የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፱


ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፱፥፱–፲፭።ዘፍጥረት ፲፱፥፰–፲ ጋር አነጻፅሩ

ሎጥ የሰዶምን ክፋት ተቋቋመ፣ እናም መላዕክት ጠበቁት።

እነርሱም ወዲያ ሂድ አሉት። እና ተናደውበትም ነበር።

እና እርስ በራሳቸውም እንዲህ አሉ፣ ይህ ሰው በመካከላችን በእንግድነት ለመኖር መጣ፣ አሁን እራሱን ዳኛ ያደርግ ዘንድ ይፈልጋል፤ አሁን በእርሱ ላይ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግበታለን።

፲፩ ስለዚህ ለሰውየውም እንዲህ አሉት፣ ወንዶቹን፣ እና ደግሞ ሴት ልጆችህንም እንወስዳለን፤ እና መልካም እንደሚመስለን እናደርግባቸዋለን።

፲፪ አሁን ይህም በሰዶም ክፉነት በኩል ነበር።

፲፫ እና ሎጥም አለ፣ አሁን እነሆ፣ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እባካችሁ፣ እነርሱን ወደ እናንተ ወደ ወንድሞቼ እንዳላወጣላችሁ እለምናችኋለሁ፣ እና በአይኖቻችሁ መልካም እንደመሰላችሁም አታደርጉባቸውም፤

፲፬ እግዚአብሔር አገልጋዩ በዚህ ነገር ተገቢ አያደርገውምና፤ ስለዚህ፣ ለዚህ አንድ ጊዜ፣ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፣ በቤቴም ሰላም እንዲኖራቸው ዘንድ እናንተን ወንድሞቼን እለምናችኋለሁ፤ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር የገቡበት ምክንያት ነውና።

፲፭ እና እነርሱም በሎጥ ተናድደው ነበር እና የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ፣ ነገር ግን ቅዱስ ሰዎች የነበሩት የእግዚአብሔር መላእክቶች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት።