2010–2019 (እ.አ.አ)
አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ለማግኘት መዘጋጀት
የሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ለማግኘት መዘጋጀት

በዳግም የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለመማር እና ለማፍቀር ያለንን የግል ሀላፊነታችንን ለመወጣት ስንጥር የማካካሻ በረከቶች እንደሚመጡ እመሰክራለሁ።

ባለፉት አጠቃላይ ጉባኤዎች ወቅት በተዋወቁት ተከታታይ ማሻሻያዎች ፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሮግራሞች እና እንቀስቃሴዎች ቤትን ያማከሉ እና በቤተክርስቲያን የተደገፉ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንደመከሩን፥ “ገና ብዙ የሚመጡም አሉ ። … የቫይታሚን ኪኒናችሁን ዋጡ። እረፍት አድርጉ። ይህም የሚያስደስት ይሆናል።”1

በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሚደረጉት ማሻሻያዎች ምን አይነት መሰረታዊ አንደምታ እንዳላቸው አብረን ስናጤን የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ ለማግኘት እጸልያለሁ እና እጋብዛለሁ።

ቤትን ያማከለ እና በቤተክርስቲያን የሚደገፍ የወንጌል ትምህርት

በቅርብ በነበረው የክህነት መሪዎች ጉባኤ ውስጥ ሽማግሌ ክሬግ ሲ. ክርስቲያንሰን ከእኔ ጋር አብረው ሄደው ነበር፣ እናም ቤትን ያማከለ በቤተክርስትያን የተደገፍን ስለመሆን ሊያጠናክሩ የሚችሉ መርሆዎችን ለማብራራት ሁለት ጥያቄዎችን አነሱ። በእሁድ ከቤተክርስቲያን ስብሰባዎች በኋላ ወደቤትሰንመለስ “ስለአዳኝ እና ስለወንጌሉ ዛሬ በቤተክርስቲያን ምን ተማርን?” ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ በቤተክርስቲያን ስብሰባዎቻችን ወቅት፣ “ስለአዳኝ እና ስለወንጌሉ በቤታችሁ ውስጥ ምን ተምራችኋል?” ብለን መጠየቅ ይገባናል። ትክክለኛ የሰንበት ቀን አከባበር፣ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት፣ እና የተሻሻለው የስብሰባ ሰዓት በሙሉ ወንጌሉን በቤቶቻችን እና በቤተክርስቲያን ውስጥ እንድንማር ይረዱናል።

እያንዳንዱ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል የጌታን ትምህርት ለመማር እና በዚህም ለመኖር እናም በትክክለኛው ስልጣን የደህንነት እና ከፍ የማለትን ስርዓቶችለመቀበል የግል ሀላፊነቶች አሉበት። እኛም መለኮታዊ ደቀመዛሙርት ለመሆን እና እስከመጨረሻ በጥንካሬ ለመፅናት የሚያስፈልጉንን ቤተክርስቲያኗ እንደ ተቋም እንድታስተምረን ወይን እንድትነግረን መጠበቅ አይገባንም።2 ይልቁንም፣ የግል ሀላፊነታችን መማር ያለብንን ለመማር፣ መኖር እንዳለብን በምናውቀው መልኩ ለመኖር፣ እናም መምህር እንድንሆን የሚፈልገንን ለመሆን ነው። ቤቶቻችንም ለመማር፣ ለመኖር፣ እና ለመሆን ከሁሉም የተሻሉ አመቺ ቦታዎች ናቸው።

፣ ጆሴፍ ስሚዝ እንደማንኛውም ልጅ ስለእግዚአብሔር ከቤተሰቡ ተማረ። እግዚአብሔር ስለእርሱ ያለውን ፍላጎት ለማወቅ በነበረው ጥረት ጆሴፍ እውነትን በተለያዩ የክርስtያን የሀይማኖት ተቋማት ውስጥ እንዲፈትሽ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን በትጋት እንዲያሰላስል፣ እና በቅንነት ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ አደረገው። ወጣቱ ጆሴፍ ስሚዝ አብ እና ወልድ ለእርሱ ከታዩ በሁኋላ ወዲያው ከቅዱሱ ጥሻ ወደቤት ሲመለስ፣ መጀመሪያ ከእናቱ ጋር ተነጋገረ። እርሱም “በእሳት ማሞቂያ ስፍራው አጠገብ [ተደግፎ እያለ]፣ እናቱ ምን [እንደሆነ ጠየቀችው]። [ጆሴፍም] መለሰ፣ ‘ምንም አታስቢ፣ ሁሉም መልካም ነው—እኔም ደህና ነኝ።’ ከዚያም [ለእናቱ] እንዲህ አለ፣ ‘ለራሴ … ተምሬአለሁ።’”3 የጆሴፍ አጋጣሚ እያንዳንዳችን ልንከተለው የሚገባ የመማሪያ መርህ ይሰጠናል። እኛም ለራሳችን መማር ይኖርብናል።

የሰማይ አባት በጣም አስፈላጊው የእቅዱ አላማ ልጆቹ ይበልጥ እንደእርሱ እንዲሆኑ ነው። በዚህም መሰረት፣ ለማደግ እና ወደፊት ለመግፋት አስፈላጊ የሚሆኑ እድሎች ሰጥቶናል። በእውነት መሰረት ለመማር እና ለመኖር ያለን ጽናት “ነውጥ”4 ውስጥ ባለው እና በተጨማሪም ግራ በተጋባና እና ክፉ በሆነው አለም ውስጥ አስፈላጊነቱ እያደገ ይሄዳል። በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ውስጥ በመገኘት ወይም በፕሮግራሞች በመሳተፍ ብቻ “ክፉውን ቀን ለመቋቋም”5 የሚያስችለንን መንፈሳዊ ትምህርት እና ጥበቃ በሙሉ ለመቀበል እንደምንችል መጠበቅ አይገባንም።

“ወላጆች ልጆቻቸውን በፍቅር እና በጽድቅ የማሳደግ የተቀደሰ ሀላፊነት አላቸው”6 ተነሳሽነት ያላቸው የቤተክርስቲያኗ መሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ እና እንቅስቃሴዎች ግለሰቦች እና ቤተሰቦችን በመንፈሳዊነት እድገት ጥረታቸው ይረዷቸዋል።። በቃል ኪዳን መንገድ ላይ ወደፊት በመግፋት ሁላችንም እርዳታ የሚያስፈልገን ቢሆንም፣ መንፈሳዊ ጥንካሬ እና ብርታት የማሳደግ የመጨረሻው ሀላፊነት የሚያርፈው በእያንዳንዳችን ላይ ነው።

ኔፊ፣ የነቢዩ ሌሂ ልጅ፣ አባቱ በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ስለህይወት ዛፍ ራዕይ የተማረውን ለማየት፣ ለመስማት፣ እና ለማወቅ እንዴት እንደፈለገ አስታውሱ። ኔፊ በወጣትነቱ እንዲባረክ “የመልካም ወላጆቹ”7 ምሳሌና ትምህርት በግልጽ ያስፈልጉት ነበር፡፡ ግን፣ ልክ እንደ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ለመማር እና ለራሱ ለማወቅ ጉጉት ነበረው።

እናንተ እና እኔ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ዳግም ስለተመለሰው ወንጌሉ የምናውቀው ሌሎች ሰዎች የነገሩንን ወይም ያስተማሩንን ብቻ ከሆነ ፣ ያ ማለት ስለእርሱ እና ስለ ድንቅ የኋለኛው ቀን ስራው ያለን ምስክርነት በአሸዋ ላይ የተገነባ ነው።8 በሌሎች ሰዎች የወንጌል እውቀትና ብርሃን ላይ ልንመረኮዝም ሆነ ልንዋስ አንችልም እምንወዳቸው እና እምናምናቸው እንኳን ሰዎች ቢሆኑ፡፡

በታላቅ ሁኔታ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳስተማረው እያንዳንዱ የኋለኛው ቀን ቅዱስ ለራሱ ወይም ለራሷ “ስለእኛ ወደ አለም መምጣት እግዚአብሔር ምን እቅድ እና አላማ እንዳለው”9 መረዳት ያስፈልገዋል ወይም ያስፈልጋታል።

