የጥናት እርዳታዎች
ሰረንጠዥ


በጥንት አባቶች ቀናት የነበሩት ድርጊቶች። (በዚህ ክፍል ውስጥ ለነበሩት ድርጊቶች እርግጠኛውን ቀን ለማወቅ አስቸጋሪ ስለሆነ፣ ቀናቶች አልተሰጡም።)

ም.ዓ.

፬ ሺህ

አዳም ወደቀ።

ሔኖክ አገለገለ።

ኖኅ አገለገለ፣ ምድር በጥፋት ውሀ ተጥለቀለቀች።

የባቢሎናውያን ግንብ ተገነባ፤ ያሬዳውያን ወደ ቃል ኪዳን ምድር ተጓዙ።

መልከ ጼዴቅ አገለገለ።

ኖኅ ሞተ።

አብራም (አብርሐም) ተወለደ።

ይስሐቅ ተወለደ።

ያዕቆብ ተወለደ።

ዮሴፍ ተወለደ።

ዮሴፍ ወደ ግብፅ ተሸጠ።

ዮሴፍ በፈርዖን ፊት ቀረበ።

ያዕቆብ (እስራኤል) እና ቤተሰቡ ወደ ግብፅ ሄዱ።

ያዕቆብ (እስራኤል) ሞተ።

ዮሴፍ ሞተ።

ሙሴ ተወለደ።

ሙሴ የእስራኤልን ህዝቦች ከግብፅ በመምራት አወጣ (ኦሪት ዘፀአት)።

ሙሴ ተለወጠ።

ኢያሱ ሞተ።

ኢያሱ ከሞተ በኋላ፣ የመሳፍንት ዘመን ተጀመረ፣ የመጀመሪያው ዳኛ ጎቶንያል የመጨረሻውም ሳሙኤል ነበር፤ የሌላዎቹ ቀናት እና ስርዓት እርግጠኛ አይደለም።

ሳኦል እንደንጉስ ተቀባ።

የተባበሩ የእስራኤል ግዛት ድርጊቶች

፩ ሺህ ፺፭

የሳኦል ግዛት ተጀመረ።

፩ ሺህ ፷፫

ዳዊት በሳሙኤል እንደንጉስ ተቀባ።

፩ ሺህ ፶፭

ዳዊት በኬብሮን ውስጥ ንጉስ ሆነ።

፩ ሺህ ፵፯

ዳዊት በኢየሩሳሌም ውስጥ ንጉስ ሆነ፤ ናታን እና ጋድ ተነበዩ።

፩ ሺህ ፲፭

ሰለሞን የእስራኤል ሁሉ ንጉስ ሆነ።

፱፻፺፩

ቤተመቅደስ ተፈጸመ።

፱፻፸፭

ሰለሞን ሞተ፤ አስሩ የሰሜን ጎሳዎች በሮብዓም ላይ አመጹ፣ ልጁና እስራኤል ተከፋፈሉ።

በእስራኤል ውስጥ የነበሩ ድርጊቶች

በይሁዳ ውስጥ የነበሩ ድርጊቶች

በመፅሐፈ ሞርሞን ታሪክ ውስጥ የነበሩ ድርጊቶች

፱፻፸፭

ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉስ ነበር።

፱፻፵፱

የግብፅ ንጉስ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ዘረፈ።

፰፻፸፭

አክዓብ በሰማርያ ውስጥ የሰሜን እስራኤልን ገዛ፤ ኤልያስ ተነበየ።

፰፻፶፩

ኤልሳዕ ታላቅ ተአምራትን ሰራ።

፯፻፺፪

አሞፅ ተነበየ።

፯፻፺

ዮናስና ሆሴዕ ተነበዩ።

፯፻፵

ኢሳይያስ መተንበይ ጀመረ። ( ሮሜ ተመሰረተች፤ በ፯፻፵፯ ውስጥ ናቦናሰር የባቢሎን ንጉስ ነበር፤ ከ፯፻፵፯ እስከ ፯፻፴፬ ድረስ ቴልጌልቴልፌልሶር የሶሪያ ንጉስ ነበር።)

፯፻፳፰

ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉስ ነበር። (ሻላማንዘር ፬ኛ የሶሪያ ንጉስ ነበር።)

፯፻፳፩

የደቡብ ግዛት ተደመሰሰ፣ አስሩ ጎሳዎች በምርኮ ተወሰዱ፤ ሚክያስ ተነበየ።

፮፻፵፪

ናሆም ተነበየ።

፮፻፳፰

ኤርምያስ እና ሶፍንያስ ተነበዩ።

፮፻፱

አብድዩ ተነበየ፣ ዳንኤል ወደ ባቢሎን በምርኮ ተወሰደ። (ነነዌ በ፮፻፮ ወደቀች፤ ከ፮፻፬ እስከ ፭፻፷፩ ድረስ ናቡከደነዖር የባቢሎን ንጉስ ነበር።)

፮፻

ሌሂ ከኢየሩሳሌም ወጣ።

፭፻፺፰

ሕዝቅኤል በባቢሎን ውስጥ ተነበየ፤ ዕንባቆም ተነበየ፤ ሴዴቅያስ የይሁዳ ንጉስ ነበር።

፭፻፹፰

ሙሌቅ ከኢየሩሳሌም ወደ ቃል ኪዳን ምድር ወጣ።

፭፻፹፰

ኔፋውያን እራሳቸውን ከላማናውያን ለያዩ (በ፭፻፹፰ና በ፭፻፸ ም.ዓ. መካከል)።

፭፻፹፯

ናቡከደነዖር ኢየሩሳሌምን ያዘ።

በአይሁድ ታሪኮች ውስጥ የነበሩ ድርጊቶች

በመፅሐፈ ሞርሞን ታሪክ ውስጥ የነበሩ ድርጊቶች

፭፻፴፯

ቂሮስ አይሁዶች ከባቢሎን መመለስ እንደሚችሉ አወጀ።

፭፻፳

ሐጌና ዘካሪያስ ተነበዩ።

፬፻፹፮

አስቴር ኖረች።

፬፻፶፰

እዝራ ለውጦችን እንዲሰራ ተመደበ።

፬፻፵፬

ነሀምያ ይሁዳን እንዲገዛ ተመደበ።

፬፻፴፪

ሚልክያስ ተነበየ።

፬፻

ጄሮም ሰሌዳዎችን ተቀበለ።

፫፻፷

ኦምኒ ሰሌዳዎችን ተቀበለ።

፫፻፴፪

ታላቁ አሌክሳንደር ሶሪያንና ግብፅን አሸነፈ።

፫፻፳፫

አሌክሳንደር ሞተ።

፪፻፸፯

ሰፕቱአጅንት፣ የአይሁዳ ቅዱሣት መጻህፍትን ወደ ግሪክ መተርጎም፣ ተጀመረ።

፻፷፯

የመካቤው ማታትዩ በሶሪያ ላይ አመጸ።

፻፷፮

ይሁዳ መካቤዎስ የአይሁዶች መሪ ሆነ።

፻፷፭

ቤተመቅደሱ እንዲጸዳ ተደረገ እናም እንደገና ተቀደሰ፤ ሀነካ ተጀመረ።

፻፷፩

ይሁዳ መካቤዎስ ሞተ።

፻፵፰

አቢናዲ ሰማእት ሆነ፤ አልማ በኔፋውያን መካከል ቤተክርስቲያኗን እንደገና መሰረተ።

፻፳፬

ቢንያም የመጨረሻውን ንግግር ለኔፋውያን አቀረበ።

ታናሹ አልማና የሞዛያ ልጆች ስራቸውን ጀመሩ።

፺፩

የመሳፍንት ግዛት በኔፋውያን መካከል ተጀመረ።

፷፫

ፖምፔ ኢየሩሳሌምን አሸነፈ፣ የመካቤው ግዛት በእስራኤል ውስጥ ተፈጸመ፣ እናም ተሮሜ ግዛት ተጀመረ።

፶፩

ክሊዮፓትራ ነገሰች።

፵፩

ሄሮድስ እና ጳጼአል የይሁዳ ተባባሪ የአራተኛው ክፍል ገዢዎች ሆኑ።

፴፯

ሄሮድስ የኢየሩሳሌም መሪ ሆነ።

፴፩

አክቲየም ጦርነት ተዋጉ፤ ከ፴፩ ም.ዓ. እስከ ፲፬ ዓ.ም. አውግስጦስ የሮሜ ንጉስ ነበር።

ክሊዮፓትራ ሞተች።

፲፯

ሄሮድስ ቤተመቅደስን አደሰ።

ላማናውያኑ ሳሙኤል ስለክርስቶስ ልደት ተነበየ።

በክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የነበሩ ድርጊቶች

በመፅሐፈ ሞርሞን ታሪክ ውስጥ የነበሩ ድርጊቶች

ዓ.ም.

ዓ.ም.

የክርስቶስ መወለድ።

የክርስቶስ አገልግሎት ተጀመረ።

፴፫

ክርስቶስ ተሰቀለ።

፴፫ ወይም ፴፬

ከሞት የተነሳው ክርስቶስ በአሜሪካ ውስጥ ተገለጸ።

፴፭

ጳውሎስ ተቀየረ።

፵፭

ጳውሎስ የመጀመሪያ የሚስዮን ጉዞውን ጀመረ።

፶፰

ጳውሎስ ወደ ሮሜ ተላከ።

፷፩

የሐዋርያት ስራ ታሪክ ተፈጸመ።

፷፪

ሮሜ ተቃጠለች፤ ክርስቲያኖች በኔሮ ስር ተሰደዱ።

ክርስቲያኖች ወደ ፔላ ሸሹ፤ ኢየሩሳሌም ተከበበች እናም ተሸነፈች።

፺፭

ክርስቲያኖች በዶሚቲያን ተሰደዱ።

፫፻፹፭

የኔፋውያን ሀገር ተደመሰሰ።

፬፻፳፩

ሞሮኒ ሰሌዳዎችን ደበቀ።