2023 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች
ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)


ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች

ከዋናው ጽሁፍ የወጣ አጭር ክፍል።

ምስል
ልጣፍ

ነቢዩ ኔፊ እንዲህ ሲል እንዳስተማረን ማድረግ አለብን፣ “የክርስቶስን ቃል ተመገቡ እላችኋለሁ፤ እነሆም የክርስቶስ ቃል ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች በሙሉ ይነግራችኋል”1 …የዛሬው መልእክቴ አዳኛችን የተናገራቸውንየተመረጡ ቃላትም ያካትታል። …

“[ከህግ ውስጥ ታላቂቱ ትዕዛዝ ይህች ናት፦] ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።

“ይህች ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትዕዛዝ ናት።

“ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርስዋም ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ የምትለው ናት።

“በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።”2

“እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ዘወትር ንቁ መሆን እና መፀለይ አለባችሁ፤ አለበለዚያ በዲያብሎስ ትፈተናላችሁ እናም የእርሱ ምርኮኛም ትሆናላችሁ።3

“ስለዚህ፣ ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ በስሜ አድርጉት፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያኗን በስሜ ጥሯት። ”4

“እንግዲህ ትዕዛዜ ይህች ናት፥ በምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ ንሰሃ ግቡ፣ እናም መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ትቀደሱ ዘንድ፤ በመጨረሻው ቀን በፊቴ ያለእንከን ትቆሙ ዘንድ ወደ እኔ ኑ፣ እናም በስሜ ተጠመቁ። ”5

በክርስቶስ እናምናለን። ትምህርቶቹን እንዴት ማወቅ እና መከተል እንዳለብን በተናገረው እቋጫለሁ፦

“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አፅናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የንገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።”6