2010–2019 (እ.አ.አ)
የቤተክርስቲያኗ ትክክለኛ ስም
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


የቤተክርስቲያኗ ትክክለኛ ስም

ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን በስሙ እንድንጠራ መመሪያ ሰጥቶናል ምክንያቱም ይህች፣ በሀይሉ የተሞላች፣ የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በዚህች በተዋበች የሰንበት ቀን ከጌታ ለተቀበልናቸው ብዙ በረከቶች አብረን እንደሰታለን። ለዳግም ስለተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ስላላችሁ ምስክርነት፣ በእርሱ የቃል ኪዳን መንገድ ለመመለስ እና ወይም ለመቆየት ስላደረጋችሁት መስዋዕት፣ እና ለቤተክርስቲያኗ ለሰጣችሁት የተቀደሰ አገልግሎትም አመስጋኞች ነን።

ዛሬ እኔ ከእናንተ ጋር በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ለመወያየት ግድ ይለኛል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ ስለቤተክርስትያን ስም ማስተካከያ መግለጫ ሰጥቼ ነበር።1 ይህን ያደረኩበት ምክንያቱም ጌታ ለቤተክርስቲያኑ ስለወሰነው ስም አስፈላጊነት, እንዲሁም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ አስፈላጊነት በአዕምሮዬ ስላነሳሳኝ ነው።2

እንደምትጠብቁት፣ ለዚህ መግለጫ እና የተሻሻለ የቅጥ መመሪያ3 የተሰጡት መልሶች የተለያዩ ናቸው። ብዙ አባላቶች ወዲያውኑ የቤተክርስቲያኗን ስም በብሎጋቸው እና በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ አስተካክለዋል። ሌሎች ደግሞ፣ በዓለም ላይ እየተከናወነ ባለው ነገር ሁሉ፣ ለምን “አላስፈላጊ” የሌለውን ነገር አጽንዖት መስጠት ላይ እንደሚተኮር አስበው ነበር። ሌሎችም ሊደረግ አይቻለም፣ ስለዚህ ለምን ይሞከራል? አሉ። ስለዚህ ጉዳይ ለምን በጥልቅ እንደምናስብ ልገለጽላችሁ። ግን በመጀመሪያ ይህ ጥረት ምን እንዳልሆነ ልግለፅ።

  • የስም ለውጥ አይደለም።

  • እንደገና የምርት ስም ለመስጠት አይደለም።

  • ከውጭ የሚታየው የሚቀየርበት አይደለም።

  • በድንገት የመጣ ለውጥ አይደለም።

  • ውጤታማነት የሌለው አይደለም።

በምትኩ፣ ማስተካከያ ነው። ይህ የጌታ ትእዛዝ ነው። ጆሴፍ ስሚዝ በእርሱ በኩል በዳግም የተመለሰችውን ቤተክርስቲያን ስም አልሰጠም፤ ሞርሞንም አላደረገውም። “በመጨረሻዎቹ ቀናትም ቤተክርስቲያኔ የምትጠራው በዚህ፣ እንዲሁም በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ ስም ነው”4 ያለው አዳኝ ራሱ ነበር።

ከዚህም አስቀድሞ፣ በ34 ም.ዓ.፣ ከሞት የተነሳው ጌታ እንዲህ አይነት መመሪያ በአሜሪካ ውስጥ የነበሩትን የቤተክርስቲያኑን አባላት በጎበኘበት ጊዜ ሰጠ። በዚያም ጊዜ እንዲህ አለ፥

“ቤተክርስቲያኗን በስሜ ጥሯት፤ …

“እናም በስሜ ካልተጠራ የእኔ ቤተክርስቲያን እንዴት ሊሆን ይችላል? ቤተክርስቲያኗ በሙሴ ስም ከተጠራች የሙሴ ቤተክርስቲያን ትሆናለች፤ ወይም በሰው ስም ከተጠራች የሰው ቤተክርስቲያን ትሆናለች፤ … በስሜ ከተጠራች የእኔ ቤተክርስቲያን ትሆናለች።”5

ስለዚህ፣ የቤተክርስቲያኑ ስም የሚደራደር አይደለም። አዻኝ በግልፅ የቤተክርስቲያኑ ስም ማን እንደሆነ ሲገልፅ፣ እና ማወጃውን “ቤተክርስቲያኔ የምትጠራው በዚህ ስም ትጠራለች” ከጀመረ፣ ኮስታራ እንደሆነ እናውቃለን። እና ቅጽል ስሞችን እንዲጠቀሙበት እና እነዚያን ቅልፅ ስሞች እንዲጠቀሙ እና ራሳችንም እንዲደገፊ ከፈቀድን፣ እርሱ ይከፋል።

በስም፣ ወይም በዚህ ጉዳይ፣ በቅጽል ስም ምን ይገኛል? ለምሳሌ እንደ “LDS ቤተክርስቲያን፣” “የሞርሞን ቤተክርስቲያን፣” ወይም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተክርስቲያን” አይነት የቤተክርስቲያኗ ቅጽል ስምን በሚመለከት፣ በግልፅ የሚታየው የተተወ ነገር ቢኖር የአዳኝ ስም ነበር። የጌታን ስም ከጌታ ቤተክርስቲያን ማውጣት ለሰይጣን ታላቅ ድል ነው። የአዳኝን ስም ስንጥል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገልንን ሁሉ—እንዲሁም የኃጢያት ክፍያውን በቀስታ መናቃችን ነው።

በእርሱ አስተያየት ይህን አስቡበት፥ ከቅድመ ምድር ህይወት በፊት እርሱ የብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ያህዌ ነበር። በእርሱ አባት አመራር ስር፣ እርሱ የዚህ እና የሌሎች አለሞች ፈጣሪ ነው።6 በአባቱ ፈቃድ ለመገዛት እናም ለሁሉም ለእግዚአብሔር ልጆች ማንም ሊያደርግላቸው የማይችለውን ለማድረግ መረጠ። በስጋ እንደ አብ አንድያ ልጅ በክፋት ወደተጠላበት፣ ወዳፌዙበት፣ ወደ ተፉበት፣ እና ወደ ተገረፈበት ምድር ለመምጣት ወሰነ። በገትሰመኔ የአትክልት ስፍራ ውስጥ፣ አዳኛችን በእናንተ እና በእኔ እናም ኖረው በነበሩት ወይም በሚኖሩት ሁሉ የተለማመዱትን ሁሉን ህመም፣ ሁሉን ኃጢያት፣ እና ሁሉን ጭንቀት እና ስቃይ በራሱ ላይ ወሰደ። በዚያ እጅግ በከፋ ሸከም ስር፣ ከእያንዳንዱ የቆዳ ቀዳዳው ደማ።7 ይህም ሁሉ ስቃይ በካልቨሪ መስቀል ላይ በሚሰቀልበት በብዙ እጥፍ ተባዝቶ ነበር።

በእነዚህ በጣም በሚያሰቅቁ አጋጣሚዎች እና በእርሱ ተከታይ ትንሳኤ—በእርሱ መጨረሻ በሌለው የኃጢያት ክፍያው—ለሁሉም ሰው አለሟችነትን ፈቀደ፣ እናም እያንዳንዳችንን ከኃጢያት ውጤቶች፣ ንስሀ በመድባት በኩል፣ ነጻ አውጥቶናል።

ከአዳኝ ትንሳኤ እና ከሐዋሪያቱ ሞት በኋላ፣ አለም በብዙ አስር አመቶች ጭለማ ውስጥ ጠለቀች። ከዚያም በ1820 (እ.አ.አ)፣ አብ እግዚአብሔር እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የጌታ ቤተክርስቲያን በዳግም መመለስ ለመጀመር በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ታዩ።

