2023 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተን የሚያጠነክርበት 4 መንገዶች
ጥር 2023 (እ.አ.አ)


“ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተን የሚያጠነክርበት 4 መንገዶች፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ጥር 2023 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ጥር 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተን የሚያጠነክርበት 4 መንገዶች

በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።
ፊልጵስዩስ 4፥13

ምስል
ካይርን

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ክርስቲያኖች በዚህ ቅዱስ ጽሁፍ ይደሰታሉ፦ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” (ፊልጵስዮስ 4፥13)።

ሰዎች ይህንን ሲሰሙ፣ አንዳንዶቹ ማንኛውንም ፈተና ማለፍ እንደሚችሉ፣ ማንኛውንም ጨዋታ ማሸነፍ እንደሚችሉና ሁሉም ምኞቶች እውን ይሆናሉ ማለት ነው ብለው ያስባሉ። ሆኖም ይህ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅስ የሚያስተምረው ያንን አይደለም።

ይህ የተጻፈው በሐዋርያው ጳውሎስ ሲሆን የጻፈውም በእስር ቤት እያለ ነበር። እንደ እስረኛ፣ ጳውሎስ ማድረግ የማይችላቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ፤ ሆኖም ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉ በላይ አስፈላጊ የሆነውን ነገር እንዲያደርግ ሊያጠነክረው እንደሚችል ያውቅ ነበር።

ለእናንተም ተመሳሳይ ነው።

1 ክርስቶስ ማወቅ እንድትችሉ ያጠነክራችኋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ እውነት የሆነውን ማወቅ የምትችሉባቸውን በርካታ ጠቃሚ መንገዶች ሰጥቷችኋል። ሁል ጊዜ እንድንጸልይ (3 ኔፊ 18፥18 ተመልከቱ) እና እውነት የሆነውን እንድናውቅ (ሞሮኒ10፥4–5 ተመልከቱ) ሁላችንንም አስተምሮናል። እንዲሁም በቅዱሳት መጻህፍት ጥናታችሁ እውነት የሆነውን ነገር መፈለግ እና ማወቅ ትችላላችሁ።

ጸሎት እና የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት መንፈሱን ወደ ህይወታችሁ ያመጣሉ። መንፈሱ “በአዕም[ሯችሁ] እና በልባችሁ” ሊናገር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 8፥2)፣ “ነፍ[ሳችሁ] በደስታ ሊሞላ፣” እና “አዕም[ሯችሁ] ሊበራ” ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11፥13)።

በእነዚህ መንገዶች “እርሱን ልትሰሙት”—የአዳኙን ቃላት መስማት እና የተናገራቸውን ነገሮች መከተል—ትችላላችሁ። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “የዚህ ህይወት ውጤታማነት፣ ደስታ፣ እና ሀሴት ንድፍ” ይህ እንደሆነ አስተምረዋል።1

2 ክርስቶስ ማድረግ እንድትችሉ ያጠነክራችኋል።

ጥንካሬ ወደ እናንተ የሚመጣው ትዕዛዛትን ለመጠበቅ እንዲሁም ወደ ሰላም እና ወደ ደስታ የሚመራን ጥሩ ምርጫ ለማድረግ ስትጥሩ ነው። እነዚህን ምርጫዎች ማድረግ ከባድ በሚሆንበት ጊዜም እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን እንድታደርጉ ያጠነክራችኋል። አንዳንድ ጊዜ መጥፎ ውሳኔዎችን ልታደርጉ ትችላላችሁ። ደስ የሚለው ነገር፣ የአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ንስሃ መግባትን የሚቻል ያደርገዋል። በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ንጹህ ልትሆኑ እና ደስታን ልታገኙ ትችላላችሁ። በየቀኑ የተሻለ “እንድታደርጉ እና የተሻለ እንድትሆኑ2 ሊያጠነክራችሁ ይችላል፡፡

3 ክርስቶስ መቋቋም እንድትችሉ ያጠነክራችኋል።

እስር ቤት በነበረበት ወቅት ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል፣ “የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬያለሁ፡፡

“መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬየለሁ” (ፊልጵስዩስ 4፥11–12)።

በሌላ አነጋገር ጳውሎስ፣ በክርስቶስ አማካኝነት ፈተናዎቹን መቋቋም እንደሚችል እንዲሁም ከፈተናዎቹ እና ከተግዳሮቶቹ እንደሚማር አወቀ። ኢየሱስ ክርስቶስ ተመሳሳይ ነገር እንድታደርጉ ሊያጠነክራችሁ ይችላል፡፡

አዳኙ “በመከራና በሁሉም ዓይነት ህመምና ፈተናዎች” ተሰቃየ፡፡ “ህዝቡን ከድካሙ እንዴት እንደሚረዳ [ማለትም እንደሚያግዝ] ያውቅ ዘንድ” ድካማችንን በላዩ ላይ አደረገ (አልማ 7፥11–12)። ምንም ነገር ቢያጋጥማችሁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትጸኑ እና በራሳችሁ ልታደርጉ የማትችሉትን ነገር ማከናወን እንድትችሉ ሊያጠነክራችሁ ይችላል።

4 ክርስቶስ መሆን ያለባችሁን እንድትሆኑ ያጠነክራችኋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤን ለሁላችንም እውን አድርጓል፣ እንዲሁም ንስሐ ለሚገቡ፣ አስፈላጊ ሥርዓቶችን ለሚቀበሉ እና ከእነርሱ ጋር የሚያያዙ ቃል ኪዳኖችን ለሚያደርጉ የዘላለም ህይወት የሚቻል እንዲሆን ያደርጋል። ያለ ክርስቶስ፣ የሰማይ አባት በጣም የሚፈልገውን መፈጸም አንችልም—ይኸውም ይበልጥ እርሱን እና ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንመስልና ለዘለአለም ከእነርሱ ጋር እንድንኖር ነው።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ

ከእርሱ ስትማሩ፣ በእርሱ ላይ ስትደገፉ እና ስትታመኑ፣ እንዲሁም የእሱን ምሳሌ ስትከተሉ፣ ይበልጥ ኢየሱስ ክርስቶስን መምሰል ትችላላችሁ። ይህ በበለጠ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር፣ ትዕግስት፣ ትህትና፣ ንጽህና እና መታዘዝ ወደ መኖር ይመራችኋል። እነዚህ ሁሉ የአዳኙ ባህርያት ናቸው።

ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ስትጥሩ ልትሆኑ እንደምትችሉ የሚያውቀውን ሁሉ እንድትሆኑ የሚመራችሁ ተስፋችሁ እና ብርሃናችሁ ይሆናል። ከዚያም ከጳውሎስ ጋር “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” ለማለት ትችላላችሁ።