2023 (እ.አ.አ)
የግል ሰላምን ማግኘት
ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)


ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)

የግል ሰላምን ማግኘት

ከዋናው ጽሁፍ የወጣ አጭር ክፍል።

ምስል
ልጣፍ

ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን የግል ሰላምን ስለማግኘት ተአምር የተማርኩትን ዛሬ እናገራለሁ። …

ከአዳኙ አስተምህሮቶች ቢያንስ አምስት እውነቶችን ተምሬያለሁ።

በመጀመሪያ፣ የሰላም ስጦታ የሚሰጠው ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ የሚያስችል እምነት ካዳበርን በኋላ ነው። …

ሁለተኛ፣ መንፈስ ቅዱስ ይመጣል እንዲሁም ከእኛ ጋር ይሆናል። …

ሶስተኛ፣ ቃልኪዳኖችን ስንጠብቅ፣ አብ እና ልጁ፣ አንዳችን ለአንዳችን እንዲሁም ለእኛ ያላቸው ፍቅር ሊሰማን ይችላል።

አራተኛ፣ የጌታን ተዕዛዛት መጠበቅ ከታዛዥነት የበለጠ ነገርንም ይጠይቃል። እግዚአብሄርን በፍጹም ልባችን በፍጹም ነፍሳችን በፍጹም አሳባችን መውደድ ይገባናል። …

አምስተኛ፣ ጌታ የሃጢያታችንን ዋጋ እስኪከፍልልን ድረስ እንደሚወደን ግልፅ ነው። ይኸም የሚሆነው በእርሱ በማመን እና ንስሃ በመግባት፣ በእርሱ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት ነው። እኛም በዚህ አለም እና ከእርሱ ጋር ለዘለአለም “አዕምሮን ሁሉ የሚያልፍ” [ፊልጵስዩስ 4፥7] የሰላም ስጦታ ልናገኝ እንችላለን።

በመላ ቤተክርስቲያኗ የሚገኙ አባላት የጌታ የግል ሰላም ስጦታ ተሰምቷቸዋል። ሌሎች ወደ እርሱ ለመምጣት እድሎችን እንዲያገኙ እንዲረዱ እና ራሳቸውም ለዚያ ሰላም ብቁ እንዲሆኑ ሁሉንም ሰዎች እያበረታታ ነው። እነርሱም በተራቸው ያንን ስጦታ ወደሌሎች እንዴት ማስተላለፍ እንደሚችሉ ለማወቅ መነሳሳትን መሻትን ይመርጣሉ።

መጪው ትውልድ የተከታዩ ትውልድ ተንከባካቢ ይሆናል። የማዳረስ ውጤቱ ተአምር ይፈጥራል። በጊዜ ሂደት ይስፋፋና ያድጋል፣ ከዚያም በምድር ላይ ያለችው የጌታ መንግስት ትዘጋጃለች እንዲሁም ሆሣዕና እያለች ልትቀበለው ዝግጁ ትሆናለች። በምድር ላይ ሰላም ይሆናል።