“ከአዳም ቀናት ጀምሮ የተጻፉትን ለማንበብ እና ለመረዳት የምንችል ቢሆን፣ ሰው ከእግዚአብሔር እና ወደፊት ከሚኖሩት መላእክት ጋር ስላለው ግንኙነት በጥቂቱ ያህል እናውቃለን። የሌሎችን አጋጣሚዎች፣ ወይም ለእነርሱ የተሰጡትን ራዕዮች፣ ማንበብ የጉዳያችንን ሙሉ ሁኔታ እና ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን እውነተኛ ግንኙነት ለእኛ መረጃ በምንም አይሰጠንም። ስለእነዚህ ነገሮች እውቀት ለማግኘት የሚቻለው ለዚያ እቅድ በተመደቡት የእግዚአብሔር ስርዓቶች በኩል ብቻ ነው።10

ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች ይህን ታላቅ መንፈሳዊ እቅድን ተፈጻሚ ማድረግ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሮግራሞች እና እንቅስቃሴዎች በዚህ የመጨረሻው የወንጌል ሙላት ላይ ቤትን ያማከለ በቤተክርስትያን የተደገፈ መሆን ዋና ምክንያቶች ናቸው።

ቤትን ያማከለ በቤተክርስትያን የተደገፈ ትምህርት እንደምታዎች

የወንጌል ትምህርት ቤት ተኮር እና በቤተክርስቲያን የተደገፈ እየሆነ መምጣቱ ያሚያሳየውን ጥቂት መሰረታዊ አንደምታዎች በአጭሩ ላጠቃልል፡፡

ዋናው የሚስዮናውያን ማሰልጠኛ ማእከል በራሳችን መኖሪያ ውስጥ ነው፤ ተከታዮቹ የወንጌል ማስልጠኛ ቦታዎች የሚገኙት በፕሮቮ፣ በማኒላ፣ በሜክሲኮ ከተማ፣ እና በሌሎች ቦታዎች ውስጥ ይገኛሉ። እጅግ በጣም አስተማሪ የሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤቶቸቻችን በመኖሪያ ቤታችን የምናደርጋቸው የግለሰብ እና የቤተሰብ ጥናቶች መሆን አለባቸው፤ የሚረዱ ግን ሁለተኛ የሆኑ የሰንበት ትምህርት ክፍሎች በስብሰባ ቦታዎቻችን ውስጥ ይካሄዳሉ።

የቤተሰብ ታሪክ ማእከላት አሁን በቤታችን ውስጥ ናቸው። ለቤተሰብ ታሪክ ፍተሻ ስራችን ተጨማሪ ድጋፍ በስብሰባ ቤቶቻችን ውስጥም ይገኛሉ፡፡

አስፈላጊ የቤተመቅደስ ዝግጅት ክፍሎችም በቤታችን ውስጥ ይከናወናሉ፤ አስፈላጊ ነገር ግን ተከታይ የሆኑ የቤተመቅደስ ዝግጅት ክፍሎችም በየጊዜው በስብሰባ ቤቶቻችን ውስጥ ለመከናወን ይችላሉ።

ቤቶቻችንን “በቅዱስ ቦታዎች የምንቆምባቸው”11 መሸሸጊያዎች እንዲሆኑ ማድረግ በእነዚህ የኋለኛው ቀናት አስፈላጊ ነው። በአሁኑ ሰአት ቤትን ያማከለ በቤተክርስትያን የተደገፈ ትምህርት ለመንፈሳዊ ጥንካሬ እና ጥበቃ አስፈላጊ እንደሆነ ሁላ፣ ለወደፊት ደግሞ በጣም አስፈላጊ ይሆናል።

ቤትን ያማከለ በቤተክርስትያን የተደገፈ ትምህርት እና የቤተመቅደስ ዝግጅት

“ቤትን ያማከለ በቤተክርስትያን የተደገፈ” መሰረታዊ መርሆ በግለሰብ ዝግጅት እና ቅዱስ ስርዓቶችንና ቃል ኪዳኖችን በጌታ ቤት ውስጥ ለመቀበል ብቁነታችን ላይ እንዴት በተግባር ላይ እንደሚውል አስቡበት።

በእርግጥም፣ ለቤተመቅደስ መዘጋጀት በደንብ የሚከናወነው በቤቶቻችን ውስጥ ነው። ብዙ የቤተክርስቲያን አባላት ግን ስለቤተክርስቲያን ልምምዶች ከቤተክርስቲያን ውጪ ሰለቤተመቅደስ ምን ማለት ወይም አለማለት ትክክለኛ እንደሆነ እርግጠኛ አይደሉም።

ፕሬዘደንት ኤዝራ ታፍት ቤንሰን ይህ ብዥታ ለምን እንደሚፈጠር ገልጸዋል።

“ቤተመቅደስ ቅዱስ ቦታ ነው፣ እናም በቤተመቅደስ ውስጥ የሚከናወኑት ስርዓቶችም የቅድስና ጸባይ ያላቸው ናቸው። በቅዱስነቱ ምክንያት ለልጆቻችን እና ለልጅ ልጆቻችን ስለዚህ ምንም ለመናገር እናመነታለን።

“በዚህም የተነሳ ፣ ብዙዎች ወደ ቤተመቅደስ የመሄድ እውነተኛ ፍላጎት አያዳብሩም፣ ወይም ወደዚያ ሲሄዱ፣ ለሚገቧቸው ግዴታዎች እና ቃል ኪዳኖች የሚያዘጋቸ ተሞክሮ የላቸውም።

ትክክለኛውን ግንዛቤ ወይም ተሞክሮ ወጣቶችንለቤተመቅደስ ለማዘጋጀት በጣም ይረዳል ብዬ አምናለሁ … [እናም] ልክ አብርሃም የክህነት በረከቶችን እንደፈለገው የመፈለግ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ያደርጋል።”12

ሁለት መሠረታዊ መመሪያዎች በፕሬዘደንት ቤንሰን የተብራራውን ተገቢውን መረዳት እንድናሟላ ሊረዱን ይችላሉ።

መመሪያ #1። ጌታን ስለምንወደው፣ ሁል ጊዜም ስለተቀደሰ ቤቱ ስናወራ በአክብሮት መሆን ይገባዋል። በቅዱስ የቤተመቅደስ ስርዓቶች ውስጥ ከምንገባቸው ቃል ኪዳኖች ጋር የተያያዙትን ልዩ ምልክቶችን ማብራራት ወይም መግለጽ አይገባንም። በተጨማሪም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ላለመግለጽ ቃል የገባናቸውን ቅዱስ መረጃዎች ልንወያይ አይገባንም።

መመሪያ #2። ቤተመቅደስ የጌታ ቤት ነው። በቤተመቅደስ ውስጥ ያለው ነገር በሙሉ ወደ አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ይመራናል። ከቅዱስ ስነስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች ጋር የተያያዙትን መሠረታዊ ዓላማዎች፣ እና ትምህርቶች እና መርሆዎች ልንወያይባቸው እንችላለን

“በቤተመቅደስ ውስጥ ያለን መንፈሳዊ ስሜት ከልጆቻችን ጋር እንካፈል“ ሲልፕሬዚደንት ሆዋርድ ደብልዩ. ኸንተር መክሯል፡፡ እንዲሁም ስለ ጌታ ቤት አላማዎች ተገቢ በሆነ መንገድ ልንናገር የምንችላቸውን ነገሮች በልበ ሙሉነት እና በተሻለ ሁኔታ እናስተምራቸው።”13

ከነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ እስከ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን የነበሩ ትውልዶች፣ የቤተመቅደስ ስርዓቶች እና ቃል-ኪዳናት አስተምህሮ ዓላማዎችንየቤተክርስቲያን መሪዎች በስፋትእያሰተማሩ ይገኛሉ።14 ስለ ማነሳሳት ስነስርዓቶች፣ ስጦታዎች፣ ጋብቻዎች እና ሌሎች የመታተም ስነስርዓቶች ለመማር እንድንችል በህትመት፣ በድምፅ፣ በቪዲዮ እና ሌሎች መንገዶች የተከማቹ ማጣቀሻዎች አሉ።15 ጌታችንን ተከትለን ቃልኪዳንን በመቀበልና በመጠበቅ የመታዘዝ ህግን፣ የመስዋእትነት ህግን ፣ የወንጌል ህግን ፣ የንጽህና ህግን እና የማካፈልን ህግጋት ለመጠበቅ የሚያስችሉንም በቂ መረጃዎችም አሉን፡፡16 ሁሉም የቤተክርስቲያኑ አባላት በtemples.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ ከሚገኙ እጅግ በጣም ጥሩ የሆኑ መረጃዎች ጋር ሊተዋወቁ ይገባቸዋል።

ምስል
temples.churchofjesuschrist.org

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በቤተመቅደስ ሥነ-ስርዓት ቅዱስ ባህርያትና እና በበቤተክርስቲያኗ የሚታተሙት ትክክለኛ፣ ተገቢ፣ እና በይፋ የሚገኙ አስፈላጊ መረጃዎች መካከል ያለውን መመጣጠን ትኩረት ሰጥተውበታል። “አባላት … እንደ ‘መቀባት፣’ ‘ቃልኪዳን፣’ ‘መስዋእቶች፣’ እና ‘ቤተመቅደስ’ አይነት ከቤተመቅደስ ጋር የተያያዙ የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ብያኔዎችን እንዲያነቡ እመክራለሁ“ሲል አብራርቷል፡፡ በተጨማሪም ዘጸአት፣ ምዕራፎች 26–29ን፣ እና ዘሌዋውያን፣ ምዕራፍ 8ንየማንበብ ፍላጎቱ ሊኖረን ይችላል። ብሉይ ኪዳን፣ እንዲሁም በታላቅ ዋጋ እንቁ ውስጥ የሚገኙትን የሙሴ እና አብርሐም መፅሐፎች፣ የቤተመቅደስ ስራን ጥንታዊነትና የፀና ስርዓቶቹ ዘላቂ ተፈጥሮ አጽንዖት ይሰጣሉ።”17

ምስል
የተቀደሰ የቤተመቅደስ አልባሳት ቪዲዮ

ስለዚህ ወንዱ ወይም ሴቷ ልጃችሁ እንዲህ ብለው ቢጠይቁ ብላችሁ አስቡ፥ “አንድ ልጅ በትምህርት ቤት ውስጥ አንድ ያልተለመደ አይነት ልብስ በቤተመቅደስ ውስጥ እንደሚለበስ ነገረኝ። ይህ ትክክል ነውን?” በtemples.churchofjesuschrist.org ውስጥ “ቅዱስ የቤተመቅደስ ልብስ” የሚል አጭር ቪድዮ አለ። ይህ ግሩም የመረጃ ምንጮች እንዴት ወንዶችና ሴቶች የውስጥ ስሜታቸውን ለእግዚአብሔር ለመግለፅ ቅዱስ ሙዚቃ፣ የተለያዩ የጸሎት ዓይነቶች፣ ተምሳሌታዊ የሃይማኖት ልብሶች፣ አካላዊ እንቅስቃሴዎች፣ እና የአምልኮ ሥርዓቶች ከጥንት ዘመናት ተቀብለዋቸው እንደነበር ይገልፃል። ስለዚህ፣ ቤተክርስቲያኗ ለተከበሩ የቤተመቅደስ በረከቶች በመሰረታዊ መርሆችን እና እንደ ቪድዮው አይነት የተመሳሰሉ አስገራሚ የመረጃ ምንጮች አማካኝነት ቤትን ያማከለን ዝግጅት ትደግፋለች። ብዙ ጠቃሚ መረጃዎች ለእናንተ ይገኛሉ።18

በጌታ መንፈስ የዋህነት ለመራመድ ስንሞክር፣19 ስለ ቅዱስ የቤተመቅደስ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች መካከል ለመወያየት ተገቢ ያልሆነ እና የሚገባውን ለማመዛዘን ለመረዳት እና በቤቶቻችን ውስጥ እንድናውል እንባረካለን።

የተስፋ ቃል እና ምስክርነት

አንዳንዶቻችሁ የእናንተ ወንጌል ትምህርት በእርግጥ ቤትን ያማከለና በቤተክርስትያን የተደገፈ ሊሆን ይችላልን ብላችሁ ልታስቡ እንደምትችሉ እገምታለሁ። ምናልባት በቤታችሁ ውስጥ ብቸኛው የቤተክርስቲያኗ አባል፣ ወይም የማይደግፍ የትዳር አጋር ያላችሁ፣ ወይም ብቸኛ ወላጅ፣ ወይም ፍችን ፈጽማችሁ ብቻችሁን የምትኖሩ የኋለኛው ቀን ቅዱስ ልትሆኑ ትሆናላችሁ፣ እናም እነዚህ መመሪያዎች እንዴት ለእናንተ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ጥያቄዎች ሊኖራችሁ ይችላል። ምናልባት “ይህን ማድረግ እንችላለን?” በማለት እርስ በራስ የምትተያዩ ባልና ሚስት ትሆኑ ይሆናል።

አዎን፣ ይህን ልታደርጉ ትችላላችሁ! ማስቻልን የሚሰጡ በረከቶች ወደ ህይወታችሁ እንደሚፈስላችሁ እናም እንደሚገኙ ቃል እገባላችኋለሁ። በሮች ይከፈታሉ። ብርሀን ይበራል። በብቃት እና በትእግስት ለመፅናት ያላችሁ ችሎታም ይጨምራል።

በዳግም የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለመማር እና ለማፍቀር ያለንን የግል ሀላፊነታችንን ለመወጣት ስንጥር የማካካሻ በረከቶች እንደሚመጡ በደስታ እመሰክራለሁ። “አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በሙሉ ለማግኘት መዘጋጀት”20 በእውነትም እንችላለን። ይህን ቃል የምገባው እና የምመሰክረው በቅዱሱ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ረሰል ኤም. ኔልሰን, በ “Latter-day Saint Prophet, Wife and Apostle Share Insights of Global Ministry,” Newsroom, ጥቅምት. 30, 2018(እ.አ.አ)mormonnewsroom.org/article/latter-day-saint-prophet-wife-apostle-share-insights-global-ministry.

  2. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 121፥29ን ይመልከቱ።

  3. ጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ 1፥17)።

  4. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥26

  5. ኤፌሶን 6፥13

  6. ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” Liahona,፣ ግንቦት 2017፣ 145።

  7. 1 ኔፊ 1፥1

  8. ማቴዎስ 7፥24–273 ኔፊ14:24–2718:13

  9. የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፧ ጆሴፍ ስሚዝ 2007 (እ.አ.አ)፣ 211።

  10. የጆሴፍ ስሚዝ ትምህርቶች 419፤ አትኩሮት ተጨምሮበታል፡፡

  11. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥22

  12. የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፧: እዝራ ታፍት ቤንሰን (2014 እ.አ.አ)፣ 174; አትኩሮት ተጨምሮበታል፡፡; በተጨማሪምእዝራ ታፍት ቤንሰንን፣ “What I Hope You Will Teach Your Children about the Temple,” ኢንዛይን, ነሃሴ (1985 እ.አ.አ) 8.

  13. የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፧: ሆዋርደ ደብልዩ. ኸንተር (2015 እ.አ.አ)፣ 184.

  14. ለምሳሌ, የጄምስ ኢ.ታልማጅ The House of the Lord (1912 እ.አ.አ)፣ 99–101 ይመልከቱ፡፡

  15. See የጄምስ ኢ.ታልሜጅ፣ The House of the Lord, 89–109 ይመልከቱ፡፡; ረሰል ኤም. ኔልሰን፣ “Personal Preparation for Temple Blessingsሊያሆና, May 2001, 37–34; Liahona, ሃምሌ (2001 እ.አ.አ); ቦይድ ኬ. ፓከር, The Holy Temple (1980 እ.አ.አ), 153–55.

  16. የእዝራ ታፍት ቤንሰን ትምህርቶች (1988 እ.አ.አ)፣121፤ የጄምስ ኢ.ታልሜጅ The House of the Lord, 100፤ Preparing to Enter the Holy Temple (መጽሄት, 2002 እ.አ.አ)ይመልከቱ፡፡

  17. ረስል ኤም ኔልሰን “ለቤተመቅደስ በረከቶች መዘጋጀት,” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና, ጥቅምት. (2010 እ.አ.አ), 47.

  18. ለምሳሌ፣ በ temples.ChurchofJesusChrist.org ውስጥ የሮም ጣሊያን ቤተመቅደስ የቪድዮ ጉብኝትን ይመልከቱ ፣ ወይም ስለቤተመቅደስ የነቢያትን ትምህርትን ያጥኑ።

  19. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥23ን ይመልከቱ።

  20. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥15