“ለመሪዎች—ለአስተማሪዎች መግለጫ መሥጠት እና መደገፍ፣” በአዳኙ መንገድ ማስተማር፦ በቤት እና በቤተክርስቲያን ለሚያስተምሩ ሁሉ [2022 (እ.አ.አ)]
‘’ለአስተማሪዎች መግለጫ መሥጠት እና መደገፍ፣’’ በአዳኙ መንገድ ማስተማር
ለመሪዎች—ለአስተማሪዎች መግለጫ መሥጠት እና መደገፍ
እንደመሪ፣ በድርጅታችሁ ውስጥ “አዲስ ከተጠሩ አስተማሪዎች ጋር የመገናኘት” እና “ለጥሪያቸው እንዲዘጋጁ እነሱን የመርዳት” ሃላፊነት አለባችሁ (የአጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ፣ 17.3፣ የወንጌል ቤተመጻሕፍት)። እነዚህ ስብሰባዎች አዲስ አስተማሪዎችን ከቅዱስ ጥሪዎቻቸው ጋር የማስተዋወቂያ እና በአዳኙ መንገድ ማስተማር ምን ትርጉም እንዳለው አስተያየት የሚሰጥባቸው የማነሳሻ እድል ናቸው። እንደመሪ፣ የሚከተሉትን በማድረግ አዲስ አስተማሪዎችን ለማገልገል እንዲዘጋጁ መርዳት ትችላላችሁ፦
-
አዳኙ በጥሪያቸው ውስጥ እንደሚረዳቸው ያላችሁን ልበ ሙሉነት ግለፁ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥78 ተመልከቱ)።
-
የዚህን ግብዓት ቅጂ ለአዲስ አስተማሪዎች ስጡ እንዲሁም መርሆዎቹን በትምህርታቸው ውስጥ ለመተግበር መንገዶች እንዲፈልጉ አበረታቷቸው።
-
እነርሱ ስለድርጅታችሁ ቢያውቋቸው የሚረዷቸውን ማናቸውንም ነገሮች ለአዲስ አስተማሪዎች አካፍሉ።
-
እንደአስፈላጊነቱ፣ አዲስ አስተማሪዎች በየትኛው ክፍል ውስጥ እንደሚያስተምሩ እና ከየትኛው ትምህርት እንደሚጀምሩ ንገሯቸው። ስለክፍላቸው እና የክፍል አባሎች የሚፈልጉትን ማንኛውንም መረጃ ስጡ።
-
በጥሪያቸው ልትረዷቸው እንደምትችሉ ለአዲስ አስተማሪዎች ግለፁ። አስፈላጊ ከሆነ በክፍል ውስጥ እና የትምህርት ግብዓቶችን በሚያገኙበት ላይ ድጋፍ ስጡ።
-
የአስተማሪዎችን ክፍሎች አልፎ አልፎ ለመከታተል አቅርቡ፣ እንዲሁም መንፈስ በሚያነሳሳበት ወቅት አስተያየቶችን ስጡ።
-
በእሩብ ዓመታዊ የአስተማሪዎች የምክክር ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ አስተማሪዎችን ጋብዙ።
በአስተማሪዎች የአገልግሎት ጊዜያት፣ ቀጣይነት ያለውን ድጋፍ ለመስጠት በየጊዜው ከእነርሱ ጋር መገናኘትን ቀጥሉ። ለምሳሌ፣ ከክፍል በፊት ወይም በኋላ ስለ በአዳኙ መንገድ ማስተማር መርሆዎች ለመወያየት ከአንድ አስተማሪ ጋር አጭር ውይይት ልታደርጉ ትችላላችሁ። አስተማሪውን ምን በጎን ነገር እያደረጉ እንዳሉ እንደሚሰማቸው እና በምን መንገድ ሊሻሻሉ እንደሚፈልጉ ጠይቁ። ለሚሰጡት አገልግሎት ከደግነት እና ከምስጋና ጋር አበረታቷቸው።
አስተማሪው ሲያስተምር በመመልከት ለዚህ ውይይት ልትዘጋጁ ትችላላችሁ። የአስተማሪውን ጥንካሬዎች በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት እና እርዳታ መስጠት የምትችሉባቸውን መንገዶች ለማግኘት ፈልጉ። በአስተማሪው ጥንካሬ ላይ መገንባት ልክ የመሻሻል እድሎችን እንደመለየት አይነት አስፈላጊ ነው።