2010 (እ.አ.አ)
በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ ውስጥ የመሳተፈ ሀላፊነታችን
ዲሴምበር 2010


የሴቶች የቤት ለቤት መልእክት፣ ታህሳስ 2010 (እ.አ.አ)

በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ ውስጥ የመሳተፈ ሀላፊነታችን

ይህን መልእክት አጥኑ፣ እና ትክክል በሆነውም ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩ። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን በህይወታችሁ ውስጥ የሚሳተፍ ክፍል እንዲኖራት ለማድረግ እንዲረዷችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

ምስል

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ካለፉት መቶ አመታት ብዙ ህዝቦች ስለወንጌሉ እውቀት ሳይኖራቸው ሞተዋል። እነዚያም አንዳንድ ህዝቦች የእናንተ የቅርብ እና የሩቅ ቤተሰቦቻችሁ ናቸው። እነርሱም ቤተሰቦቻችሁን ለማያያዝ እና ለእነርሱም የሚያድነውን ስነስርዓት ለማከናወን የሚያስፈልጋችሁን እንድትመረምሩ ይጠብቋችኋል።

ብዙዎቹ የአለም ቤተመቅደሶች ስራ የበዛባቸው አይደሉም። ጌታ ልቦቻችሁ ወደ አባቶቻችሁ እንደሚዞሩና ስለዚህ መላው ምድር በምጽአቱ እንደማይጠፋ ቃል ገብቷል (D&C 2:2–3 ተመልከቱ)።

በቤተመቅደስ ውስጥ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ምክንያት የምንቀበላቸው የግል በረከቶች አሉ። ከእነዚህ አንዱም ቅድመ አያቶቻችሁን ስታገለግሉ የሚሰማችሁ ደስታ ነው። ሌላውም ለጌታ ብቁነታችሁን የሚገልጸውን የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ለማግኘት ብቁ ስትሆኑ ነው። ይህን ፈቃድ የማግኘት እድል በዚህ ቀን ብቁ ያልሆኑት ከኤጲስ ቆጶስ ወይም ከቅርንጫፍ ፕሬዘደንት ጋር ወዲያው ብቁ ለመሆን እንዲችሉ መስራት ይገባቸዋል። እባካችሁ ይህ በጣም አስፈላጊ የሆነ ብቁነት ሳይኖራችሁ አትቅሩ። የኃጥያት ክፍያው እውነተኛ እንደሆነ እና ትክክለኛው በሆነው መንገድ ንስሀ በመግባት ኃጥያቶች ስርየት ለማግኘት እንደሚችሉ እመሰክራለሁ።

በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ ላይ ስንሳተፍ፣ በፈተናችን እንዲያፅናናን እና በአስፈላጊው ውሳኔዎቻችን እንዲመራን መንፈስ እንደሚኖረን እርግጠኛ ነን። የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ እርዳታ የመስጠት ስራችን ወይም ለቅድመ አያቶቻችን የምናገለግልበት የስራ ክፍላችን ነው።

ከታሪካችን

“ነቢዩ ጆሴፍ እንዳለው፣ ‘ጌታ ከሰጠን ሀላፊነቶች ታላቁ ሙታኖቻችንን መፈለግ ነው’ (History of the Church, 6:313)። ከመጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች ይህን ታላቅ ስራ ደግፈዋል። በ1842 (እ.አ.አ) ፣ ሴራ ኤም ኪምባል የቤተመቅደስ ሰራተኞችን ለመርዳት የነበራት ፍላጎት የሴቶች ቡድኖች በውጤታማነት ለማገልገል እንዲችሉእራሳቸውን እንዲያደራጁ ገፋፋቸው። መሰብሰብ ሲጀምሩ፣ ነቢዩ… የክህነት ስልጣን ንድፍን በመከተል የሴቶች መረዳጃ ማህበርን አደራጀ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች የናቩ ቤተመቅደስ ስራን ለማከናወን ረዱ።

“በ1855 (እ.አ.አ) ቅዱሳን ወደ ዩታ ከደረሱ ከስምንት አመት በኋላ፣ የመንፈስ ስጦታ ቤት ተመሰረተ። የመጀመሪያው የሴቶች መረዳጃ ማህበር አባል ከነበሩት አንድ የነበሩት እና የዚያን ድርጅት መዝገብ የጠበቁት እላይዛ አር ስኖው በፕሬዘደንት ብሪገን ያንግ በ1866 (እ.አ.አ) እንደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ተጠርተው ነበር። እርሳቸው እና ሌሎች እህቶች በመንፈስ ስጦታ ቤት ውስጥ ታማኝ ሰራተኞች ነበሩ። ከዛም፣ የሴይንት ጆርጅ፣ የሎገን፣ እና የማንታይ ቤተመቅደሳት ሲጨረሱ፣ እነዚህ እህቶች ወደእያንዳንዱ ቤተመቅደስ ለሙታን ስራዎችን ለማከናወን ተጓዙ።1

ማስታወሻ

  1. Mary Ellen Smoot, “Family History: A Work of Love,” Ensign, መጋቢት 1999, 15።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. እህቶቼን ቅድመ አያቶቻቸውን ፈልገው ለማግኘት እና የቤተመቅደስ ስራዎቻቸውን ለማከናወን እንዲችሉ እንዴት ለመርዳት እችላለሁ? የእያንዳንዷን እህት ጉዳይ የሚያስፈልጋትን እንዴት ለማሟላት በምታሰላስሉበት ጊዜ አስቡ። የቤተሰብ ታሪክ ስራ አዲስን፣ የምትመለስን፣ እና ሁልጊዜም ተሳታፊ ያልሆኑትን አባላት እንደሚያጠናክር አስቡበት።

  2. የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ መቼ አፅናንቶኛል ወይም በአስፈላጊ ውሳኔዎች ላይ መርቶኛል?

ለተጨማሪ መረጃዎች ወደ www.reliefsociety.lds.org ሂዱ።