የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፯


ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፯፥፫–፲፪።ዘፍጥረት ፲፯፥፫–፲፪ ጋር አነጻፅሩ

ህዝቡ፣ ከጥምቀት በተጨማሪ፣ የወንጌል ስርዓቶችን አላከበሩም። እግዚአብሔር የግርዘት ቃል ኪዳን እና የልጆች ተጠያቂነት እድሜ ለአብርሐም ገለጸ።

እና እንዲህ ሆኖ አለፈ፣ አብራምም በግምባሩ ወደቀ፤ እና የጌታን ስም ጠራ።

እና እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ አናገረው፣ ህዝቦቼ ከአስተያየቴ በተሳሳተው ይጓዛሉ፣ እና ለአባቶቻቸው የሰጠሁትን ስነ ስርዓቶቼንም አልጠበቁም፤

እኔ ትእዛዝ የሰጠኋቸው ቅባትን፣ የቀብር ስነ ስርዓትን፣ ወይም ጥምቀትን አላከበሩም፤

ነገር ግን ከትእዛዝ ዞር ብለዋል፣ እና ልጆችን ወደማጠብ፣ እና ደም መርጨትን በእራሳቸው ጀምረዋል፤

እና የጻድቁ አቤል ደም የፈሰሰው ለኀጥያት ነው ብለዋል፤ እና በፊቴ በምን ተጠያቂ እንደሆኑም አላወቁም።

ስለአንተ ግን፣ እነሆ፣ ቃል ኪዳኔን ከአንተ ጋር አደርጋለሁ፣ እና አንተም የብዙ አሕዛብ አባት ትሆናለህ።

እናም ይህን ቃል ኪዳን የምገባው፣ ልጆችህ በአሕዛብ መካከል እንዲታወቁ ነው። ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል፤ ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።

እጅግም አበዛሃለሁ፥ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ፣ እና ከዘሮችህም።

፲፩ እና የግርዘት ቃል ኪዳኔንን ከአንተ ጋር እመሰርታለሁ፣ እና ይህም በእኔና በአንተ መካከል፣ እና ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን ይሆናል፤ ልጆችህ ስምንት አመት እስከሚሆናቸው ድረስ በፊቴ ተጠያቂ እንዳልሆኑ ለዘላለም እንድታውቅ ዘንድ።

፲፪ እና ከአባቶቻችሁ ጋር ቃል የገባሁትን ቃል ኪዳኖቼን በሙሉ ጠብቅ፤ እና በአፌ የምሰጥህን ትእዛዛትንም ጠብቅ፣ እና ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆናለሁ።

ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፯፥፳፫–፳፬።ዘፍጥረት ፲፯፥፲፯–፲፰ ጋር አነጻፅሩ

አብርሐም የይስሀቅ መወለድ በተተነበየበት ጊዜ ተደሰተ እና ለእስማኤልም ጸለየ።

፳፫ አብርሃምም በግምባሩ ወደቀ እናም ተደሰተ፣ በልቡም አለ፣ የመቶ ዓመት ሰው በውኑ ልጅ ይወልዳል፣ እና ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለች።

፳፬ አብርሃምም እግዚአብሔርን አለው፣ እስማኤል በፊትህ በቅንነት ቢኖር በወደድሁ ነበር!