በሁሉም ነገሮች ከፀና በኋላ—ለሰው ዘር ካደረጋቸው ሁሉ በኋላ፣ በዳግም የተመለሰችው የጌታ ቤተክርስቲያንን ስም እንዲቀየር፣ እያንዳንዱም የኢየሱስ ክርስቶስ ስምን እንደማያካትት፣ ባለማወቅ መስማማታችንን በታላቅ ፀፀት ተረዳሁኝ።

በየሰንበቱ በብቁነት ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል፣ ለሰማይ አባታችን በራሳችን ላይ የልጁን፣ የኢየሱስ ክርስቶስን፣ ስም ለመውሰድ ፈቃደኛ እንደሆንን የገባነውን ቅዱስ ቃል ኪዳን እናድሳለን።8 እርሱን ለመከተል፣ ንስሀ ለመግባት፣ ትእዛዛቱን ለመጠበቅ፣ እና ሁልጊዜም እርሱን ለማስታወስ ቃል እንገባለን።

የእርሱን ስም ከቤተክርስቲያኑ ውስጥ ስናስወጣ፣ እርሱን እንደ ህይወታችን ዋና ትኩረት ባለማወቅ እያስወጣን ነውን?

የአዳኝን ስም መውሰድንም—በስራዎቻችን እና በቃላቶቻችን—ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ለሌሎች ማወጅን እና መመስከርን ያካትታል። “ሞርሞን” ብለው የሚጠሩንን እናስከፋለን ብለን በመፍራት ለአዳኝ ራሱ ተከላካይ ለመሆን፣ እንዲሁም በስሙ ለምትጠራው ቤተክርስቲያኑ ተከላካይ ለመሆን አልቻልንምን?

እኛ እንደ ህዝቦች እና እንደ ግለሰቦች—እኛን ለማጽዳት እና ለመፈወስ፣ እኛን ለማጠናከር እና ለማጉላት፣ እናም በመጨረሻም እኛን ከፍ ለማድረግ—ለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ሀይል መዳረሻ እንዲኖረን እርሱን እንደዚያ ሀይል ምንጭ እንደሆነ በግልፅ ማስታወቅ ይገባናል። ይህን ለመጀመር የምንችለውም ቤተክርስቲያኑን እርሱ ባወጀበት ስም በመጥራት ነው።

ለአብዛኛው አለም፣ የጌታ ቤተክርስቲያን አሁን “ሞርሞን ቤተክርስቲያን” በመሆን ተደብቋል። ነገር ግን እንደ ጌታ ቤተክርስቲያን አባላት ማን በእርሷ መሪነት እንደሚቆም እናውቃለን፥ እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ሞርሞን የሚለውን የሚሰሙ ብዙዎች ሞርሞንን የምናመልክ ይመስላቸዋል። ይህ አይደለም! ያን ታላይ የጥንት አሜሪካ ነቢይን እናከብራለን።9 ነገር ግን እኛ የሞርሞን ደቀመዛሙርቶች አይደለንም{62}። እኛ የጌታ ደቀመዛሙርቶች ነን።

በዳግም በተመለሰው ቤተክርስቲያን በመጀመሪያ ቀናት፣ ሞርሞን ቤተክርስቲያን እና ሞርሞኖች የሚሉት ስሞ 10 በእነዚህ በመጨረሻው ቀናት ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን በዳግም ለመመለስ የእግዚአብሔር እጅን የነበረበትስ ለማጥፋት ጭካኔ የተሞላባቸው እና የሚበድሉ ስሞች የተጠቀሙበት ቅፅል ስሞች ነበሩ።11

ወንድሞች እና እህቶች፣ የቤተክርስቲያኗ ትክክለኛ ስም በዳግም መመለስን የሚቃወሙ ብዙ አለማዊ ክርክሮች አሉ። የምንኖርበት የዲጂታል አለም በመሆኑ እና በፍጥነት የፍላጎታችንን መረጃ—የቤተክርስቲያኗን መረጃ አካቶ—እንድናገኝ በሚረዳን የፍለጋ ማሻሻያ ሀይሎች ምክንያት ተቺዎች የቤተክርስቲያኗን ስም ማስተካከል ጥበባዊ አይደለም ይላሉ። ሌሎችም እንደ “ሞርሞን” እና እንደ “ሞርሞን ቤተክርስቲያን” በመባል በብዛት ስለምንታወቅ፣ ይህንን ሁኔታ በተሸለ እንጠቀምበት ይላሉ።

ይሄ በሰው የተሰራን ድርጅት ስም ስለመስጠት የምንወያየይ ቢሆን፣ እነዚህ ክርክሮች ያሸንፉ ይሆን ይሆናል። ነገር ግን በዚህ አስፈላጊ ጉዳይ፣ ይሄ ቤተክርስቲያኑ ስለሆነው ወደ እረሱ እንመለከታለን እናም የጌታ መንገድ የሰው መንገድ አንዳልሆኑ እና በምንም እንደማይሆኑ እናቃለን። ትዕግስተኛ ከሆንን እና ድርሻችንን በደንብ ካከናወንን፣ ጌታ በዚህ አስፈላጊ ስራ ይመራናል። ይህም ቢሆን፣ እርሱ ኔፊ ባህር የሚያሻግር መርከብ የመገንባትን ስራ እንዲያከናውን እንደረዳ፣ ጌታ የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ የሚፈልጉትን እንደሚረዳ እናውቃለን።12

እነዚህን ስህተቶች ለማረም ባደረግነው ጥረት ትዕግስት እና የትህትና ተግባር ያለን ለመሆን ያስፈልገናል። ሀላፊነት ያላቸው የመረጃ መስኮቶች ለምንጠይቀው ምላሽ ይሰጣሉ።

ባለፈ አጠቃላይ ጉባኤ፣ ሽማግሌ ቤጃሚን ዴ ሆይስ ስለዚህ አይነት ድርጊት ተናገሩ። እንዲህም አሉ፥

“ከጥቂት አመታት በፊት በሜክሲኮ ውስጥ ባለው ቤተክርስቲያን ጉዳዮች ቢሮ ውስጥ እያገለገልኩ እያለሁ፣ [አብሮ የሚያገለግል እና እኔ] በራዲዮ የንግግር ፕሮግራም እንድንሳተፍ ተጋብዘን ነበር። … [ከፕሮግራሙ መሪዎች አንዱ እኛን] እንዲህ ጠየቀ፣ ‘ቤተክርስቲያኗ ለምንድነው እንደዚህ ረጅም ስም ያላት? …

“ከእኔ ጋር አብሮ የሚያገለግል እና እኔ በዚህ አስደናቂ ጥያቄ ፈገግ አልን እና ከዚያም የቤተክርስቲያኗ ስም በሰው የተመረጠ እንዳልሆነ ገለፅን። የተሰጠውም በአዳኝ ነበር። … የፕሮግራሙ መሪ ወዲያው እና በክብር መለሰ፣ ‘ስለዚህ በደስታ ይህን እንደግመዋለን።’”13

ያም ሀተታ ንድፍን ይሰጣል። አንድ በአንድ፣ በአመታት ውስጥ በቀስታ የገቡትን ስህተቶች ለማስተካከል እንደ ግለሰብ ያሉን የሚሻሉ ጥረቶች ያስፈልጋሉ።14 የተቀረው ዓለም በትክክለኛው ስም እኛን በመጥራት ሊከተሉን ወይም ላይከተሉን ይችላሉ። ነገር ግን አለም ቤተክርስቲያኗን እና አባላቷን ትክክል ባልሆነ ስም እመጥራታቸው እየተናደድን ራሳችን እንደዚህ ካደረግን እኛ ቅንነት ያለን አይደለንም ማለት ነው።

የተከለሰው የምልከታ መመሪያችን ጠቃሚ ነው። እንዲህም ይላል፥ “በመጀመሪያው ማጣቀሻ፣ ተቀባይ የሆነው የቤተክርስቲያኗ ሙሉ ስም፥ ‘የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን’ ነው። የታጠረ [ሁለተኛ] ማጣቀሻ ሲያስፈልግ፣ ‘ቤተክርስቲያኗ’ ወይም ‘የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን’ የሚባሉ ስሞች ለመጠቀም የሚበረታቱ ናቸው። ‘በዳግም የተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን’ ደግሞም ትክክለኛ እና ለመጠቀም የሚበረታታ ነው።15

“ሞርሞን ነህ?” በሎ ሰው ከጠየቀ እናንተም እንዲህ መመለስ ትችላላችሁ“እኔ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ነህ ብለህ የምትጠይቅ ከሆነ፣ አዎን፣ ነኝ!”

“የኋለኛ ቀን ቅዱስ ነህ?”16 ብሎ ሰው ከጠየቀ እናንተም እንዲህ ለመመለስ ትችላለሁ፣ “አዎ፣ ነኝ። በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ እናም የእርሱ በዳግም የተመለሰ ቤተክርስቲያን አባል ነኝ።”

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የጌታን ቤተክርስቲያን ትክክለኛ ስም በዳግም ለመመለስ የምንችለውን ጥረት ካደረግን፣ የእርሱ ቤተክርስቲያን የሆነው እርሱም ሀይሉን እና በረከቶቹን በኋለኛ ቀን ቅዱሳን ራሶች ላይ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መንገድ እንደሚያፈስ ቃል እገባላችኋለሁ።17 በዳግም የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በረከቶች ለእያንዳንዱ ሀግረ፣ ዘር፣ ቋንቋ፣ እና ህዝብ ለመውሰድ እና አለምን ለጌታ ዳግም ምፅዓት ለማዘጋጀት የእግዚአብሔር እውቀት እና ሀይል ይኖረናል።

ስለዚህ፣ በስም ምን አለ? የጌታን ቤተክርስቲያን በሚመለከት፣ መልሱ “ሁሉም ነገር” ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን በስሙ እንድንጠራ መመሪያ ሰጥቶናል ምክንያቱም ይህች፣ በሀይሉ የተሞላች፣ የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት።

እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ አውቃለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዛሬም የእርሱን ቤተክርቲያን ይመራል። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “ጌታ ለቤተክርስቲያኑ ስለወሰነው ስም አስፈላጊነት, እንዲሁም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ አስፈላጊነት በአዕምሮዬ አሳይቶኛል። ራሳችንን ከእርሱ ፍላጎት ጋር ለማስማማት በፊታችን ስራ አለን። በቅርብ ሳምንቶች፣ የተለያዩ የቢእተክርስቲያን መሪውዎች እና የድርጅት ክፍሎች ይህን ለማከናወን አስፈላጊ ደረጃዎችን ጀምረዋል። ስለዚህ አስፈላጊ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎች በሚመጡት ወራት ይገኛሉ” (Russell M. Nelson, “The Name of the Church” [official statement, Aug. 16, 2018], mormonnewsroom.org)።

  2. ከዚህ በፊት የነበሩ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንቶች እንደዚህ አይነት ጥያቄ ሰጥተዋል። ለምሳሌ፣ ፕሬዘደንት ጆርጅ አልበርት ስሚዝ እንዲህ አሉ፣ “ይህችን የሞርሞን ቤተክርስቲያን በማለት በመጥራት ጌታን ቅር አታሰኙ። እርሷን ሞርሞን ቤተክርስቲያን ብሎ አልጠራትም” (in Conference Report, Apr. 1948, 160)።

  3. Style Guide—The Name of the Church,” mormonnewsroom.org. ተመልከቱ።

  4. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥4

  5. 3 ኔፊ 27፥7–8

  6. ሙሴ 1፥33 ይመልከቱ።

  7. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥18 ይመልከቱ።

  8. ሞሮኒ 4፥3ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37፣ 77 ይመልከቱ።

  9. ሞርሞን የመፅሐፈ ሞርሞን አራት ዋና ጸሀፊ አንዱ ነበር፣ ሌሎቹም ኔፊ፣ ያዕቆብ፣ እና ሞሮኒ ነበሩ። የተነሳሳው ተርጓሚ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደነበረው፣ ሁሉም የጌታ የአይን ምስክሮች ነበሩ።

  10. ሞርሞናዊ የሚለው ይጠቀሙበት የነበረው የስድብ ስምም ነበር (History of the Church, 2:62–63, 126 ይመልከቱ)።

  11. ሌሎች ቅልፅ ስሞች በአዲስ ኪዳን ውስጥ ደርሰውም ነበር። ሐአርያ ጳውሎስ በፍሌክሰስ ፊት ለፍርድ በቀረበበት፣ ጳውሎስ “የናዝሬታያን ቡድን መሪ ነው” ተብሏል (ስራ 24፥5)። “ናዝራዊ” ስለሚለውን ቃል ጥቅም አንድ ተንታኝ እንዲህ ፃፈ: “ይሄ በንቀት ለክርስቲያኖች የተሰጠ ስም ነበር። እነርሱ እንደዛ የተጠሩት ኢየሱስ ናዝራዊ ስለነበረ ነው” (Albert Barnes, Notes, Explanatory and Practical, on the Acts of the Apostles [1937], 313).

    በተመሳሳይ, ሌላ ተንታኝ እንዲህ አለ: “ጌታችን በንቀት ናዝራዊ ተብሎ እንደተጠራ (ማቴዎስ 26፥71)፣ አይሁዶች የእርሱን ደቀመዛሙርትም ናዝራዊያን አሏቸው። ክርስቲያን መሆናቸውን አይቀበሉም ነበር, ለምሳሌ፤ የመሲሁ ደቀመዛሙርቶች” (The Pulpit Commentary: The Acts of the Apostles, ed. H. D. M. Spence and Joseph S. Exell [1884], 2:231)።

    በተመሳሳይ መልኩ, ሽማግሌ ኒይል ኤ. ማክስዌል እንዲህ አስተዋሉ: “በቅዱስ መጻህፍት ታሪክ፣ ነብያትን ለመቃወም ማጣጣሎች—እነርሱን ለማስወገድ ስም ሲሰጣቸው በተደጋጋሚ እናያለን። ሆኖም፣ በይበልጥ በተከታዮቻቸው እና በታሪክ አዋቂዎች በቀላሉ ይተዋሉ። ያም ሆኖ፣ የመጀመሪያ ክርስቲያኖች “የናዝራዊያን እምነት” ተብለው የጠሩ ነበር።’ (ስራ 24፥5.)” (“Out of Obscurity,” Ensign, Nov. 1984, 10).

  12. 1 ኔፊ 18፥1–2 ይመልከቱ።

  13. Benjamín De Hoyos, “Called to Be Saints,” Liahona, May 2011, 106.

  14. ሌሎች እኛን ምን ብለው እንደሚጠሩን መቆጣጠር ባንችልም፣ እኛ እራሳችንን የምንጠራበትን ግን ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር አለን። እኛ አባላቱ የቤተክርስቲያኑን ትክክለኛ ስም ማክበር ካልቻልን እንዴት ሌሎች እንዲያደርጉት መጠጠበቅ እንችላለን?

  15. Style Guide—The Name of the Church,” mormonnewsroom.org.

  16. ቅዱስ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ተጠቅሷል። ለምሳሌ፣ ለኤፌሶኖች ጳውሎስ በፃፈው ደብዳቤ, ቅዱስ የሚለውን ቃል ቢያንስ አንዴ በየምእራፉ ተጠቅሞበታል። ቅዱስ ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን እና እርሱን ለመከተል የሚተጋ ነው።

  17. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 121፥33 ተመልከቱ።