የመነሳሳት ምንጭ ሊሆን ይችላል። ከሰማይ አባት ለእኛ የተሰጠ የግል ምክርን ይይዛል እንዲሁም የዘለአለም ማንነታችንን እና ዓላማችንን እንድንገነዘብ ይረዳናል። የፓትርያርክ በረከቶችን ጠቀሜታ እና ቅዱስ ተፈጥሮ በማስተማር ልጃችሁ የፓትርያርክ በረከትን ለመቀበል እንዲዘጋጅ እርዱ።

የበለጠ ለመማር የወንጌል ርዕሶች፣ “የፓትርያርክ በረከቶች” ይመልከቱ topics.ChurchofJesusChrist.org.

  • የፓትርያርክ በረከትን የመቀበል ልምዳችሁን ለልጃችሁ አካፍሉ። ለመቀበል እንዴት እንደተዘጋጃችሁ፣ ወደ እግዚአብሔር የበለጠ ለመቅረብ እንዴት እንደረዳችሁ እና በረከቱን በህይወታችሁ ውስጥ እንዴት እንደምትጠቀሙበት የመሳሰሉትን ነገሮች ልታካፍሉ ትችላላችሁ። ልጃችሁ የፓትርያርክ በረከትን ከተቀበሉ ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር እንዲነጋገር መጋበዝ ትችላላችሁ።

  • በወንጌል ርዕሶች፣ “ፓትርያርክ በረከቶች” ውስጥ ያሉ አንዳንድ ግብዓቶችን በጋራ ለመከለስ ጊዜ ውሰዱ። የፓትርያርክ በረከትን ስለመቀበል ሂደት ለመማር General Handbook [አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ]18.17 ይመልከቱ።

  • የፓትርያርክ በረከቶችን የተቀበሉ የቅድመ ዓያቶች ካሏችሁ የተወሰኑትን ከልጃችሁ ጋር ማንበብ የሚያነሳሳ ሊሆን ይችላል። የሞቱ ቅድመ ዓያቶችን በረከቶች ለመጠየቅ፣ በሚከተለው አካውንት ይግቡ ChurchofJesusChrist.orgበገፁ በቀኝ ጥግ ላይ በኩል ያለውን የአካውንቱን ምስል ይጫኑ እና “የፓትርያርክ በረከት” የሚለውን ይምረጡ።

  • ልጃችሁ የፓትርያርክ በረከትን ከተቀበለ በኋላ፣ የተሰማቸውን ስሜት ለመመዝገብ እና ለልጃችሁ ለማጋራት የተገኙ ማንኛውም የቤተሰብ አባሎች ጋብዙ።

ወደ ቤተመቅደስ መሄድ—መንፈሳዊ ስጦታ

እግዚአብሔር ሁሉንም ልጆቹን “ከላይ የሚመጣ ኃይል” ሊባርክ ይፈልጋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 95፥8)። የግላችንን መንፈሳዊ ስጦታ ለመቀበል አንዴ ብቻ ወደ ቤተመቅደስ እንሄዳለን፣ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርጋቸው ቃል ኪዳኖች እና እንደ መንፈሳዊ ስጦታ አካል የሚሰጠን መንፈሳዊ ኃይል በህይወታችን ውስጥ በየቀኑ ሊባርኩን ይችላሉ።

ስለ ቤተመቅደስ ቡራኬ የበለጠ ለመማር “ስለ ቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታዎች” temples.ChurchofJesusChrist.org፤ ረስል ኤም. ኔልሰን “ለቤተመቅደስ በረከቶች መዘጋጀት፣” ኢንዛይን ጥቅምት. 2010 (እ.አ.አ)፣ 41–51 ይመልከቱ።

  • የቤተመቅደስን ምስል በቤታችሁ ውስጥ ስቀሉ። በቤተመቅደስ ውስጥ የተሰማችሁን ስሜት ለልጃችሁ ንገሩ። ለጌታ እና ለቤቱ እንዲሁም እዚያ ስለገባችኋቸው ቃል ኪዳኖች ያላችሁን ፍቅር በተደጋጋሚ ለልጃችሁ ንገሩ።

  • በጋራ ፈልጉ temples.ChurchofJesusChrist.org. ስለቤተመቅደስ ቡራኬ እና ለቤተመቅደስ በረከቶች ተዘጋጁ ያሉ ጽሁፎችን በጋራ አንብቡ። ልጆቻችሁ ስለቤተመቅደስ ያሏቸውን ማናቸውንም ጥያቄዎች እንዲጠይቁ ፍቀዱላቸው። ከቤተመቅደስ ውጪ ስለምን ማውራት እንደምትችሉ ምሪት ለማግኘት የሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር መልዕክትን “Prepared to Obtain Every Needful Thing” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019, 101–4፤ በተለይም “Home-Centered and Church-Supported Learning and Temple Preparation [በቤት የተመሰረተ እና በቤተክርስቲያን የተደገፈ ትምህርት እና ለቤተመቅደስ መዘጋጀት]” የሚለውን ይመልከቱ)።

  • እናንተ እና ልጆቻችሁ በስርዓቶች ውስጥ ስትሳተፉ ወይም ሌላ (እንደ ቅዱስ ቁርባን ወይም የፈውስ በረከት) ስርዓቶችን ስትመለከቱ በስርዓቱ ውስጥ ያለውን ምልክት ለመወያየት ጊዜ ውሰዱ። ምልክቶቹ ምንን ይወክላሉ? ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ይመሰክራሉ? ይህ ልጃችሁ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክሩ የቤተመቅደስ ስርዓቶችን የምልክት ትርጉም ለማሰላሰል እንዲዘጋጅ ሊረዳ ይችላል።

  • ልጃችሁ በሞዛያ 18፥8–10፣ 13 የተገለፀውን የጥምቀት ቃል ኪዳን እየጠበቀ/ቀች ስለመሆኑ/ኗ እንዲገነዘብ/እንድትገነዘብ እርዱ። እንዲሁም ጌታ ልጃችሁን እንዴት እየባረከው/ካት እንዳለ እንዲገነዘብ/እንድትገነዘብ አግዙ። ልጃችሁ ያለውን/ላትን ቃል ኪዳኖችን የመጠበቅ ችሎታ መተማመን ገንቡ።

  • የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖቻችሁ ምርጫዎቻችሁን ስታደርጉ እንዴት እንደመራችሁ እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትቀርቡ እንዴት እንደረዳችሁ በግልፅ እና በተደጋጋሚ ተናገሩ። በቤተመቅደስ ውስጥ የምንገባቸውን ቃል ኪዳኖች ለመከለስ General Handbook [አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ]27.2ን መጠቀም ትችላላችሁ።

በሚስዮን ማገልገል

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፦ “ለማገልገል የምትዘጋጁበት በጣም ጠቃሚ የሆነው ነገር ቢኖር፣ ወደ ሚስዮን ከመሄዳችሁ ከረዥም ጊዜ በፊት ሚስዮናዊ መሆን ነው። … ጉዳዩ ወደ ሚስዮን መሄድ አይደለም፤ ከዚያ ይልቅ ጉዳዩ ሚስዮናዊ መሆን እና በመላ ህይወታችን ውስጥ በሙሉ ልባችን፣ ሃይላችን፣ አዕምሮአችን፣ እና ጥንካሬአችን ማገልገል ነው። … ለእድሜልክ የሚስዮናዊ ስራ እየተዘጋጃችሁ ነው” (“Becoming a Missionary [ሚስዮን መሆን]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2005 (እ.አ.አ)፣ 45–46)። ልጃችሁ ሚስዮናዊ በመሆን ያሉት ልምዶች ሚስዮናዊ በመሆን በሚያገለግልበት/በምታገለግልበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለዘለአለም ይባርከዋል/ይባርካታል።

የበለጠ ለመማር፣ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Preaching the Gospel of Peace [የሰላምን ወንጌል መስበክ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 6–7፤ ኤም. ራስል ባላርድ፣ “Missionary Service Blessed My Life Forever [የሚስዮን አገልግሎት ህይወቴን ለዘለአለም ባረከ]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 8–10፤ Missionary Preparation: Adjusting to Missionary Life [ለሚስዮን ዝግጅት፦ ህይወትን ሚስዮን ወደመሆን ማስተካከል፣ ይመልከቱ ChurchofJesusChrist.org.

  • ተፈጥሯዊ በሆኑ መንገዶች ወንጌልን በማካፈል ረገድ ምሳሌ ሁኑ። ለሌሎች ስለ የሰማይ አባት እና ስለ አዳኝ እንዲሁም የእርሱ ቤተክርስቲያን አባል በመሆናችሁ ስለተቀበላችኋቸው በረከቶች የሚሰማችሁን ስሜቶች ለማካፈል ለሚገኙት እድሎች ሁሌም ንቁ ሁኑ። በቤተክርስቲያን ውስጥ እና ቤተሰብ ነክ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ሌሎች ሰዎች ከቤተሰባችሁ ጋር እንዲቀላቀሉ ጋብዙ።

  • ቤተሰባችሁ ከሚስዮናውያን ጋር መስተጋብር የሚፈጥሩበትን እድሎች ፈልጉ። ጓደኞቻችሁን እንዲያስተምሩ ጋብዟቸው ወይም ሰዎችን በቤታችሁ ውስጥ እንዲያስተምሩ ፍቀዱላቸው። ሚስዮናውያን ስላሏቸው ልምዶች እና የሚስዮናዊ አገልግሎት እንዴት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲቀርቡ እየረዳቸው እንደሆነ ጠይቋቸው። ሚስዮናዊ ለመሆን ለመዘጋጀት ምን እንዳደረጉ (ወይም ይህን አድርገን ቢሆን ኖሮ ብለው የሚመኟቸውን ነገሮች እንዳሉ) ጠይቋቸው።

  • በሚስዮን አገልግላችሁ የምታውቁ ከሆነ ስለልምዳችሁ በግልፅ እና በተደጋጋሚ ተናገሩ። ወይም በሚስዮን ያገለገሉ ጓደኞች ወይም የቤተሰብ አባሎች እንዲናገሩ ጋብዙ። ወንጌልን በመላ ህይወታችሁ ለሌሎች ስላካፈላችሁባቸው መንገዶችም መናገር ትችላላችሁ። ልጃችሁ ወንጌልን የሚያካፍልበት መንገዶች እንዲያስብ አግዙ።

  • ልጃችሁ የወንጌልን መርሆዎች ለቤተሰባችሁ እንዲያስተምር እድሎችን ስጡ። ልጃችሁ እምነቱን/ቷን ከሌሎች ጋር ማካፈልም ይችላል/ትችላለች። ለምሳሌ፣ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን መወያየት ትችላላችሁ፦ “መጽሐፈ ሞርሞንን ሰምቶት ለማያውቅ ሰው እንዴት ማስተዋወቅ እንችላለን?” ወይም “ክርስቲያን ላልሆነ ሰው የአዳኝን አስፈላጊነት እንዴት መግለፅ እንችላለን?”

  • ልጃችሁ ከሰዎች ጋር መነጋገር በማለማመድ አግዙ። ንግግርን ለመጀመር የተወሰኑ መልካም መንገዶች ምንድን ናቸው? ሌሎች የሚሉትን ለመስማት፣ በልባቸው ውስጥ ያለውን ለመረዳት እና ህይወታቸውን ሊባርክ የሚችሉ የወንጌል እውነቶችን እንዴት ማካፈል እንደሚችል/እንደምትችል እንዲማር/እንድትማር ልጃችሁን አበረታቱ።

  • ልጃችሁን ስለ ሌላ ባህሎች እና እምነቶች ለማስተማር እድሎችን ፈልጉ። በሌሎች እምነቶች ውስጥ ያሉ መልካም እና ትክክለኛ መርሆዎችን እንዲገነዘብ/እንድትገነዘብ እና እንዲያከብር/እንድታከብር እርዱ።

ወደ ቤተመቅደስ መሄድ—እትመት

በቤተመቅደስ ውስጥ ባል እና ሚስት ለዘለአለም መጋባት ይችላሉ። ይህ እትመት በሚባል ስርዓት ውስጥ ይከሰታል። ምንም እንኳን ይህ ስርዓት ለወንድ ወይም ሴት ልጃችሁ ከብዙ ዓመታት በኋላ የሚከሰት ቢሆንም፣ በእነዚያ ዓመታት ውስጥ በጋራ የምታደርጉት ትንሽ፣ ቀላል፣ ቀጣይነት ያላቸው ነገሮች ለዚህ አስደናቂ በረከት እንዲዘጋጅ/እንድትዘጋጅ ይረዳል።

የበለጠ ለመማር “እትመት፣” የሚለውን በወንጌል ርዕሶች ውስጥ ይመልከቱ topics.ChurchofJesusChrist.org.

  • ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅን” በጋራ አንብቡ ChurchofJesusChrist.org. በቤተሰብ ህይወት ውስጥ ስለ ደስታ እና ስለ ውጤታማ ጋብቻ ይህ አዋጅ ምን ያስተምራል? በአዋጁ ውስጥ ከተጠቀሱት መርሆዎች አንዱን ከልጃችሁ ጋር ለማጥናት ምረጡ ። ከዚያ መርህ ጋር የሚዛመዱ ቅዱሳት መጻህፍትን በየቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ ውስጥ ማየት ትችላላችሁ። ያንን መርህ በህይወታችሁ ውስጥ በይበልጥ ለመተግበር ግቦችንም ማቀድ ትችላላችሁ። ግቦቻችሁ ለማከናወን ስትሰሩ፣ ያንን መርህ መኖር በህይወታችሁ ላይ ያለውን ተፅዕኖ በጋራ ተወያዩ።

  • የፕሬዚዳንት ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ መልዕክት “የሚያድኑትን በማመስገን” [ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ) 77–80] ከልጃችሁ ጋር አንብቡ። “ተጠቅሞ የሚጥል ህብረተሰብ፣” ወደሚለው ክፍል ስትደርሱ በቤታችሁ ውስጥ ሊጣሉ የሚቻሉ እና የማይቻሉ ነገሮችን መፈለግ ትችላላችሁ። ነገሮች ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ ስትፈልጉ ነገሮችን እንዴት በተለየ መልኩ እንደምትንከባከቡ ተናገሩ። የጋብቻን እና የቤተሰብ ግንኙነቶችን እንዴት መንከባከብ እንደሚገባን ይህ ምን ሀሳብ ያቀርባል? ከፕሬዚዳንት ኡክዶርፍ መልዕክት አዳኙ ጠንካራ ጋብቻን እና ቤተሰቦችን ለመገንባት እንዴት እንደሚረዳችሁ ሌላ ምን ትማራላችሁ?

  • ያገባችሁ ከሆነ፣ እንደ ጥንድ መልካም እያደረግን ነው ብላችሁ ስለሚሰሟችሁ ነገሮች፣ እየተማራችኋቸው ስላሉት ነገሮች እና ለመሻሻል ስለምትሞክሩባቸው መንገዶች ለልጃችሁ ግልፅ ሁኑ። እናንተና የትዳር አጋራችሁ በቤተመቅደስ ውስጥ ከታተማችሁ፣ እርስ በእርስ እና ከጌታ ጋር ቃል ኪዳናችሁን ለመጠበቅ እንዴት እንደምትጥሩ ለልጃችሁ በምሳሌ አሳዩ። የሰማይ አባትን እና አዳኙን የግንኙነታችሁ ማዕከል ለማድረግ እንዴት እንደምትጥሩ እና እንዴት እንደሚረዷችሁ ለልጃችሁ ንገሩ።

  • የቤተሰብ ውሳኔዎች መደረግ ሲኖርባቸው፣ የቤተሰብ ምክርን እና ውይይትን አድርጉ። የሁሉም የቤተሰብ አባሎች ሃሳብ መሰማቱን እና ዋጋ መሰጠቱን አረጋግጡ። ሁሉም ነገሮችን በተመሳሳይ መንገድ ባያዩትም ጤነኛ ንግግርን እና በቤተሰብ ግንኙነቶች ውስጥ በጎነትን ምሳሌ ለማድረግ እነዚህን ውይይቶች እንደ እድሎች ተጠቀሙ።

  • በቤተሰብ ውስጥ አለመግባባት ወይም ግጭት ሲኖር፣ ትህትናን እና ርህራሄን አሳዩ። ልጃችሁ ግጭትን በክርስቶስ መሰል መንገዶች እንዲያይ መርዳት ለደስተኛ ትዳር እንዲዘጋጅ ሊረዳው እንደሚችል አሳዩ። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥41–42ን በጋራ አንብቡ እና በዚህ ቁጥሮች ውስጥ ያሉ መርሆዎች እንዴት በትዳር ላይ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተናገሩ።